Fitsum Media

Fitsum Media ዜና ተዓማኒ እና ወቅታዊ መረጃ ፤ አስተማሪ እና አዝናኝ ፕሮግራም!

 #ዶክተር  #አብይን  #የሚመስሉት  #ሰው!ከወደ ሶማሊያ ፑንትላንድ የተሰማው ዜና ፈገግታን የሚጭር ሆኗል።"የኢትዮጵያውን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን በመምሰሌ የደህንነት ስጋት ስላለብ...
15/11/2023

#ዶክተር #አብይን #የሚመስሉት #ሰው!

ከወደ ሶማሊያ ፑንትላንድ የተሰማው ዜና ፈገግታን የሚጭር ሆኗል።

"የኢትዮጵያውን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን በመምሰሌ የደህንነት ስጋት ስላለብኝ ጥበቃ ይደረግልኝ" ያሉት በፑንትላንድ ግዛት የዋኢዮ ወረዳ አስተዳዳሪ ኢሳቅ አህመድ ሀሰን በሶማሊያ ሶሻል ሚዲያዎች የእለቱ ሳቅ የሚጭር መነጋገሪያ ሆኗል።

ሰውዬው በሶሻል ሚዲያ ብቅ ብለው በአፍ ሶማሊ ቋንቋ "አብይን ትመስላለህ እያሉ ህይወቴን አደጋ ውስጥ የከተቱብኝ ሰዎች አሉ። እኔ ሳልሆን አብይ ነው እኔን የሚመሰለው። በዚህ ምክንያት ለህይወቴ ሰለሰጋሁ ያለጠባቂ መንቀሳቀስ አቁሜለሁ።

በዛ ላይ የአባቱ እና አባቴ ስም አንድ ነው። ወደ ኢትዮጵያ የሄድኩት በመለስ ዘመን ነው አሁን መሄድ ብፈልግም ለደህንነቴ ስጋት ስላለብኝ ጠባቂ ያስፈልገኛል።" ብለዋል።

በፑንትላንድ ግዛት የዋኢዮ ወረዳ አስተዳዳሪ ይህን መልእክት ያስተላለፉት ለቀልድ ይሁን የምራቸውን ግን የታወቀ ነገር የለም።

14/11/2023
 #ኢትዮጵያ  #ድምፀ  #ተአቅቦ  #ያደረገችበት  #የተመድ  #አስቸኳይ  #እና  #ልዩ  #ጉባኤ  #ተካሄደ።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዓርብ ምሽት በእስራኤል እና ሃማስ የጋዛ ...
28/10/2023

#ኢትዮጵያ #ድምፀ #ተአቅቦ #ያደረገችበት #የተመድ #አስቸኳይ #እና #ልዩ #ጉባኤ #ተካሄደ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዓርብ ምሽት በእስራኤል እና ሃማስ የጋዛ ጦርነት ጉዳይ አስቸኳይ እና ልዩ ጉባዔ አካሂዷል።

በዚህም ጉባኤ በ " ዮርዳኖስ " አቅርቢነት በጋዛ " አስቸኳይ የሰብአዊ ተኩስ አቁም " እንዲደረግ የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ ቀርቦ ነበር።

የሰብዓዊ ተኩስ አቁም ጥሪ የቀረበበት የውሳኔ ሀሳቡ ፦
- በ120 ድጋፍ፣
- በ14 ተቃውሞ
- በ45 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ጸድቋል።

በዚህም መሰረት ተመድ በጋዛ አስቸኳይ የሰብዓዊ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፏል።

የውሳኔ ሃሳቡን ከተቃወሙት ውስጥ አሜሪካ ፣ እራሷ እስራኤል ፣ ሃንጋሪ ፣ ኦስትሪያ ይገኙበታል።

ድምፅ ተአቅቦ ካደረጉት መካከል ደግሞ ሀገራችን #ኢትዮጵያ ፣ ጀርመን ፣ ካናዳ፣ ግሪክ፣ ፊንላንድ፣ ዴንማርክ፣ ስውዲን፣ ኢራቅ፣ ጃፓን፣ ጣልያን፣ ሕንድ ፣ዩናይትድ ኪንግደም፣ ዩክሬን፣ ቱኒዝያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ዛምቢያ ይገኙበታል።

የተመድ አስቸኳይ እና ልዩ ጉባዔ የተካሄደው በእስራኤል እና ሃማስ መካከል ጦርነቱ ተባብሶ በቀጠለበት ሁኔታ ነው።

እስራኤልም በጋዛ የምድር ዘመቻ ማካሄድ ጀምራለች።

የእስራኤል ጠ/ሚ ቤንያሚን ኔታንያሁ አማካሪ ማርክ ሬጅቭ የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን #ሃማስ በሰብአዊነት ላይ በርካታ የግፍ ወንጀሎችን መፈፀሙን ገልጸው ለዚህም ደግሞ ከዓርብ ምሽት (ትላንት) ጀምሮ ክፍያውን #እንደሚከፍል እና እስራኤልም መመለስ መጀመሯን ተናግረዋል።

ሀማስ እስራኤል ለምታካሂደው የምድር ላይ ዘመቻ አፀፋውን ለመስጠት ሙሉ ዝግጁነት እንዳለው ገልጿል።

የሀማስ የፖለቲካ ቢሮ ከፍተኛው አመራር ኢዛት አል-ሪሻቅ " ኔታንያሁ ወደ ጋዛ ለመግባት ከወሰነ እኛም ዝግጁ ነን " ያሉ ሲሆን " የወታደሮቹ ሬሳ በጋዛ ምድር ይዋጣል " ብለዋል።

21ኛ ቀኑን በያዘው በእስራኤልና ሃማስ ጦርነት በእስራኤል ጥቃት ጋዛ የተገደሉ ሰዎች ከ7300 መብለጣቸውን በሃማስ ስር ያለው የጤና ሚኒስቴር የገለፀ ሲሆን በእስራኤል በኩል በሃማስ የተገደሉም ከ1400 በልጠዋል።

 #እስራኤል  #ወደ  #ጋዛ  #እግረኛ  #ተዋጊ  #የማስገባት  #እቅዷን  #እንዳራዘመች  #አስታወቀችእስራኤል ወደ ጋዛ የእግረኛ ጦር ለማስገባት ያወጣችውን እቅድ ማራዘሟን ጠቅላይ ሚኒስትር...
27/10/2023

#እስራኤል #ወደ #ጋዛ #እግረኛ #ተዋጊ #የማስገባት #እቅዷን #እንዳራዘመች #አስታወቀች

እስራኤል ወደ ጋዛ የእግረኛ ጦር ለማስገባት ያወጣችውን እቅድ ማራዘሟን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጋዛ የምድር ዘመቻ ለማድረግ በወጣው እቅድ ላይ አለመፈረማቸውን ተከትሎ ከጦራቸው ጋር አለመግባባት ውስጥ ገብተዋል የተባለ ሲሆን ኔታኒያሁ ውሳኔያቸውን ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት እንዲያገኝ ጠይቀዋል፡፡

የእስራኤል ጦር አመራሮች ለሃማስ አፀፋ ከመስጠት በተጨማሪ ቡድኑን ለማጥፋት ቢስማሙም ሃማስን ለማጥፋት በሚደረጉ የጦር ስልቶች ላይ ግን መግባባት ላይ እንዳልደረሱ ምንጮችን ጠቅሶ አር ቲ ዘግቧል፡፡

እስራኤልከ ከሃማስ ጥቃት በኋላ 360 ሺህ የሚጠጉ ተጠባባቂ ወታደሮችን ያሰባሰበች ሲሆን ለሶስት ሳምንታት በተመረጡ የሃማስ ኢላማዎች ላይ የአየር ድብደባ ስታደርግ ቆታለች፡፡

እስካሁን እግረኛ ተዋጊ ወደ ጋዛ ሰርጥ ባይገባም በተወሰኑ የፍልስጤም ግዛቶች መጠነኛ የምድር ተዋጊ ወታደሮች እንቅስቃሴ እንደነበር ተዘግቧል፡፡

ቀደም ሲል ዋሽንግተንና የተወሰኑ የአውሮፓ አጋር ሀገራት ቴል አቪቭ በምድር ላይ አካሂደዋለሁ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ እንድታዘገየው ጫና ሲያደርጉ መቆየታቸው የሚታወስ ነው፡፡

