Yo ትረካ

Yo  ትረካ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Yo ትረካ, Media, .
(2)

ሳልሳዊ ክፍል 29ቴሌግራም ላይ ተለቋል ተቀላቀሉንhttps://t.me/kiya2313
10/07/2022

ሳልሳዊ ክፍል 29ቴሌግራም ላይ ተለቋል
ተቀላቀሉን

https://t.me/kiya2313

እንማር:Biz Gitar:ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ (የሸዋ ልጅ) biz gitarየቀድሞዋ የአለሜ ነሽ እና የፅናት ደራሲሳልሳዊክፍል 19 (አስራ ዘጠኝ)         ፨ "ዶክተር ችግር አለ ምነው ...
08/07/2022

እንማር:
Biz Gitar:
ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ (የሸዋ ልጅ) biz gitar

የቀድሞዋ የአለሜ ነሽ እና የፅናት ደራሲ

ሳልሳዊ

ክፍል 19 (አስራ ዘጠኝ)

፨ "ዶክተር ችግር አለ ምነው በሀሳብ ነጎድክ" አሉ የዕዝራ እናት ዶክተሩ ወደ አስሚ ዞሮ "አስሚ ከዕዝራ ጋር ስትሄዱ ያጋጠመሽ ነገር ካለ አሁኑኑ ንገሬኝ" አለ። ወደ ዕዝራ እናትም ዞር ብሎ "ማዘር የሆነ የገባኝ ነገር አለ" አላቸው አይኑን ከአስሚ ነቅሎ የዕዝራን እናት ጋር ተክሎ። የዕዝራ አባት "ምንድነው የገባህ ዶክተር" አሉት። "እሱን አስሚ አሁን ትነግረናለች አስሚ ከዕዝራ ጋር እየሄድሽ ያጋገመሽ ነገር ካለ እስቲ ንገሪኝ" አላት። አስሚም ከዕዝራ ጋር ስትሄድ ያጋጠማትን አንዱንም ሳታስቀር ተናገረች። ሁሉም ደነገጡ ዶክተሩ "ጠረጥሬ ነበር ይሄው አሁን በቃ ዕዝራን ትንሽ ፋታ እንስጠውና ከዛ ግን ወደ ሀይምሮ ህሙማን መግባት አለበት" አለ ማንም ምንም ማለት አልቻለም ዝም ነው ያሉት። ዶክተሩ "እናቴ ያሰባችሁት ነገር ከተሳካ ስለ ትዳራችን ወስነን እንድንነግራት አደራ ብላ ደጋግማ ነው የለመነችኝ እኔና አስሚም ወደ እዚህ እየመጣን መጋባት እንዳለብን ወስነናል ከሶስት ወር በኋላ እንጋባለን" አለ። የዕዝራ እናት እና አባትም "በጣም ደስ ይላል" አሉ እኩል። አስሚም "እናመሰግናለን በቃ አሁን የግድ መሄድ እና እረፍት ማረግ አለብኝ በጣም ደክሞኛል" አለች። ዶክተሩም ብድግ እያለ እና ለመሄድ እየተሰናዳ "በቃ እኔም ለሁለት ወር ከግማሽ ያክል ወደ ብራዚል ለአንድ ስራ እሄዳለሁ ሰረጋችን ወር ከአስራ አምስት ቀን ሲቀረው እመጣለሁ እስከዛው በቃ ልሰናበታቹ ዕዝራን ደውዬም ቢሆን አወራዋለሁ ተነሽ አስሚ አንቺንም ላድረስሽ" አላት። አስሚ የዕዝራን እናት ስማቸው አባቱን ጨብጣቸው ተሰናብተዋቸው ሄዱ።
፨አስሚ እና ዶክተሩ መንገድ ላይ ናቸው። ዝምም ከተባባሉ በኋላ ዶክተሩ "ምነው አስሚዬ የተፈጠረ ነገር አለ በጣም አኩረፈሻል" አላት። አስሚ "ቆይ ስለምን እና ስለየትኛው ጉዞ ነው የምታወራው እ ቆይ ለእኔ ምንም ነገር ስለ ጉዞህም ሳትነግረኝ ከእነሱ ጋር ነው የምትነግረኝ" አለችው። ዶክተሩ ያለ ማቋረጥ ስቆ ስቆ ስቆ ሲወጣለት "እንዴ አስሚ ቆይ የምረሽኝ ነው?" አላት። አስሚ "ቆይ ምን ያስቅሀል" አለችው። ዶክተሩም "እንዴ ወደ እዝህ እየመጣን መኪና ውስጥ ተኝተሽ ተደውሎልኝ ለአስቸኳይ የሙያ ጉዳይ ወደ ብራዚል ትሄዳለህ ሲባል ተኝተሽ "አስሚ ሰማሽ አደል " ስልሽ "ሰምቻለሁ ሰምቻለሁ ጥሩ ነው አላልሽኝም እንዴ ምን ነካሽ" አላት። አስሚ ግራ ገብቷት "አትቀልዳ ሀኪሜ ቆይ ለምን ትቀልዳለህ ስትለው"ፈገግ ብሎ " ወላሂ አስሚዬ አለ ምን ነካሽ ተኝተሽ ነበር በእንቅልፍ ልብሽ ነው ማለት ነው" አለ። አስሚ "እና ነግረከኝ ነበር?" አለችው። እየሳቀ "አዎ አስሚዬ" ብሎ ስቅስቅ ብሎ ሳቀ።
፨ ሰአታት ቀናት እና ወራት አለፉ።
አሁን ላይ አስሚ እና ዶክተር ሊሞሸሩ ነው። የዶክተሩ ቤት በጣምምም ቅውጥጥ ብሏል። ዶክተሩም በጣም ደስ ብሎታል። ምክንያቱም ዛሬ ላይ የሚወዳት ሴትን ለዘላለም የግሉ ሊያረጋት ነው። አስሚም በበኩልዋ ልእልት መስላላች እሷም ከጎኑዋ ንጉስዋን ዘላለማዊ ልታረገው ነው። ሁሉም ሰው ደስተኛ ነው። የእነ ዕዝራ ቤትም ቤቱ በአንድ እግሩ ቆሞል። እነ አስሚ የሰረግ ስረአት ጋር ለመሄድ። ዕዝራ እና አባቱ ጥቁር ሱፍ አረገዋል የዕዝራ እናት ደሞ የሀበሻ ቀሚስ ለብሰው። ሰራተኛቸውም የሚያምር ቀሚስ አረጋ ድግሱ ጋር ለመሄድ ተሰናድተዋል።
፨ በጣም የሚያምር አዳራሽ ላይ አስሚ እና ዶክተሩ ዙፍናቸው ጋር ተቀምጠዋል። ከቆይታ በኋላ ሚዜዎቹ ተነስተው።
ያምራል ሊናችን
ኧረ ያምናል ሊናችን
ኧረ ያምራል ሊናችን
ያምራል ሊናችን
የእኛማ አስሚዬ
ያምራል ሊናችን ኖራለች በሱና......
እያሉ ሲቀውጡት አስሚ እና ዶክተሩም ተነስተው ማጨብጨብ ጀመሩ። በጣም ደስስ የሚል ድግስ ነበር። ድግሱ ላይ ያሉት ሴቶች በሙሉ አይናቸውን ከዕዝራ አልነቅል አሉ። ዕዝራ ግን ዞር ብሎም አላያቸውም። አስሚ እና ዶክተሩ በሴቶቹ ሁኔታ እየተሳሳቁ ነው። አስሚ ወደ ዕዝራ ስታይ ዕዝራ ፊቱ ሲቀያየር እና እጁ ሲንቀጠቀጥ አየችው በድንገት የፍጥነት እረምጃ እየተራመደ ከአዳራሹ ሲወጣ ስታየው አስሚ ያን ጊዜ አስታወሰችው። "ሀኪሜ መጣው" ብላ በፍጥነት እየሮጠች ሄደች። ዶክተሩ ተከትሏት ወጣ። ሁሉም ሰው በሁኔታቸው ተገሞ መንሾካሾክ ጀመሩ። ግማሹ ውጪ ወጥቶ በአይኑ ተከተላቸው። ዕዝራ በፍጥነት እየተራመደ ነው ዶክተሩ እና አስሚ ልባቸው እስኪጠፈ እሮጠው ደረሱበት። የዕዝራ እናት፣ አባትም እና ሰራተኛ መሮጥ እያቃታቸው በመከራ ሩጫ እየሮጡ ነው። ዶክተሩ ዕዝራ ጋር ደረሶ እጁን ሲይዘው። ዕዝራ በይበልጥ የዶክተሩን እጅ ይዞ ልክ አስሚን በጉልበት ጭምቅ አረጎ ይዞ እንደሄደው መሄድ ጀመረ። ዶክተሩ "ዕዝራ ወዴት እየሄድን ነው?" አለው። ዕዝራ ወደፊት ፍጥጥ ብሎ እያየ። "ተመልከታት እየሮጠችም እየሄደችም አደለም ብሮጥ ትሮጣለች ስለ እዚህ ልክ እንደ እሷ ሳንሮጥም ሳንራመድም ሳናሰደነግጣት እንደረስባታለን" አለ። ዶክተሩ "ማን ጋር?" አለው። ዕዝራ "ሲማይ ጋር ነዋ" አለና እረምጃውን አቀዝቅዞ በዝግታ መራመድ ጀመረ። የዶክተሩን እጅም ላላ አረጎ ያዘው። ዕዝራ ተረጋጋ፤ ዕዝራ ሰከን አለ።
ዶክተሩም " እሺ አሁን እንመለስ" ሲለው። "ሄደች በቃ እንመለስ" ብሎ ተመለሰ።
፨ ዶክተሩ እና ዕዝራ ተመልሰው መጡ። አስሚ መንገዱ ላይ የዕዝራን እናትና አባት እስከ ሰራተኛዋ እያረጋጋቸው ነው። ዕዝራ ልክ እነሱ ጋር ሲደረስ አራቱም ዕዝራን አቀፋት እና ወደ ዝግጅቱ ተመለሱ። ዝግጅቱ በጣም አሪፍ ነበር። አመሻሹ ላይ ሁሉም ወደየ ቤታቸው ሄዱ።
፨የእነ አስሚ ሰረግ ካለፈ ከሶስት ቀን በኋላ እነ ዕዝራ ቤት የምሳ ግብዣ ተደረጎላቸው እየበሉ ነው በጣም ብዙ እጅ የሚያስቆረጥሙ ምግቦች ጠረጼዛውን ከበውታል እየበሉ ነው። የዕዝራ እናትና አባት ፊታቸው ብረት ብሏል። ምግባቸውን እየበሉ ነው አስሚም እንደዛው ዶክተሩ ግን ዕዝራን በማየት ተጠምዶል። የዕዝራ ፊት በእየ ደቂቃው ይቀያየራል። አንዴ ይስቃል ፤ አንዴ ሊያለቅስ ያቃጣዋል ከዛ በጣም ኮስተር ይላል በመጨረሻ ፊቱ ልክ እንደ ኮከብ እያበራ ምግብን ሳይበላ ተነስቶ ሄደ። ከዶክተሩ በቀር ማንም ልብ አላለውም።
፨ዶክተሩም ልክ የዕዝራን ክፍሉ መግባት እንዳየ ደቂቃዎች ቆየ ወዲያው የዕዝራ ድምፅ ተሰማው ዕዝራ እያወራ ነው። ዶክተሩ "ስሙ ዕዝራ እያወራ ነው" አለ። የዕዝራ አባትም "አዎ ልጄ ከሆነች ልጅ ጋር ያወራል ከእዚህ ቀደም እንደነገረኩክ" አሉ። ዶክተሩ "አይ ዕዝራ ምን አልባት ብቻውን እያወራ ቢሆንስ?" አላቸው። የዕዝራ እናት "ኧረ ዶክተር ይቅር ይበልህ " አሉ። ዶክተሩ ግን "እሱን ለማረጋገጥ ኑ ሁላችንም ዕዝራ መኝታ ቤት በረ ላይ እንሂድ" አላቸው። የዕዝራ አባትም "እንዴ ለምን የሚለውን ለመስማት ነው?" አሉ። ዶክተሩ "አይ እውነታውን ለማወቅ" አለ። የዕዝራ እናትም "እውነታውማ ልጄ አባቱ በሰጠው ስልክ ፍቅረኛውን እያወራ ነው" አሉ። ዶክተሩ "ባይሆንስ ቆይ እኔ ያንን ግጥም ሳነበው የተረዳውት አንድ ነገር አለ በእረግጠኝነት ዛሬ አንድ ነገር እናውቃለን ከዛ ዕዝራ የሀይምሮ ህሙማን ጊቢ ይግባ አይግባ እንወስናለን" አለ። የዕዝራ አባት ግን "አይ ልጄ በስልክ ከሴት ጋር እያወራ ነው" አሉ። ዶክተሩ ተነሱ ተነሱ ብሎ ወደ ዕዝራ

