Daily News

Daily News ትኩስ መረጃዎችን እናደርሳለን

ይህ ካርታ በሃያ ዓመታት ጊዜ ውስጥ የንስርን እንቅስቃሴ ያሳያል።መከታተያው በሩሲያ ውስጥ ተጭኖ በመጨረሻ ከሃያ ዓመታት በኋላ በህፃናት ሸለቆ, ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ሞተ.ይህ ንስር በሃያ አመ...
14/08/2022

ይህ ካርታ በሃያ ዓመታት ጊዜ ውስጥ የንስርን እንቅስቃሴ ያሳያል።
መከታተያው በሩሲያ ውስጥ ተጭኖ በመጨረሻ ከሃያ ዓመታት በኋላ በህፃናት ሸለቆ, ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ሞተ.
ይህ ንስር በሃያ አመት ህይወቱ ምን ያህል እንደተጓዘ እና በብዙ ሀገራት የተጓዘበትን ትልቅ ርቀት ማየት በጣም የሚያስደስት ነው።
በተጨማሪም አስደናቂው ማስታወሻ ባሕሩን ከመሻገር የተቆጠበበት መንገድ ነው።
በመሬት ላይ መብረርን ለመቀጠል ረጅሙ መንገድ የት እንደተወሰደ በግልፅ ማየት ይችላሉ።
ብዙ የአእዋፍ ዝርያዎች ሙሉ ሕይወታቸውን በባህር ላይ ሲበሩ ያሳልፋሉ, ነገር ግን አንድ ነገር በእርግጠኝነት ነው እና ይህ ንስር በእርግጠኝነት ባህርን ከመሻገር ተቆጥቧል.
ተፈጥሮ ድንቅ ነው!♥️

09/08/2021
Samantha Power: The goddess and bringer of war to Ethiopia (U.S.-E.U.-NATO war plan exposed)እኛ ኢትዮጵያውያን ሁሌም ነፃ ነን። ነፃ መሆ...
06/08/2021

Samantha Power: The goddess and bringer of war to Ethiopia (U.S.-E.U.-NATO war plan exposed)

እኛ ኢትዮጵያውያን ሁሌም ነፃ ነን። ነፃ መሆናችንን እንቀጥላለን። ዛሬ ድሆች ልንሆን እንችላለን። ነገ እኛ እንበለጽግና የአፍሪካ አክሊል ጌጥ እንሆናለን። ለዓለም ምሳሌ እንሆናለን። እኛ ኢትዮጵያዊነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለእነዚህ የሃብሪስት ታዳጊዎች እናስተምራቸዋለን… ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ግንቦት 15 ቀን 2021 በኢትዮጵያ ጉብኝት ዋዜማ የዩኤስኤአይዲ ኃላፊ ሳማንታ ፓወር በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት አውጀዋል።

በአፍሪካ ምርጥ 10 ወጣት የህዋ ተመራማሪዎች ዝርዝር ውስጥ 2 ኢትዮጵያውያን ተካተቱ*********************ትንሳኤ አለማየሁ እና ቤተልሔም ግርማ የተባሉ ሁለት ኢትዮጵያውያን የህዋ ...
05/08/2021

