Jeilu Tv /ጄይሉ ቲቪ

  • Home
  • Jeilu Tv /ጄይሉ ቲቪ

Jeilu Tv /ጄይሉ ቲቪ ዛሬን ለተሻለ ነገ !
(1)

በጀልባ መገልበጥ አደጋ የ16 ኢትዮጵያውያን ሕይወት አለፈ።ጄይሉ ቲቪ 15/08/2016 ዓ.ል   በጀልባ መገልበጥ አደጋ የ16 ኢትዮጵያውያን ሕይወት ሲያልፍ በጀልባዋ የነበሩ ሌሎች 28 ዜጎች...
23/04/2024

በጀልባ መገልበጥ አደጋ የ16 ኢትዮጵያውያን ሕይወት አለፈ።ጄይሉ ቲቪ 15/08/2016 ዓ.ል

በጀልባ መገልበጥ አደጋ የ16 ኢትዮጵያውያን ሕይወት ሲያልፍ በጀልባዋ የነበሩ ሌሎች 28 ዜጎችን እስካሁን ማግኘት አለመቻሉ ተገለጸ፡፡

ትላንት ምሽቱን ከየመን የባህር ዳርቻ ልዩ ስሙ አራ ከሚባል ስፍራ 77 ኢትዮጵያውያን ሕገ ወጥ ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ ጅቡቲ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ጎዶሪያ በሚባል አካባቢ በደረሰባት የመገልበጥ አደጋ እስካሁን የ5 ሕፃናት እና ሴቶችን ሕይወት ጨምሮ 16 ዜጎቻችን ሕይወታቸውን አጥተዋል።

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት
ድህረ ገጽ፡- https://jeilumedia.com
ዩትዩብ:- https://www.youtube.com/c/JeiluTube/videos
ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/jeilutv
ኢሜል :- [email protected]
ቴሌግራም :- https://t.me/Jeilumedia
ጄይሉ ቲቪ ዛሬን ለተሻለ ነገ

ከአላማጣ እና አከባቢዋ ተፈናቅለው ቆቦ እና ሰቆጣ የተጠለሉ ሰዎች ቁጥር 50 ሺ መሻገሩ ተገለጸ።ጄይሉ ቲቪ 15/08/2016 ዓ.ል   በቅርቡ በራያ አላማጣ አከባቢ ተከስቶ በነበረው አለመረጋ...
23/04/2024

ከአላማጣ እና አከባቢዋ ተፈናቅለው ቆቦ እና ሰቆጣ የተጠለሉ ሰዎች ቁጥር 50 ሺ መሻገሩ ተገለጸ።ጄይሉ ቲቪ 15/08/2016 ዓ.ል

በቅርቡ በራያ አላማጣ አከባቢ ተከስቶ በነበረው አለመረጋጋት ሳቢያ ከቀያቸው ተፈናቅለው በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ እና በዋግ ህምራ ዞን ሰቆጣ ከተማ ተጠልለው የሚገኙ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሺ በላይ መሆኑን የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

የተፈናቃዮቹ ቁጥር ያገኘሁት ከሁለቱ ዞኖች አስተዳደር ነው ያለው የቢሮው መግለጫ በአከባቢው ከሚያዚያ 5 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በተፈጠረው አለመረጋጋት እስከ ሚያዚያ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ሪፖርት የተደረገ ተፈናቃዮች ቁጥር 29 ሺ እንደሚጠጋ አስታውሷል።

በቆቦ ከተማ ተጠልለው የሚገኙ ተፋናቃዮች ቁጥር 42 ሺ መድረሱን የጠቆመው ቢሮው በሰቆጣ የሚገኙ ተፈናቃዮች ቁጥር 8 ሺ 300 መሆኑን ገልጿል።

አብዘሃኛዎቹን ተፈናቃዮች የቆቦ ከተማ ማህበረሰብ አስጠልሏቸው እንደሚገኝ የጠቆመው ቢሮው ሌሎቹ ደግሞ ከከተማዋ በሶስት ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኝ ጋሪያ ሌንጫ በተባለ ቦታ ላይ የድንኳን መጠለያ ዘርግተው እየኖሩ መሆኑን ገልጿል።

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት
ድህረ ገጽ፡- https://jeilumedia.com
ዩትዩብ:- https://www.youtube.com/c/JeiluTube/videos
ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/jeilutv
ኢሜል :- [email protected]
ቴሌግራም :- https://t.me/Jeilumedia
ጄይሉ ቲቪ ዛሬን ለተሻለ ነገ

እስራኤል በራፋህ የፈጸመችው ጥቃት ለመውለድ የምትጠባበቅ እናትን ከባለቤቷና ሴት ልጇ ጋር ቀጥፏል።  ጄይሉ ቲቪ 15/08/2016 ዓ.ል.   ነፍስጡሯ ህይወቷ ቢያልፍም በማህጸኗ የያዘቻትን ህ...
23/04/2024

እስራኤል በራፋህ የፈጸመችው ጥቃት ለመውለድ የምትጠባበቅ እናትን ከባለቤቷና ሴት ልጇ ጋር ቀጥፏል። ጄይሉ ቲቪ 15/08/2016 ዓ.ል.

ነፍስጡሯ ህይወቷ ቢያልፍም በማህጸኗ የያዘቻትን ህጻን ግን ማትረፍ ተችሏል።

ከሟች ማህጸን የወጣችው ህጻን የጤና ሁኔታዋ እየተሻሻለ መምጣቱንም በራፋህ ሆስፒታል ክትትል የሚያደርጉላት ሀኪም ተናግረዋል።

በሆስፒታሉ ሙቀት መስጫ ማሽን ውስጥ እስከ አራት ሳምንት ትቆያለች የተባለችው ህጻን ይህቺን ምድር ሳትመለከት በእናቷ ማህጸን ውስጥ ከመሞት ብትተርፍም “ወላጅ አልባ" ሆና በመወለዷ ከሆስፒታል የሚያስወጣና ልጄ ብሎ የሚያሳድግ ቤተሰብ የላትም።

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት
ድህረ ገጽ፡- https://jeilumedia.com
ዩትዩብ:- https://www.youtube.com/c/JeiluTube/videos
ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/jeilutv
ኢሜል :- [email protected]
ቴሌግራም :- https://t.me/Jeilumedia
ጄይሉ ቲቪ ዛሬን ለተሻለ ነገ

እንግሊዝ በሀገሯ የሚገኙ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለማዛወር የነደፈችው ረቂቅ ሕግ ፀደቀ። =================ጄይሉ ቲቪ 15 /08/2916 እንግሊዝ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ ለ...
23/04/2024

እንግሊዝ በሀገሯ የሚገኙ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለማዛወር የነደፈችው ረቂቅ ሕግ ፀደቀ።
=================
ጄይሉ ቲቪ 15 /08/2916

እንግሊዝ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ ለማዛወር የነደፈችው እና ከፍ ያለ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር የታመነው ረቂቅ ሕግ በሃገሪቱ ፓርላማ መጽደቁ ተሰምቷል።

ለሁለት ዓመታት ክርክር ሲደረግበት የቆየው ይህ ውሳኔ በእንግሊዝ ጠቅላይ ሚስቴር ሪሺ ሱናክ እና በሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ መካከል የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ የተደረሰ መሆኑ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

ውሳኔው የተወሰኑ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ከእንግሊዝ ወደ ሩዋንዳ የሚየዘዋውር ሲሆን ስደተኞቹም የጥገኝነት ጥያቄያቸው እስከሚጠናቀቅ ድረስ በሩዋንዳ እንደሚቆዩ ነው የተጠቀሰው።

ለሚቀጥሉት 664 ቀናት ስደተኞችን የያዙ አውሮፕላኖች ወደ ሩዋንዳ መብረር እንደሚጀምሩ የተገለፀ ሲሆን፤ በእቅዱ መሰረት 52 ሺህ የሚደርሱ ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ሩዋንዳ እንደሚዘዋወሩ ተጠቅሷል፡፡
ዘገባው የቢቢሲ ነው ።

በፒያሳ ለኮሪደር ልማት የፈረሱ ሰፈሮችና በርካታ ቦታዎች ላይ የሊዝ ጨረታ ወጣ።ጄይሉ ቲቪ 14/08/2016 ዓ.ል   የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ፣ በአ...
22/04/2024

በፒያሳ ለኮሪደር ልማት የፈረሱ ሰፈሮችና በርካታ ቦታዎች ላይ የሊዝ ጨረታ ወጣ።ጄይሉ ቲቪ 14/08/2016 ዓ.ል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ ከአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም ፊት ለፊት ለኮሪደር ልማት በሚል የፈረሱ ሰፈሮችን ጨምሮ ከ250 በላይ በሚሆኑ ቦታዎች ላይ የሊዝ ጨረታ ማውጣቱን ቪኦኤ ዘግቧል።