ክፍል ጠጋ አለ።

፨ ሁሉም ዕዝራ መኝታ ቤት ተጠግተው የዕዝራን ንግግረ እየሰሙ ነው።ዶክተሩ በቀስታ "ስሙ ዕዝራ ሲያወራ በየመሀሉ ፋታ የለውም ፋታ ከሊለው ደሞ ብቻውን ስለሚያወራ ነው ካስፈለገ ስልኩ ላይ መደወል እና ማረጋገጥ እንችላለን" አለ። የዕዝራ አባትም ለዕዝራ የሰጡትን ቁጥረ ለዶክተሩ ነግረውት ስልኩ ላይ ፅፎ ደወለ። ስልኩ ዝግ ነው! አባቱ በቀስታ የዕዝራን ክፍል በረ ከፈቱት ዕዝራ የሰማቸው አይመስልም ዞረም አላለም ልጃቸውን ሲያዩት ማመን ሁሉ አቃታቸው።
ልጃቸው የሲማይን ስእል እግረጊው ጋር ያለው ግድግዳ ጋር አስደግፎ እሱ ደሞ አልጋው ላይ ሆኖ እያወራ ነው።
፨ ዶክተሩ የዕዝራን አባት ገለል አረጎ ዕዝራን አየው እንዳሰበው እንደጠረጠረው ነው። እንዲያምኑ እናቱንም ኑ ብሎ አሳያቸው እናቱን ገለል አረጎም አስሚንም አሳያት። ሰራተኛዋ ሁኒታቸውን እያየች ባይገባትም ተመስጦ ላይ ናት። ሁሉም በውስጣቸው ዕዝራ የሀይምሮ ህሙማን ጊቢ እንዲገባ ወስነዋል። ከዕዝራ ክፍል በር ላይ ገለል ብለው ሳሎን ሶፋው ላይ ቁጭ አሉ። ሁሉም ተክዘዋል ከትካዜያዘው ግን የዕዝራ ልብ ቀጥ የሚያረግ ሳቅ አነቃቸው።

ክፍል 20 (ሀያ) ይቀጥላል........

እንማር:Biz Gitar:ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ (የሸዋ ልጅ)biz gitarየቀድሞዋ የአለሜ ነሽ እና የፅናት ደራሲሳልሳዊክፍል 18(አስራ ስምንት)              ፨ዕዝራ በፈጥነት መራመዱ...
07/07/2022

እንማር:
Biz Gitar:
ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ (የሸዋ ልጅ)biz gitar

የቀድሞዋ የአለሜ ነሽ እና የፅናት ደራሲ

ሳልሳዊ

ክፍል 18(አስራ ስምንት)

፨ዕዝራ በፈጥነት መራመዱን ገታውና ቆመ። አስሚ የዕዝራን ፊት አየችው የሆነ የጭንቀት ፊት ይታይበታል የፍጥነት እረምጃውን ቢገታውም የአስሚን እጅ ግን ድብን አረጎ አጥብቆ እንደየያዘው ነው። አስሚ ፈራች በጣም ለብዙ ደቂቃ የአስሚን እጅ አጥብቆ ይዞ ሊለቃት አልቻለም አስሚ እንባዋ ይፈስ ጀመረ። ግን ምንም ነበር ማለት ፈረታለች።
፨ሁሉም የሰውየው ቤት በረዳ ላይ ተሰብስበተው በእየ ድንጋዩ ተቀምጠዋል የዕዝራ አባት ሰውየውን "በሉ አሁን ንገሩን የእስካሁኑ ዝምታ ይበቃል" አሉ። ዶክተሩ ለዕዝራ አባት ዝም እንዲሉ ምልክት ሰጣቸው። ሰውየው "ልክ እንደ ልጆት ኖት ልጆትም ትግስት የለውም" ሲሉት። የዕዝራ አባት ተናደዱና "ቆይ ምንም አልገባኝም እሺ የፈለጉትን ይበሉ ችግር የለውም ግን ንገሩን እየጠበቀን ነው" አሉዋቸው። ሰውየው መናገር ጀመሩ "ከየት ልጀምረላቹ? " ሲሉ የዕዝራ አባት የሆነ ነገር በንዴት ሊናገሩ ሲሉ ዶክተሩ በድጋሜ አስቆማቸው። የዕዝራ አናትም
"ልጄ ግልፅ ባልሆነ መንገድ የተወሰ ነገር ነግሮናል እረሶ ግን ከመጀመሪያው ጀምረው ቢገግሩን ደስስስ ይለናል ሁሉንም ነገር እንድናውቅ" አሉዋቸው።
ሰውየው "ጥሩ! መልካም" ብለው ጀመሩ። " ጠዋት ከቤተ ክረስቲያን ስመለስ ልጃቹ መንገድ ላይ የሚያልፈውን ሰው ሁሉ ስለ አንዲት ልጅ እየጠየቃቸው ነበር ሁኒታውን ሳየው ልክ አደለም የሆነ አይነት ችግር ያለበት ይመስል ነበር። ሰው ሁሉ መጠቋቆሚያ እና መሳለቂያ አረጎትም ነበር። ጠጋ ብዬ ሳየው እኔንም ስለ ልጅትዋ ጠየቀኝ "ና" ብዬ እጁን ይዤ ወደ እዝህ አመጣውት ስንመጣ መንገዱን ሙሉ ስለ እሷ ሲያወራ እና ሲጠይቀኝ ነበር ምን እንደሆነ ጠየኩት። መጀመሪያ ዝም ብሎ ነበር ከዛ ግን ማውራት ጀመረ። ሲያወራ እጁን ጭብጥ አረጎ ይዞ በእጁ የያዘውን ጊጥ እየሳመ ነበር። ጭንቅ ብሎት አንገቱን ድፍት አረጎ "ሲማይ ስለምትባል ሴት ነገረኝ በፍቅር ታሪኩ በጣም ተገረሜ ነበር ምክያቱም እኔ ከአንድም አምስት ሚስት አግብቼያለሁ ግን ላንዳቸውም ይህ ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም ፍቅሩ ጥልቅ ነበር። በጣም የሚገረም እና የሚደንቅ ፍቅር ያው ስለ ሲማይ ያላብራራውት ለቤተስቦቹ ሁሉ ስለ እስዋ እንደተናገረ ስለተረደው ነው አሉ" የዕዝራ እናት "አዎ ልክ ነው" አሉ።
፨ ዕዝራ የአስሚን እጅ ለቆታል አሁን የሆነ ዞፍ ስር ቁጭ ብለዋል ዕዝራ እያለቀሰ ነው። አስሚ ጭንቀት ላይ ናት ልታባብለው ትልና ከዛ ግን ትተወዋለች።
ምንም ቃል አልተናገረም ግን ለቅሶ ውስጥ ብዙ ቃላቶች አሉ። ዕዝራን ማፅናናት በጣም ይከብዳል። እሱን ስለምታውቅ ዝምታን መረጣለች አልቅሶ እስኪወጣለት ድረስ ዝምም አለችው። ወደ አስሚ ዞሮ አስሚን አቅፎ ማለቀስ ጀመረ። አቅፎትም ሲያለቅስ አቀፈችው አስተቃቀፋ ጠንካራ ነበር። አስሚ ሰውነቷ እስኪንቃቃ ድረስ ጥብቅ አረጎ አቀፋት። ዝም አለችው እሷም በስሱ አቀፈችው። ቆይቶ ዝም አለ አስሚንም ለቀቃት።
፨ የስውየው ንግግር ትግስት አስጨራሽ ነበረ። በየመሀሉ ዝም የሚሉት ነገር አለ። ዝምታቸው እዥም ነው። የዕዝራ አባት ሊናገሩዋቸው ሲሉ የዕዝራ እናትና ዶክተሩ ሲያስቆሞቸው ቆዩ። ሰውየው አሁን መናገረ ጀመሩ። "ያው ገዳም ቢሄድ ወደ እረሱ ይመለሳል ብዬ አስብኩኝ ምክንያቱም ሰውነቱም ሆነ ውስጡ በጣም ይንቀዠቀዥ ነበር። ከተገናኘን በኋላ ያሉትን ሰአቶች እሱን ሳዳምጠው ቆየው እንቅልፍ በመሀል አሸነፈን እና ሁለታችንም በየአለንበት ተኛን ብዙ መተኛት አልቻልንም ምክንያቱም ደሞ ወደ ገዳም የመሄጃ ሰአታችን ስለደረሰ። ተነስተን ሄድን ገዳም ከገባን ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ዕዝራ ላይ ያሉ የሰውነት አለመረጋጋቶች ተወገዱ ሰውነቱም ተመለሰ። ገዳም ውስጥ ስራ አለ ዶቤ የሚጋገረበት እንጨት እናመጣለን ክረምት ሲሆን ደሞ በገዳሙ ማሳ ላይ እናረሳለን እንዘራን እንኮተኮታለን
ልጃቹ በሚገረም ሁኔታ ጥሩ ለውጥ አመጣ። በሄድን በአንድ አመት ውስጥ ዕዝራ ገዳም ውስጥ የሚገኑ የዘፍ ቀለሞች ምስላድኖች እና ቅረፃ ቅረፆችን ሰራ ሁሉም በጥበብ በጣም ተደነቀ እኔንም ጨምሮ። ከዛ ግን በተለያዩ ክልልሎች ባሉ ገዳማት እየዞረ እናንተ ጋር ከመምጣቱ በፊት ያሉትን ወራት እና መቶች ሁሉ ለገዳማት እየዞረ በመሳል ጊዜውን አሳለፈ ከእኔ ጋር መጀመሪያ በሄደበት ገዳም ውስጥ ለአመት ከሁለት ወራት ከቆየ በኋላ ነው በየ ገዳማት መዞር እና ጥበብን ተጠቅሞ ገዳማትን ማስዋብ የጀመረው። ከአስራ አምሰት ቀን በፊት ወደ እኔ ያለውበት ገዳም ተመልሶ መጥቶ ነበር ከዛ ወዲያው ነው የመጣውት ምክያቱም እሱ እናንተ ጋር እንዳደረሰው ስለፈለገ በገዳሙ ውስጥ አምሰት ቀን አስልፈን ወደ እዝህ ተመለስን እኔ እሱን እየጠበኩት ነበር ለእናንተ የምነገራቹ ነገር ስላለ ነው ቤተሰቦችህን እና የነገረከኝ የራስህ ታሪክ ውስጥ ያሉ ሰዎችን አምጣቸው ያልኩት" አሉ። ዶክተሩ "ይሄው ጠረጥሬ ነበር በሉ ንገሩኝ" አላቸው ለመስማት ጥድፍ ብሎ።
፨ እሳቸውም "ልጆቹ በጣምም የጨነቀው እና የማይፈታ ህመም ይዞታል ውስጡ ያለውን ጥያቄዎች ሁሉ ለመመለስ ደሞ ልክ በእሱ መንገድ ከሚጓዙ ሰዎች ጋር መቀላቀል አለበት" አሉ። ዶክተሩ "ማለት ጋሼ እሱን መስል ሲሉ የሀይምሮ ህመምተኞች ጋር ማለት ነው?" አላቸው። ሰውየው "በትክክል ገብቶሀል እያልኩኝ ያውት እሱን ነው እዛ ብታስገብት መልካም ነው" አሉ። የዕዝራ እናት "አይይ ልጄ አሁን በጣም ጤነኛ ነው እዛ ማስገባት በይበልጥ ልጄን ጨረቁን ጥሎ እንዲያብድ ነው የሚያረገው" አሉ። አባቱም "አዎ ልክ ናት እሱ በጭራሽ አይሆንም ልጃችን እዝህ የሚያደረስ ህመም ላይ አደለም ያለው" አሉ። ዶክተሩ "እኔ ግን ከሁለታችሁም የተለየ ሀሳብ ነው ያለኝ ጋሼ ልክ ናቸው ዕዝራን ትንሽ ቀን እንየው እና ካልሆነ እንወስናለን" አላቸው። ሰውየው "ምረጫው የእናንተ ነው"ብለው ዝም አሉ።
፨ ዶክተሩ አሁን የምፈልገው ነገር ተመልሶልኛል ሁሉንም ነገር ቀስ በቀስ አስረዳችኋለው አለ። ሰውየውም "ጥሩ ባለፈው እናንተ ጋር ሊመጣ ሲጣደፈ ይህ ወረቀት ከእቃው ላይ ወደቀ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ላስቀረው ፈለኩ እና አስቀረውት አነበብኩት የሚገረም ነገር አግኝቼበታለሁ ሊላው ሲሄድ በመንገድ አልፎ አልፎ የሚሰውረው ነገር አለ ሳታሰሰብት ወደ ድሮው ይመለሳል" አሉና ወረቀቱን ለመቀበል እጁን ለዘረጋው ዶክተር ሰጡት።
፨ አስሚ ዕዝራን እያየችው ዕዝራ ነው ዕዝራ ደሞ ጭብጥ ብሎ ተቀምጦ ቆይቶ ተነሳና ወደ አስሚ እጁን ልኮ "ነይ ተነሽ በቃ" አላት። አስሚም እጁን ይዛ ተነሳች። "ወደእነ አባባ እንመለስ አደል" አላት። አስሚ "አዎ እንመለስ"አለችው ፈገግ ብላለት። ዞረው እየተመለሱ ዕዝራ "አስሚ ከዶክተር አኪም ጋር አብራቹ ናቹ" አላት። አስሚ "አዎ ያንተን መምጣት ማለቴ መገኘት እየጠበቅን ነበር እንጂ ልንጋባም ወስነናል" አለችው። ዕዝራ "ጥሩ ነው አንድ ላይ በጣም ታምራላቹ እና መቼ ነው ሰረጉ" ሲላት። "አሁን እንወስናለን" አለችው። አስሚ በጣም ፈረታለች። በድጋሜ ዕዝራ ያንን ማንነቱን እንዳያመጣ ብላ። እጃን ለቆ አቀፋት እና "ታቂያለሽ በጣም ጥሩ እህቴ እንደሆንሽ ይሰማኛል የእውነት ልክ ከአንድ አባት እና እናት እንደተፈጥርን ነው የሚሰማኝ" አላት።