በአፍሪካ ምርጥ 10 ወጣት የህዋ ተመራማሪዎች ዝርዝር ውስጥ 2 ኢትዮጵያውያን ተካተቱ
*********************
ትንሳኤ አለማየሁ እና ቤተልሔም ግርማ የተባሉ ሁለት ኢትዮጵያውያን የህዋ ምርምር ባለሙያዎች በአፍሪካ ምርጥ 10 እድሜያቸው ከ30 በታች የሆኑ የህዋ ምርምር ባለሙያዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን ኢን አፍሪካ ዘርዝሯል።
የ29 ዓመቷ ቤተልሔም በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ውስጥ በረዳት ተመራማሪነት እያገለገለች የምትገኝ ሲሆን በተለያዩ የምህንድስና ፕሮጀክቶች ላይ ተሳታፊ ስለመሆኗም ተነግሯል።
የ23 ዓመቱ ትንሳኤ በበኩሉ የመጨረሻ ዓመት የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ተማሪና በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ነው።
ላለፉት ሦስት ዓመታትም የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት-የመቀሌ ካውንስ (EiT-M) አባል ሆኖ ቆይቷል። በተጨማሪም በበርካታ ዓለም አቀፍ ስልጠናና ትምህርቶች ላይ ተሳታፊ ለመሆን በቅቷል።
ትንሳኤ በአሁኑ ሰዓት ከስፔስ ቴክኖሎጂ ፎር ኧርዝ አፕሊኬሽንስ (STEA) ጋር በመቀናጀት ሳተላይት ላይ ተንተርሶ የእርሻ ግብርና እና ጤና ቁጥጥር አገልግሎቶችን በሚሰጥ ስርዓት ላይ እየሰራ ይገኛል።
በዝርዝሩ ውስጥ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ከአልጄሪያ፣ ናይጄሪያ፣ ግብፅ፣ ሞሪሺየስ፣ ዚምቧብዌ፣ አንጎላ እና ሴራሊዮን የተውጣጡ ወጣት ባለሙያዎች ሲካተቱ እያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት ወጣቶችን በማስመረጥ ግብፅ እና ኢትዮጵያ ብቸኛዎቹ ሀገራት ሆነዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ከዚህ ቀደም በግማሽ ሚሊዮን የሚጠጋ ልገሳችንን በመጨመር ተጨማሪ 1.2+ ሚሊዮን የጆንሰን እና ጆንሰን ክትባቶችን ለኢትዮጵያ ሰጠች። የኮቪድ -19 ክትባቶችን ከኢትዮጵያ በማ...
05/08/2021

ዩናይትድ ስቴትስ ከዚህ ቀደም በግማሽ ሚሊዮን የሚጠጋ ልገሳችንን በመጨመር ተጨማሪ 1.2+ ሚሊዮን የጆንሰን እና ጆንሰን ክትባቶችን ለኢትዮጵያ ሰጠች። የኮቪድ -19 ክትባቶችን ከኢትዮጵያ በማድረስ ሕይወት አድን በሆነው ሥራ በመሳተፋችን ክብር ይሰማናል። የአሜሪካ ሰዎች። የኢትዮጵያ የቅርብ የጤና አጋር እንደመሆናችን መጠን ብዙ ሰዎችን ለመከተብ ፣ ህይወትን ለማዳን እና ወረርሽኙን ለማጥፋት ቁርጠኛ ነን ብለዋል አምባሳደር ጌታ ፓሲ።

አሸባሪው ህወሓት የሚያሰራጨውን ሃሰተኛ መረጃና የሚያካሂደውን የሰብአዊ መብት ጥሰት አለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይረዳዋልሐምሌ 29 ቀን 2013 (ኢዜአ) አሸባሪው ህወሓት የሚያሰራጨውን ሃሰተኛ መ...
05/08/2021