የሊዝ ጨረታው ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ውጭ በተቀሩት የከተማው አስር ክፍለ ከተሞች ባሉ ቦታዎች ላይ ወጥቷል። የሊዝ ጨረታው ለአመታት ከተቋረጠ በኋላ ሲወጣ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

የጨረታው ሰነድም ከረቡዕ ሚያዝያ 9 2016 አ.ም ጀምሮ መሸጥ የተጀመረ ሲሆን ፣ የሰነድ ሽያጩ እስከ ሚያዝያ 24 ቀን 2016 አ.ም ድረስ እንደሚቀጥል ተነግሯል።

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት
ድህረ ገጽ፡- https://jeilumedia.com
ዩትዩብ:- https://www.youtube.com/c/JeiluTube/videos
ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/jeilutv
ኢሜል :- [email protected]
ቴሌግራም :- https://t.me/Jeilumedia
ጄይሉ ቲቪ ዛሬን ለተሻለ ነገ

በመዲናዋ የሰራተኛ ምደባን በመቃወም ስራ ያልገቡ ሰራተኞች ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ ጥሪ ቀረበ።ጄይሉ ቲቪ 14/08/2016 ዓ.ል   በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተደረገውን የመንግስ...
22/04/2024

በመዲናዋ የሰራተኛ ምደባን በመቃወም ስራ ያልገቡ ሰራተኞች ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ ጥሪ ቀረበ።ጄይሉ ቲቪ 14/08/2016 ዓ.ል

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተደረገውን የመንግስት ሰራተኞች ምዘና ተከትሎ የተከናወነውን የሰራተኛ ምደባ በመቃወምና በሌሎች ግላዊ የጥቅም ጥያቄዎች ምክንያት ስራ ያልገቡ ሰራተኞች ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ የከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት አስተዳደር ቢሮ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ሰራተኞች ባስመዘገቡት ውጤት መሰረት የስራ ድልድል መደረጉንና ሰራተኞች በተቻለ መጠን በሚኖሩበት ወረዳ እና ክፍለ ከተማ አካባቢ እንዲመደቡ መደረጉን የከተማዋ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት አስተዳደር ቢሮ የስራ አመራር ዘርፍ ሀላፊ አቶ መላኩ ጉራቻ አስታውቀዋል።

ምደባው ከተከናወነ በኋላ በሁሉም ክፍለ ከተማ አገልግሎቶች ሳይቋረጡ እንዲሰጡ እየተደረገ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፤ በዚህ ሁኔታ ግን መመሪያውን በመቃወም እና በሌሎች ምክንያቶች ወደ ስራ ገበታቸው ያልተመለሱ ሰራተኞች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

አሁንም በምደባው ላይ ቅሬታ እየቀረበ በመሆኑ ወደ ስራ ገበታቸው ያልተመለሱ ሰራተኞችን ሙሉ ቁጥር አሁን ላይ ማወቅ እንደማይቻል አመላክተዋል፡፡

በስራ ምደባው 3ሺ 266 ሰራተኞች ከነበሩበት ደረጃ ዝቅ ሳይደረጉ፤ ወደ ሌላ ቦታ በማዘዋወር መመደባቸውን ሃላፊው አስታውቀዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት
ድህረ ገጽ፡- https://jeilumedia.com
ዩትዩብ:- https://www.youtube.com/c/JeiluTube/videos
ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/jeilutv
ኢሜል :- [email protected]
ቴሌግራም :- https://t.me/Jeilumedia
ጄይሉ ቲቪ ዛሬን ለተሻለ ነገ

የእስራኤል ወታደራዊ መረጃ ሃላፊ የጥቅምት ሰባቱን ጥቃት መከላከል አልቻሉም በሚል ከስልጣን ለቀቁየእስራኤል ወታደራዊ መረጃ ሃላፊ የሆኑት አሮን ሃሊቫ በሃማስ ጥቃት ዙሪያ በተፈጠረው ውድቀት ...
22/04/2024

የእስራኤል ወታደራዊ መረጃ ሃላፊ የጥቅምት ሰባቱን ጥቃት መከላከል አልቻሉም በሚል ከስልጣን ለቀቁየእስራኤል ወታደራዊ መረጃ ሃላፊ የሆኑት አሮን ሃሊቫ በሃማስ ጥቃት ዙሪያ በተፈጠረው ውድቀት ምክንያት ስልጣን የለቀቁ የመጀመሪያው ባለስልጣን ሆነዋል፡፡ ጄይሉ ቲቪ ሚያዝያ 14/2016

የእስራኤል ጦር በመግለጫው የወታደራዊው ዋና አዛዥ የሃሊቫን የስራ መልቀቂያ ተቀብሎ ለአገልግሎታቸዉ አመስግነዋል። እርምጃው ጥቃቱን ባለመከላከላቸዉ ምክንያት ጥፋተኛነቱን እንዲቀበሉ እና ከስልጣን እንዲወርዱ ያደረገ ሲሆን በርካታ የእስራኤል ከፍተኛ የጸጥታ ሃይሎች ተመሳሳዩን መንገድ ሊከተሉ እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡ሃሊቫ በጥቅምት ወር እንደተናገሩት የእስራኤል መከላከያ ኃይል ጥቃቱን ለማስቆም ባለመቻሉ ሃላፊነቱን እንደሚወስዱ መናገራቸዉ ይታወሳል፡፡

ቢያንስ 1 ሺ 1 መቶ 39 እስራኤላውያን በጥቃቱ ሲገደሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተይዘው ወደ ጋዛ ተወስደዋል።ሜጀር ጄኔራል አሮን ሃሊቫ በስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤያቸው ላይ የወታደራዊው የስለላ ክፍሉ የተጣለበትን ኃላፊነት አልወጣም ብለዋል። ሃማስ በእስራኤል ግዛት ላይ ካደረሰው መጠነ ሰፊ ጥቃት እንዲያመልጠን የሆነዉ ከፍተኛ የመረጃ ውድቀት እንዳለ እናውቃለን ብለዋል።ከአንድ አመት በፊት የእስራኤል የስለላ ድርጅት የጥቅምት 7ቱን ጥቃት እቅድ በትክክል ያስቀመጠ የሃማስ ሰነድ እጁ ላይ ገብቶ ነበር፡፡

ጥቃቱ ከመፈጸሙ ባሉት ሳምንታት እና ወራት ውስጥ በጋዛ ዙሪያ ካሉት ማማዎች የእስራኤል ወታደራዊ ስፔሻሊስቶች የሃማስ ሻለቃዎች ለአንድ ጥቃት ሲዘጋጁ ማየታቸውን እናውቃለን ሲሉ ደብዳቤዉ ላይ አስፍረዋል።ይህ ሁሉ በወታደራዊ እና በመንግስት ከፍተኛ አመራረፐች ደረጃ ችላ ተብሏል ምክንያቱም ሃማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ፍላጎት የለውም ከሚል የተሳሳተ እምነት ነበረ። ሃማስ የበለጠ ጋዛን የማስተዳደር ፍላጎት አለዉ የሚለዉ በእስራኤል አስተዳደር በኩል አጋድሏል። ለዚህም የወታደራዊ መረጃ ሃላፊዉ ባልተወጣዉ ስራዉ ምክንያት ለጥቃቱ ሃላፊነቱን ተቀብሏል።

የጦር ኃይሎች መሪ ሌተና ጄኔራል ሄርዚ ሃሌቪ እና የአገር ውስጥ የስለላ ድርጅት ኃላፊ ሺን ቤት ኃላፊ ሮነን ባር ከጥቃቱ በኋላ ኃላፊነቱን ቢቀበሉም በጋዛ ያለዉ ጦርነቱ በመቀጠል ስልጣናቸዉን አይለቁም፡፡በአንፃሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በሃማስ ለተፈጸመዉ ጥቃት እስካሁን ድረስ ኃላፊነቱን አልወሰዱም፣ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት አብዛኞቹ እስራኤላውያን ጥቃቱን ለመከላከል በቂ ጥረት ባለማድረጋቸው ግን ይተቿቸዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት
ድህረ ገጽ፡- https://jeilumedia.com
ዩትዩብ:- https://www.youtube.com/c/JeiluTube/videos
ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/jeilutv
ኢሜል :- [email protected]
ቴሌግራም :- https://t.me/Jeilumedia
ጄይሉ ቲቪ ዛሬን ለተሻለ ነገ

በኢራን የሚደገፈው ሄዝቦላ በደቡባዊ ሊባኖስ የእስራኤልን ድሮን መትቶ ጣለ።ጄይሉ ቲቪ 14/08/2016 ዓ.ል   በኢራን የሚደገፈው የሊባኖሱ ሄዝቦላ ታጣቂ ቡድን በደቡባዊ ሊባኖስ ውጊያ ላይ ...
22/04/2024