እንዲህ እያወሩ ሰውየው ቤት ደረሱ።

፨ ዶክተሩ ውይ እነ አስሚም መጡ በቃ እንግዲህ ጋሼ እንገነኛለን አሁን ወደ ቤት እንመለስ። ሰውየውን ሁሉም ተሰናብተዋቸው ወደ እነ ዕዝራ ቤት ተመለሱ። ዕዝራ በጣም ደከመኝ በቃ ልተኛ ብሎ ክፍሉ ገባ። ዕዝራ ልክ ክፍሉ ከገባ ከደቂቃዎች በኋላ። ስሙኝ አሁን ይህንን ወረቀት ከፈቼ ለሁላችሁም አነብላችኋለው። የዕዝራ እናት "ልጆት ከተኛ ሄደው ከማንበቤ በፊት ይዩት" ሲላቸው ተነስተው ሄደው በሩን በቀስታ ከፈተው አዩት ዕዝራ ተኝቶል። ወደ ሳፈው ሄደው እየተቀመጡ "ተኝቷል" አሉ። ዶክተሩ ጥሩ ብሎ ወረቀቱን ኋላ ኪሱ አውጥቶ ዘረጋግቶ ማንበብ ጀመረ።
፨፨፨፨፨፨፨፨
ችምችም ካለው ጫካ
ችምችም ካለው ጫካ እኔናአንቺ ሆነን
ፍቅር ስንሻማ ፍቅርን ተከናንበን
የሆነ አይነት ደስታ ደስ የሚል ስሜት
ዛፎች አሸብሽበው ሲዘምሩ አዋፋት
ትዝ ይልሻል
ይታወስሻል
እኔ
እንደኔ
አረሳውም ያንን ጊዜ ያንን እለት
ትዝ ይለኛል ቀን ከለሊት
ኡፍፍፍ
ኡፍ ኡፍፍፍ
ቃል ጠፋብኝ
ሁሉ አቃተኝ
ዛሬ የለሽም ካፈሩ ላይ ተኝተሻል
አልፈልግም ይህን ማስተዋል
ለምን ተኛሽ
ለምንስ ሞትሽ
ለምን መጣሽ
ለምንስ ሄድሽ
ይጨንቀኛል የት ናት የሚል ሰው ሲመጣ
ብነግራቸው አንዳች ለውጥ ላያመጣ
ስተነፍስ
አተነፍስ
እኔ ስስቅ
እሷ አትስቅ
እኔ ሳለቅስ
እሷ አታቅስ
ኧረ በስማም ኧረ በውልድ
ይህ ፍቅር ውስጥ ሲያነድ
ሞትሽ አልልም
ካፌ አይወጣም
ይከብደኛል
ያስፈራኛል
ግን ይህሞት ቅኔ ካለው
ፍቺው የእሱ ነው እሱ ይፍታው
በስማም ሲባል የማይጠፈ
በወልድ ሲባል የማይጠፈ
አንቺ ግን ለምንስ ሄድሽ
አንቺ ግን ለምንስ ሞችሽ
ሞች ስለሆንኩ እንዳትይኝ
እንደ ልማድሽ ዝም በይኝ"
፨ ዶክተሩ ይህንን ካነበበ በኋላ በሀሳብ ነጎደ

ክፍል 19 (አስራ ዘጠኝ) ይቀጥላል........

እንማር:Biz Gitar:ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ (የሸዋ ልጅ)biz gitarየቀድሞዋ የአለሜ ነሽ እና የፅናት ደራሲሳልሳዊክፍል 17 (አስራ ሰባት)           ፨ ዕዝራ ከብዙ ዝምታ በኋላ ...
04/07/2022

እንማር:
Biz Gitar:
ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ (የሸዋ ልጅ)biz gitar

የቀድሞዋ የአለሜ ነሽ እና የፅናት ደራሲ

ሳልሳዊ

ክፍል 17 (አስራ ሰባት)

