DanDagne

DanDagne Igoto new info

25/04/2023

አንድ ንጉስ አስር ተናካሽ ውሾች (Wild dogs) ነበሩት ፤ እነዚህን ውሾችም አገልጋዮቹን ሲያጠፉ ለማሰቃየትና ለማስበላት ይጠቀምባቸው ነበር፤
:
ከዕለታት አንድ ቀን አንዱ አገልጋይ ያልተገባ ንግግር ንጉሱን ተናገረው ፤ በዚህም ምክንያት ንጉሱ እጅግ ተቆጣ ፤ ወዲውም ወደ ውሾቹ ጉድጓድ እንዲወረወር ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡ አገልጋዩም በሀዘን "አስር አመታት አገለገልኩህ ፤ ተገዛውልህ ያልከኝን ሁሉ አደረኩልህ ፤ አሁን ግን ይህንን አደረክብኝ ፤ እባክህ ወደ ውሾች ጉድጓድ ከመወርወሬ በፊት አስር ቀን ስጠኝ" ብሎ ተማጸነው፡፡

ንጉስም ተስማማ "ፈቀደለት" ፡፡ ይወረወር ዘንድ የተፈረደበት አገልጋይ ውሾቹን ወደሚንከባከበው ሌላኛው አገልጋይ ሔደና "እባክህ እነኝህን ውሾች ለአስር ቀን ልንከባከባቸው"ብሎ ጠየቀው፡፡ የውሾቹ ጠባቂም ግራ ቢጋባም ይፈቅለታል ፡፡

የተፈቀደለት አገልጋይም ውሾቹን መንከባከብ ጀመረ ፤ ቆሻሻቸውን ማጸዳዳት ፤ ምግባቸውን በሰዓቱ ማቅረብ ፤ ማጠብና አስፈላጊውን እንክብካቤ ሁሉ አደረገላቸው ፤ አስር ቀኑም አለቀ፡፡

ከዚያም በኋላ ከንጉስ ጋር በተነጋገሩት መሰረት …አገልጋዩ ተጠርቶ ወደ ተናካሽ ውሾቹ ጉድጓድ ይወረወር ዘንድ አዘዘ ፤ ወረወሩትም ፡፡ ወርዋሪዎቹም ይህ አሽከር እንዴት በውሾቹ ሊበላ እንደሚችል እየዘገነናቸው መመልከት እንደጀመሩ ያላሰቡትን ሁኔታ በአይናቸው አየ፤

ንጉሱም በሚመለከተው ሁኔታ ግራ ተጋባና «እነዚህ ተናካሽ ውሾቼ ምን ሆነው ነው ዛሬ? ምንስ ገጠማቸው?» ማለት እንደጀመረ…

የተወረወረው አገልጋይ በውሾቹ መሃል ውሾቹ እያተሻሹት በኩራት እየተራመደ እንዲህ አለ "እነዚህን ውሾች ለአስር ቀናቶች ብቻ መገብኳቸው ተንከባከብኳቸው እነርሱም ያደረኩላቸውን በፍጹም አልዘነጉም ፤ አንተን ግን አስር አመት ሙሉ ተገዛሁልህ አገለገልኩህ ነገር ግን በአንዲት ጥፋት ምክንያት ሁሉንም ረሳህና ለሞት አሳልፈህ ሰጠኸኝ" አለው ፡፡

ንጉሱም ሁኔታውን ሁሉ በማስተዋልና ፤ ከውሾች እንዳነሰም በመገንዘብ አገልጋዩ ነጻ እንዲሆን አዘዘ ፤ ነጻም ሆነ፡፡

ሰው በጣም ብዙ ውለታ ውሎላቸው ነገር ግን በአንድ ጥፋት ምክንያት የተደረገላቸውን ሁሉ እየረሱ በክፋት ለሚነሳሱ ሁሉ ይሁን፡፡ በመልካም ነገር የተሞላ ታሪክን ፤ በአንድ ስህተት ምክንያት ከንቱ አናድርግ፡፡
መልእክቱ አስተማሪ ሆኖ ካገኙት ሼር ላይክ እና ሼር በማድረግ ለሌሎች አጋሩ።

Tesfaye
photo credit - Teddy beer,Hyderabad
Source:[Occasion.com]

06/10/2022

✅ የሳይኮሎጂ ፕሮፌሰሩ ወደ ክፍል ገብቶ የእለቱን ወሳኝ ትምርት ለመጀመር ወደ ቦርድ እንደዞረ ፉጨት ሰማ።

ወደ ተማሪዎቹ ዞሮ ማን እንዳፏጨ ጠየቀቃቸው ፣ሁሉም ዝም አሉ።

ፕሮፊሰሩ ተረጋግቶ ፣እስክሪቢቶውን ወደ ኪሱ እየከተተ ፣የዛሬው ሌክቸር እዚ ላይ ያበቃል፣ፈገግ ብሎ ነገር ግን መጀመሪያ አንድ ታሪክ እነግራችዋለው አላቸው።ሁሉም በጉጉት መጠበቅ ጀመረ

" ትላንት ቤቴ እንቅልፍ ስላስቸገረኝ ፣ዝም ብዬ ተነስቼ ነዳጅ ልሞላም በዛውም ልናፈስ ለዛሬም ጊዜ ለመቆጠብ ከመሽ ወጣሁ🚗🚗🚗,ነዳጅ ከሞላሁ በኋላ ከትራፌክ ነጻ የሆነው መንገድ ላይ እየተንሸራሸርኩ ከሆነ ፖርቲ ነገር የወጣች የምትመል ቆንጂዬ ወጣት አየሁ።

መኪናዬን አዙሬ እርዳታ እንደምትፈልግ ጠየኳት "ታክሲ እንዳጣች እና ቤቷ እንዳደርሳት ነገረችኝ"

ጋቢና ገባች....ማውራት ጀመርን....ውበት ብቻ ሳይሆን ባወራነው ርእስ ሁሉ በጣም ስማርት ጭንቅላት እንዳላት ከምታወራው መገመት ቻልኩ።

ቤቷ እንደደረስን ፣በጣም ጥሩ ሰው እንደሆንኩ ነገረችኝ፣እኔም ጥሩ አስተሳሰብ እንዳላት ነግሬአት እንደወደድኳት ነገርኳት፣ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር እንደሆንኩ አውርተን ፣ስልክ ተለዋወጥን።

አንድ ነገር ላስቸግርህ ስትለኝ ፣ምንም ችግር የለውም አልኳት ።"ወንድሜ አንተ የምታስተምርበት ዩኒቨርስቲ ተማሪ ነው፣በኛ ግንኙነት እንዳይጎዳ ቃል ግባልኝ" አለችኝ ....ችግር የለም ብዬ ስሙን ጠየኳት።አንድ መለያ ባህሪ አለው በሱ ታውቀዋለህ፣ፉጨት ማፏጨት ያዘወትራል። አለችኝ

ከዛ ሁሉም ተማሪ ወደ አፏጨው ልጅ ዞሮ ማየት ጀመረ

ፕሮፌሰሩ
"የሳይኮሎጂ PHD ዬን አልገዛውትም፣ሰርቼ ነው ያገኘውት ና ውጣ "🙆‍♂😂😂
ከተመቻችሁ ሼርርርር
ምርጥ መጣጥፎች

Address


Telephone

+251955949897

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when DanDagne posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share