26/09/2023

#እየተዝናኑ #የሚማሩበት #ልዩ #የመስቀል #በዓል #ዝግጅት

ልዩ የመስቀል በዓል ዝግጅት በዕለተ ሐሙስ ሊቀርብ ነዉ።አብርሃም ግዛው ኢንተርቴይመንት ፕሬስ ስራዎች ኃ.የተ. የግ. ማህበር አርትስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር በመተባበር ‹‹ መስቀልና ባህላዊ አከባበር ›› በሚል ልዩ የመዝናኛ ዝግጅት በአገር ውስጥ እና በውጪ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሐሙስ መስከረም 17 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ10:ዐ0-12:00 ሠዓት እንደ ተዘጋጀ ተገልጿል።።በዝግጅቱም ላይ ከመዝናናት በዘለለ በርካታ ቤተሰባዊ ጉዳዮች ለመማሪያነት እና በበአሉም ላይ ለመዝናናት እንዲረዱ ተደርገው ይቀርባሉ፡፡ በፕሮግራሙ ላይ ከተካተቱ ዝግጅቶች ውስጥ በጥቂቱ ፡፡ 1.1.1. መዝናኛ የመስቀል በዓል ባህላዊ ጨዋታ ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ፣ የሃገር ሽማግሌዎች ምርቃት፣ የእንግዶች ምርጥ ተሞክሮ፣ የመስቀል ጨዋታዎች በልዩ ሁኔታ ይቀርባል፡፡ የኮሜዲያን ዝግጅቶች፣ ታዋቂ ሰዎች ስለ በዓሉ ምን ይላሉ? በዓሉን በሚመለከት ባህላዊ ሙዚቃዎች በታዋቂ ድምፃውያንና የሙዚቃ ባንድ ይቀርባሉ፡፡ አንጋፋ ሙዚቀኞች ቆየት ያሉ ሙዚቃዎችን በመድረክ የሚቀርቡበት ፕሮግራም እንዲሁም የመስቀል በዓልን የሚያከናውኑ ባህላዊ በዓል አከባበር ሥርዓቶች ወደ ትውልድ እንዴት ይሸጋገራሉ ፡፡ የመስቀል በዓል ሚከናወኑ ባህላዊ በዓል አከባበር ሥርዓቶች ወደ ትውልድ እንዴት ይሸጋገራሉ ፡፡ ባህላዊ የበዓሉን አከባበር በተመለከተ ፡፡ ባህላዊ ጨዋታዎችና ጭፈራዎች ይደረጋሉ ፡፡ የክርስትና እምነት አባቶች የመስቀል በዓል ላይ ትኩረት ያደረጉ በተለይ የቤተክርስቲያን እምነት እና ሥርዓት ያቀርባሉ ፡፡ በሚሉ ዙሪያዎች ፕሮግራም አካል ናቸዉ ፡፡ የታዋቂ ሰዎች ንግግር ማስመሰል ውድድር የደመራ ኘሮግራምና እና ሌሎች ጨዋታዎች እንዲሁም ባህላዊና ዘመናዊ ሙዚቃዎች ለዝግጅቱ ታዳሚዎች በዕለቱ የሚቀርቡ ይቀርባሉ በዝግጅቱም ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ አርቲስቶችና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በተገኙበት በድምቀት እንደሚተላለፍ አዘጋጆቹ ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀውልናል፡፡

26/09/2023

#ልዩ #የመስቀል #በዓል #ዝግጅት

ልዩ የመስቀል በዓል ዝግጅ በዕለተ ሐሙስ ሊቀርብ ነዉ አብርሃም ግዛው ኢንተርቴይመንት ፕሬስ ስራዎች ኃ.የተ. የግ. ማህበር አርትስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር በመተባበር ‹‹ መስቀልና ባህላዊ አከባበር ›› በሚል ልዩ የመዝናኛ ዝግጅት በአገር ውስጥ እና በውጪ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሐሙስ መስከረም 17 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ10:ዐ0 እስከ12:00 ሠዓት እንደ አዘጋጀ ሲገልፅ በዝግጅታችን ከመዝናናት በዘለለ በርካታ ቤተሰባዊ ጉዳዮች ለመማሪያነት እና በበአሉም ላይ ለመዝናናት እንዲረዱ ተደርገው ይቀርባሉ፡፡ በፕሮግራሙ ላይ ከተካተቱ ዝግጅቶች ውስጥ በጥቂቱ ፡፡ 1.1.1. መዝናኛ የመስቀል በዓል ባህላዊ ጨዋታ ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ፣ የአገር ሽማግሌዎች ምርቃት፣ የእንግዶች ምርጥ ተሞክሮ፣ የመስቀል ጨዋታዎች በልዩ ሁኔታ ይቀርባል፡፡ ኮሜዲያን ዝግጅቶች፣ ታዋቂ ሰዎች ስለ በዓሉ ምን ይላሉ? በዓሉን በሚመለከት ባህላዊ ሙዚቃዎች በታዋቂ ድምፃውያንና የሙዚቃ ባንድ እንዲቀርቡ ያደርጋል፡፡ አንጋፋ ሙዚቀኞች ቆየት ያሉ ሙዚቃዎችን በመድረክ የሚቀርቡበት ፕሮግራም ፡፡ የመስቀል በዓልን የሚያከናውኑ ባህላዊ በዓል አከባበር ሥርዓቶች ወደ ትውልድ እንዴት ይሸጋገራሉ ፡፡ የመስቀል በዓል ሚከናወኑ ባህላዊ በዓል አከባበር ሥርዓቶች ወደ ትውልድ እንዴት ይሸጋገራሉ ፡፡ ባህላዊ የበዓሉን አከባበር በተመለከተ ፡፡ ባህላዊ ጨዋታዎችና ጭፈራዎች ይደረጋሉ ፡፡ የክርስትና እምነት አባቶች የመስቀል በዓል ላይ ትኩረት ያደረጉ በተለይ የቤተክርስቲያን እምነት እና ሥርዓት ያቀርባሉ ፡፡ በሚሉ ዙሪያዎች ፕሮግራም አካል ናቸዉ ፡፡ የታዋቂ ሰዎች ንግግር ማስመሰል ውድድር የደመራ ኘሮግራምና እና ሌሎች ጨዋታዎች እንዲሁም ባህላዊና ዘመናዊ ሙዚቃዎች ለዝግጅቱ ታዳሚዎች በዕለቱ የሚቀርቡ ይቀርባሉ በዝግጅቱም ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ አርቲስቶችና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በተገኙበት በድምቀት እንደሚተላለፍ አዘጋጆቹ ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀውልናል፡፡

 #ሩሲያ  #ከኔቶ  #ጦር  #ጋር  #የመዋጋት  #መብት  #እንዳላት  #ተገለጸየሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ 450 ቀናት ያለፈው ሲሆን ጦርነቱ እንዲቆም የተለያዩ ጥረቶች በበርካታ ሀ...
01/09/2023

#ሩሲያ #ከኔቶ #ጦር #ጋር #የመዋጋት #መብት #እንዳላት #ተገለጸ

የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ 450 ቀናት ያለፈው ሲሆን ጦርነቱ እንዲቆም የተለያዩ ጥረቶች በበርካታ ሀገራት ቢደረጉም እስካሁን መፍትሔ አልተገኘለትም፡፡አሜሪካንን ጨምሮ የኔቶ አባል ሀገራት እና ሌሎች የዓለማችን ሀገራት ለዩክሬን የጦር መሳሪያ እና ወታደራዊ ቴክኖሎጂዎችን በመርዳት ላይ ይገኛሉ፡፡ሩሲያ ሀገራት ለዩክሬን የሚሰጡትን ድጋፍ እንዲያቆሙ በተደጋጋሚ ያሳሰበች ቢሆንም ለኪቭ የሚሰጠው ድጋፍ እንደቀጠለ ነው፡፡ዩክሬንም በድጋፍ መልክ ባገኘቻቸው ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች ወደ ሩሲያ ምድር ዘልቃ በመግባት ተደጋገሚ ጥቃቶችን በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡ይህንን ተከትሎም የሩሲያ ጸጥታ ምክር ቤት ሃለፊ የሆኑት ድሚትሪ ሜድቬዴቭ ሩሲያ ከኔቶ ጋር የቀጥታ ጦርነት የመጀመር መብት አላት ብለዋል፡፡ዩክሬን በሩሲያ ላይ ለምትሰነዝራቸው እያንዳንዱ ጥቃቶች የኔቶ ድጋፍ እና ይሁንታ አለው ያሉት ሜድቬዴቭ ይህም ሩሲያ ከኔቶ ጋር ጦርነት ለመጀመር በቂ ምክንያት መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡እንደ ዩሮ ኒውስ ዘገባ የኔቶ ልዩ ወታደሮች በዩክሬን ግዛት ውስጥ የገቡ ሲሆን ወታደሮቹ ለምን ዓላማ እንደገቡ እስካሁን አልተገለጸም፡፡የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት በጊዜ ካልተቋጨ ለሶስተኛው የዓለም ጦርነት መጀመር ምክንያት ሊሆን እንደሚችል በተደጋጋሚ ተገልጿል፡፡ሩሲያ ብሔራዊ ሉዓላዊነቴ ጥያቄ ውስጥ ከገባ የኑክሌር አረር ጦር መሳሪያዬን ለመጠቀም እገደዳለሁ በሚል ማስጠንቀቋ አይዘነጋም፡፡ሞስኮ በተደጋጋሚ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ልምምድ በየብስ፣ ባህር እና ሀይር ሀይሏ አማካኝነት ያካሄደች ሲሆን የተወሰኑ መሳሪያዎችን ወደ ጎረቤት ሀገር ቤላሩስ እንዲሰፍርም አድርጋለች፡፡