፨ ዕዝራ ከብዙ ዝምታ በኋላ መናገር ጀመረ። " ሲማይን እየፈለኳት ነበር። መንገድ ላይ ከቤት የወጣው ቀን እሷን የሚያቃት ሰው ካለ ብዬ እየጠየኩኝ ነበር። በመጠየቄ በዛን ሰአት አንድ አዛውንት ሰውዬ "ና ልጄ" ብለው እጄን እየጎተቱ መሄድ ጀመሩ። እኔም በጥያቄ አጣደፈኮቸው "አባ ሲማይን ያውቋታል? ሲማይ ጋር እየወሰዱኝ ነው? ብዬ ጠየኳቸው እሳቸው ግን አንድም ቃል አልተነፈሱም እጄን ይዘው የሆነ የላስቲክ ቤት ውስጥ አስገብኝ ፀጥ ብዬ ተቀመጥኩ የላስቲኩ ቤት ውስጥ አንድ ልክ እንደ ቆጥ የተራች ፍራሽ አለች። ከአጠገብ ሳጥን አለ። እኔ የቤቱ ጠረዝ ጥቅግ ላይ ያለው ዱካ ጋር ተቀመጥኩ። ሰውየው ምንም አላወሩም። እኔ ግን ሲማይን እየጠበቁ እንደሆነ አስቤ ተቀሙጥኩኝ። በጣም ስጨቀጭቃቸው ችግሬ ምን እንደሆነ ጠየቁኝ። ስለ ሲማይ፤ ስላሳያችሁኝ የሲማይ ቦታ ፤ ሲማይ በሊት ላይ መጥታ እኔን እዳዋራችኝ ግን ማንም እንዳላመነኝ ብቻ ሁሉንም ነገር አስረዳዋቸው። እሳቸውም በእጄ የያዝኩት ምን እንደሆነ ጠየቁኝ የሲማይ ስጣታ እንደሆነ ነገረኳቸው ሲማይ የት ናት ብለው ጠየቁኝ ታቃላቹ ይንን ጥያቄ በጭራሽ አልወደውም አለች! እላለው እና የት ናት ስባል ይጨንቀኛል ከዛ ይልቅ ምን አሳለፋቹ ብባል ጥሩ መልስ ከልቤ እሰጣለሁ ደስ ብሎኝ።" አለ።
፨ዶክተሩ "እኒን ሰውዬ ማግኘት አብን" ሲለው "ዕዝራ አዎ ብትተዋወቁ እኔም ደስ ይለኛል እንደውም ጋሼ እራሳቸው ቤተሰቦችህን ታስተዋውቀኛለህ እያሉኝ ነበር" አለው። አባቱ "እሺ ቆይ ከዛስ" አሉ በጉጉት ዕዝራን እያዩ። ዕዝራ ካቀረቀረቀበት ቀና ብሎ አያቸው አይኖቹ እንባ ላለማውጣት የሚታገሉ ይመስላሉ ደሞም ያስታውቃሉ ግን እንባውን መቆጣጠር ጭራሽ ባለመቻሉ ዘረገፈው። እና "ጋሼ ነገ ወደ ገዳም እሄዳለሁ እዛ አብረን እንሂድና የተወሰነ ጊዜ እራስህን ታረጋጋለህ ፈጣሪ ለጥያቄዎቹ ሁሉ ከሰዎች በበለጠ መልስ ይሰጥሃል አሉኝ። ተስማማው ከእሳቸው ጋር ሰአታትን ካሳለፍኩኝ በኋላ ለሊት ተነስተን ጉዞ ጀመረን።
፨ በቅጥቅጥ መኪና ተጭነን ሄደን። ገዳም ውስጥ የመጀመሪያዎቹ ቀናት ቢጨንቁም እየቆየው ስሄድ ግን አለማዊ ህይወቱ አስጠላኝ እራሴን እና ማንነቴን እዛው ገዳሙ ውስጥ ያገኘው ያክል ተሰማኝ አግቺያለውም ከጋሼ
ጋር ገዳም ውስጥ ለገዳሙ ገዳምተኞች ከምግብ ሰሪዎች ጋር ማዘጋጀት ጀመረኩ። የሲማይን ስጦታ ሁሌም ከአጠገቤ አለየውም በልብሴ ላይ እንደ ኪስ ሰረቼ በሄድኩበት ይዤው እዞራለው።
ብዙ ወራትን አስቆጥሬ ሰላም የሆንኩኝ ያህል ሲሰማኝ ወደ እዝህ ተመለስኩ" አለ። ዶክተሩ "ስለዚህ ሰውየውም አብረው ነው የመጡት?" አለው። "አዎ አብረውኝ ነው የመጡት ኑ እና ቤተሰቦቼን ላስተዋውቆት ስላቸው ቤተሰቦችህን ያለሁበት አምጣቸውና አስተዋውቀኝ ብለውኛል" ሲል ዶክተሩ "ስለዚህ አሁኑኑ ሄደን ለምን አንተዋወቃችሁም" አለ አስሚ " እንዴ ሀኪሜ ይህ ነገር ያን ያክል አስፈላጊ ነው? አጣዳፊስ ነው?" አሉት። ዶክተሩ "ቆይ አንዴ ውጪ እናውራ" አላቸው። "እሺ" ብለው ብድግ አሉ። ዶክተሩ እና የዕዝራ አባት ተከታትለው ወጡ።
፨ የዕዝራ አባት "ዶክተር ምንድነው ችግር አለ እንዴ?" ሲሉት። "ይመስለኛል ዕዝራ አሁንም ድረስ አልተሻለውም ደና ቢመስልም አደለም" አላቸው። "ማለት ዶክተር ምን እያልከኝ ነው ቆይ" ሲሉት። እሱን በዝረዝረ ለማስረዳት እነዛን ሰውዬ ስናገኝ ነው።" አላቸው። የዕዝራ አባትም "እመነኝ ዶክተር ልጄ ወደ እራሱ ተመልሷል ከትናት ወዲያ ከሆነች ሴት ጋር ሲያወራ ነበር" አሉት።
፨ዶክተሩ "በምን ስልክ ስልክ መጠቀም ጀመረ እንዴ" ሲላቸው። "አዎ የመጣ እለት ነው እኔ እራሴ አጋጣሚ አዲስ ሲም አውጥቼ ስለበር ቀፎም ስለነበረኝ የሰጠውት " አሉት። ዶክተሩ ግራ ተጋብቶ " ቆይ ምን እያለ ነው እሺ ምንድነው ሲያወራ የሰማችውት" አላቸው እንዲያስረዱት በጉጉት እያያቸው ። "አባትየው የመጀመሪያ ቀን ልጄ ሲመጣ ከእናቱ ጋር ቤተ ክረስቲያን ሄዶ መጣና ብና ከጠጣን በኋላ ልተኛ ብሎ ገባ። ሊተኛ ሲል ሄጄ ልጄ ድንገት ይህ ካስፈለገክ ብዬ ስልኩን ሰጠውት እና ወጣው እኔም ወደ ስራ ሄድኩኝ እናቱም ተኛች።
፨ከስራ ስመለስ ልጄ ከክፍሉ አልወጣም ነበር። ሰራተኛዋ ቡና እያፈላች እራት ቀረቦ ልንበላ ስንል እናቱ እሱን ለመጥራት ሄደች። እና ወዲያው ተመልሳ 'ናና ልጃችን ሴት እያወራ ነው ና ስማው' አለችኝ እኔም ልክ እንዳንተ ነበር ያላመንኩት በቀስታ ወደ ክፍሉ በር ጠጋ ብለን ማዳመጥ ጀመረን ልጄ "ይገረምሻል ዛሬ በጣም ነው ደስ ያለኝ.... ደሞ አባባ እኮ ስልክ ሰጠኝ.... ሀሀሀሀሀ እና እንዴት አልደሰትም ስታስቢው በጣም ነው እንጂ ደስ ያለኝ.... በቃ አሁን ወደ ሳሎን ልሄድ ነው አታስቢ ስመጣ ከመተኛቴ በፊት አወራሻለሁ ቻው አፈቅርሻለሁ" ብሎ ነበር ያወራው እኛም ቶሎ ከበሩ ገለል አልን ትንሽ ቆይቶ ደስ በሚል ፊት ተመለሰ እራት እየበላን በመሀል ፊቱ በጣም ያበራ ነበር በጣም አልፎ አልፎ ግን ልክ ሲማይን ካጉኘ በኋላ ወደነበረው ድረጊት ይመለሳል ወዲያው ደሞ ይተወዋል።
፨ዛሬ እራሱ ጠዋት ላይ ሳቁን ሰምቼ ወደ መኝታ ቤቱ በረ ጠጋ ስል "አንቺ ደሞ ገዳሙ ውስጥ ያለውን ሰውዬ ነግሬሽ የለ እያወቅሽው...... ያኔ በደብ አልሰማሽኝም ማለት ነው ማለት ነው?.... በጣም ያስቅ ነበር.... ኧረ ጉደኛ ነው እሱ ሰውዬማ በቃ ሻውር ልግባ እና ቤተ ክረስቲያን መሄድ አብኝ ኦ ሳልነግረሽ ትናት ሳሻል ሚዲያ እያየው በጣም ያሳቀኝን ልንገረሽ! የሆነ በጣም ወፋራም ሰውዬ እየሄደ ቀጭኑ ሰውዬ መጥቶ በጥፊ ሲመታው እንዴት እንደተሽከከረ ብታይ...ሀሀሀ ኧረ አለም በጣም ቀልደኛ ሆናለች... ኧረ በቃ ቻው ሰአት ሄደብኝ ቻው አፈቅርሀለው ሁሌም' ብሎ ዘጋው።" እኔም እንዳልሰማው ሆኒ ሳሎን ቁጭ አልኩኝ ቆይቶ ወጥቶ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄደ።" አሉት። ዶክተሩ የዕዝራ አባትም ያበዱ መሰለው ማመን ሁሉ አልቻለም።
፨ ዶክተሩ "በቃ የዕዝራ አባት ነገሩን የግድ ማወቅ አለብን ዕዝራ ከእኛ ተለይቶ በነበረበት ጊዜ ምን እንዳሳለፈ ትክክለኛውን ነገር ማወቅ ከፈለግን ዕዝራ ጋሼ የሚላቸውን ሰውዬ የግድ ማግኘት አብን እረሶም እንደዛው እንደውም አብረን እንሄዳለን ዕዝራ ከፔሸንትነቱ ባለፈ ልክ እንደ ወንድሜ ነው የማየው" ብሎ ቤት ሲገባ ዕዝራ እና አስሚ ሳሎን የሉም ሳሎን ሰራተኛዋ እና የዕዝራ እናት ብቻ ነበሩ። ዶክተሩ "አስሚ እና ዕዝራስ?" አላቸው እናቱን "አስሚ ሽንት ቤት ናት ልጄ ደሞ መጣው ብሎ ክፍሉ ገብቶል" አሉ። ዶክተሩ የዕዝራ መኝታ ቤት ከሳሎኑ አጠገብ ስለነበር ወደ ዕዝራ መኝታ ቤት ጠጋ ብሎ ዕዝራ የሚለውን መስማት ጀመረ። ዕዝራ እያወራ ነው "በጣም ስትናፍቂኝ እኮ ነው ላወራሽ ብዬ ክፍሌ የመጣውት የእውነት በጣም ነው እኮ የምትናፈቂኝ" አለ ዕዝራ። ዶክተሩ ደነገጠ የዕዝራን የቃላት ድረደራ ሲስማ ያልተዋጠላት ነገር አለ። ዶክተሩ "ዕዝራ ዕዝራ" አለው። ዕዝራም "መጣው ዶክተር ብሎ ከክፍሉ ወጣ። ዶክተሩ "በሉ ኑ ዛሬውኑ ሰውየውን ማግኘት አለብን።" አለ። አስሚም መጥታ "ምነው የተፈጠረ ነገር አለ እንዴ?" ስትል ዕዝራ "ኧረ ምንም የተፈጠረ ነገር የለም ቆይ በቃ

መጣው" ብሎ ክፍሉ ገባ።

፨ ዕዝራ ጆኬቱን ደረቦ ከክፍሉ ወጣ። እናቱ "እኔም እመጣለው" አሉ። ዕዝራም "አዎ እማማ ነይ አንቺም አለ።
ሁሉም ተሰብስበው ወደ ሰውየው ሄዱ።
የሰውየው መኖሪያ ቦታ ሲደረሱ ዕዝራ "ጋሼ ጋሼ " አለ። "አቤት ማነው" ብለው ወጡ። ዕዝራም " ጋሼ እንዴት ኖት ይሄው ቤተሰቦቼን በሙሉ ይዤያቸው መጥቻለው" አላቸው። ሰውየው ከቤታቸው ወተው "ሰላም ለእናንተ ይሁን ስጠብቃቹ ነበር እንደምትመጡ እረግጠኛ ነበረኩ" አሉ። የዕዝራ አባት ግራ ተጋብተው "እንዴት ሆኖ ነው እረግጠኛ ሊሆኑ የሚችሉት" ሲሏቸው ዶክተሩ በቀስታ ወደ አስሚ ጆሮ ጠጋ ብሎ "አስሚ አንቺ እና ዕዝራ ትንሽ ዞር ዞር ብላቹ አየር ተቀበሉ ዕዝራን አዝናኚው ስንጨረስ እንደውላለን ዕዝራ ስናወራ መስማት የለበትም ላንቺ ሁኒታውን እኔ እነግርሻለሁ እናት እና አባቱ ማወቅ ያለባቸው ነገር አለ " አላት። አስሚ ወደ ዕዝራ ሄዳ " ዕዝራ ና እስቲ ትንሽ ዞር ዞር ብለን እንምጣ ትንሽ ዘና ብትል ላንተም ጥሩ ነው ከሁሉም ጋር ዞር ዞር ብል ያስደብሩኛል ና" ብላ እጁን ያዛ ሄደች። ትንሽ እንደሄዱ ዕዝራ የአስሚን እጅ ጥብቅ አረጎ ያዛት። እረምጃውን እያፈጠነ መጣ የሆነ ሰው ሊፈለም የሚሄድ ይመስል ነበር የአስሚን እጅ በጣም በይበልጥ ጥብቅ አረጎ ያዛት አስሚ ደነገጠች ፣እጆን አመማት፣ ግራ ገባት።

ክፍል 18 (አስራ ስምንት) ይቀጥላል...

