26/01/2020
አብረን እንደግ.
ዱንያ ሩጫ ናት፡፡ ስትቀድም አንደኛ ነህ ተብለህ የምትሸለምበት ዓለም፡፡ ሁሉን ጣጥለህ ብቻህን ስትገባ የምትደነቅበት ምድር፡፡
በዲን ዓለም ዉስጥ ግን ጥሎ መግባት አይበረታታም፡፡ ራስ ወዳድነት አይመከርም፡፡ ሰዎች ስለ ራሣቸው ነፍስ ብቻ ሳይሆን ስለ ሌሎችም እኩል መጨነቅ አለባቸው፡፡ “ለራሣችሁ የምትወዱትን ለወንድማችሁ እስካልወደዳችሁ ድረስ በርግጥ አላመናችሁም፡፡” ይላል ሐዲሡ፡፡
በመንፋሳዊነት ዓለም ክብርህ የበለጠ ከፍ የሚለው የደረሰህን መልካም ነገር ለሌላው ሼር ስታደርግ፣ በጎ ለሚሠሩት ላይክ ስትገጭ፣ ወደኋላ የቀረዉን ስትጎትት፣ የደከመዉን ስታግዝ፣ የወደቀዉን ስታነሳ ነው፡፡ ረሱላችን ስለኛ እንዳሰቡ ነው ወደ አኺራ የተሸጋገሩት፡፡ ስለጠፉት ህዝቦቻቸው እንደተጨነቁ ነው ይህንን ዓለም የለቀቁት፡፡
ዱንያ ላይ ስትኖር ልክ እንደመጀሪያ ልጅ ልትሆን ግድ ይልሃል፡፡ ተጠባቂ እንጂ ጠባቂ አትሁን፣ ተረጂ ከመሆን እርዳታ ሰጭ ለመሆን ጣር፡፡ የሚያሻግርን ከምትጠብቅ አሻጋሪ ሁን፡፡
በመጀመርያ ልጅ ላይ ሁሌም ጫና ይበዛል፡፡ ታናናሾቹን ከወደቁበት ጎትቶ ከማስነሳት ጀምሮ እስከ ተሸክሞ ማሳደግ ይደርሳል ልፋቱና ድካሙ፡፡ ቢከብደውም ትችላለህ ተሸከም ይባላል፡፡ በዚያዉም ትከሻው እየደነደነ ያድጋል፡፡ እኛም እንዲሁ የተሠጠንን ዕውቀትና አቅም በመጠቀም በዲን ዉስጥ ብዙ ልጆችን እናሳድግ፡፡ ትንሽ ብትሆንም ከዕውቀት፣ ከሀሳብም ሆነ ከጉልበት የተሠጣችሁን አካፍሉ፡፡ እንዲያ ስንሆን እኛ እናድጋለን፤ ሌሎችንም እናሳድጋለን፡፡
ሌሎችንም ሆነ የሌሎችን ጉዳይ መሸከም መቻላችን ትልቅ ለመሆናቸውን ማሳያ ነው፡፡ የሌሎችን ሀሳብ ከባለቤቱ በላይ ተሸክመው የሚዞሩ ብዙ አዛኝ አማኞች አሉ፡፡ ዲን መተሳሰብ ነውና፡፡
ሰዉን መሸከም ሲባል ሲሞት ጀናዛዉን ተሸክሞ ወደ መቃብር መውሰድ ሳይሆን አሁን በሕይወት እያለ አካሉን፣ ሀሳቡንና ጭንቀቱን መጋራት ነው፡፡
እንዲህ ማዶ ለማዶ ተለያየተን የቀረነው መሸካከም ስላቃተን እኮ ነው
አስተማሪ እና መልእክት አዘል የሆኑ ማስታወሻዎችን፣ ትረካዎችን፣ አነቃቂ ንግግሮችን እንዲሁም ዳዕዋዎችን የምታገኙበት የናንተው ቻናል
ቴሌግራም ላይ ይቀላቀሉን
telegram group: t.me/fejirmedia
telegram channel: t.me/fejir2
Whatsapp: https://chat.whatsapp.com/BlNXkoD8nhLGBRXYoQsUTe
አስተማሪ እና መልእክት አዘል የሆኑ ማስታወሻዎችን፣ ትረካዎችን፣ አነቃቂ ንግግሮችን እንዲሁም ዳዕዋዎችን የምታገኙበት የናንተው ቻናል ቴሌግራም ላይ ይቀላቀሉን telegram group: t.me/fejirmedia te...