 /24_የአውሮፓ_ቻምፒዮንስ_ሊግ_ድልድል_ይፋ_ሆነተወዳጁ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የ2023/24 የውድድር መርሀ ግብር በፈረንሳይ ሞናኮ ይፋ ተደርጓል።በውድድሩ አራት ክለቦችን ከሳተፈው የእን...
01/09/2023

/24_የአውሮፓ_ቻምፒዮንስ_ሊግ_ድልድል_ይፋ_ሆነ

ተወዳጁ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የ2023/24 የውድድር መርሀ ግብር በፈረንሳይ ሞናኮ ይፋ ተደርጓል።በውድድሩ አራት ክለቦችን ከሳተፈው የእንግሊዝ ክለቦች ውስጥ ኒውካስትል ዩናይትድ በምድብ ስድስት ከፒኤስጂ፣ ቦርሲያ ዶርትሙንድ እና ኤሲ ሚላን ጋር ተደልድሏል።በምድብ አንድ የጀርመኑ ባየር ሙኒክ ፣ማንችስተር ዩናይትድ ፣ኮፐንሀገን እና የቱርኩ ጋላታሳራይ ተደልድለዋል።በምድብ ሁለት ደግሞ ሲቪያ፣ አርሰናል፣ ፒኤስቪ እንዲሁም ሌንስ ሲደለደሉ የጣልያኑ ሻምፒዮን ናፖሊ ፣ሪያል ማድሪድ፣ ብራጋ እና ዩኒየን በርሊን ደግሞ በምድብ ሶስት የተደለደሉ ክለቦች ናቸው።በምድብ አራት፣ቤኔፊካ፣ የአምናው የቻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ተፋላሚ ኢንተር ሚላን፣ ሳልዝበርግ እና ሪያል ሶሴዳድ ሲደለደሉ፣ ፊኖርዶ፣ አትሌቲኮ ማድሪድ፣ ላዚዮ እና ሴልቲክ በምድብ አምስት ላይ ተቀምጠዋል።የአምናው ቻምፒዮንስ ሊግ ውልንጫ አሸናፊው ማንችስተር ሲቲ፣ ሌፕዚግ፣ ክሬቭና ዝቬዝዳ እና ያንግ ቦይስ በምድብ ሰባት ተደልድለዋል።በመጨረሻው ምድብ ስምንት ደግሞ ባርሴሎና ፣ፖርቶ፣ ሻካታር ዶኔስክ እና ሮያል አንትዌርፕ መደልደላቸውን የውድድሩ ባለቤት የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ በድረገጹ አስታውቋል።የ2023/24 ዓመት የቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር መስከረም 8 ቀን 2016 ዓ. ም የሚጀመር ሲሆን የፍጻሜው ጨዋታ በእንግሊዝ ለንደን ዊምብሌይ ስታዲያም ይካሄዳል ተብሏል።

 #ከጣራ  #ላይ  #በሚወድቅ  #አካል  #ላለመመታት  #ሲሉ  #ሄልሜት  #ለማድረግ  #የተገደዱት  #የመንግስት  #ሰራተኞችበህንዷ ቴላንጋና ግዛት ያለ አንድ መንግስታዊ የልማት ድርጅት ህን...
01/09/2023

#ከጣራ #ላይ #በሚወድቅ #አካል #ላለመመታት #ሲሉ #ሄልሜት #ለማድረግ #የተገደዱት #የመንግስት #ሰራተኞች

በህንዷ ቴላንጋና ግዛት ያለ አንድ መንግስታዊ የልማት ድርጅት ህንጻ ውሃ ማስገባቱን ተከትሎ ጣሪያው ተሰነጣጥቆ በስራ ላይ ባሉ ሰራተኞች ላይ እየወደቀ እንደሆነ ተገልጿል፡፡የድርጅቱ ሰራተኛ የሆነ አንድ ግለሰብ በቅርቡ ከጣሪያ ላይ በወደቀ አካል ጭንቅላቱን ተመትቶ ሆስፒታል ገብቷል ተብሏል፡፡ይህን ተከትሎ ቀሪዎቹ ሰራተኞች የሞተር ሳይክል አደጋ መከላከያ ሄልሜት አድርገው ስራቸውን ለመቀጠል ተገደዋል፡፡ሰራተኞቹ ለመንግስታቸው በተደጋጋሚ ህንጻው እያረጀ እና ውሃ እየገባበት በመሆኑ እንዲጠገን ቢያመለክቱም ሰሚ አልተገኘም ተብሏል፡፡ስራቸውን ላለማጣት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው የሚጠበቅባቸውን ለመስራት የተገደዱት እነዚህ ሰራተኞች የአደጋ መከላከያ ወይም ሄልሜት አድርገው ስራቸውን ሲቀጥሉ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ለቀዋል፡፡ሰራተኞቹ ላለፉት 12 ወራት በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ስራቸውን ሲሰሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡ይህ ተንቀሳቃሽ ምስልም በበማህበራዊ ትስስር ገጾች በተጋራ በጥቂት ጊዜ ውስጥ የበርካቶችን ትኩረት መሳቡ ሲገለጽ የሀገሪቱ መንግስትም ትችቶችን ማስተናገዱ ተገልጿል፡፡ከህዝብ ቁጣ እና ትችት የበረታበት መንግስትም ሰራተኞቹን ወደ ሌላ ደህንነቱ ወደ ተጠበቀ ህንጻ እንደሚያዛውር አስታውቋል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡

 #ሩሲያ  #ከሚቀጥለው  #ሳምንት  #ጀምሮ  #በትምህርት  #ቤቶቿ  #አማርኛን  #ማስተማር  #እንደምትጀምር  #ገለጸችሩሲያ ባሳለፍነው ግንቦት ወር ላይ ከመስከረም ወር ጀምሮ አማርኛ እና ...
01/09/2023

#ሩሲያ #ከሚቀጥለው #ሳምንት #ጀምሮ #በትምህርት #ቤቶቿ #አማርኛን #ማስተማር #እንደምትጀምር #ገለጸች

ሩሲያ ባሳለፍነው ግንቦት ወር ላይ ከመስከረም ወር ጀምሮ አማርኛ እና ስህዋህሊ ቋንቋዎችን በሞስኮ በሚገኙ በአራት ትምህርተ ቤቶች ማስተማር እንደምትጀምር ገልጻ ነበር።በዚህም መሰረት ከመጪው ሰኞ ጀምሮ መስከረም በሞስኮ የሚገኙ ትምህ ቤቶች የአፍሪካ ቋንቋዎችን ማስተማር ይጀመራል ሲል የሞስኮ ትምህርት እና ሳይንስ ክፍል አስታውቋል ሲል ስፑትኒክ ዘግቧል።እንደ ዘገባው ከሆነ 1517 የተሰኘው የፔዳጎጂ ትምህርት ቤት ስዋህሊ ቋንቋን ሁለተኛው የውጭ ቋንቋ አድርጎ ያስተምራል ተብሏል።እንዲሁም 1522 የተሰኘው ትምህርት ቤት ደግሞ አማርኛ ቋንቋን እንደሚያስተምር ተገልጿል።ሩሲያ የአፍሪካ እና ሞስኮን ወዳጅነት ለማጠናከር በሳምንት አንድ ወይም ሁለት የትምህርት ክፍለ ጊዜዎች ለአፍሪካ ቋንቋዎች ማስተማሪያ እንዲውሉ ይደረጋል ብላለች።ሩሲያ በቀጣይም በምዕራብ አፍሪካ ሰፊ ተናጋሪ ያለው ዩርባ ቋንቋን ማስተማር እንደምትጀምር ገልጻለች።በመቀጥልም ሶማልኛ እና የዙሉ ቋንቋዎችን በሩሲያ ትምህርት ቤቶች ለማስተማር የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ እንደሆነም ከዚህ በፊት ተናግራለች።ሌላኛዋ የሩቅ ምስራቋ ሀገር ቻይና አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ድግሪ ደረጃ ማስተማር እንደምትጀምር መግለጿ ይታወሳል።አማርኛ ቋንቋ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) ከሚሰጡ 101 የውጭ ቋንቋ ትምህርቶች አንዱ ሆኖ ይሰጣልም ተብሏል።ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ባሳለፍነው ግንቦት ወር ላይ ወደ ቤጂንግ ለጉብኝት ባቀኑበት ወቅት ለቻይናውያን ተማሪዎች የተዘጋጁ የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጽሃፍት መመረቃቸው አይዘነጋም።የማስተማሪያ መጽሀፍቱ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲ ለቻይናውያን ተማሪዎች የተዘጋጁ እንደሆኑ በወቅቱ ተገልጾም ነበር።