Biz Gitar:ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ (የሸዋ ልጅ) biz gitarየቀድሞዋ የአለሜ ነሽ እና የፅናት ደራሲሳልሳዊ ክፍል 16 (አስራ ስድስት)        ፨ የዕዝራ አባት ወደታች ውረደው እና...
02/07/2022

Biz Gitar:
ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ (የሸዋ ልጅ) biz gitar

የቀድሞዋ የአለሜ ነሽ እና የፅናት ደራሲ

ሳልሳዊ

ክፍል 16 (አስራ ስድስት)

፨ የዕዝራ አባት ወደታች ውረደው እናቱን ሲያዩዋት ስልክ ጆሮቸው ላይ አረገዋል። ስልኩን ከጆሮዋቸው ወስደው። "ሄሎ" አሉ። የዕዝራን እናት እያዩ እናቱ እያለቀሱም እየሳቁም ነው። ስልኩ ተዘጋ። የዕዝራ አባት "ምን ሆነሽ ነው? ምን ተፈጥሮ ነው? ልጄ ስትይ ሰማው ልበል?" አሉ። የዕዝራ እናት "አዎ ልጄን ድምፁን ሰምቼዋለው እማማ ብሎ ጠረቶኛል" ሲሉ አባቱ "ተይ ባክሽን አትቀልጂ"ብለው ጥለዋቸው ሄደው ደረጃውን ሊወጡ ሲሉ ስልኩ በድጋሜ ጠራ ተመልሰው መተው አነሱት እናት መሬቱ ላይ ተደፈተው እያለቀሱ ነበር። "ሄሎ" አሉ። "አባባ" አለ የዕዝራ አባት ማመን ሁሉ አቃታቸው። "ልጄ?" አሉት። ዕዝራ "አዎ አባባ ልጅህ ነኝ" አላቸው። አባቱ እንባ እየተናነቃቸው "ልጄ ልጄ ደና ነህ? የኔ አንበሳ የት ነበርክ የት ነህ" አሉት።
፨ዕዝራም " አለው አባባ አለው አባባ ጠዋት አንድ ሰአት ላይ ድሮ ኢለመንተሪ ስማር የነበረበትን ትምህት ቤት እማማ ስለምታቀው እዛ መታቹ ተቀበሉኝ" አላቸው። አባቱ "አምላኬ ተመስገን ተመስገን እሺ ልጄ መጥተን እንቀበልሀለን" አሉት። ስልኩ ተዘጋ ስልኩን እንደዘጉት "የልጄ እናት ነይ እቀፊኝ ደስ ብሎኛል አሉ" የዕዝራ እናትም ተነስተው አቀፏቸው ተቃቅፈው ተላቀሱ የደስታ እንባ የፌሽታ እንባ ተራጩ። ለሊቱ እንደምንም አልፎ 12:25 ላይ ሄደው ዕዝራ ያላቸው ቦታ ተሰይመዋል። መኪና ውስጥ ሆነው ዕዝራን በጉጉት እየጠበቁት ነው። ልክ አስር ጉዳይ ለአንድ ሲሆን ከመኪናቸው ፊት ለፊት ዕዝራ ሲመጣ አዩት። ሰውነቱ ተመልሷል ጥሩ አቋም ያለው ዕዝራ ሆኖል በፊስታል እቃ ይዞል። እንደ ከእዚህ ቀደሙ አይቀጠቀጥም ልብሱንም አይበላም ጉዳቱ ግን እንዳለ ነው ፂሙ ችምችም ብሏል ተጉድቷል። እናትየው በደስታ ዘለው ከመኪናው ወጡና " ልጄጄጄ ልጄጄጄ" ብለው። ተጠመጠሙበት ዕዝራ እቅፍ አረጋቸው። "እማማ" አለ። አቅፎቸው ወደ እሱ በቀስታ እየመጡ ያሉትን አባቱን እያየ። እናቱ አለቀሱ ከእቅፋቸው አስወጥተው አገላብጠው ሳሙት እሱም ሳማቸው። አባቱ እሱ ጋር ልክ ሲደረሱ ዕዝራ "አባባ" ብሎ አባቱን እቅፈ አረጋቸው። አባቱ የዕዝራን ጀረባ መታ መታ እያረጉ እንኳን ደህና መጣህ ልጄ" አሉት። ዕዝራም "እንኳን ደና ቆያችሁኝ አባባ" አለ።
፨ መኪና ውስጥ ገብ እና ወደ ቤታቸው ሄዱ። ቤት እስኪደረሱ ድረስ ዕዝራ እና እናቱ ከኋላ እቅፍቅፍ ብለው ተቀምጠው ነበር። ቤት ደረሰው ወደ ሳሎን ሲገብ ሳሎን ማንም የለም ጠዋት ስለሆነ ሰራተኛዋም እንደተኛች ናት። የዕዝራ አባት ዕዝራን "ልጄ ክፍልክን እናትህ እስክታዘጋጅልህ ለምን እኛ ክፍል እረፍት አትወስድም ሲሉት። "አይ አባባ መጀመሪያ ቤተ ክረስቲያን ልሂድ ስመለስ እታጠባለሁ" ሲል። እናትየው "ልጄ አብሬህ ልምጣ " ሲሉት። "ይቻላል እማማ ነይ ነጠላ ለብሰሽ እጠብቅሻለው" አላቸው። እናትየው ነጠላቸውን ለብሰው መጡ። ቤተ ክረስቲያን ሲሄዱ ዕዝራ ልክ ድሮ እናቱን በመንገድ ሲሄዱ እንደሚያቅፋቸው አቅፎቸው ነበር ከቤቱ በር ጀምሮ የሄዱት። እናቱ ደስ ብሏቸዋል ቤተ ክርስቲያን ሲደረሱ ስርአቱን ጠብቀው ገብ። ገና በጣም ጠዋት ስለነበር ብዙ ሰው አልነበረም። ገብተው አጠገብ ላጠገብ ቆመው ፀሎት አረጉ አስቀደሱ ። ልክ ሲመጡ እንደነበሩት አልነበሩም ምእመናኑ ቤተ ክረስቲያኑዋን ሞልተዋታል። ሰላም ግብ ተብሎ ዕዝራ እና እናቱም ተቃቅፈው ወደ ቤት ተመለሱ።
፨ ቤት ሲደረሱ ቡና ቀራረቦ ቤቱ ሞቅ ሞቅ ብሎ ነው የጠበቃቸው። ቤት ገና ሲገብ ሰራተኛዋን ሰላም ብሏት። "እማማ በቃ ሻውር ልግባ እና እመጣለሁ" ብሎ ወደ መኝታ ቤቱ ገብቶ ቁም ሳጥኑን ከፈቶ ሊበቃው የሚችለው ልብስ ካለ ማየት ጀመረ። የበፊት ልብሶቹ ማለትም ሳይከሳ ሲያረጋቸው የነበሩት ሁሉ ልኩ ነበሩ። ሰማያዊ ቲሸረት እና ቢጫ ቱታ መረጦ አልጋው ላይ አረገ ነጭ ፎጣም አውጥቶ መኝታ ቤቱ ወዳለው ሻውር ቤት
ገብቶ መታጠብ ጀመረ።
፨ አስሚ እና ዶክተሩ ከዶክተሩ ቤተሰቦች ጋር የቤታቸው በረንዳ ላይ ብና ተፈልቶ ወጥ ተሰረቶ ሞቅ ሞቅ እያረጉት ነው። ጨዋታቸው ደምቋል ደስተኞችም ናቸው። የዶክተሩ እናት አስሚን በጣም ወደዋታል። ሁሉም ቢወዶትም የእሶቸው ግን በጣም ይለያል። ከጨዋታው መሀል የዶክተሩ እናት ወደ ልጆቸው እያዩ "ልጄ ታዲያ ሰረጉ መቼ ነው ቸኮልሽ አትበለኝና በአንተ በኩል ደሞ የልጅ ልጄን ባይ ደስ ይለኛል አላህ ፈቅዶ አንድ ላይ እንዳረጋቹ እሱ በጥበብ ዘላለም ያኑራቹ" አሉ። አስሚ እና ዶክተሩ "አሜን አሜን" አሉ። የአባትም "እና ልጆቼ ሰረጋችሁን መቼ እንጠብቅ" ሲሉ።ዶክተሩ "አይ አባቴ እሱን አላህ ነው የሚያውቀው አንድ እኔንም እሷንም የሚያሳስበን ነገር አለ እሱ ሲሳካ ሰከንድ አንቆይም" አላቸው። አስሚም "ልክ ነው" አለች።
፨ ዕዝራ ገላውን ታጥቦ ፅድት ብሎ ከእናት እና ከአባቱ ጋር ሰራተኛዋ ያፈላችላቸውን ብና እየጠጣ ነው። በሰሀን ዳቦ ቆሎ እየበላ ነው። የዕዝራ አባትም "ልጄ እስቲ አሁን ተረጋግተሀል የት እንደነበረክ ንገረን" ሲሉት። "እሺ አባባ ግን አስሚ እና ዶክተር የት ናቸው?" አለ።
እናቱም "ዶክተር እና አስሚ ትናት ነው እኮ አዳራቸውን እዚህ አረገው ተያይዘው የወጡት" አሉት። ዕዝራ "እና አይመጡም እንደውልላቸዋ" ብሎ ወደ ስልኩ ሄዶ "እእ አባባ የአስሚን ወይም የዶክተረን ስልክ ቁጥር ልትነግረኝ ትችላለህ?" ብሎ የስልኩን እጀታ ጆሮው ላይ አረጎ የአባቱን ቃል መጠበቅ ጀመረ። አባቱም "ስልክ ዝረዝሩ እሱ ጋር ያለ ትንሽዬ ደብተር ላይ አለልህ" አሉት። "ኣ አገኘውት አባባ" ብሎ ከስልክ ዝረዝሮች ውስጥ ስም መፈለግ ጀመረ። አገኘው ዶክተር የሚለውን መጀመሪያ ስላገኘ እሱ ጋር ደወለ አይሰራም ደግሞ ደጋግሞ ቢደውልም ሲሰራ አልቻለም ከስር አስሚ የሚል አለ። በእሷ ቁጥርም ላይ ደወለ ልክ እንደ ዶክተር የእሷም ስልክ የደወሉላቸ ውን ደንበኛ አሁን ማግኘት አይችሉም ይላል። ስልኩን ዘግቶ ወደ ነበረበት ቦታ ተመልሶ ተቀመጠ። የዕዝራ እናት "ምንነው ልጄ አያነሱም?" ሲሉት። "አይ እማማ ስልካቸው ጭራሽ አይሰራም በቃ እኔ ልተኛ ዶክተር እና አስሚ ሲመጡ ሁሉንም ነገር እነግራቸዋለው" ብሏቸው ሲነሳ እናቱ "ልጄ ሶስተኛውን አጠጣም" ሲሉት። "ይቅረብኝ እማማ በቃ ሰላም ሁኑ" ብሎ ወደ መኝታ ቤቱ ገባ። "ተመስገን " አሉ።
፨ አስሚ እና ዶክተሩ ጉብኝት ላይ ናቸው። የደሴ ከተማን የዶክተሩ የመጨረሻ ታናሽ ወንድም ነው እያስጎበኛቸው ያለው። በጣም ጥሩ ጊዜ እያሳለፉ ነው። አስሚ ከዶክተሩ እናት ጋር በደብ ተግባብታለች። ደሴን በረገጡ በሳምታቸው የዶክተሩን ቤተሰቦች ተሰናብተው ጉዞቸንውን ወደ አዲስ አበባ አቀኑ። በመንገዳቸው በመሀል በመሀል ዘፈን እየከፈቱ የተቋጠረላቸውን ምግብ እየበሉ ልክ ከቀኑ 7:51 ላይ አዲስ አበባን እረገጡ። ወዴትም አልሄዱም ቀጥታ የሄዱት ወደእነ ዕዝራ ቤት ነበር። የእነ ዕዝራን ቤት አንኳኩት ዕዝራ በረንዳ ላይ ተቀምጧ ነበር። ተነስቶ ከፈተው ልክ አስሚ ዕዝራን ስታየው "እእእ" አለች። ዕዝራ ፈገግ ብሎ አያት ዶክተሩ "ዕዝራ?" አለ። ዕዝራ "እንዲህ እንደምደነግጡ አውቄ ነበር እኮ አስቀድሜ ላሳውቃቹ የደወልኩት አለ። ሁለቱም ግን ዕዝራን የእውነት በአካል በጭራሽ ያዩት አልመሰላቸውም በጣም ደንግጠዋል።