በኢራን የሚደገፈው ሄዝቦላ በደቡባዊ ሊባኖስ የእስራኤልን ድሮን መትቶ ጣለ።ጄይሉ ቲቪ 14/08/2016 ዓ.ል

በኢራን የሚደገፈው የሊባኖሱ ሄዝቦላ ታጣቂ ቡድን በደቡባዊ ሊባኖስ ውጊያ ላይ የነበረችውን የእስራኤል ድሮን መትቶ መጣሉን ገለጸ።

በአል አሺየህ አካባቢ ሰማይ ላይ ተመትታ የወደቀችው ድሮን "በአይበገሬው ህዝባችን ላይ ጦርነት ከፍታ ነበር " ሲል ቡድኑ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

እስራኤል እና ሄዝቦላ በ2006 ከባድ የሚባል ጦርነት ካካሄዱ ወዲህ በጋዛ እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጎን ለጎን ከስድስት ወራት በላይ ተኩስ በመለዋወጥ ላይ ይገኛሉ።

ሄዝቦላ እንደገለጸው ተመትታ የወደቀችው ድሮን ሄርሜስ 450 የተባለች እና በእስራኤሉ የጦር መሳሪያ አምራች ኢልቢት ሲስተም የተሰራች ነች።
ይህ ጦርነቱ የበለጠ ይባባሳል የሚል ስጋትን ፈጥሯል።

ሮይተርስ እንደዘገበው ከሆነ የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ከባለፈው ጥቅምት ወር ወዲህ 240 የሄዝቦላ ተዋጊዎችን እና 68 ንጹሃንን ጨምሮ 370 ሊባኖሳውያን ተገድለዋል።

በእስራኤል በኩል ደግሞ ንጹሃን እና ወታደሮችን ጨምሮ 18 እስራኤላውያን መገደላቸውን ዘገባው ጨምሮ ገልጿል።

ሄዝቦላ፣ ከእስራኤል ጋር እየተዋጋ ለሚገኘው የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ አጋርነቱን ለማሳየት በእስራኤል ላይ ጥቃት መክፈቱን መግለጹ ይታወሳል።

የጥቅምት ሰባቱን የሀማስ ጥቃት ተከትሎ እስራኤል በጋዛ እየወሰደችው ባለው መጠነሰፊ የምድር እና የአየር ጥቃት ከ32ሺ በላይ ፍልስጤማውያንን መገደላቸው የጋዛ የጤና ባለስልጣናት ተናግረዋል።

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት
ድህረ ገጽ፡- https://jeilumedia.com
ዩትዩብ:- https://www.youtube.com/c/JeiluTube/videos
ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/jeilutv
ኢሜል :- [email protected]
ቴሌግራም :- https://t.me/Jeilumedia
ጄይሉ ቲቪ ዛሬን ለተሻለ ነገ

22/04/2024

እስልምና ላይ የተከፈተው ግልፅ ዘመቻ በጎንደር!!

ሙሉ ዘገባውን ምሽት 1:30 በጄይሉ ቲቪ የዩትዩብ ቻናል ላይ ይጠብቁን !

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት
ድህረ ገጽ፡- https://jeilumedia.com
ዩትዩብ:- https://www.youtube.com/c/JeiluTube/videos
ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/jeilutv
ኢሜል :- [email protected]
ቴሌግራም :- https://t.me/Jeilumedia
ጄይሉ ቲቪ ዛሬን ለተሻለ ነገ

ቲክ ቶክ በአሜሪካ ሊታገድ መሆኑን ተከትሎ ኩባንያው የመናገር ነፃነትን ይጥሳል ሲል አስጠንቅቋል   ጄይሉ ቲቪ ሚያዝያ 14/2016   ቲክ ቶክ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በመተግበሪያው ላይ እ...
22/04/2024

ቲክ ቶክ በአሜሪካ ሊታገድ መሆኑን ተከትሎ ኩባንያው የመናገር ነፃነትን ይጥሳል ሲል አስጠንቅቋል ጄይሉ ቲቪ ሚያዝያ 14/2016

ቲክ ቶክ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በመተግበሪያው ላይ እገዳ ሊጣል መሆኑን ተከትሎ የ170 ሚሊዮን አሜሪካውያንን “የመናገር ነፃነትን ይረግጣል” ሲል ኩባንያው አስታውቋል። የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት የመተግበሪያው ባለቤት ከቻይና ጋር ያለውን ግንኙነት ካላቋረጠ ቲክ ቶክን እንዲያግድ ድምጽ ሰጥቷል።

በቅርብ ወራት ውስጥ የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት ቲክቶክ በወጣቶች ዘንድ ስላለው ተወዳጅነት ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። የቲክቶክ ባለቤት ባይቴዳንስ ለቤጂንግ አስተዳደር ታዛዥ ነው ስትል ዋሽንግተን ክስ ብታቀርብም ባይቴዳንስ ግን ክሱን ደጋግመው ውድቅ አድርገዋል።የቲክ ቶክ ህግ በሕግ አውጭዎች የጸደቀው፣ ለ61 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ዕርዳታን ወደ ዩክሬን እንዲሁም ለእስራኤል እና ለታይዋን ገንዘብ በሚልክ ጥቅል ውስጥ ተካቶ ነው። የተወካዮች ምክር ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ በቲክ ቶክ የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ ድምጽ ሰጥቷል ።

በተሻሻለው የዳይቭስት ወይም እገዳ ህግ ላይ 360 ለ58 ድምጽ ተሰጥቷል። ሴኔቱ በሚቀጥለው ሳምንት በህጉ ላይ ድምጽ ይሰጣል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ቀደም ሲል የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ህጉን እንደሚፈርሙ ተናግረዋል ። ይህው ረቂቅ ህግ ሆኖ ከፀደቀ ባይቴዳንስ ድርሻውን ለመሸጥ ዘጠኝ ወራት ይኖረዋል። ሽያጭ በሂደት ላይ እያለ ለሶስት ወራት ሊራዘም ይችላል።የቲክ ቶክ ቃል አቀባይ ህጉን አውግዘዋል፣ “የ170 ሚሊዮን አሜሪካውያንን የመናገር መብት ይረግጣል፣ ሰባት ሚሊዮን ንግዶችን ይዘጋል፣ እንዲሁም በአሜሪካ ኢኮኖሚ ላይ ያለውን የ24 ቢሊዮን ዶላር አስተዋጽኦ የመድረኩ መታገድ ያስቀረዋል ሲሉ ተደምጠዋል።

ቲክ ቶክ ባይት ዳንስ “የቻይና ወይም የሌላ አገር ወኪል አይደለም” ይላል። ባይት ዳንስ 60 በመቶውን የያዙትን በርካታ ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ድርጅቶችን በማመልከት የቻይና ኩባንያ እንዳልሆነ አጥብቆ ተናግሯል። የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ለባይት ዳንስ ቲክቶክን ለቻይና ላልሆኑ ባለቤቶች እንዲሸጥ ወይም መተግበሪያው በአሜሪካ እንዲታገድ በመጋቢት ወር ድምጽ ሰጥቷል። ነገር ግን ይህ ህግ አሁንም የሴኔት ይሁንታ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት
ድህረ ገጽ፡- https://jeilumedia.com
ዩትዩብ:- https://www.youtube.com/c/JeiluTube/videos
ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/jeilutv
ኢሜል :- [email protected]
ቴሌግራም :- https://t.me/Jeilumedia
ጄይሉ ቲቪ ዛሬን ለተሻለ ነገ

የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ጥቂት ከሚባሉ በአሜሪካ ከሚኖሩ ከኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያን ጋር መወያየታቸው ተነገረ    ጄይሉ ቲቪ ሚያዝያ 14/2016   በአማራ ክልል የብ...
22/04/2024

የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ጥቂት ከሚባሉ በአሜሪካ ከሚኖሩ ከኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያን ጋር መወያየታቸው ተነገረ ጄይሉ ቲቪ ሚያዝያ 14/2016

በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ኃላፊ የተመራ ልዑክ ቡድን በሰሜን አሜሪካ በኒውዮርክ ከተማ ጥቂት ከሚባሉ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር መወያየቱ ዳጉ ጆርናል ከክልሉ ፓርቲ ያገኘዉ መረጃ ያመላክታል።

በአሜሪካ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ የተመራው ቡድን በኒውዮርክ ከተማ የሥራ ጉብኝትም አድርጓል።