አሸባሪው ህወሓት የሚያሰራጨውን ሃሰተኛ መረጃና የሚያካሂደውን የሰብአዊ መብት ጥሰት አለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይረዳዋል
ሐምሌ 29 ቀን 2013 (ኢዜአ) አሸባሪው ህወሓት የሚያሰራጨውን ሃሰተኛ መረጃና በትግራይ ክልል የሚያካሂደውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በተመለከተ አለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንደሚረዳው ተገለጸ።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የውጭ ቋንቋዎች መገናኛ ብዙሃን ሀላፊ ቢለኔ ስዩም ዛሬ ለውጭ እና ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።
ብሌኒ ስዩም በመግለጫቸው መንግስት በትግራይ ክልል ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ የሰብአዊ ድጋፍ ያለምንም የጸጥታ ችግሮች እንዲደርሱ እያደረገ ነው ብለዋል።
ሆኖም ድጋፎቹ ከደህንነትና ከጸጥታ ጋር በተያያዘ አስፈላጊ የሆኑ የደህንነት ስራዎችን በማካሄድ እንደሚንቀሳቀሱ ገልጸዋል።
“ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ ችግሮችን አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን የተሳሳተና የተዛባ ዘገባ በማቅረብ ከፀሐይ በታች የሚፈጠሩ ሁሉንም ችግሮች ለመንግስት የመስጠትና መንግስትን ተጠያቂ በማድረግ ተግባር ላይ ተሰማርተዋል” ሲሉ ነው ገለጹት።
አሸባሪው ህውሃት ባለው አለም አቀፍና የአገር ውስጥ ትስስር ሃሰተኛ መረጃዎችን እያሰራጨ እንደሚገኝ አመልክተው “የሚሰራጨው የተሳሳተ መረጃና በዜጎች ላይ የሽብር ቡድኑ የሚያካሂደውን የሰብአዊ መብት ጥሰት አለም አቀፉ ማህበረሰብ ቀስ በቀስ መረዳቱ አይቀርም” ብለዋል።
በሽብር ቡድኑ አገዛዝ የትግራይ ክልል በጭቆናና በመብት ጥሰት ውስጥ መኖሩን አመልክተው፤ ህበረተሰቡ ለዓመታት በሴፍቲነት እና በሰብአዊ ድጋፎች መቆየቱን አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ በተወካዮች ምክር ቤትም ድርጅቱ በሚፈጽማቸው ተግባራት በአሸባሪነት መፈረጁን አስታውሰዋል።
በሌላ በኩል በጎ ፈቃደኞች የሽብር ቡድኑን እንቅስቃሴ ለህይወታቸው ሳያሳሳቸው የሰብአዊ ድጋፍ ተግባራትን በክልሉ እያከናወኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
የሽብር ቡድኑ የሰብአዊ ድጋፎች መደናቀፍ ሳያሳስበው ወደ አጎራባች አፋርና አማራ ክልሎቸ ጥቃት በማድረስ ዜጎች እንዲፈናቀሉ ማድረጉንም ነው የገለጹት።
ከአሸባሪው ቡድን ጋር ትስስር ባላቸው አካላትም ኢኮኖሚያዊ አሻጥር ለማድረስ መንቀሳቀሱንና ሃሰተኛ መረጃዎችን እየሰራጨ እንደሚገኝም ተመልክቷል።
በዚህም ፍርሃት እንዲፈጠርና በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ደግሞ የኢትዮጵያን ሁኔታ በተመለከተ የተዛባ ገጽታ በመገንባት ላይ ይገኛል ብለዋል።
መንግስት በትግራይ ክልል የሚያደርገው ድጋፍ በከፍተኛ ሁኔታ ተደራሽ መሆኑንም ገልጸዋል።
መንግስት በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ ጥቃት መድረሱን ተከትሎ ወደ ህግ ማስከበር ዘመቻ ተግባር መግባቱን አሁንም ቢሆን አንዳንድ አካላት ማየት አልፈለጉም” ሲሉ አመልክተዋል።
በህግ ማስከበሩ ዘመቻው ወቅት ክልሉን መልሶ ለማቋቋም መንግስት 100 ቢሊዮን ብር ማውጣቱንም ገልጸዋል።

 #የእኛ አንበሳ አንተ ባትኖር ኑሮ ምን ሊውጠን ነበር ።Ms powerን በመጣችበት እግሯ ስለላክልን እናመሰግናለን መሪያችን
04/08/2021

#የእኛ አንበሳ አንተ ባትኖር ኑሮ ምን ሊውጠን ነበር ።
Ms powerን በመጣችበት እግሯ ስለላክልን እናመሰግናለን መሪያችን

ኤርትራ ጦሯን ወደሱዳን አስጠጋች !!ለአሸባሪዉ የህወሃት ቡድን በሱዳን በኩል መንገድ ለማስከፈት አሜሪካ ሳማንታን ወደኢትዮጵያ መምጣቷን ተከትሎ ምናልባት የኢትዮጵያ መንግስት ተፅእኖዎች በመፍ...
04/08/2021