፨የዕዝራ እናት እና አባት ፣ዶክተር ፣ አስሚ ሰብሰብ ብለው ሳሎን ተቀምጠዋ ል። ዕዝራ "እእ በቃ እንዲህ ሰብሰብ ካላቹ አይቀር ከእናንተ ውጪ የነበረኝን ህይወት ልንገራቹ አደል" አላቸው ሁሉም አዎንታቸን ገለፁ። ዕዝራ አንገቱን ደፈቶ እረዥም ሰአት ቆየ። ሁሉም ከዕዝራ በቀር እረስ በእረስ እየተያዩ ነው። ምክንያቱም ለማወቅ በጣም ጓጉተዋል። ሁሉም ልብ ውስጥ ዕዝራ እንዴት ከእዚህ ቀደም የነበረበትን ሁኒታ ትቶ ወደ ቀድሞ ማንነቱ ተመለሰ የሚለው ጥያቄ ጭንቅላታቸው ውስጥ አለ ዶክተሩም ይህ ጥያቄ ውስጡ አለ እሱ ግን የፈራ ይመስላል ግራም ጉብቶታል። ምክንያቱም ዕዝራ ልክ ከሲማይ ከተለየ በኋላ የሚያረጋቸው እንደ ልብስ መብላት፤ የሲማይን ስጣታ ይዟ በስሱ መሳም እና ደጋግሞ ማየት እጆቹን ማፋተግ የሆነ ሀይል እንደተቆጣው ኩምሽሽ ማለት ሁሉ የሉም።
፨እንደ ዕዝራ አይነት ሁኔታ ውስጥ ያሉ የሀይምሮ ህሙማን በሙያው ብዙ ያውቃል ግን በእዚህ ፍጥነት ሲቀየሩ ችግር እንዳለ ያውቃል ህመሙ ወይም ትንሽ ፕረሰቱ ህሙማን የምረም ተሽሎቸው ሊሆን ይችላል። ሁሉም ግራ የገባቸው እንዴት እንዲህ ደና ሆነ የሚለው ጥያቄ ነው። ለዛም ነው ዕዝራ ስላሳለፋቸው ነገሮች ሁሉ ማወቅ የፈለጉት። ዕዝራ እንዴት በምን ተአምር ነው ወደ ቀድሞ ዕዝራ የተመለሰው በእረግጥ ፊቱ ላይ የተጎዳ ስሜት ይታያል ግን ለውጡም ይገረማል። ሁሉም በጉጉት እያዩት ነው አይናቸውን እረስ በእረስ መተያየታቸውን ትተው ዕዝራ ላይ አፋጥጠዋል።

ክፍል 17(አስራ ሰባት)ይቀጥላል.....

እንማር:Biz Gitar:ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ (የሸዋ ልጅ) biz gitarየቀድሞዋ የአለሜ ነሽ እና የፅናት ደራሲሳልሳዊክፍል 15 (አስራ አምስት)           ፨ዶክተሩ እየነዳ አስሚ "...
01/07/2022

እንማር:
Biz Gitar:
ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ (የሸዋ ልጅ) biz gitar

የቀድሞዋ የአለሜ ነሽ እና የፅናት ደራሲ

ሳልሳዊ

ክፍል 15 (አስራ አምስት)

፨ዶክተሩ እየነዳ አስሚ "በፈጠረክ ሀኪሜ የምንሄድበትን እንኳን ንገረኝ ቢያስ" ስትለው "አታስቢ ጥሩ ቦታ ነው ይዤሽ የምሄደው" ሲላት። "ያ አላ አኪም በፈጠረህ ምንድነው ምትለው ከቅድም ጀምሮ አታስቢ ጥሩ ቦታ ነው ይዤሽ የምሄደው ስትለኝ ነበር እኮ ይሄው አሁን ጉዞ ከጀመረን 5ስአት አለፈን አኪም እየመሸ እኮ ነው ታይቶሀል?" ስትለው ፈገግ ብሎ "ምግብ ከራበሽ መኪና ውስጥ ምግብ አለ አልኩሽ" ሲላት። ክትክት ብላ ስቃ "ዛሬ ልታሳብደኝ ነው" ስትለው "እና አላበድኩም ነው የምትይኝ" ሲላት። "አንተ ትቀልዳለህ ይሄው ከቅድም ጀምሮ በየመሀሉ ላለማውራት አፌን በምግብ እየያዝኩ ቁንጣን ያዘኝ" አለችው።" ደረሰናል በቃ" ብሎ ከመኪናው ወረጅ። አስሚ "ተመስገን" ብላ ወረደች።
ጨለማ ነበር ግን የስልኩን መብራት አብረቶ አነስ ወዳለች ጎጆ ቤት ወሰዳት። በቅድሚያ እሱ "ቤቶች እንዴት አመሻቹ ብሎ አንገቱን አስገባ የአስሚን እጅም ይዞ አስገባት። ውስጥ እሳት እየነደደ ነው ብዙ ሰዎች ውስጥ ነበሩ።
፨" አስሚ ምንም አልገባትም ምንድነው ሀኪሜ የት ነው ይዘከኝ የመጣከው" አለችው። "ቤተስቦቼ ናቸው አያ እማዬ ይቺት የምወዳት ሴት" አሉዋቸው። ፊት ለፊት የተቀመጡትን እናትና አባቱን አስሚ በጣም ደስስ አላት። ደስታዋ ፊቷ ላይ በሰፊው ይታይ ነበር ግን ያልጠበቀችው ነገር ስለነበር ድንጋጤዋ ፊቷ ላይ በደብ ያስታውቅ ነበር። ደስታዋም እንደዛው። የዶክተሩ እናት እና አባት "ቆይታቹ አስጨነቃችሁን እኮ እንኳን በደህና መጣቹ ግቡ ግቡ" ብለው እየተፈራረቁ ሰላም አሉዋቸው። የቤቱ መደብ ላይ መደዳውን ከዶክተሩ ጋር ፍፁም አንድ አይነት የሆኑ 7ወንዳች አሉ ከዶክተሩ ጋርም እያንዳዳቸው የእድሜ ልዩነታቸው ቢያስታውቅም አንድ አይነት ሳይሆን አንድ ናቸው የሚለው ቃል አባታቸውን ጨምሮ ይመጥናቸዋል። ሁለት እናታቸውን የሚመስሉ ሴቶችም አሉ አነሱም አንድ አይነት ሳይሆን አንድ ናቸው። አስሚ ከመቀመጥዋ በፊት ሁሉንም በመደዳ ሰላም አለቻቸው እና ጥግ ያለው መደብ ላይ ከዶክተሩ ጋር ተቀመጠች። ወደ ጆሮ ጠጋ ብላ "ይገረማል አንድ አይነት ናቸው። መተው ሀሚም ነኝ ብሉኝ አምናቸዋለው በጣም ትመሳሰላላቹ ነገ በብረሀኑ እስካያቸው ጓጓው እኔ የገመኝ እናንተ አባታችሁን ሴቶች እናታቸውን መምሰላቸው ነው" ስትለው። "እዛኛው ጥግ ጋር ያለው ትንሹ የመጀመሪያ ወንድማችን ልጅ ነው ግን እኛን ነው የሚመስለው" አላት።
፨ አስሚ ተገረመች። ትንሽዬዋ ሴት ልጅ ተነስታ እጅ አስታጠበች እናታቸው እና ሊላኛዋ ሴት ልጃቸው ምግብ አቀረብ በጣም ደስ የሚል ምሽት አሳለፈ ጨፈሩ ዘፈኑ ልክ መጨረሻ ላይ ማስንቆ ይዞ አንደኛው ተለቅ ያለው ወንድማቸው ተነሳና መጫወት ሲጀምር ትንሹ ወንድሙ "ተቀበል ወንድም ጋሼ ብሎ ጠላውን ተጎነጨ ቀጠለ
"የኔማ ሀሚኬ እንደም ቆየህ
ወንድሜ አምሳዬ ምነው ቆየህ
ብዬ እያሰብኩኝ እየናፈኩህ
ለበጎ ነው ለካ እንዲህ መቆየትህ" አለ። ታላቅ ወንድድማቸው ተቀብሎ አስረቀረቀው። ሁሉም ሳቁ እና አጨበጠብ ሀኪምም ተቀበለኝ ብሎ እንደ ማሰብ አለና:-
"የእኔ ወንድምዬ የኔ መከታዬ
አንተን እና እናንተን ልረሳ እንዴት ብዬ
ልቤ ውስጥ አላቹ በፍቅር ኖራቹ
ፍፁም ላትረሱ ከልብ እማረሳቹ
አልፋ እና ኣሜጋ ቤተሰቤ ናቹ "
አለ። ሁሉም ደስ አላቸው። ሴትዋም ተቀበልኝ ወንድሜ አለችውና ፈገግ ብላ
"እኒ ፉንጋ ፋንጋ እንዴት ያስቀናሉ"
ስትል ሁሉም በጣም ሳቁ ሳቁ ሲያባራ ቀጠለች።
"እኒ ፉንጋ ፋንጋ በጣም ያስቀናሉ
አምሳያ ላምሳያ ይነፋፈቃሉ" አለች። የልጅ ልጁን ተነስቶ
"አክስቴ አክስቴ የኔ እቴትዬ
የፉገራ አለቃ የኔ ቆንጅይዬዬ
እነኒህ አምሳያዎች እኔን ይመስላሉ
እኔ ቆንጃ ነኝ ቃላትሽም ቢሆን ቅኔ ነው አሉ" አለ። አሁንም በጣም ተሳሳቁ ተቀባይ ዘፈኑ ወንድማቸውም አንጎራጎረና
"የድርሻዬን ላውራ ለእኔም እድል ስጡኝ
ለሙሽራችንም እንጣል ስንኝ
የእኛ ሙሽራችን የልጃችን እጩ
መቼም ስትታዩ ብዙ ነው ደንጋጩ" አለ። አስሚ በደስታ ውስጥ ጥልቅ ሳቅ ሳቀች።
፨ተቀበለኝ እኔን አለች ሳቋን ስጨረስ:-
"ሀኪም ሀኪሜ ነው በሳቅ የሚያክመኝ
ቃሉ ሀኪሜ ነው በጤና የሚያኖረኝ
ሳቁ ህይወቴ ነው የሚያገለግለኝ
ደስተኛው ይደሰት ደንጋጩ ይደንቅጥ
ልክ የኛን ፍቅር ለፈጥረታት ይስጥ" አለች
ወንድማቸውም ደገመው። ሀሚም እቅፍ አደረጋት። ሁሉም እነ አስሚን ማየት ጀመሩ።
፨ የእነ ዕዝራ ቤት ጭር ብሏል። የዕዝራ እናት ሳሎን ቁጭ ብለው በዝምታ ውስጥ ሆነው እያለቀሱ ነው። የዕዝራ አባት መኝታ ቤታቸው ይንጎራደዳሉ የግድግዳ ሰአቱ ድምፅ በጣም ይረብሻል። ቤቱ ፀጥ ከማለቱ የተነሳ እንኳንስ የግድግዳ ሰአቱ ቀረቶ የቢንቢ ድምፅ ነግሶ ይሰማል ቤቱ የጭንቀት ትልቁ ከተማ ሆኖል። የእናቱ የለቅሶ ድምፅም ይሰማል። ለሊቱ ለእሳቸው በጣም ከባድ እና የማይገፈ ነው። አባቱ መተው በቀስታ ከደረጃው ቁልቁል ወደ ሳሎን ሲያዩ የሳሎኑ ድባብ ከባድ ነበር። ዕዝራ ከጠፈ እና እሳቸው ቤት ከተመለሱ ጀምሮ ቤቱ ውስጥ ሰላም የለም ሰላም ማጣቱ በጣም ይጨንቃል። ግን ባይለመድም አንዳንድ ነገሮች አብረውን መኖራቸው ግድ ይሆናል። የዕዝራ አባት ተመልሰው መኝታ ቤታቸው ገብ። የዕዝራ እናትም ከሳሎኑ ካሊደር አጠገብ ያለው የዕዝራ ክፍል ውስጥ ገብ። ክፍሉ ሙሉ ዕዝራ ዕዝራ ዕዝራራራ ዕዝራራራ ይላል የእሳቸው ልብም ልጄን ልጄ ፤ ዕዝራን የክፉ ቀኒን ፤ ህይወቴን ፣የአብራኪ ክፈይን ዕዝራን ፤ አጫዋች አሳቂ ልጄን ይላል። ግን በፈላጎት የሚሆኑ ነገሮች አለም ላይ ትንሽ ናቸውና የሚፈልጉት ሊሆን አልቻለም እንደ ምኖታቸው ቢሆንማ ልጃቸው ዛሬ ላይ ፊት ለፊታቸው ያለው አልጋ ላይ ተነኝቶ እሳቸውም ሀገር ሰላም ብለው በተኑ። ግን አልሆነም!።
፨በአብጀጊ ጨረቅ የተሸፈነ የስእል ሸራ አዩ ቀስ ብለው ከፈቱት። የሲማይ ስእል ነበር "በጣም ቆንጆ ናት" አሉ። ይህንን ስእል ሲያዩ የመጀመሪያ ጊዚያቸው ነው በውስጣቸው "ልጄ እንዴት ከእኔ ተደብቆ ስእል ሊስል ቻለ?" አሉ። እውነተኛ ጥያቄ ነው ወደ ውስጣቸው የገባው ምክንያቱም ዕዝራ እናቱ እና ህዝብ ፊት ካልሆነ ስሎ አያውቅም። የስእሉ ሸራ ላይ ያረፈችው በፍቅር እብድ የሆነላት ሲማይ እንደሆነች ተረዱ። አልጋው ጠረዝ ላይ ተቀምጠው በአትኩሮት የሲማይን ስእል ማየት ጀመሩ። "በጣም ቆንጆ ነሽ በጣም ልጄ ላያዛልቀው ፍቅረሽ ህመም ሆነበት የልጄን ክፍል ከሄደ በኋላ ዛሬ መግቢቴ ነው ይናፈቀኛል ብዬ ፈረቼ እኮ ነው።" አሉና እሪሪሪ ብለው አለቀሱ። ህይወትን ታዘቧት ህይወት ተስፈ አስቆረጣቸዋለች። ህይወትን ጠልዋታል እንዴት አረጋ ብክሳቸው ልባቸው እራረቶላት እረቅ እንደሚያወረዱ ምንም አያውቁም። ውስጣቸው ተጎድቶል።