 #በኡጋንዳ  #ግብረሰዶም  #ፈጽሟል  #የተባለው  #ወጣት  #የሞት  #ቅጣት  #እንደሚጠብቀው  #ተነገረየ20 አመቱ ወጣት በተከሰሰበት የግብረሰዶም መፈጸም ወንጀል ከሁለት ሳምንት በፊት ፍ...
31/08/2023

#በኡጋንዳ #ግብረሰዶም #ፈጽሟል #የተባለው #ወጣት #የሞት #ቅጣት #እንደሚጠብቀው #ተነገረ

የ20 አመቱ ወጣት በተከሰሰበት የግብረሰዶም መፈጸም ወንጀል ከሁለት ሳምንት በፊት ፍርድ ቤት መቅረቡ ተነግሯል።በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል ሶሮቲ በተባለች ከተማ በሚገኝ ፍርድ ቤት የቀረበው ተከሳሽ በእስር ላይ የሚገኝ ሲሆን፥ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ጉዳዩን እስኪመለከት እየጠባበቀ ነው ተብሏል።ኡጋንዳ ከፈረንጆቹ 2005 ወዲህ የሞት ቅጣትን ተፈጻሚ አላደረገችም፤ ይሁን እንጂ የሞት ቅጣት ውሳኔ ማሳለፍን አልከለከለችም።ካምፓላ በግንቦት ወር ያወጣቸውና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን የሚከለክለው ጠበቅ ያለ የጸረ ግብረሰዶም ህግ የሞት ቅጣትን የሚያስከትሉ ወንጀሎችን ዘርዝሯል።አዲሱ ህግ በማንኛውም የግብረሰዶማዊነት ተግባር የተሳተፈ አካል በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ያዛል።ወንጀሉ የተፈጭጸመው በህጻናት እና በአቅመ ደካሞች ላይ ከሆነ ደግሞ በሞት እንደሚያስቀጣ ነው የሚያስቀምጠው።በዚህም ምክንያት የአለም ባንክ በቅርቡ ለኡጋንዳ ብድር መከልከሉ ይታወሳል።ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒም “የዓለም ባንክ ባህላችንን እና ሀይማኖታችንን በገንዘብ እንድንቀይር እያስገደደን ነው" በማለት የባንኩን ውሳኔ መቃወማቸው አይዘነጋም።ኡጋንዳ ያለ ዓለም ባንክ ብድር ማደግ እንደምትችልም ነው ሲናገሩ የተደመጡት።

 #በአፍሪካ  #ወታደራዊ  #መንግስት  #ግልበጣዎች  #ለምን  #ተበራከቱ?ስራ አጥነት፣ ሙስና፣ ማህበራዊ ቀውሶችና የውጭ ሀገራት ተጽዕኖ ለመፈንቅለ መንግስት ሰፊ አበርክቶ አላቸው ተብሏል፡፡...
31/08/2023

#በአፍሪካ #ወታደራዊ #መንግስት #ግልበጣዎች #ለምን #ተበራከቱ?

ስራ አጥነት፣ ሙስና፣ ማህበራዊ ቀውሶችና የውጭ ሀገራት ተጽዕኖ ለመፈንቅለ መንግስት ሰፊ አበርክቶ አላቸው ተብሏል፡፡የኒጀር መንግስት በተገለበጠ በአምስተኛ ሳምንቱ የጋቦን መንግስትን በጦሩ መሪዎች ተመሳሳይ እጣ ደርሶታል።የጋቦን ፕሬዝዳንት አሊ ቦንጎ በመኖሪያቸው እንደታፈኑ ተናግረዋል።ባለፈው እሁድ የተደረገውን ምርጫ እንዳሸነፉ የተነገረላቸው ፕሬዝዳንት ቦንጎ የድሉ ዜና በብሄራዊ ቴሌቭዥን በተነገረ በደቂቃዎች ልዩነት የሀገሪቱ ወታደሮች ስልጣን መቆጣጠራቸውን አስታውቋል።ጋቦናዊያን በመንግስት ግልበጣው ደስታቸውን ሲገልጹ ተስተውለዋል። ገልባጩ ወታደራዊ መንግስት አሊ ቦንጎ ለምርጫው ደህንነት የዘጉትን የኢንተርኔት አገልግሎት መልሷል።ተገልባጩ አሊ ቦንጎ ኢንተርኔትን ተጠቅመው ባስተላለፉት መልዕክት ወዳጆቻቸው እንዲጮሁላቸው ጠይቀዋል።ቢቢሲ በዘገባው ፕሬዝዳንቱና ሌሎችም የአፍሪካ መሪዎች ሳይጠብቁት መፈንቅለ መንግስት ገጥሟቸዋል ብሏል።የኒጀር ግልበጣ ለምዕራብና ማዕከላዊ አፍሪካ "የግልበጣ ወረርሽኝ" መጨረሻ እንዳልሆነ አመላካች ነበር።ቡርኪናፋሶ፣ ቻድ፣ ጊኒና ማሊ የመሰሉ ሀገራት በምዕራብና ማዕከላዊ አፍሪካ ምን እየሆነ ነው? የሚለውንና የፈረንሳይ የቀድሞ ቅኝ ተገዥዎች ለምን ግልበጣው ጠናባቸው? የሚለውን መጠየቅ የግድ ብሏል።ያለፈው ሦስት ዓመት በአምስት ሀገራት ሰባት መንግስት ግልበጣን አስተናግዷል።የሀገራቱ ሁኔታና አካሄድ ወታደሩ ጣልቃ እንዲገባ ጉትጎታ እና ብዙ ጊዜ የከተማውን ህዝብ በተለይም ወጣቶችን ያበሳጩባቸው የተለመዱ ምክንያቶችን ፈጥሯል።በአብዛኛዎቹ የምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ ወጣቶች በህጋዊ መንገድ ቢመረጡም ባህላዊውን የፖለቲካ መደብ ይቃወማሉ።እንዲህ አይነቱ ብስጭት፣ ስራ አጥነት፣ ከፍተኛ ሙስናና ሌሎችም ማህበራዊ ችግሮች ተደምረው ግልበጣን ብቸኛ አማራጭ እያደረገው ነው።

 #ኢራናዊው  #ክብደት  #አንሺ  #ከእስራኤላዊ  #ተወዳዳሪ  #ጋር  #ፎቶ  #በመነሳቱ  #ዕግድ  #ተጣለበትፖላንድ በተካሄደ የዓለም ማስተርስ ሻምፒዮና ላይ ከእስራኤላዊ ክብደት የማንሳት ...
31/08/2023