ኤርትራ ጦሯን ወደሱዳን አስጠጋች !!
ለአሸባሪዉ የህወሃት ቡድን በሱዳን በኩል መንገድ ለማስከፈት አሜሪካ ሳማንታን ወደኢትዮጵያ መምጣቷን ተከትሎ ምናልባት የኢትዮጵያ መንግስት ተፅእኖዎች በመፍራት ሃሳቡን ቢቀበል በሱዳንና በትግራይ የሚገኙ በአስር ሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿን ለመጠበቅ
በስሜን-ምዕራብ በኩል አዋሳኝ ወደሆነዉ የሱዳን ድንበር ጦሯን አስጠግታለች
የኤርትራ ጦር ሃይሎች አዛዥም
የኢትዮጵያ መከላከያ ወደ ትግራይ የሄደው ህግ ለማስከበርና በተለይም የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ያደረሰውን የወንጀል አመፅ መሪዎችን ለመያዝ ፣ ለህግ ለማቅረብ፣ ሰላምን ለማስፈን እና የህግ የበላይነትን ለማስከበር ነው መሆኑን በመገንዘብ አሜሪካ ለአሸባሪው የህወሓት ቡድን የምታደርገውን ድጋፍና ሌሎች ምዕራብያዊያን ጣልቃ ገብነታቸውን በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ጠይቀዋል.

There ain’t no such thing as a free lunch (By Abebe Gellaw) #ወ / ሮ ፓወር በሰሜናዊ ኢትዮጵያ አውዳሚ ጦርነት እየተባባሰ ባለበት ወቅት በረሃብ የተጋለጡት...
04/08/2021

There ain’t no such thing as a free lunch (By Abebe Gellaw)

#ወ / ሮ ፓወር በሰሜናዊ ኢትዮጵያ አውዳሚ ጦርነት እየተባባሰ ባለበት ወቅት በረሃብ የተጋለጡትን ለመርዳት በሚችሉ መንገዶች ላይ ብቻ ያተኮረች አትመስልም። እሷም የፖለቲካ ጨዋታዎችን እየተጫወተች ነው። ከአሜሪካ ወይም ከሌሎች የምዕራባውያን አገሮች የሚደረግ እርዳታ በነፃ አይመጣም። እነሱ እንደሚሉት ፣ “ነፃ ምሳ የሚባል ነገር የለም”።

 # እነሆ_በግልፅ_የሚዋጉንን_በግልፅ ማስረጃ▬▬▬▬▬▬▬በትግራይ በኩል በግልፅ የሚዋጋን ስውሩና አደገኛው እጅ የማነው ብሎ መጠየቅ አያስፈልግም! ከሚቆጠርና ከሚታይ ማስረጃ ጋር በአደባባይ ደ...
04/08/2021