፨አስሚ እና ዶክተር ለሊት 8 ሰአት ቢሆንም አንድ ፎጣ ለሁለት ለብሰው በረንዳው መደብ ላይ ቀጭ ብለው ጨረቃዋን እያዩ ነው። ዶክተሩ አስሚን በትከሻው ነካ አረጋትና " አስሚ የዕዝራ እንዲህ መሰለብ ግን አይገረምሽም እንዴት ላይገኝስ ቻለ ሁሉም ሰው ፈልጎታል እኮ ግን ሊገኝ አይችልም ሞቶል ቢባለስ አስክሬኑ የታለ አለ ቢባልስ አካሉ የታለ።በጣም ግራ ያጋባል" አለ። አስሚ "ኧረ የሸይጣን ጆሮ ይደፈን ፈጣሪ ሰላም ያረገው እና ወደ ቤቱ ይመለስ ለወላጆቹ " አለች።

፨ዶክተሩም "ልክ ነው ክፉ ሀሳቤ ጀሀነም ይግባ" አለ። አስሚም "አሚን" አለችና ትንሽ ዝም እንደተባባሉ "አይገረምም ግን ሀኪሜ በእነሱ አሳቦ እኛን እንዴት እንዴት አረጎ እንዳገናኘን ሁሌም ሳስበው ይገረመኛል" አለችው። ዶክተሩ "አዎ እኔም በጣም እንደተገረምኩኝ ነው ፈጣሪ ሁሌም ይገረመኛል። ለእኔ ጠቃሚ የሆነ ነገር ይሰጠኛል ያውም ደሞ ላይነጥቀኝ ምክንያቱም የሚነጥቀኝን ነገር እንዳይሰጥኝ እንደለመኩት ነው ጥሩ ነገሮች ይመጣሉ እና አይነጥቀኝም" አለ። አስሚ "ፈጣሪ ለዕዝራም ያንተን አይነት እድል ቢሰጠው አስበከዋል እህኔ እንደ እሱ የተረጋጋ ፍቅር ውስጥ ያለ ሰው ላይኞር ይችላል" አለችው። ዶክተሩ "እኛስ" ሲላት "እኛማ አንገናኝም ነበር ፈጣሪ በእነሱ ፍቅር መቅረት ውስጥ ለምን የእኛን ፍቅር እንዳነገሰ ባይገባኝም ብቻ ይሁን ለበጎ ነው" አለች።
፨ የዕዝራ አባትም "ልጄ የት ነህ ልጄ እባክህ" እያሉ መንጎራደዳቸውን ቀጥለዋል። የቤታቸው ስልክ ጠራ በእዝህ ለሊት ማን ሊደውል ይችላል? የስልኩን ጥሪ የሰሙት የዕዝራ እናት ነበሩ ምክንያቱም አባቱ በሀሳብ ስምጥ ብለዋል። የቤቱ ስልክም ከዕዝራ ክፍል ትይዩ ነበር። ሰራተኛዋም መስማት የተሳናት ናት በፈጥነት ሄደው አነሱት።
"ሄሎ" አሉ። ፀጥ በድጋሜ "ሄሎ" ዝም ዘግተው እጃቸውን ከስልኩ መያዣ ሳያነሱ ጠራ አነሱት "ሄሎ" አሉ ፀጥ አራት ጊዜ "ሄሎ ሄሎ ሄሎ ሄሎ" ብለው ሊዘጉት ሲሉ "ሄሎ እማማ እናቴ" የሚል ድምፅ ሰሙ ዛሬም ልክ እንደ ከእዝህ ቀደሙ ድምፁ አንጀት ይበላል ፤ አጠራሩ ልብ ያባባል "ልጄ ዕዝራዬ አንተ ነህ?" አሉት። "አዎ እማማ እኔ ነኝ ልጅሽ ነኝ" ሲል ድምፃቸውን አፈ አረገው "ልጄ የኔ ልጅ ልጄጄጄ አካሌ" ሲሉ የዕዝራ አባት ከሀሳባቸው ባነው በፈጥነት ወደታች ወረዱ።

ክፍል 16 (አስራ ስድስት ይቀጥላል...)

ሳልሳዊ ቴሌግራም ቻናችን ላይ በመቀላቀል ያንብቡ https://t.me/kiya2313
30/06/2022

ሳልሳዊ ቴሌግራም ቻናችን ላይ በመቀላቀል ያንብቡ
https://t.me/kiya2313

Biz Gitar:ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ (የሸዋ ልጅ)biz gitar የቀድሞዋ የአለሜ ነሽ እና የፅናት ደራሲሳልሳዊክፍል 14 (አስራ አራት)          ፨ እረፋድ ስድስት ሰአት ላይ ሁሉም ...
29/06/2022

Biz Gitar:
ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ (የሸዋ ልጅ)biz gitar

የቀድሞዋ የአለሜ ነሽ እና የፅናት ደራሲ

ሳልሳዊ

ክፍል 14 (አስራ አራት)