#ኢራናዊው #ክብደት #አንሺ #ከእስራኤላዊ #ተወዳዳሪ #ጋር #ፎቶ #በመነሳቱ #ዕግድ #ተጣለበት

ፖላንድ በተካሄደ የዓለም ማስተርስ ሻምፒዮና ላይ ከእስራኤላዊ ክብደት የማንሳት ተወዳዳሪ ጋር እጅ ሲጨባበጥ እና ሲነጋገር ፎቶ የተነሳው ኢራናዊ ክብደት አንሺ በአገሩ ባለሥልጣናት እግድ ተጣለበት።የኢራን ክብደት የማንሳት ፌዴሬሽን በክብደት አንሺው ሙስጣፋ ራጃይ ላይ ከዚህ በኋላ በማንኛውም ውድድር እንዳይሳተፍም ነው የእድሜ ልክ እግድ ያስተላለፈበት።በውድድሩ ላይ ብር ለአገሩ ማምጣት የቻለው ሙስጠፋ ካሸነፈም በኋላ ከእስራኤላዊው የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ተወዳዳሪ ጋር መድረክ ላይ ቆሞም ታይቷል።ይህንንም ተከትሎ ፌዴሬሽኑ በአገሪቱ ውስጥ ከሚገኙ ሁሉም የስፖርት ማዘውተሪያዎች ዝር እንዳይልም ነው ክልከላ ያስተላለፈበት።ኢራናዊ አትሌቶች በማንኛውም ስፖርታዊ ውድድሮች ከእስራኤላውያን ጋር እንዳይወዳደሩም በአገሪቱ ባለሥልጣናት ተከልክለዋል።በዚህም ምክንያት የኢራን ስፖርተኞች ከውድድሮች ራሳቸውን በማግለል፣ እንደተጎዱ በማስመሰል እና ሌሎችንም ዘዴዎችንም በመጠቀም ከእስራኤላውያን ተፎካካሪዎች ጋር አይሳተፉም።የ40 ዓመቱ ሙስጠፋ ቅዳሜ ዕለት በፖላንዷ ዌሊዝካ ግዛት ከነበረው ውድድር በኋላም ከእስራኤላዊው አትሌት ማክሲም ስቪርስኪ አጠገብ በቆመበት ወቅት የአገሩን ሰንደቅ ዓላማ ለብሶ ነው።ሙስጠፋ ከዚህ ቀደም ኢራንን ወክሎ በጎሮጎሳውያኑ 2015 በታይላንድ በተካሄደ የእስያ ክብደት የማንሳት ሻምፒዮና ላይ ተሳትፏል።ክብደት አንሺው የቀድሞ የኢራን ብሔራዊ ቡድንም አባል ነው።ኢርና የተሰኘው የኢራን መንግሥት የዜና ወኪል ክብደት አንሺው “የእስላሚክ ሪፐብሊክን ቀይ መስመሮችን ተላልፏል” ሲል ዘግቧል።በዚህ ክስተት ምክንያት ፌዴሬሽኑ ከሙስጠፋ በተጨማሪም የቡድኑ መሪ ሃሚድ ሳሌሂኒያን ከሥራ አሰናብቷል።የኢራን ልዕለ መሪ አያቶላህ አሊ ኾሜይኒ ኢራናውያን አትሌቶች ሜዳሊያ ለማግኘት ሲሉ ከእስራኤላውያን ተፎካካሪዎች ጋር መጨባባጥ እንደሌለባቸው ከሁለት ዓመት በፊት አሳስበው ነበር።በዕገዳው ምክንያት አንዳንድ አትሌቶችም አገራቸውን ጥለው ለግዞት ተዳርገዋል።ከነዚህም መካከል የቼዝ ጨዋታ ተወዳዳሪው አሊሬዛ ፊሮጃ ከጥቂት ዓመታት በፊት ከእስራኤላዊ ጋር እንዳይወዳደር በሚል እግድ በመጣሉም ምክንያት አገሩን ለቆ ለስደት ተዳርጓል።

 #በርካቶች  #ራሳቸውን  #እንዲያጠፉ  #ለመርዳት  #መርዝ  #የሸጠው  #ካናዳዊ  #ክስ  #ተመሰረተበትበርካቶች ራሳቸውን እንዲያጠፉ በማማከር እንዲሁም መርዝ የሸጠው ካናዳዊ ተጨማሪ 12 ...
31/08/2023

#በርካቶች #ራሳቸውን #እንዲያጠፉ #ለመርዳት #መርዝ #የሸጠው #ካናዳዊ #ክስ #ተመሰረተበት

በርካቶች ራሳቸውን እንዲያጠፉ በማማከር እንዲሁም መርዝ የሸጠው ካናዳዊ ተጨማሪ 12 ክሶች ቀረቡበት።በቶሮንቶ ተቀማጭነቱን ያደረገው የ57 ዓመቱ ኬኔት ሎው ግለሰቦች ራሳቸውን እንዲያጠፉ በማማከር እንዲሁም በማገዝ ሁለት ክሶች የተመሰረተበት ግንቦት ወር ላይ ነበር።ግለሰቡ ገዳይ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን የያዙ 1 ሺህ 200 እሽጎችን ወደ 40 አገራት ልኳል ብሎ እንደሚያምን ፖሊስ አስታውቋል።የብሪታንያ መርማሪዎች እንዳሉት ኬኔት መርዝ የሸጠላቸው 88 የዩናይትድ ኪንግደም ዜጎች ህይወታቸው አልፏል።ኬኔት በቅርብ ጊዜ የቀረቡበት ክሶች በካናዳዋ ኦንታሪዮ ግዛት ውስጥ ራሳቸው ያጠፉ ሰዎችን አማክሯል እንዲሁም አግዟል የሚሉ ናቸው።የሟቾቹ እድሜያቸው ከ16 እስከ 36 ዓመታቸው እንደሆነም ተገልጿል።በኦንታሪዮ የሚገኙ አስራ አንድ የፖሊስ ኤጀንሲዎች በምርመራው የተሳተፉ ሲሆን የዮርክ ግዛት ፖሊስ ኢንስፔክተር ሲሞን ጄምስ “ውስብስብ” እና አሁንም ያላለቀ ምርመራ መሆኑንም አስታውቀዋል።መርማሪዎች “መረጃዎችን በአለም አቀፍ ደረጃ ላሉ ህግ አስከባሪ አካላት እያካፈሉ ነበር” ሲሉም ኢንስፔክተሩ አክለዋል“በማህበረሰባችን ውስጥ ያሉ ተጋላጭ ዜጎችን ኢላማ ያደረጉ የወንጀል ድርጊቶችን አንታገስም” ሲሉም አስረድተዋል።ኬኔት ሎው ሰዎች ህይወታቸውን እንዲያጠፉ የሚያግዙ መሳሪያዎችን እንዲሁም መርዞችን የሚያቀርቡ በርካታ ድረ ገጾችም እንደነበሩት የካናዳ መርማሪዎች ገልጸዋል።በለንደን የሚገኘው የብሔራዊ ወንጀል ኤጀንሲ (ኤንሲኤ) ከቀናት በፊት ግለሰቡ በዩናይትድ ኪንግደም ብቻ ለ272 ሰዎች መርዝ መላኩን አስታውቋል።ከእነዚህም መካከል 88ቱ መሞታቸውን የብሪታንያ ፖሊስ ቢያስታውቅም ለግለሰቦቹ ህይወት ማለፍ ብቸኛውና ቀጥተኛው መንስዔ መርዝ ስለመሆኑ ማረጋገጥ አልቻለም።“በእነዚህ ሁኔታዎች የሚወዷቸውን ሰዎች ላጡ ቤተሰቦች የሚሰማን ሃዘን ጥልቅ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን። በአሁኑ ወቅት በፖሊስ ኃይል የሰለጠኑ መኮንኖች ድጋፍ እያደረጉላቸው ይገኛሉ” ሲሉም የኤንሲኤ ምክትል ዳይሬክተር ክሬግ ተርነር አርብ ዕለት ገልጸዋል።ኤጀንሲው አክሎም “በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ተፈጽሟል ብለው በሚጠረጥሯቸው ወንጀሎች” ላይ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ገልጿል።

 #የረሃብ  #አድማ  #ላይ  #የነበሩት  #የስፔን  #እግር  #ኳስ  #ፌደሬሽን  #ፕሬዝዳንት  #እናት  #ከሆስፒታል  #ወጡየዘንድሮውን የሴቶች የአለም ዋንጫ የስፔን ድል ያደበዘዘው የ”ከ...
31/08/2023

#የረሃብ #አድማ #ላይ #የነበሩት #የስፔን #እግር #ኳስ #ፌደሬሽን #ፕሬዝዳንት #እናት #ከሆስፒታል #ወጡ

የዘንድሮውን የሴቶች የአለም ዋንጫ የስፔን ድል ያደበዘዘው የ”ከንፈር ቅሌት” አሁንም መነጋገሪያ ርዕስ ሆኖ ቀጥሏል።ጀኒ ሄርሞሶ የተባለችውን ተጫዋች ከንፈር የሳሙት የስፔን እግርኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት ልዊስ ሩቤልስ እናት ታመው ሆስፒታል መገባታቸው ትናንት የመገናኛ ብዙሃን ትኩረት ነበር።አንጅለስ ቤጃር የተሰኙት የሩቤልስ እናት ልጃቸው በስፔን ብሎም በአለማቀፍ ደረጃ የደረሰበት ውግዘት “አይገባውም” ብለው የረሃብ አድማ መጀመራቸው ይታወሳል።ሩቤልስ ባደጉበት ከተማ በሚገኘው “ዲቪና ፓስቶራ” ቤተክርስቲያን ውስጥም በር ዘግተው ሌትም ቀንም ለልጃቸው መጸለይ ጀምረው ነበር።“በልጄ ላይ የሚደርሰው ውግዘት እስካልቆመ ድረስ የረሃብ አድማዬን እቀጥላለሁ” ማለታቸውም አይዘነጋም።ትናንት ለጋዜጠኞች መግለጫ ይሰጣሉ ተብለው ሲጠበቁ ግን አንቶኒዮ የተባሉ የሃይማኖት አባት “አንጅለስ ቤጃር በዚህ የሉም፤ ታመው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል” የሚል መረጃን ለሬውተርስ ተናግረዋል።ከሶስት ቀናት የረሃብ አድማ በኋላ እናት አንጅለስ ክፉኛ መዳከማቸውን ተከትሎ ሞትሪል በተሰኘችው ከተማ ወደሚገኘው ሳንታና ሆስፒታል መወሰዳቸውንም በማከል።የ72 አመቷ አዛውንት ለስድስት ስአታት ህክምና የተደረገላቸው ሲሆን፥ ከ10 ቀናት በላይ የመላው አለም መነጋገሪያ የነበረው ልጃቸው ልዊስ ሩቤልስ ሆስፒታል ድረስ መጥቶ ወደ ቤት ወስዷቸዋል ተብሏል።ልጃቸውን ከስድብና ውግዘት በጸሎት ሃይል ለማትረፍ የረሃብ አድማ ጀምረው የነበሩት እናት ከሞት አፋፍ ተመልሰዋል፤ ሩቤልስን በፊፋ እና በስፔን ከመታገድ ባይታደጉትም ቢያንስ እናት ለልጇ ማድረግ የምትችለውን ለአለም አሳይተዋል።እንግሊዝን በማሸነፍ የሴቶች የአለም ዋንጫን ያነሳው የስፔን ብሄራዊ ቡድን ድል የ”ከንፈር ቅሌት” የሚል ስያሜ በተሰጠው የሩቤልስ እና ሄርሞሶ መሳሳም መደብዘዙ በርካታ የስፖርት ቤተሰቦችን አስቆጭቷል።የመብት ተከራካሪዎች ግን የስፔን እግርኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንቱ ድርጊት በወሲባዊ ትንኮሳ የሚያስከስስ ጭምር አድርገው እያቀረቡት ሲሆን፥ ክስ ለመመስረትም ምርመራ የጀመሩ የህግ ባለሙያዎች አሉ ተብሏል።ልዊስ ሩቤልስ ግን “ከተጫዋቿ መልካም ፈቃድ ቢኖር ነው የተሳሳምነው” በሚል የሚቀርብባቸውን ወቀሳ ሲያጣጥሉት ቆይተዋል።የአለማቀፉ የእግር ኳስ ማህበርም ፕሬዝዳንቱ በገዛ ፈቃዳቸው ከሃላፊነት እንዲለቁ ቢጠይቃቸው እምቢታን ስለመረጡ ባለፈው ቅዳሜ እንዳገዳቸው የሚታወስ ነው።