"የልዑክ ቡድኑ በሀገር ደረጃ እና ክልላዊ የለውጥ ጉዞ፣ ያጋጠሙ ችግሮች እና የመፍትሔ መንገዶች ላይ" ውይይት አድርጓል የተባለ ሲሆን ክልሉን ወደ ተሟላ ሰላም ለማምጣት መንግሥት እያደረገ ስላለው ጥረትና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እየተደረገ ስላለው ጥረት ውይይት ማድረጉን አሳዉቋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም ስለክልሉ የሰላም ሁኔታ ፣ የልማት ሥራዎችና ድህነት ቅነሳ ፣ ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ የማድረግ ሥራ ፣ የሀገራዊ አካታች የምክክር መድረክ ላይ የአማራ ክልል ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ እየተከናወነ ያለውን ሥራ እና ለሥራ እድል ፈጠራ ያለውን ምቹ ሁኔታ የተመለከቱ ጥያቄዎችን አንስተዋል ተብሏል።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ሚሲዮን ጽሕፈት ቤት አምባሳደሮች ፣ ዲፕሎማቶች ፣ ኢትዮጵዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ተወካዮች በዉይይቱ መሳተፋቸው ታዉቋል።

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት
ድህረ ገጽ፡- https://jeilumedia.com
ዩትዩብ:- https://www.youtube.com/c/JeiluTube/videos
ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/jeilutv
ኢሜል :- [email protected]
ቴሌግራም :- https://t.me/Jeilumedia
ጄይሉ ቲቪ ዛሬን ለተሻለ ነገ

ኢራናውያን ከዘጠኝ አመት በኋላ ለኡምራ ወደ ሳኡዲ አቀኑጄይሉ ቲቪ ሚያዚያ 14/2016   ሳኡዲ አረቢያ እና ኢራን ባለፈው አመት በቻይና አደራዳሪነት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ማደሳቸው ይታ...
22/04/2024

ኢራናውያን ከዘጠኝ አመት በኋላ ለኡምራ ወደ ሳኡዲ አቀኑጄይሉ ቲቪ ሚያዚያ 14/2016

ሳኡዲ አረቢያ እና ኢራን ባለፈው አመት በቻይና አደራዳሪነት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ማደሳቸው ይታወሳል
ኢራናውያን የኡምራ ተጓዦችን ያሳፈረ አውሮፕላን ወደ ሳኡዲ ማቅናቱ ተነገረ።
ከዘጠኝ አመት በኋላ ከኢራን ወደ ሳኡዲ የተደረገው የኡምራ ጉዞ የሀገራቱ ግንኙነት መሻሻሉን ያሳያል ተብሏል።
በኢራን የሳኡዲ አምባሳደር አብዱላህ ቢን ሳውድ አል አንዚ በቴህራን አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ለ85 የመጀመሪያው ዙር ተጓዦች ሽኝት አድርገዋል።
ኢራናውያኑ የኡምራ ተጓዦች በታህሳስ ወር 2023 ጉዞውን እንደሚያደርጉ ተገልጾ የነበረ ቢሆንም “በቴክኒካዊ ችግሮች” ምክንያት መዘግየቱን የኢራን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
በአሁኑ ወቅት ግን የበረራ እና የማረፊያ ቅድመ ሁኔታዎች በመስተካከላቸው ጉዞው መጀመሩን ነው ያስታወቁት።
እስከ ግንቦት 10 2024 ድረስም ከ5 ሺህ በላይ ኢራናውያን ወደ መካ እንደሚጓዙ መገለጹን ሬውተርስ ዘግቧል።
ኢራን በመጋቢት ወር 2015 ሁለት ታዳጊ ዜጎቿ በጂዳ አውሮፕላን ማረፊያ ውክቢያና እንግልት ደርሶባቸዋል ካለች በኋላ የኡምራ ተጓዦችን ወደ ሳኡዲ አረቢያ መላክ ማቆሟ ይታወሳል።
ከዚህ እገዳ አንድ አመት በኋላም ሪያድ የሺያ የሃይማኖት አባት የሆኑትን ኒምር ባቂር አል ኒምር መግደሏና በቴህራን በሚገኘው የሳኡዲ ኤምባሲ ላይ ሁከት መፈጠሩን ተከትሎ ሀገራቱ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ማቋረታቸው አይዘነጋም።
ቻይና ባለፈው አመት መጋቢት ወር ሁለቱ የመካከለኛው ምስራቅ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ለሰባት አመት ያቋረጡትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲያድሱ ማድረጓ የሚታወስ ነው።
ሀገራቱ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ዳግም እስኪያድሱ ድረስ ኢራናውያን ወደ ሳኡዲ ማቅናት የሚችሉት ለሃጂ ጉዞ ብቻ ነበር።
ኡምራ አቅሙ ያላቸው ሙስሊሞች በየትኛውም ጊዜ ሊያደርጉት የሚችሉት ሃይማኖታዊ ጉዞ ነው።

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት
ድህረ ገጽ፡- https://jeilumedia.com
ዩትዩብ:- https://www.youtube.com/c/JeiluTube/videos
ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/jeilutv
ኢሜል :- [email protected]
ቴሌግራም :- https://t.me/Jeilumedia
ጄይሉ ቲቪ ዛሬን ለተሻለ ነገ

የአሜሪካው ም/ቤት የ95 ቢሊዮን ዶላር የውጪ ዕርዳታ አጸደቀጄይሉ ቲቪ ሚያዝያ 14/2016   በአሜሪካ የተወካዮች ም/ቤት ለዩክሬን እና ለእስራኤል የሚሰጥን የ95 ቢሊዮን ዶላር የዕርዳታ ጥ...
22/04/2024

የአሜሪካው ም/ቤት የ95 ቢሊዮን ዶላር የውጪ ዕርዳታ አጸደቀጄይሉ ቲቪ ሚያዝያ 14/2016

በአሜሪካ የተወካዮች ም/ቤት ለዩክሬን እና ለእስራኤል የሚሰጥን የ95 ቢሊዮን ዶላር የዕርዳታ ጥቅል ሕግ ከወራት ሙግት በኋላ ትናንት ቅዳሜ አጽድቋል።

በኮንግረስ ያሉ መሪዎች ከቀኝ ዘመም ወግ አጥባቂዎች የደረሰባቸውን ተቃውሞ ወደ ጎን በማለት፣ ብዙም ባልተለመደ ሁኔታ ቅዳሜ ዕለት በተገናኘው ም/ቤት ሕጉን እንዲጸድቅ አድርገዋል።

አሁን የቀረው ሕጉን ወደ ሕግ አውጪው ሸንጎ ወይም ሴኔቱ መላክ ሲሆን፣ በዲሞክራቶቹ ቁጥጥር ስር ያለው ሴኔት እስከ ማክሰኞ ድረስ እንደሚያጸድቀው ይጠበቃል።

ከፓርቲያቸው ከፍተኛ ግፊት ያላባቸው ሪፐብሊካኑ የም/ቤቱ አፈጉባኤ ማይክ ጆንሰን፣ ወንበራቸውን እንደሚያጡ በፓርቲያቸው አባላት ዛቻ እየደረሰባቸው ሲሆን፣ ሕጉን ለማጽደቅ በተደረገው እያንዳንዱ እርምጃ የዲሞክራቶቹን ዕገዛ አግኝተዋል ተብሏል።

አራት ክፍሎች ያሉት ሕግ፣ ለዩክሬን፣ እስራኤል እና በኢንዶ ፓሲፊክ ለሚገኙ የአሜሪካ አጋሮች ገንዘብ የሚመድብ ሲሆን፣ ቲክ ቶክ በአሜሪካ ማኅበረሰብ ዘንድ ፈጥሯል የሚባለውንም ችግር የሚመለከት ነው።

ሕጉ በም/ቤቱ የሚጸድቅ ከሆነ፣ በፊርማቸው እንደሚያጸኑት ፕሬዝደንት ባይደን ሲያስታውቁ ቆይተዋል።

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት
ድህረ ገጽ፡- https://jeilumedia.com
ዩትዩብ:- https://www.youtube.com/c/JeiluTube/videos
ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/jeilutv
ኢሜል :- [email protected]
ቴሌግራም :- https://t.me/Jeilumedia
ጄይሉ ቲቪ ዛሬን ለተሻለ ነገ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የእንጨት እና ፊኒሺንግ ስራዎችን ጨምሮ 12 የሙያ ትምህርቶች ይሰጣሉ ተባለ ጄይሉ ቲቪ ሚያዚያ 14/2016   የማ...
22/04/2024

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የእንጨት እና ፊኒሺንግ ስራዎችን ጨምሮ 12 የሙያ ትምህርቶች ይሰጣሉ ተባለ ጄይሉ ቲቪ ሚያዚያ 14/2016

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2017 የትምህርት ዘመን ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሙያ ትምህርት መስጠት እንደሚጀምር አስታዉቋል።

ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ከቢሮዉ ያገኘዉ መረጃ እንደሚያመለክተው ለተማሪዎች ይሰጣሉ የተባሉት የሙያ አይነቶችም ይፋ ተደርገዋል።

በዚህም በክልሉ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተፈጥሮ ሳይንስ በ7 የሙያ አይነቶች እና በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ በ5 የሙያ አይነቶች ትምህርቱ ይሰጣል ሲል ቢሮዉ አሳዉቋል።

በዚህም መሰረት በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ የእንጨት ስራ ቴክኖሎጂ ፣ ፊኒሺንግ ኮንስትራክሽን ስራ ፣ ዌብ ዲዛይን እና ዴቬሎፕመንት ፣ ኮምፒውተር ጥገና ፣ አኒማል ፕሮዳክሽን ፣ ተፈጥሯዊ ሀብት አስተዳደር እና ማህበረሰብ ጤና የተሰኙ የሙያ ትምህርት አይነቶች ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎቹ ይሰጣሉ ብሏል።

በተጨማሪም በማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ጋዜጠኝነት ፣ ስነ ልቦናዊ ክብካቤ ፣ አካውንቲንግ እና ፋይናንስ ፣ ማርኬቲንግ እና ሽያጭ አስተዳደር ፣ ቮካል ፐርፎርማንስ እና ዳንስ መሆናቸውን ቢሮዉ ገልጿል።

እንደ ሀገር በ 40 የሙያ አይነቶች ትምህርቱ የሚሰጥ መሆኑን የጠቀሰው የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከ12ቱ የሙያ ትምህርቶች በተጨማሪ ወደፊት ሌሎች የሙያ አይነቶች ወደፊት በተጨማሪነት እንደሚካተቱም አሳዉቋል።

የሙያ አይነት ትምህርቶቹ ከቀለም የትምህርት አይነቶች ጋር ጎን ለጎን ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚሰጡ መሆኑን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ያገኘዉ መረጃ ያመላክታል።

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት
ድህረ ገጽ፡- https://jeilumedia.com
ዩትዩብ:- https://www.youtube.com/c/JeiluTube/videos
ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/jeilutv
ኢሜል :- [email protected]
ቴሌግራም :- https://t.me/Jeilumedia
ጄይሉ ቲቪ ዛሬን ለተሻለ ነገ

የአምራች ኢንዱስትሪዎች ኢግዚቢሽን በአረብ ኢምሬትስ ተከፈተ።  ጄይሉ ቲቪ ሚያዝያ 14/2016   ሁለተኛው የአምራቾች ኢግዚቢሽን በአረብ አምሬትስ በዛሬው እለት ተከፍቷል።በርካታ ሚኒስትር መ...
22/04/2024

የአምራች ኢንዱስትሪዎች ኢግዚቢሽን በአረብ ኢምሬትስ ተከፈተ። ጄይሉ ቲቪ ሚያዝያ 14/2016

ሁለተኛው የአምራቾች ኢግዚቢሽን በአረብ አምሬትስ በዛሬው እለት ተከፍቷል።

በርካታ ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች በጋራ በመሆን ነው ኢግዚቢሽኑን የከፈቱት።
የአረብ ኢምሬትስ ኢንዱስትሪ እና አድቫንስድ ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ አድኖክ ግሩፕ፣ ሂማን ሪሶርስ እና ኢምሬታይዜሽን ሚኒስቴር እና ናሽናል ካድሬስ ኮምፒቴቲቭነስ ካውንስል ተባብረው ኢግዚቢሽኑን አዘጋጅተው መክፈታቸውን የአረብ ኢምሬትስ ኢንዱስትሪ እና አድቫንስ ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በትዊተር ገጹ አስታውቋል።

ዛሬ የተከፈተው ኢግዚቢሽን አላማው ለኢምሬቶች በ80 ኩባንያዎች 800 የስራ ዕድሎችን መፍጠር ነው ብሏል።
በአቡ ዳቢ እየተካሄደ ያለው ኢግዚቢሽኑ ለሶስት ቀናት ይቆያል ተብሏል።

የመጀመሪያው የአምራቾች ኢግዚቢሽን በርካታ ኢንዱስትሪዎች የተገኙበት እና አበረታች ውጤት የተገኘበት ነበር። በዚህ ኢግዚቢሽን በ73 ኩባንያዎች 500 የሚሆኑ የስራ እድሎችን መፍጠር ተችሎ ነበር።

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት
ድህረ ገጽ፡- https://jeilumedia.com
ዩትዩብ:- https://www.youtube.com/c/JeiluTube/videos
ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/jeilutv
ኢሜል :- [email protected]
ቴሌግራም :- https://t.me/Jeilumedia
ጄይሉ ቲቪ ዛሬን ለተሻለ ነገ

በሸገር ከተማ ስር መልካ ኖኖ የሚገኘው ሰኢድ መስጅድ የመስጅዱ ቦታ ለግሌ ይገባኛል በሚሉ ባለስልጣን ምክንያት የመስጅዱ ህልውና አደጋ ላይ መውደቁን በሸገር ሲቲ የመልካኖኖ ክ/ከተማ መጅሊስ ...
20/04/2024

በሸገር ከተማ ስር መልካ ኖኖ የሚገኘው ሰኢድ መስጅድ የመስጅዱ ቦታ ለግሌ ይገባኛል በሚሉ ባለስልጣን ምክንያት የመስጅዱ ህልውና አደጋ ላይ መውደቁን በሸገር ሲቲ የመልካኖኖ ክ/ከተማ መጅሊስ አስታወቀ።ጄይሉ ቲቪ ሚያዚያ 12/2016

በሸገር ከተማ፣ መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ፣ በመልካ ገፈርሳ ወረዳ ድሬ ለገ ቡዌ ዞን የሚገኘው የሰኢድ መስጂድ በ2010 በቡራዩ ከተማ አስተዳደር 5700 ካሬ ሜትር የተወሰነለት ቢሆንም ከነበረው ይዞታ ላይ 1400 ካሬ ሜትር ተቀንሶ 4300 ካሬ ሜትር የሚሆነው የመስጅዱ ይዞታ ህጋዊ ካርታ ተሰጥቶት አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። ነገር ግን በቦታው ላይ ባለቤትነት የሌለው አቶ ደጀኔ ድሪባ የተባለ ግለሰብ (በወቅቱ የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ሰራተኛ የነበረ እና በአሁኑ ወቅት በሸገር ከተማ ከፍተኛ ስልጣን ያለው) ስልጣኑን ያለአግባብ በመጠቀም ህጋዊ የመስጅድ ቦታን ለግል ጥቅሙ ለመውሰድ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል ሲሉ የአካባቢው ምዕመናን ገልጸዋል።

ለዚህም እንዲያግዘው ስልጣኑን በመጠቀም ዶክመንት በማዘጋጀትና ሁከት በመቀስቀስ ከዚህ በፊት እግድ ቢፃፍበትም እስካሁን ጉዳዩ መፍትሄ ባለማግኘቱ ምክንያት ከመስጂዱ ይዞታ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ችግሮች እየተከሰቱ እንደሚገኝ የአካባቢው ነዋሪዎችና የመስጅዱ አስተዳደር ገልጸዋል።

ሰኢድ መስጂድ ከአራት መቶ እስከ ስድስት መቶ የሚሆኑ ተማሪዎችን በየቀኑ ቁርአን የሚያስተምር እና በርካታ ሙስሊም ማህበረሰብ የሚጠቀምበት መስጅድ ቢሆንም በዚሁ ሰው ምክንያት መስጅዱን ወደተሻለ ግንባታ እንዳያስድጉ በተለያዩ ጊዜያት መከልከላቸውን ገልፀውልናል።በተጨማሪም እኒሁ ባለስልጣን በተለያዩ ጊዜያት ወጣቶችን ሰብስበው በመምጣት የመስጁን አጥር ማፍረስ እንዲሁም ቁርአን የሚቀሩ ህፃናትን እና የመስጅዱ ጥበቃዎች ላይ ድብደባ መፈፀምን ጨምሮ ከፍተኛ ሰብአዊ ጥሰት እየፈጸሙባቸው እንደሚገኝ የመስጅዱ አስተዳዳሪዎች ገልፀዋል።

የመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ መጅሊስ በ ጉዳዩ በሰጠው አስተያየት ከአቅማቸው በላይ መሆኑንና ለሚመለከተው አካል ማሳወቃቸውን ተናግረው በክፍለ ከተማው ይህ ብቻ ሳይሆን በሌሎች መስጅዶችም ላይ ለግሪን ኤሪያ እና ለኢንቨስትመንት እየተባለ በካርታ ላይ ካርታ እየወጣ መሆኑን ገልፀዋል።