፨ እረፋድ ስድስት ሰአት ላይ ሁሉም ከእንቅልፋቸው ተነሱ። አምሽተው ስለተኑ እና ማታ ጥሩ ጊዜ ስላሳለፉ ጥሩ እንቅልፍ ወስዶቸው ነበር። ዶክተሩ ተነቶ "ወይኔ ወይኔ" ሲል የዕዝራ አባት "ምነው ምን ሆንክ ዶክተር" ሲሉት ዛሬ በጠዋት ወደ ስራ መግባት እና ስራዎቼን ጨረሼ ማስረከብ ነበረብኝ" አለ። "እንዴ ለምን ዶክተር ከስራ ልትለቅ ነው እንዴ?" ሲሉት። "አይ አይ እረፍት ልወጣ ነው ለአስሚ ጥሩ ስረፕራይዝ አለኝ ግን በጣም ዘግይቼያለው በቃ አሁን መሄድ አለብኝ" ብሎ ተስተካከለና "ደና ዋሉ በቃ እንገናኛለን" ብሏቸው ወጣ። የዕዝራ አባትም ተከትለውት ወጡ። ልክ ሊወጣ ሲል የዕዝራ እናት እና አስሚ ጋር ተገጣጠሙ አስሚ "እንዴ ሀኪምዬ የት ልትሄድ ነው?" አልችው። ዶክተሩም "አሚዬ በጠዋት መሄድ ነበረብኝ ጨረሼ መምጣት ያለብኝ ነገር ነበር ስራ ቦታ ስጨረስ እዚሁ እመጣለሁ ጠብቂኝ እስከዛ አጫውቻቸው" ብሎ ወጣ።
፨አስሚ ከዕዝራ እናት ጋር ሳሎን እግራቸው ላይ ተኝታ እያወራች ነው። "እእእ እኔ እምለው ከዕዝራ አባት ጋር በምን እና እንዴት ተገናኛቹ የፍቅር ታሪክ
መስማት በጣም እወዳለሁ ድሮ ጓደኞቼ ፍቅረኛ ሲይዙ ምን እንደተስማቸው እጠይቃቸው ነበር። እእ እረሶም ቢነግሩኝ በጣም ደስ ይለኛል" አሉ። የዕዝራ እናትም " እኔ እና እሱ በጣም እንዋደድ ነበር። እሱ በጣም የሀብታም ልጅ ሲሆን እኔ ደሞ በጣም ደሀ እና ብቸኛ ነበረኩኝ። የተገናኘነው ኑሮ በጣም ከብዶኝ የምበላውም አጥቼ ውስጤ ምግብም ስለሌለው እራሴን ስቼ ወደኩኝ የወደኩት የዕዝራ አባት በር ላይ ነው ማለትም ዝም ብዬ የቤት ሰራተኝነት ሀብታሞች ጊቢ ለመቀጠር መዞር ጀመረኩ እንዳልኩሽ ምግብ የሚባል ነገር በአፌ አልዞረም ከዛ ያው እራሴን እንደመሳት ሲያረገኝ የሆነ ቤት በር ላይ አረፈ አልኩኝ ዞፍ ስለነበረው ዞፉ ስር ነበረኩ። ቆይቼ ስነቃ የሆነ ገነት የሚመስል ቤት ውስጥ ነኝ ገና ጣሪያውን ሳይ ነው የደነገጥኩት እግሬ የሆነ ሰው ታፉላይ እንደተቀመጠ ተሰማኝ" ስሉ የዕዝራ አባት "ኦ ጥሩ በቃ አስሚ አንቺ እሶን ካጫወትሸመት እኔ ደረጅት ሄዴ ማኔጅ ያለብኝ ነገር ስላለ አረጌ እመጣለሁ ሰላም ሁኑ የሚያስፈልጋቹ ነገር ካለ ደውሉልኝ" ብለው ወጡ። አስሚ "ደና ዋሉ" ስትል የዕዝራ እናትም "ሰላም ተመለስ" ብለው ተሰናበቱት።
፨ አስሚ "ይቀጥሉልኝ በጣም ጓጉቻለው" አለች። የዕዝራ እናት የአስሚን ግን ባር በስሱ እየነካኩ " ወደ እግሬ ሳይ የዕዝራ አባት ነበረ። ደነገጥኩኝ "ደና ነሽ እንዴት ነሽ አሁን?" አለኝ ደንግጭኤ ዝም አልኩኝ። አይዞሽ አደንግጪ በር ላይ ነው ወድቀሽ ያገኘውሽ ምነው አሞሽ ነው ዶክተር ጠረቻለው መጥቶ ያይሻል አለኝ። ድምፁ፣ ትህትናው፣ አወራሩ ፣ስረአቱ ፣መልኩ ፣ አቋሙ በቃ ምንም የማይወጣለት ነበር አሁንም እንደዛ ነው ግን ያኔ ይለያል አይኔን ከእሱ ላይ መንቀል በጭረሽ አልቻልኩም በእረግጥ እሱም እያየኝ ነው። በዛ መተያየት ውስጥ እንደማጥወልወል አለኝ እና ሆዴም ቦዶ ስለነበር ሀማት የሚመስል ነገር ወደ ላይ አለኝ እጁን ደቅኖልኝ ነበር። በጣም ልዩ ሰው ነው። አስገረመኝ" የዕዝራ እናት ይህንን ሲናገኑ ወደ እዛ ጊዜ ሙሉ ለሙሉ ተመልሰው ነበር እና ባወሩት ልክ ስሜታቸው ይቀያየራል።
፨" በእጁ የያዘውን ሆዴ ያወጣውትን ወደ እጅ መታጠቢያ ይዞት ሄደ እና የአብጀዴ ጨረቅ እና ማስታጠቢያ ይዞ መጥቶ ጠራረገልኝ አፌን ሊጠረግልኝ ሲል በእረግጥ በእጄ ይዤ ልከለክለው ነበር። እሱ ግን አልፈቀደልኝም ጨረሶ ማስታጠቢያውን ይዞ ሲነሳ ዶክተሩ መጣ። የልብ ምቴን ፣የደም ዝውውሬን እና ትኩሳቴን አየኝ። የዕዝራ አባት በጉጉት "ምን ተፈጠረ የሆነችው ነገር አለ ሲል" ዶክተሩ "አይ" ልጅ ስምኦን በጭራሽ ምንም አልሆነችም ሲለው ስሙን አወኩት "ስሞን?" አልኩኝ ቀስ ብዬ የዕዝራ አባትም "አዎ ስሞን ስሞን ሀይለእየሱስ እባላለው አንቺስ" አለኝ። ዶክተሩ ገረሞት አታቃትም እንዴ አለው "አዎ አላቃትም ዛሬ ግን አውቄያታለው" ሲለው እኔ "የእኔ ስም ደስታ ነው" አልኩት። ከዛም ፈገግ ብዬ "ደስታ ታሪኩ" ስለው ሳቀ ሳቁን ስለጠበኩት አብሬ ሳኩኝ። ዶክተሩ በቃ መሄዴ ነው ፈሳሽ ነገርም ሆነ ምግብ ውስጦ የለም ስለዚህ እኔ ልሂድ አንተ ተንከባአባት" ብሎ ወጣ።
፨ የዕዝራ አባት ሾረባ ሰራልኝ እና ቀስ እያለ በማንኪያ ኡፍፍ እያለ እያጠጣኝ። አባቱ መጡ በጣም አስፈሪ ነበሩ። ሲያዩኝ ልዩ ፈላጎታቸው ያስታውቃል ለስሞንኤ አልነገረኩትም ነግሬውም አላውቅም አስተያየታቸው የፍቅር ሳይሄን የጊዜያዊ ስሜትን የሚያስተናግዱ ሰዎች የሚያዩት ቀፋፌ አስተያየት ነበር። ያኔ በጣም ልጅ እና በጣም ቆንጆ ነበረኩኝ። አስተያየታቸውንም እሳቸውንም አልወደድኳቸውም። ብቻ እሱም ሾረባውን አስቀምጦ "አባ ተዋወቃት ፍቅረኛዬ ናት።" አላቸው። እንደዛ ሲል ግራ ገባኝ። የአባቱ ፊት ወዲያው ተኮሰታተረና ወደ ደረጃው ወጡ። ስሞኦን ቀስ ብሎ "አባቴ አተራማሽ ሰው ነው የኔ እንደሆንሽ ካላሳወኩት ይተናኮስሻል ያው እስኪሻልሽ እዝህ እንከባከብሻለው" አለኝ። እኔ "አይ በጭራሽ እኔ ወደ ቤቴ ነው የምሄደው" ስለው" ፈገግ ብሎ "አይይ ቤት እራስሽን የምትንከባከቢበት ቤት እንደሊለ ስትቃዢ ሰምቼሻለሁ አትሸማቀቂ እባክሽ ተሸማቀሽ አታሸማቂኝ" አለኝ። እሺታዬን ገለፅኩለት።
፨ ያን ጊዜ ቤታቸውን እንደቤቴ እንዳይ አረገኝ ልክ እንደ ልጄ ቀዥቃዣ ነበረኩ። እሱ ግን በጣም የተረጋጋ ነበር። ልክ ሻል ሲለኝ ወደ ገበያ ሄደን ልብሶች ገዛልኝ። በቃ እነሱ ቤት አብሬ መኖር ጀመረኩ። ስሞን ከሊለ እና አጋጣሚ አባቱ ከመጡ ሳላስበው መተው ጡቴን ይነኩኛል ሊያቅፉኝም ያቃጣቸዋል ይህንን ሁሉ ነገር ለስሞን ሳልነግረው ትምህረቱን ጨረሶ ተመረቀ። ከዛ ግን አባቱ "እኔን ምረጭ እሱን ተይው" ይሉኝ ጀመረ በጣም አስጨነቁኝ ይህ ፈላጎታቸው እየገፋ ሲመጣ ለስሞኔ መናገር ስለነበረብኝ ነገረኩት። ተበሳጨ ተናደደ ያንን ስአት ነበር ስሞን እንደሚያፋቅረኝ የነገረኝ እኔም ተረትቼለት ስለነበር ጊዜ ሳላጠፈ ነበር እሺ ያልኩት። እኔ እና እሱ ፍቅራችን ጠንካራ ሆነ የአባቱም ትንኮሳ በጣም ባሰ የሆነ ቀን ጠዋት መኝታ ቤቴ ተኝቼ አባቱ መጡ ሁኒታቸው ሊላ ነገር ይመስላል በጣም ፈራሁ "ስሞን አድነኝ ብዬ ጮኩኝ" እሳቸው ደንግጠው ወጡ። ስሞን ሲመጣ ኩረትም ብዬ ተኝተቼ ነበር መጣና አቅፎኝ "መኝታ ቤቴ ድረስ አድነኝ ብለሽ ስትጮሂ ድምፅሽን ሰምቼያለሁ ሲለኝ እኔ ቅዠት እንደሆነ ነገረኩት። አቅፎ እንደረጋጋ አረገኝ። በነጋታው ግን ከእዚህ ቤት እኔንድንወጣ እና አብረን እንድንኖረ ጠየኩት። እሱም ሊጫነኝ ለምን ሊለኝም አልፈለገም እና ቤት ፈልጎ ሲያገኝ ከዛ ቤት ወጣን። ኑሮ ብዙ አልከበደንም እሱም ይሰራል ከአባቱም ድጎማ ያገኘው ብር አለ። ብቻ እየኖረን የሆነ ጊዜ ላይ የስሞን አባት መጡ "ጋሽ ሀይለ እየሱሰሰ ምነው ምን ፈለጉ" ስላቸው ቁጭ ብለው የታሸገ ብር ሰጡኝ ምን ላረገው ስላቻው "ወደ እኔ ከመጣሽ ገና ብዙ ታገኛለሽ ወደ እኔ ከመጣሽ" አሉኝ። እኔም ብሞት እንኳን ከእሳቸው ጋር እንደማልሆን እና በህይወቴ ወልጄ ለማመጣው ልጅ አያት እንጂ አባት እንደማይሆኑ ባል ሳይሆን የባሌ አባት እና የልጄ አያት እንደማረጋቸው ነግሬ አባርኳቸው። ተናደው ነበር የወጡት።

፨ ከዛን ቀን ጀምሮ ነበር የእኔ እና የስሞን ህይወት የከበደው አባቱ ከስራ ቦታው አባረሩት ሊላ ቦታ እንዳይቀጠረም አረጉት የድጎሞ ብሩም ቀረ። ህይወት ሰትከብደን እቃችንን ሽጠን የረከሰ ቤት ገባን ትንሽ ጥሬ ብር ቤት ውስጥ ስለነበረ በእዛች እጣን ሰንደል እና አትክልት ጎን ለጎን መነገድ ጀመረኩ። በአንዴ ሰዎች ወደውኝ ጥሩ መስራት ጀመረኩኝ። ለመጀመሪያ ጊዜ ከዕዝራ አባት ጋር እንደ ሴት እና ወንድ ተኛን ከወራት በኋላ ዕዝራ ተረገዘ በጣም ደስ ብሎን ነበር። ግን እኔም ንግዱን ትቼ ስቀመጥ እና እረግዝናዬም ከባድ ስለነበር ለመዳኒት ለምግብ እየተባለ ብራችን አለቀ። በቃ እጅ ወደላይ አልን ከዛ የዕዝራ አባትም ከአባቱ እኔን እንደተወኝ ተናግሮ ብር ተቀበላቸው ምክንያቱም እሷን ከተውካት የፈለከውን አረጋለው ስላሉት በመጨረሻም ልክ ዕዝራ 3 አመት ሲሆነው ለህይወታችን ለመለውጥ ብሎ ተሰደደ እኔም በተወልኝ ብር ያቋረጥኩትን ንግድ ጀምሬ እኔ እና ልጄን ማኖር ጀመረኩ" ብለው ከዛን በኋላ ያለውን የዕዝራ አባት አቶ ስሞን የነገራቸውን ሁሉ ለአስሚ ነገሯት። አስሚ በጣም ተደመመች።
፨ ዶክተረ መጣ። "አስሚ ተነሽ በቃ መሄዳችን ነው" አላት። "ወዴት ሀሚም" ስትለው። እሱን ስንሄድ ታይዋለሽ በጣም ትወጅዋለሽ የዕዝራ እናት በቃ እንመጣለን እሺ እንደዋወላለን እዝህ ውስጥ ልብስ አለ ቀይረሽ ነይ" ብሎ ፊስታል ሰጣት አስሚ ተቀብላው ወደ መኝታ ቤት ገብታ ቀይራ ወዲያው ወጣች። አምሮባት ነበር ከዛማ አስሚን እጆን ይዞ መኪና ውስጥ አሰሰገባትና መኪናውን አስነስቶ በረረ ከነፈፈፈፈ "ወዴት ነን ለምን አትናገረም በፈጠረክ ቆይ ምን እየሆንክ ነው" አለችው። ዶክተሩ "ዝም ማለት አትችይም እንዴ በአላህ እስቲ ለደቂቃ ዝም በይ በእረግጥ ጉዟችን ለሰአታት ነው ግን ለስለስ ያለ ዘፈን እየሰማን እንሄዳለን አለና ዘፈን ከፈተ
"አንቺ አጋሬ ሆነሽ ለህይወቴ ምን ብዬ ልጥራሽ...... " ዘፈኑ ተቀወጠ አስሚ "እብድ ነህ እኮ ሲነሳብህ ያ አላ" አለች።

ክፍል 15 (አስራ አምስት ይቀጥላል...)

Address


Telephone

+251985401154

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yo ትረካ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share