 #የአርባ  #ምንጭ  #ዩኒቨርሲቲ  #ከቆጮ  #እንደ  #ኬክ  #ያሉ  #ምግቦችን  #መሥራት  #ይቻላል  #አለየአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እንሰት ከኢትዮጵያ አልፎ በዓለም ደረጃ እንዲታወቅ ከቆ...
31/08/2023

#የአርባ #ምንጭ #ዩኒቨርሲቲ #ከቆጮ #እንደ #ኬክ #ያሉ #ምግቦችን #መሥራት #ይቻላል #አለ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እንሰት ከኢትዮጵያ አልፎ በዓለም ደረጃ እንዲታወቅ ከቆጮ እንደ ኬክ ያሉ ምግቦች መሥራት ይቻላል አለ።በዩኒቨርሲቲው መምህር እና ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት አዲሱ ፍቃዱ (ዶ/ር) ከቆጮ እንደ ኬክ እና ኩኪስ የመሳሰሉ ምግቦችን በማዘጋጀት አጠቃቀሙን እና የሚቀርብበትን መንገድ ማሻሻል እንደሚቻል ለቢቢሲ ተናግረዋል።የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከቆጮ አዘገጃጀት ጋር በተያያዘ ያስተዋወቃቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለአገር ገቢ ከማስገኘቱ በተጨማሪ ቆጮ ለማምረት ሴቶች ያወጡት የነበረውን ጉልበት መቀነሱንም ተጠቃሚዎች ይገልጻሉ።“ሁለት ሆነን አንድ እንሰት ፍቀን ለመጨረስ እስከ አራት ቀን ይወስድብን ነበር። አሁን ግን 30 ደቂቃ ብቻ ይበቃናል” ይላሉ የጋሞ ዞን ጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት እና የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ውጤትን መጠቀም የጀመሩት ገበያነሽ አለታ።ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ወቅት እንሰት የሚፍቅ፣ ቆጮው በፍጥነት እንዲብላላ የሚያደርግ እንዲሁም ቆጮ የሚፈጭን ጨምሮ አዳዲስ ፈጠራ አስተዋውቆ የአካባቢውን ማኅብረሰብ ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል።የዩኒቨርሲቲው እንሰት ፕሮጄክት አስተባባሪ የሆኑት አዲሱ ፍቃዱ (ዶ/ር) ባለፉት 10 ዓመታት እነዚህን የቴክኖሎጂ ውጤቶች እውነት ለማድረግ ጥናት እና ምርምር ሲደረግ መቆየቱን ይገልጻሉ።“እንሰት ላይ የተሰሩት አብዛኞቹ ሥራዎች ጥናትን መሠረት ያደረጉ ናቸው። እንሰት የሚያመርቱ አርሶ አደሮች የመሚያጋጥማቸውን ችግር በጥናት በመለየት ነው የሠራነው” ይላሉ።እንሰት ኢትዮጵያ ያልተጠቀመችበት ሃብት ነው የሚሉት አዲሱ (ዶ/ር)፤ “በአንድ አርሶ አደር ግቢ ውስጥ ከ50 እስከ 100 የእንሰት ዛፍ ዝም ብሎ ነው የሚቀመጠው። ከቤት አልፎም ሌላ ጥቅም ላይ ሲውል አልታየም” ይላሉ።የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቆጮ ማምረት ሂደትን ቀላል ከሚያደርጉ የቴክኖሎጂ አበርክቶዎቹ መካከል አንዱ ቆጮ የሚፍቀው ማሽን ነው።“ቆጮን በባሕላዊ መንገድ መፋቅ ጉልበት እና ጊዜ ይፈጃል። ቆጮ ለመፋቅ ጥቅም ላይ የሚውለው መሳሪያም በጣም ኋላ ቀር ነው። አጥንት ወይም እንጨት ነው ለመፋቅ የሚጠቀሙት” ይላሉ አዲሱ (ዶ/ር)።ሌላኛው ዩኒቨርሲቲው ያስተዋወቀው ማሽን ደግሞ ቆጮ በፍጥነት እንዲብላላ የሚያደርግ ዘዴ ነው።“ቆጮ እስኪብላላ ድረስ ሁለት ወር እና ከዚያ በላይ ሊወስድ ይችላል። ይህ ማለት ግቢ ውስጥ ያለን እንሰት አንድ አርሶ አደር መብላት ቢፈልግ ሁለት ወር እና ከዚያ በላይ መጠበቅ ግድ ይላል። ይህን ለማስቀረት አዲስ እርሾ በላብራቶሪ ውስጥ አምርተናል” ይላሉ አዲሱ (ዶ/ር)።ይህ እርሾ ቆጮ ከ7 አስከ 10 ባሉ ቀናት ውስጥ እንዲብላላ በማድረግ ለአገለግሎት እንዲበቃ ያደርጋል።ቆጮ በባሕላዊ መንገድ እንዲብላላ የሚደረገው መሬት ውስጥ በመቅበር ሲሆን፣ ይህ ረዥም ጊዜ ከመውሰዱ በተጨማሪ ምርቱ ለብልሽት እና ለብክነት ይጋለጣል።“ቆጮ ጉድጓድ ውስጥ ሲቀበር ጎርፍ ይገባበታል። ይህ እንዳይሆን ዘመናዊ ቆጮ ማስቀመጫ እና ማብላያ መሳሪያ አዘጋጅተን ለአርሶ አደሮች ለማስተዋወቅ እና ለማከፋፈል እየሠራን እንገኛለን” በማለት በዩኒቨርሲቲው መምህር እና ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት አዲሱ ፍቃዱ (ዶ/ር) ለቢቢሲ ተናግረዋል።“ቆጮ ፍቀን ስንቀብረው ትል ይገባበታል፣ ንጽሕናም አይኖረውም። በጣም አስቸጋሪ ነው” የሚሉት ገበያነሽ፤ ዩኒቨርሲቲው የሠራው ማሽን የቆጮውን ንጽሕና በከፍተኛ ሁኔታ የሚያስጠብቅ ነው ይላሉ።ዩኒቨርሲቲው ሌላ ያስተዋወቀው የቴክኖሎጂ ውጤት የእንሰት ስር የሚፈጭ ማሽን ነው።ቆጮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በስፋት ለምግብነት የሚውል ተክል ቢሆን በአብዛኛው በቂጣ እና በገንፎ መልክ እንጂ በተለያየ ዓይነት ማዘጋጀት የተለመደ አይደለም።አዲሱ (ዶ/ር) በተለያየ መንገድ ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል ዱቄት ከቆጮ ማምረት እንደሚቻል ይናገራሉ፤ “ከእንሰት ድፎ ዳቦ መጋገር ይቻላል፣ እንዲሁም ኬክ እና ኩኪስ ማዘጋጀትም ይቻላል” ብለዋል።አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አርሶ አደሮች እነዚህን የቴክኖሎጂ ውጤቶች እንዲጠቀሙ የተለያዩ ማዕከላትን አደራጅቶ በሥራ ላይ እንደሚገኝ ተመራማሪው ይገልጻሉ።ዩኒቨርሲቲው ባቋቋማቸው ሦስት ማዕከላት ከ3ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ እየሆነ እንደሆኑ ተናግረዋል።ዩኒቨርሲቲው ያስተዋወቃቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች ተጠቃሚ የሆኑት ገበያነሽ አለታ፣ እንሰትን በባህላዊ መንገድ ስንፍቅ “እጃችን እስኪዝል ነበር የምንሰራው። ጉዳትም አለው። በጣም በጣም አድካሚ ነበር” ይላሉ።