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት
ድህረ ገጽ፡- https://jeilumedia.com
ዩትዩብ:- https://www.youtube.com/c/JeiluTube/videos
ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/jeilutv
ኢሜል :- [email protected]
ቴሌግራም :- https://t.me/Jeilumedia
ጄይሉ ቲቪ ዛሬን ለተሻለ ነገ

ፓኪስታን፣ "እስራዔል ኃላፊነት የጎደለው ድርጊት ፈጽማለች" ማለቷ ተሰምቷል።ጄይሉ ቲቪ 11/08/2016 ዓ.ል   የፓኪታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባ፣ "የጽዮናዊዋ መንግስት የማይመጥን...
19/04/2024

ፓኪስታን፣ "እስራዔል ኃላፊነት የጎደለው ድርጊት ፈጽማለች" ማለቷ ተሰምቷል።ጄይሉ ቲቪ 11/08/2016 ዓ.ል

የፓኪታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባ፣ "የጽዮናዊዋ መንግስት የማይመጥን ድርጊት ፈጽማለች" ማለታቸውን የIRNA ዘገባ ያመለክታል።

ፓኪስታን፣ "እስራዔል በደማስቆ በሚገኘው የኢራን ቆስላ ያደረሰችው ጥቃት ነው ለዚህ ሁሉ ውጥረት ዋና መነሻ የሆነው ስትል" የእስራዔልን ድርጊት አውግዛለች ብሏል ዘገባው፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት
ድህረ ገጽ፡- https://jeilumedia.com
ዩትዩብ:- https://www.youtube.com/c/JeiluTube/videos
ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/jeilutv
ኢሜል :- [email protected]
ቴሌግራም :- https://t.me/Jeilumedia
ጄይሉ ቲቪ ዛሬን ለተሻለ ነገ

በአፋር እና በኢሳ መካከል ዘላቂ የተኩስ አቁም ለማድረግ ስምምነት ላይ መደረሱ ተገለፀ ።ጄይሉ ቲቪ ሚያዚያ 11/2016   በሁለት ወንድማማች ህዝቦች መካከል ለረጅም ጊዜያት እየተፈጠረ ያለው...
19/04/2024

በአፋር እና በኢሳ መካከል ዘላቂ የተኩስ አቁም ለማድረግ ስምምነት ላይ መደረሱ ተገለፀ ።ጄይሉ ቲቪ ሚያዚያ 11/2016

በሁለት ወንድማማች ህዝቦች መካከል ለረጅም ጊዜያት እየተፈጠረ ያለውን ደም አፋሳሽ ግጭት በዘላቂነት መፍትሄ ለማበጀት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ምክር ቤት የጀመረውን እንቅስቃሴ በማጠናከር በአፋር እና በኢሳ በኩል ያሉ ታላላቅ ኡጋዞች እና መሪዎች የተሳተፉበት ሰፊ ውይይት በአል ነሀሪ ሆቴል ተከናውኗል::

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ምክር ቤት አመራሮች አማካኝነት ለአንድ ቀን ከግማሽ በተካሄደው ጥልቅ ውይይት የሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች ግጭት በዘላቂነት እንዲያበቃ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ በመግባባት ላይ መድረስ ተችሏል::

በውይይቱ ላይ የሁለቱም ህዝቦች የጎሳ መሪዎች፣ ኡጋዞች፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንቱን እና ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንቱን ጨምሮ የፕሬዝደንቱ ልዩ አማካሪ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ውይይቱ የተካሄደ ሲሆን ከመንግስት በኩልም ከሰላም ሚኒስቴር በኩል ታዛቢዎች ታድመውበታል::

የሁለቱም ህዝቦች ከፍተኛ የጎሳ መሪዎች ይህን ስምምነት መሬት ላይ ለማውረድ በሳምንት ውስጥ በጠቅላይ ምክር ቤቱ ሰብሳቢነት ዳግም በመገናኘት የትግበራ ሂደቱን እና ቀጣይ ሂደቱን አቅጣጫ ለማስቀመጥ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል::

የሁለቱ ህዝቦች በሀይማኖትም፣ በባህልም የተቀራረቡ ወንድማማች ህዝቦች ሆነው ሳለ እየተፈጠሩ ባሉ ግጭቶች ለረጅም አመታት የሰው ህይወት እየጠፋ ይገኛል::

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ምክር ቤትም እንደ ሐይማኖት ተቋም የሚጠበቅበትን ኃላፊነትን ለወጣት የሁለቱን ወንድማማች ህዝቦች ግጭት በዘላቂነት ለማስቆም እና መፍትሄ ለማበጀት ሰፊ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል::

በዛሬው እለት የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ ሆኖ በዘላቂነት የሰላሙ አየር በሁሉም ወገኖች ዘንድ ይተነፍስ ዘንድ ሁሉም በዱዓ ሊያግዝ እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል።

ታላቁ አሊም ሼህ አብድልለጢፍ ሸረፈዲን በጠና መታመማቸው ተገለፀ ጄይሉ ቲቪ ሚያዚያ 11/2016   ሼህ አብድልለጢፍ ሸረፈዲን ፣በመዲና ዩንቨርስቲ በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቁና  በወሎ ከሚሴ ...
19/04/2024

ታላቁ አሊም ሼህ አብድልለጢፍ ሸረፈዲን በጠና መታመማቸው ተገለፀ ጄይሉ ቲቪ ሚያዚያ 11/2016

ሼህ አብድልለጢፍ ሸረፈዲን ፣በመዲና ዩንቨርስቲ በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቁና በወሎ ከሚሴ እንዲሁም በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በዳአዋ በርካቶችን በማስተማር እና በሀገር ሽማግሌነት ትልቅ ተሰሚነት ያላቸው ታላቅ አሊም ናቸው።

ሼህ አብድልለጢፍ ሸረፈዲን በሰሜን ኢትዮጵያ ተከስቶ በነበረው ጦርነት ወቅት ህዝቡን በማሰተባበር ለተቸገሩ ወገኖች መሰረታዊ ቁሳቁሶችን በማቅረብ ህዝቡን በጦርነት ውስጥ ሲታደጉ የቆዩ ቢሆንም ለሁለት አመታት በአዋሽ አርባ እና በከሚሴ እስር ቤት ታስረው እንደነበር ይታወሳል።

እስር ቤት ውስጥ በነበሩ ሰአት ህመሙ የጀመራቸው ሲሆን ከእስር ከተፈቱ በኋላ በሀገረ በቱርክዬ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው የነበረ ሲሆን፣አሁን ላይ የህክምና ወጪው ከቤተሰብ አቅም በላይ በመሆኑ በአሊሞች እና የሀገር ሽማግሌዎች የተዊቀረ ኮሚቴ በተከፈተ አካውንት ድጋፍ እንድታደረግላቸው ጥሪ ቀርቧል።

ድጋፍ ለማድረግ፦
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የአካውንት :-1000392652788
ሸኽ ጡሃ ሸኽ መሀመድ
ሸኽ ሁሴን ሀሰን ሱሩር
ሸኽ አህመድ አሊ ሃሰን

ለስራም ሆነ ለትምህርት ዜጎችን ወደ ውጭ ሀገር መላክ በስራ እና ክህሎት ሚኒቴር ኃላፊነት የሚተገበር መሆኑ ተገለጸ።ጄይሉ ቲቪ 11/08/2016 ዓ.ል.   ዜጎችን ለስራም ሆነ ለትምህርት ወደ...
19/04/2024

ለስራም ሆነ ለትምህርት ዜጎችን ወደ ውጭ ሀገር መላክ በስራ እና ክህሎት ሚኒቴር ኃላፊነት የሚተገበር መሆኑ ተገለጸ።ጄይሉ ቲቪ 11/08/2016 ዓ.ል.