# እነሆ_በግልፅ_የሚዋጉንን_በግልፅ ማስረጃ
▬▬▬▬▬▬▬
በትግራይ በኩል በግልፅ የሚዋጋን ስውሩና አደገኛው እጅ የማነው ብሎ መጠየቅ አያስፈልግም! ከሚቆጠርና ከሚታይ ማስረጃ ጋር በአደባባይ ደምቆ ተፅፎልሀል። እስኪ የአሜሪካንን በኢትዮጵያ ላይ የተሰጡ መግለጫዎች እንቁጠራቸው።
በነገርህ ላይ ባይደን እስኪመጣ ብቻ ሳይሆን፣ ከመጣም በኋላ በጦርነቱ ላይ የአሜሪካ መንግስት ምንም አላለም ነበር። እና ከመቼ ጀምሮ የተሰጡ ናቸው? ብሊንከን ቢሮውን ከተረከቡ በኋላ። ብሊንከን ቢሮውን ከተረከበ በኋላ መስጠት መጀመራቸው ብቻ ሳይሆን ... ቁጥሩም አስደንጋጭ ነው።
የባይደን አስተዳደር ወደ ስልጣን ከመጣ 32 ሳምንቱ ነው። በዚህ ጋዜ ውስጥም: በኢትዮጵያ ላይ ብቻ:- 28 press briefing ... 23 press release ... ብሊንከን ብቻውን ደግሞ 6 መግለጫዎችን በኢትዮጵያ ላይ በ32 ሳምንት ውስጥ ሰጥቷል. .. በዚህ ሁሉ ጊዜ ውስጥ በሱዳን ላይ 9 ... በግብፅ ላይ ደግሞ 14 ጊዜ ብቻ ጋዜጣዊ መግለጫዎችን አውጥተዋል።
የመግለጫዎቹ ብዛት፣ ከኛ መንግስት በላይ ስለ እኛ ... ከማነኛውም ሀገር በላይ ስለ ኢትዮጵያ ... በዘመናቸው ሁሉ ከሰጡት ይልቅ በዚህ 32 ሳምንታት ውስጥ እነ ብሊንከን ከመጡ በኋላ ብቻ የተሰጠው የሚበልጥበትን እንቆቅልሽ እንዴት እንረዳው? ይህ ቡድን የሚመራው የአሜሪካንን ወይስ የኢትዮጵያን ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት?!
ስለዚህ ጉዳዩ የት ነው ያለው? እነ ብሊንከን ጋር! የነሱ ቡድን አባላትና አለቆች እነማን ናቸው?
ራይስ (የቡድኑ መሪ)
ብሊንከን
ሳማንታ ፓወር እና መሰሎቻቸው...
ከቡድኑ ዘዋሪት በመነሳት ነጭ ወያኔ በላቸው። በግልፅ የሚዋጉን አሜሪካ ዙፋን የሰጠቻቸው ነጭ ወያኔዎች ናቸው። የሚዋጉህ ሰዎች በግልፅ አይን ያወጣ ቅኝ ግዛት ላይ ናቸው።
# የነመለስ ያረጁ ወዳጆች የጠነሰሱትና የሚመሩት ያረጀ ሴራ ... ላፈጀው አስተሳሰብና ስርዓት ሲባል የሚሟገቱ ናቸው። ይህ የግፈኞች ማህበር ነው። ስንዴው ሽፋን ነው። ዋነኛዋ አጀንዳ ፖለቲካዋ▯ጥይቷ▯በረሀብ መነገዷ ናት።
ሌላ ተጨባጭ ማስረጃ እነሆ:-
በእርዳታ ስም የምትመጣው ሴትዮ የምትጎበኘው እነማንን ነው? የተራቡትን እንዳይመስልህ? ህወሓታውያንን ብቻ ነው። ጉዳያቸው ረሀብ ቢሆን .. የሚጮሁለት ሰብአዊ እርዳታ ቢሆን፣ ከአፋርና ከአማራ ክልል ብቻ ከ300ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለው በረሀብ ላይ አሉ። በመላው ኢትዮጵያ በራሷ የወያኔ ሴራ የተራቡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች አሉ። እነዚህን ልይ አትልም።
ጉዳዩ ሌላ ነዋ! ለደረሱት ድራማ የሚጠቅማቸው ላይ ብቻ ነው የሚተውኑት። ስለተቀረው ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን፣ ስለ ዓለም ረሀብም ቢሆን አይገዳቸውም! በማስረጃ እንየው። በዓለም ላይ በ55 ሀገራት ውስጥ ከ68 ሚሊየን በላይ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልገውና ለረሀብ የተጋለጠ ሰው አለ። የኛ በጦርነት ነው ካላችሁ፣ ከዚህ ቁጥር ውስጥ 2/3ኛው በተመሳሳይ በጦርነት ለረሀብ የተጋለጠ ነው። እና ለምን የትግራዩ ብቻ ከዚህ ሁሉ የዓለም ህዝብ ተለይቶ ትኩረት ሳበ?! መልሱ ወደ ተዋጊዎችህ ይመራሀል።