 #በካናዳ  #አምስት  #ሚሊዮን  #ንቦች  #ከመኪና  #ወደቁበካናዳ በጭነት መኪና ሲጓዙ የነበሩ አምስት ሚሊዮን ንቦች ከመኪናው መውደቃቸውን ተከትሎ የአገሪቱ ንብ አናቢዎች ንቦቹን በመሰብሰ...
31/08/2023

#በካናዳ #አምስት #ሚሊዮን #ንቦች #ከመኪና #ወደቁ

በካናዳ በጭነት መኪና ሲጓዙ የነበሩ አምስት ሚሊዮን ንቦች ከመኪናው መውደቃቸውን ተከትሎ የአገሪቱ ንብ አናቢዎች ንቦቹን በመሰብሰብ እርዳታ ሰጥተዋል።ማይክል ባርበር የተባለ ንብ አናቢ ከፖሊሶች ተደውሎለት ነበር ቦታው ላይ የደረሰው።አምስት ሚሊዮኑ ንቦች ቀፎ ውስጥ ሆነው እየተጓዙ ሳለ ቀፎው የታሰረበት ገመድ በመላላቱ ነበር ከጭነት መኪናው ተንከባለው የወደቁት።ንብ አናቢው እንደሚለው አካባቢው በንቦች ለመወረር ጊዜ አልወሰደበትም።“በጣም ብዙ ንቦች ነበሩ። ከቀፎው ስለወጡ ግራ ተጋብተውና ተቆጥተውም ነበር” ብሏል።በአካባቢው የነበሩ አሽከርካሪዎች መስኮታቸውን እንዲዘጉ እግረኞችም ከአካባቢው ዘወር እንዲሉ ተነግሯቸዋል።በካናዳዋ ኦንታሪዮ በምትገኘው ቡርሊንግተን የተፈጠረው የንቦች ግርታ በ11 ዓመታት የንብ አናቢነት ሕይወቱ አይቶት የማያውቅ መሆኑን ማይክል ገልጿል።“ከዚህ በኋላ እንዲህ ዓይነት ነገር እንዲገጥመኝ አልመኝምም” ብሏል። ‘ትራይ ሲቲ’ የተባለ የንብ ማቆያ ያለው ማይክል ከፖሊስ ተደውሎለት ነበር ስለክስተቱ የተነገረው።ለሌሎች ንብ አናቢዎች ደውሎም በቦታው ተገኝተዋል።ፖሊስ ለንብ አናቢዎች ከመደወሉም በተጨማሪ በማኅበራዊ ሚዲያም የእርዳታ ጥሪ አድርጓል።ማይክል እንደሚለው ንቦቹ በ400 ሜትር ርቀት ተበትነው ነበር። በአካባቢው ባሉ መኪኖችና ሌሎችም መጠለል የቻሉባቸው ቦታዎች አርፈዋል።“በሺዎች የሚቆጠሩ ንቦች መኪናዬ ላይ ብቻ አርፈው ነበር” ይላል ንብ አናቢው።ከሰዓታት በኋላ ንቦቹን በቀፎ ማስገባት ተችሏል። ቀፎ ውስጥ ከመግባታቸው በፊት በመቶዎች የሚቆጠሩ ንቦች ሞተዋል።በሂደቱ በንብ የተነደፉ ንብ አናቢዎችም ነበሩ። የጭነት መኪናው አሽከርካሪ ከ100 ጊዜ በላይ ተነድፏል።በቦታው ሐኪሞች ስለነበሩ እርዳታ ሰጥተዋል።ንብ አናቢዎች ተረባርበው ንቦቹን ቀፎ ውስጥ በማስገባታቸው ሰዎችን ከአደጋ ማዳን እንደቻሉም ተገልጿል።

 #ማይክ  #ሀመር  #ግጭቱ  #በድርደር  #ስለሚፈታበት  #ሁኔታ  #ለመመካከር  #ወደ  #ኢትዮጵያ  #እንደሚመጡ  #ተገለጸየአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልክተኛ ከፈረንጆቹ ነሐሴ 28 እስ...
31/08/2023

#ማይክ #ሀመር #ግጭቱ #በድርደር #ስለሚፈታበት #ሁኔታ #ለመመካከር #ወደ #ኢትዮጵያ #እንደሚመጡ #ተገለጸ

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልክተኛ ከፈረንጆቹ ነሐሴ 28 እስከ መስከረም 8 ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ ናይሮቢ እና አዲስ አበባ በመምጣት ከኬንያ እና ኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር እንደሚመክሩ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።ማይክ ሀመር በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች "እየተካሄደ ያለው ግጭት" በድርድር መፍትሄ በሚያገኝበት ሁኔታ እንደሚመክሩ ሚኒስቴር ገልጿል።ሚኒስቴሩ እንዳለው ማይክ ሀመር የሚመጡት በግጭቱ ሰላማዊ ሰዎች የጥቃቱ ሰለባ እንዳይሆኑም ለማሳሰብ ጭምርም ነው ብሏል።የፌደራል መንግስት በአማራ ክልል ተፈጻሚ የሚሆን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጆ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የመከላከያ ሰራዊት አሰማርቷል።በክልሉ በትጥቅ የታገዘ እንቅስቃሴ መኖሩን እና ይህንንም በመደበኛው ስርአት መቆጣጠር እንደማይቻል በመግለጽ ነበር መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጀው።መንግስት በወሰደው "የህግ ማስከበር" እርምጃ በርካታ የክልሉ ከተሞችን ከታጣቂዎች ስጋት ነጻ ማድረጉን እና የጸጥታው ችግር መቀልበሱን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዕዝ መምሪያ መግለጹ ይታወሳል።ምንምእንኳን ትላልቅ ከተሞች ወደ ሰላም መሆናቸውን ቢገልጽም በአንዳንድ ከተሞች ግጭት ማገርሸቱን የሚያሳዩ መረጃዎች እየወጡ ናቸው።በክልሉ ከትላልቅ ከተሞች ራቅ ባሉ አካባቢዎች በመከላከያ ሰራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያዎች መኖራቸው እየተነገረ ነው።በግጭቱ ንጹሃን ሰዎች የሞት እና የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን(ኢሰመኮ) በክልሉ እየተካሄደ ባለው ግጭት በርካታ ንጹሃን መገደላቸውን መግለጹ ይታወሳል።ግጭቱ እንዲቆም እና ችግሩ በንግግር እንዲፈታም ኢሰመኮ አሳስቦ ነበር።

 #ኒውደልሂ  #የቡድን  #ሃያ  #ጉባኤ  #በዝንጀሮዎች  #እንዳይረበሽ  #እየተዘጋጀች  #ነውየህንድ ዋና ከተማ ኒው ደልሂ ከ10 ቀናት በኋላ የቡድን 20 አባል ሀገራት ስብሰባን ታስተናግዳ...
31/08/2023