ዜጎችን ለስራም ሆነ ለትምህርት ወደ ውጭ ሀገር የመላክ ፍቃድ ለስራና ክህሎት ሚኒስቴር ብቻ የተሰጠ ሃላፊነት መሆኑን በሚኒስቴሩ የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት የኤጀንሲዎች ፈቃድ መስጫ ዴስክ ሃላፊ አቶ ተክሌ ተስፉ አስታውቀዋል።

አሁን ላይ በተለያዩ ከተሞች በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ኤጀንሲዎች ሰዎችን ካናዳና ወደ ሌሎችም የውጭ ሀገራት ስራ እናስቀጥራችኃለን በሚል የሚስተላለፉት ማስታወቂያ ፈጽሞ ፈቃድ የሌለው እና ህገ ወጥ መሆኑን በመጥቀስ በጥቆማና በፍለጋ ሲደረስባቸው እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ሃላፊው ገልጸዋል።

ለኤጀንሲዎች ፈቃድ መስጠቱንም መቆጣጠሩንም የሚመለከተው የመንግስት ተቋም ስራና ክህሎት ሚኒስቴር መሆኑን በመናገር በፌደራልም በክልልም ያሉ ኤጀንሲዎች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፈቃድ ከተሰጣቸው ብቻ ስራው ላይ መሰማራት እንደሚችሉ አቶ ተክሌ ገልጸዋል።

በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች እየተበራከቱ የመጡት ህገ ወጥ ኤጀንሲዎች በጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እርምጃ እንደሚወሰድባቸውና ህጋዊ በሆነ አሰራር ላይ ብቻ ተመስርተው የዜጎችን የስራ ሁኔታ እንደሚያግዙ የዴስክ ሃላፊው አመላክተዋል።

ዜጎችን ወደ ውጭ እንልካለን የሚሉ ህገ ወጦች ምንም አይነት እውቅና የሌላቸው በመሆኑ ሲደረስበት ከፖሊስ ጋር በመሆን እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ተነግሯል።

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት
ድህረ ገጽ፡- https://jeilumedia.com
ዩትዩብ:- https://www.youtube.com/c/JeiluTube/videos
ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/jeilutv
ኢሜል :- [email protected]
ቴሌግራም :- https://t.me/Jeilumedia
ጄይሉ ቲቪ ዛሬን ለተሻለ ነገ

መዲናን የረገጠ ሁሉ የማይረሳቸው ሼክ ኢስማኤል አል ዛይም አረፉ።ጄይሉ ቲቪ 11/08/2016 ዓ.ል   የሳኡዲ አረቢያዋን መዲና ከተማ የረገጠ ሁሉ ያውቃቸዋል አልያም ደግነታቸውን ሰምቷል የሚ...
19/04/2024

መዲናን የረገጠ ሁሉ የማይረሳቸው ሼክ ኢስማኤል አል ዛይም አረፉ።ጄይሉ ቲቪ 11/08/2016 ዓ.ል

የሳኡዲ አረቢያዋን መዲና ከተማ የረገጠ ሁሉ ያውቃቸዋል አልያም ደግነታቸውን ሰምቷል የሚባልላቸው ሼክ ኢስማኤል የማይነጥፍ ችሮታቸው እስከህልፈታቸው ድረስ ዘልቋል።

ለሀጂና ኡምሯ ከተለያየ የአለም ክፍል የመጣ ሙስሊምም ሆነ መዲናን የሚጎበኝ የሌላ እምነት ተከታይ የሼህ ኢስማኤልን የነጻ በረከት ተቋድሷል ነው የሚባለው።

እኝህ አባት ባለፉት 40 አመታት በቀን ከ300 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ውሃ፣ ቡና፣ ወተት፣ ሻይ፣ ዳቦና ቴምር በነጻ ሲያቀርቡ ቆይተዋል።

ኢትዮ ጂቡቲ ባቡር የአገልግሎት የግንባታ ማሽኖችን ለመጀመሪያ ጊዜ ማጓጓዙን አስታወቀ።ጄይሉ ቲቪ 11/08/2016 ዓ.ል.   ድርጅቱ እንዳስታወቀው ከጅቡቲ ናጋድ ባቡር ጣቢያ ተጭነው እንዶዴ ...
19/04/2024

ኢትዮ ጂቡቲ ባቡር የአገልግሎት የግንባታ ማሽኖችን ለመጀመሪያ ጊዜ ማጓጓዙን አስታወቀ።ጄይሉ ቲቪ 11/08/2016 ዓ.ል.

ድርጅቱ እንዳስታወቀው ከጅቡቲ ናጋድ ባቡር ጣቢያ ተጭነው እንዶዴ የባቡር ጣቢያ የደረሱ አምስት ኤክስካቫተሮችን በትላንትናው እለት ለደንበኞች አስረክቧል፡፡

መሰል ጭነት በኢትዮ ጅቡቲ የባቡር አገልግሎት ሲጓጓዝ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ያስታወቀው ድርጅቱ በቅርቡ ተጨማሪ የኮንስትራክሽን ግዙፍ ተሽከርካሪዎች ከጂቡቲ ናጋድ ባቡር ጣቢያ ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ ብሏል።

በተመሳሳይ ሌሎች አዳዲስ አገልግሎት እንደሚያስጀምርም ድርጅቱ ቀደም ሲል ለካፒታል ተናግሯል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት
ድህረ ገጽ፡- https://jeilumedia.com
ዩትዩብ:- https://www.youtube.com/c/JeiluTube/videos
ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/jeilutv
ኢሜል :- [email protected]
ቴሌግራም :- https://t.me/Jeilumedia
ጄይሉ ቲቪ ዛሬን ለተሻለ ነገ

በአሜሪካ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን (የኦሮሞ እና የትግራይና ማኅበረሰብ) አባላት ጦርነት እንዲቆም የሚጠይቅ ሰልፍ አካሄዱ።ጄይሉ ቲቪ 11/08/2016 ዓ.ል.   ዋሺንግተን ዲሲ አካባቢ ...
19/04/2024

በአሜሪካ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን (የኦሮሞ እና የትግራይና ማኅበረሰብ) አባላት ጦርነት እንዲቆም የሚጠይቅ ሰልፍ አካሄዱ።ጄይሉ ቲቪ 11/08/2016 ዓ.ል.

ዋሺንግተን ዲሲ አካባቢ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት፣ የኦነግ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ የነበሩት የአቶ በቴ ዑርጌሳ ግድያን የሚቃወም ሰልፍ እና የሻማ ማብራት ሥነሥርዐት አከናወኑ። ኢትዮጵያ ውስጥ በኦሮሞ ተወላጆች ላይ ይደርሳል ያሉትን ግድያ ተቃውመው ጦርነት እንዲቆም ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል በዚሁ አካባቢ ሰልፍ ያደረጉት ትውልደ ኢትዮጵያ የትግራይ ተወላጆች፣ ጦርነት እንዲቆም፣ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሙሉ ለሙሉ እንዲከበር እና ተገቢው ርዳታ ወደ ክልሉ እንዲገባ የሚጠይቅ ሰልፍ አካሂደዋል ሲል የአሜሪካ ድምፅ ዘገባ ያመላክታል።

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት
ድህረ ገጽ፡- https://jeilumedia.com
ዩትዩብ:- https://www.youtube.com/c/JeiluTube/videos
ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/jeilutv
ኢሜል :- [email protected]
ቴሌግራም :- https://t.me/Jeilumedia
ጄይሉ ቲቪ ዛሬን ለተሻለ ነገ

እስራኤል በኢራን ላይ የአጸፋ ጥቃት ሰነዘረችጄይሉ ቲቪ ሚያዚያ 11/2016   እስራኤል ኢስፋሃን በተባለ የማዕከላዊ አራን አካባቢ ባሉ ወታደራዊ ካምፖች ላይ በድሮኖች ጥቃት መሰንዘሯን አለማ...
19/04/2024

እስራኤል በኢራን ላይ የአጸፋ ጥቃት ሰነዘረችጄይሉ ቲቪ ሚያዚያ 11/2016

እስራኤል ኢስፋሃን በተባለ የማዕከላዊ አራን አካባቢ ባሉ ወታደራዊ ካምፖች ላይ በድሮኖች ጥቃት መሰንዘሯን አለማቀፍ ሚድያዎች እየዘገቡት ነው፡፡

ይህን ተከትሎ ኢራን የጸረ-ሚሳኤል መከላከያ ማስወንጨፏንና የተተኮሱባትን ሦስት ድሮኖች መታ መጣሏን አስታውቃለች።

ኢስፋሃን የኢራን አየር ኃይል እና የኒዩክሌር ጣቢያ የሚገኝ ከተማዋ ሲሆን በአካባቢው የተሰማው ፍንዳታ ኢራን ያስወነጨፈቻቸው የጸረ ሚሳኤል መከላከያ መሆኑን አገሪቱ ባወጣችው መረጃ ገልጻለች።

የእስራኤልን ጥቃት ተከትሎ የአየር በረራዎች ተስተጓጉለው እንደነበርና በአሁኑ ሰዓት በረራ መጀመሩን እንዲሁም አካባቢው ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሱን የአልጃዚራ ዘገባ አመላክቷል።

በፈረንጆቹ ሚያዝያ 1 ቀን እስራኤል ሶሪያ በሚገኘው የኢራን ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ላይ ባደረሰችው ጥቃት 13 ዜጎቿ መገደላቸውን ተከትሎ በእስራኤል ላይ ባሳለፍነው ቅዳሜ 300 ሚሳኤልና የድሮን ጥቃት ማድረሷ ይታወሳል።