የህወሃት አሸባሪ ቡድን ስርአት የሚይዝ ከሆነ መንግስት በየትኛውም አማራጭ ለትግራይ ህዝብ ሰብአዊ ድጋፍ ማቅረብ ይችላል።*******************(ኢፕድ)ለጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት የ...
04/08/2021

የህወሃት አሸባሪ ቡድን ስርአት የሚይዝ ከሆነ መንግስት በየትኛውም አማራጭ ለትግራይ ህዝብ ሰብአዊ ድጋፍ ማቅረብ ይችላል።
*******************
(ኢፕድ)
ለጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት የአሜሪካ መንግሥት የተራድኦ ድርጅት ኃላፊ ሳማንታ ፓዎር ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱም ወቅት በትግራይ ክልል በተፈጠረው ሁኔታና የህወሃት አሸባሪ ቡድን እየፈጠረ ባለው ችግር ዙሪያ ለሃላፊዋ ሰፊ ገለፃና ማብራሪያ እንደተደረገላቸው የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል ገልጸዋል።
የአሜሪካ መንግሥት የተራድኦ ድርጅት ኃላፊ ሳማንታ ፓዎር ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው የህወሃት አሸባሪ ቡድን እየፈፀመ ያለውን ጥፋት በትክክል እንዲረዱ ማስቻሉን ነው የጠቆሙት።
የህወሃት አሸባሪ ቡድን በአገር ላይ በፈጠረው የሀገር የህልውና አደጋ መንግስት ተገዶ ወደ ጦርነት መግባቱንም እንዲረዱ ተደርጓል ብለዋል። ሆኖም የህወሃት አሸባሪ ቡድን በአገሪቱና በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖርና ዜጎች ለችግር እንዲጋለጡ በጥፋት መንገድ መቀጠሉን አስረድተናቸዋል ብለዋል ወይዘሮ ሙፈሪያት።
ለተራድኦ ድርጅት ኃላፊዋ በተደረገላቸው ገለፃ የህወሃት አሸባሪ ቡድን ስርአት የሚይዝ ከሆነ መንግስት በየትኛውም አማራጭ ለትግራይ ህዝብ ሰብአዊ ድጋፍ ማቅረብ እንደሚችል አረጋግጠውላቸዋል።
በትግራይ ክልል ለሚደረገው ሰብአዊ ድጋፍ በአግባቡ እንዳይደርስ አሸባሪ ቡድኑ እያስተጓጎለ መሆኑን ማስረዳታቸውን አመልክተው፤ ቡድኑ ከእኩይ አላማው የሚታቀብ ከሆነ መንግስት ለህዝቡ ማንኛውንም ሰብአዊ ድጋፍ እንደሚያደርስ አረጋግጠንላቸዋል ነው ያሉት ሚኒስትሯ።
አሸባሪው ህወሃት በመንግስት የተሰጡትን የሰላም አማራጮች እና የመንግስትን የተናጠል ተኩስ አቁም ባለመቀበል በጥፋቱ መቀጠሉን ሃላፊዋ እንድረዱ ተደርጓል።
ቡድኑ በከፈተው ጦርነት በአማራ እና አፋር ክልሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተፈናቅለው ለከፍተኛ ችግርና እንግልት መዳረጋቸውንም አስረድተናቸዋል ብለዋል።
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ለተፈጠሩት ወቅታዊ ችግሮች ከጅምሩ አስካሁን የህወሃት የሽብር ቡድን ጥፋት መሆኑን ማስረዳት መቻሉን የሰላም ሚኒስትሯ ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቦአል።

Address


Telephone

+251988020093

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Daily News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Daily News:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share