ለኢራን ጥቃት እስራኤል አጸፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ ዝታ እንደነበርም የሚታወስ ነው።
የሁለቱ አገራት የሰሞኑ ግጭትን ተከትሎ አገራት ዜጎቻቸውን ወደ እስራኤል እንዳይጓዙ እያስጠነቀቁ ነው።

ከስውር ጦርነት አልፎ ወደ ይፋዊና ቀጥተኛ ግጭት ውስጥ የገባው የሁለቱ አገራት የሰሞነኛ ፍጥጫ በቋፍ ላይ የነበረ የአካባቢውን ሰላምና ጸጥታ ወደለየለት ጦርነት እንዳይከተው ተሰግቷል።

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት
ድህረ ገጽ፡- https://jeilumedia.com
ዩትዩብ:- https://www.youtube.com/c/JeiluTube/videos
ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/jeilutv
ኢሜል :- [email protected]
ቴሌግራም :- https://t.me/Jeilumedia
ጄይሉ ቲቪ ዛሬን ለተሻለ ነገ

በሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ለሚደረገው የአጀንዳ ልየታ የሃይማኖት ተቋማት ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ አጀንዳዎችን ሊለዩ ይገባል ተባለጄይሉ ቲቪ ሚያዚያ 10 ቀን 2016   የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር...
18/04/2024

በሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ለሚደረገው የአጀንዳ ልየታ የሃይማኖት ተቋማት ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ አጀንዳዎችን ሊለዩ ይገባል ተባለጄይሉ ቲቪ ሚያዚያ 10 ቀን 2016

የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሀገሪቱ ያሉ ችግሮችን በምክክር ለመፍታት በሚያደርገው ሂደት ተሳታፊ ከሆኑት ውስጥ የሃይማኖት ተቋማት ተጠቀሾቹ ናቸው፡፡

አሁን ላይ በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የሚሳተፉት የሃይማኖት ተቋማት የአጀንዳ ልየታ በማድረግ ላይ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡

በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ጉባኤ በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ አጀንዳ ልየታ ላይ ባይሳተፍም የእምነት ተቋማት ግን አጀንዳቸውን እንዲለዩ በማማከር እና በመደገፍ ላይ እንደሆነ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ጽሃፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ለጣቢያችን ገልፀዋል፡፡

በሀገራዊ ምክክሩ የሃይማኖት ተቋማት ያላቸው ሚና ከፍተኛ እንደመሆኑ ተቋሙ እያስተባበረ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

በሀገሪቱ የሚፈጠሩ ግጭቶች በዘር ላይ መሰረት ያደረጉ ሲሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ ሃይማኖትን መሰረት ያደረጉ እንደመሆናቸው የሃይማኖት ተቋማት ከዚህ አንፃር ጠቃሚ የሆኑ የአጀንዳ ልየታዎችን ሊያደርጉ ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ የሃይማኖት ተቋማት በምክክሩ ላይ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን መግለፁ የሚታወስ ነው

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት
ድህረ ገጽ፡- https://jeilumedia.com
ዩትዩብ:- https://www.youtube.com/c/JeiluTube/videos
ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/jeilutv
ኢሜል :- [email protected]
ቴሌግራም :- https://t.me/Jeilumedia
ጄይሉ ቲቪ ዛሬን ለተሻለ ነገ

በአለም ተወዳጁ የአረቢካ ቡና ዝርያ ከ600ሺ ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ መገኘቱ በጥናት ተረጋገጠ።ጄይሉ ቲቪ 10/08/2016 ዓ.ል   በአለም ተወዳጅነትን ያተረፈው የአረቢካ ቡና ዝርያ ከ60...
18/04/2024

በአለም ተወዳጁ የአረቢካ ቡና ዝርያ ከ600ሺ ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ መገኘቱ በጥናት ተረጋገጠ።ጄይሉ ቲቪ 10/08/2016 ዓ.ል

በአለም ተወዳጅነትን ያተረፈው የአረቢካ ቡና ዝርያ ከ600,000 ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ደኖች ውስጥ በሁለት ሌሎች የቡና ዝርያዎች ተፈጥሯዊ ውህደት ስለመፈጠሩ ዓለማቀፍ የሳይንስ ተመራማሪዎች ቡድን በጥናት ማረጋገጣቸውን በኔቸር ጄኔቲክስ ላይ የወጣው የምርምር ውጤት ያመላክታል።

ይህ የአረቢካ ቡና ተክል መነሻው ኢትዮጵያ ሲሆን ተመራማሪዎች የዚህን የቡና ተክል የጂኖሚክ መረጃን በመጠቀም የቡናውን የረዥም ጊዜ ታሪክ ለማጥናት እና በዘመናዊ መንገድ ከሚመረቱ ሌሎች የቡና ተክሎች ጋር ያለውን ግንኙነት ለመለየት ጥናት ማድረጋቸው ተገልጿል።

በዚህም የአረቢካ ቡና ከ "Coffea canephora" እና " Coffea eugenioides " ከተባሉ የቡና ዝርያዎች ከእያንዳንዳቸው ሁለት ክሮሞዞሞችን በመውሰድ ከ600ሺ አመታት በፊት ስለመፈጠሩ የሳይንስ ተመራማሪዎቹ በተጠቀሙት የጊዜ ስሌት ቀመር ማረጋገጣቸውን ተጠቁሟል።

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት
ድህረ ገጽ፡- https://jeilumedia.com
ዩትዩብ:- https://www.youtube.com/c/JeiluTube/videos
ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/jeilutv
ኢሜል :- [email protected]
ቴሌግራም :- https://t.me/Jeilumedia
ጄይሉ ቲቪ ዛሬን ለተሻለ ነገ

እስራኤል ለኢራን ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ውሳኔ ማሳለፉ ግልፅ ነው ሲሉ ዴቪድ ካሜሮን ተናገሩ ጄይሉ ቲቪ ሚያዚያ 10/2016   የብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን እስራኤል ለኢራን...
18/04/2024

እስራኤል ለኢራን ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ውሳኔ ማሳለፉ ግልፅ ነው ሲሉ ዴቪድ ካሜሮን ተናገሩ ጄይሉ ቲቪ ሚያዚያ 10/2016

የብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን እስራኤል ለኢራን ሰው አልባ እና ሚሳኤል ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ውሳኔ እንዳሳለፈች ግልፅ ነው ብለዋል። ካሜሮን የበቀል እርምጃው “በሚቀንስ” መንገድ እንደሚከናወን ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል። ካሜሮን በእስራኤል ውስጥ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እስራኤላውያን እርምጃ ለመውሰድ እየወሰኑ እንደሆነ ግልጽ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

የአፀፋ ጥቃቱ ግን በተቻለ መጠን ውጥረትን ሊያባብስ በማያስችል መንገድ እንደሚያደርጉት ተስፋ እናደርጋለን ሲሉ ገልፀዋል።ብሪታንያ በኢራን ላይ የተቀናጀ ማዕቀብ ማየት ትፈልጋለች በማለት የቡድን ሰባት ሀገራት ግልጽ የሆነ የማያሻማ መልእክት ለኢራን ሊሰጣር ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል።

ከዚህ በኋላ ስለሚሆነው ነገር ሃሳባችንን በግልፅ ማሳየታችን ትክክል ነው፣ነገር ግን እስራኤላውያን እርምጃ ለመውሰድ እየወሰኑ እንዳለ ግልጽ ነው ብለዋል። ትናንት እንዳልኩት ብልህ እና ጠንካራ በሆነ መንገድ እስራኤል ምላሽ መስጠት ይኖርባታል ሲሉ ተደምጠዋል። እውነተኛው የእስራኤል ፍላጎት በሃማስ ላይ እንደገና ማተኮር ነው,፤ ታጋቾቹን ማስለቀቅ እና, እርዳታ እንዲገባ የጋዛ ግጭት ለአፍታ ማቆም ነው ሲለ አክለዋል።ሜሮን በኢራን ላይ የተቀናጀ ማዕቀብ እንዲጣል በሚመክረው የቡድን 7 ሚኒስትሮች ስብስብ ለመታደም ከእስራኤል ቆይታቸው በኃላ ወደ ጣሊያን ተጉዘዋል።

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት
ድህረ ገጽ፡- https://jeilumedia.com
ዩትዩብ:- https://www.youtube.com/c/JeiluTube/videos
ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/jeilutv
ኢሜል :- [email protected]
ቴሌግራም :- https://t.me/Jeilumedia
ጄይሉ ቲቪ ዛሬን ለተሻለ ነገ

Address


Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Telephone

+251 91 122 6885

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jeilu Tv /ጄይሉ ቲቪ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Jeilu Tv /ጄይሉ ቲቪ:

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Opening Hours
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share