#ኒውደልሂ #የቡድን #ሃያ #ጉባኤ #በዝንጀሮዎች #እንዳይረበሽ #እየተዘጋጀች #ነው

የህንድ ዋና ከተማ ኒው ደልሂ ከ10 ቀናት በኋላ የቡድን 20 አባል ሀገራት ስብሰባን ታስተናግዳለች።ከተማዋ እንግዶቿን ለመቀበል እያደረገችው ባለው ሽር ጉድ ውስጥ ለአንድ ጉዳይ የተለየ ትኩረት ሰጥታለች፤ ዝንጀሮዎችን ከመሰብሰቢያ አዳራሽ የማራቅ ዘመቻ።በከተማዋ የተለያዩ አቅጣጫዎች አስፈሪ የዝንጀሮ ምስሎች እና ቅርጾችን እያስቀመጠች ሲሆን፥ የእንሰሳት ድምጽን የሚያስመስሉ የሰለጠኑ ሰዎችንም ለማሰማራት አቅዳለች ተብሏል።በኒው ደልሂ ከ20 ሺህ በላይ ዝንጀሮዎች እንዳሉና በየአመቱ በአማካይ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች በዝንጀሮዎች እንደሚነከሱ የታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ዘገባ ያሳያል። “ላንገርስ” የሚሰኙት ጥቁር ፊትና ለረጅም ጭራ ያላቸው ዝንጀሮዎች ባህሪያቸው ቁጡ እና ሃይለኛ ናቸው።በባለሙያዎች ቁጥጥር ካልተደረገባቸውም ጉዳት እንደሚያደርሱ የህንድ የዱር እንሰሳት ጥበቃ ተቋም ይገልጻል።እናም ኒው ደልሂ ከፈረንጆቹ መስከረም 8 እስከ 9 2023 የምታስተናግደው የቡድን 20 አባል ሀገራት ስብሰባ በዝንጀሮዎች እንዳይታወክ ከ30 በላይ የሰለጠኑ ባለሙያዎች በየሆቴልና ስብሰባ አዳራሹ ተመድበው ይሰራሉ ተብሏል።የዝንጀሮዎቹን ድምጽ የሚያስመስሉት ባለሙያዎች ዝንጀሮዎቹ እንግዶቹን እንዳይረብሹ እንደሚያደርጉ ተገልጿል።ዝንጀሮዎቹ ምግብ ፍለጋ ወደ ስብሰባ አዳራሾች እና ሆቴሎች እንዳያንዣብቡም ከተማዋ በየስፍራው የምግብ ማቅረቢያ እያዘጋጀች ነው ተብሏል።ኒው ደልሂ በፈረንጆቹ 2014 የላንገርስ ድምጽ የሚያስመስሉና ወደ ፓርላማ እና ሌሎች ቢሮዎች እንዳይገቡ የሚያስፈራሩ 40 ባለሙያዎችን ቀጥራ ነበር።በ2010 የኮመንዌልዝ ጨዋታዎች በከተማዋ ሲደረግም አትሌቶች በእነዚህ ዝንጀሮዎች ጉዳት እንዳይደርስባቸው 38 የሰለጠኑ ባለሙያዎችን ማሰማራቷን ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል።

 #የለንደን  #ኬሚስቶች  #አርቲፊሻል  #አልኮል  #መስራታቸውን  #ገለጹዎል ስትሪት ጆርናል ዋና መቀመጫውን ለንደን ያደረገው ጋባ ኩባንያን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው አልካሬል የተሰኘ አርቲ...
31/08/2023

#የለንደን #ኬሚስቶች #አርቲፊሻል #አልኮል #መስራታቸውን #ገለጹ

ዎል ስትሪት ጆርናል ዋና መቀመጫውን ለንደን ያደረገው ጋባ ኩባንያን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው አልካሬል የተሰኘ አርቲፊሻል አልኮል ሰርተዋል፡፡ሰዎች አልኮል መጠጥ ሲወስዱ በአእምሮ ላይ በሚፈጥረው ጉዳት ምክንያት ሰዎች ቀጥ ብለው እንዳይጓዙ፣ የራስ ህመም እንዲያጋጥማቸው፣ ንግግራቸውን እና ድርጊታቸውን እንዳይቆጣጠሩ በማድረግ ይታወቃል፡፡አልካሬል የተሰኘው ሴንተቲክ ወይም አርቲፊሻል አልኮል ግን ከላይ የተጠቀሱትን እና ሌሎች ጉዳቶች በማያስከትል መልኩ መሰራቱን ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡ምርቱን እንዲጠጡ የተደረጉ በጎ ፈቃደኞች የስካር ስሜት እንደሌላቸው ነገር ግን የመዝናናት እና መፍታታት ስሜት እንደተሰማቸው እንዲሁም አስተሳሰባቸውን መቆጣጠር እና መንቀሳቀስ ላይ ምንም አይነት ችግር እንዳልገጠማቸው ተናግረዋል ተብሏል፡፡ስሜቱ ልክ አንድ ብርጭቆ ወይን እንደመጠጣት ነው የተባለ ሲሆን ምርቱ በተለይም አልኮል መጠጣት ለሚፈልጉ ነገር ግን ጉዳቱን በመፍራት ከመጠቀም ለተቆጠቡ ሰዎች ዋነኛ ምርጫ እንደሆነ ተገልጿል፡፡አልካሬል አልኮል የሚያስከትላቸውን ጉዳቶች በመቀነስ ጥቅሞቹን ግን በያዘ መልኩ በቤተ ሙከራ መሰራቱን ተመራማሪዎቹ ለዚሁ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡አዲሱ ምርት ከፈረንጆቹ 2026 ጀምሮ ለዓለም ገበያ እንደሚቀርብ የተገለጸ ሲሆን እስከዛው ተጨማሪ ማሻሻያዎች እንደሚደረጉበት ተገልጿል፡፡በርካቶች አልኮል መጠጥን መጠቀም ቢፈልጉም በጤና እና በአዕምሮ ላይ በሚያደርሰው ጉዳት ምክንያት አልኮልን የማያጠቀሙ ወይም የሚጠጡትን መጠን ይቀንሳሉ፡፡አልካሬል የተሰኘው ሴንተቲክ ምርት ግን እንደ ጉበት ህመም፣ አካልን እና ስሜትን አለመቆጣጠር ጉዳቶችን እንደማያደርስ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡

 #በጆሃንስበርግ  #በአንድ  #ሕንጻ  #ላይ  #በተቀሰቀሰ  #የእሳት  #አደጋ  #የሰባ  #ሦስት  #ሰዎች  #ሕይወት  #አለፈበደቡብ አፍሪካዊቷ መዲና ጆሃንስበርግ በሚገኝ ሕንጻ ላይ በተቀ...
31/08/2023

#በጆሃንስበርግ #በአንድ #ሕንጻ #ላይ #በተቀሰቀሰ #የእሳት #አደጋ #የሰባ #ሦስት #ሰዎች #ሕይወት #አለፈ

በደቡብ አፍሪካዊቷ መዲና ጆሃንስበርግ በሚገኝ ሕንጻ ላይ በተቀሰቀሰ የእሳት አደጋ ቢያንስ 73 ሰዎች መሞታቸውን የደቡብ አፍሪካ ባለሥልጣናት አስታወቁ።በአደጋው ከ50 በላይ ነዋሪዎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል።የከተማዋ ማዕከል ላይ በሚገኘው ባለ 5 ፎቅ ሕንጻ ላይ የተቀሰቀሰው እሳት መንስኤ እስካሁን ግልጽ እንዳልሆነም የጆሃንስበርግ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት ቃለ አቀባይ ሮበርት ሙላውድዚ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የእሳት አደጋ ሠራተኞች የተወሰኑ ነዋሪዎችን ከሕንጻው በማውጣት ሕይወታቸውን ታድገዋል።እሳቱ ሕንጻውን ማውደሙ ቢገለጽም በሕይወት ሊኖሩ የሚችሉ ተጎጂዎችን የማፈላለግ ሥራ መቀጠሉንም ቃለ አቀባዩ ተናግረዋል።ከአደጋ የተረፉ ነዋሪዎችን የሚያስፈልጓቸውን እርዳታዎችም ለመለገስም የአደጋ አስተዳደር ባለሥልጣናት በአካባቢው ተሰማርተዋል።የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ፍለጋቸውን ካጠናቀቁ በኋላም መንስኤውንና ሌሎች ጉዳዮችን ለማጣራት የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ይሰማራል ተብሏል።“በየፎቁ እና በእያንዳንዱ መኖሪያ ቤት እና ክፍል እየገባን በሕይወት ሊኖሩ የሚችሉ ሰዎችን እየፈለግን ነው” ሲሉም ሮበርት ለደቡብ አፍሪካው ሚዲያ ኢኤንሲኤ ተናግረዋል።ሮበርት ቀድሞ ትዊተር በመባል ይታወቅ በነበረው ኤክስ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ ላይ ባጋሩት ቪዲዮ የእሳት አደጋ ማጥፊያ መኪኖች፣ አምቡላንሶች መስኮቶቹ ተለብልቦ ከሚታየው ሕንጻ ውጭ ቆመውም አሳይቷል።በተጨማሪም የተቃጠለው ሕንጻ አካባቢ የተሸፈኑ አስከሬኖችም የሚታዩበት ፎቶዎችም ወጥተዋል።አንዲት እናት በሕንጻው ላይ ነዋሪ የሆነችውን የ24 ዓመት ልጃቸውን እየፈለጉ እንደሆነ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።“ሕንጻው መቃጠሉን ስሰማ ልጄን ለመፈለግ እየሮጥኩ ነው የመጣሁት” ብለዋል።“እዚህ ከደረስኩ በኋላ ግን ምን እየተፈጠረ እንደሆነ አላወቅኩም። ልጄ በሕይወት ትኑር አትኑር የማውቀው ነገር የለም። ማንም ምንም እያለኝ ይደለም። በጣም ነው የተጨነቅኩትም” ሲሉም አስረድተዋል።ሕንጻው በጆሃንስበርግ ውስጥ የንግድ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኝ ሲሆን በርካቶችም ኢ-መደበኛ በሆነ መልኩ የሚሰፍሩበት ነው ተብሏል።‘የተጠለፉ ሕንጻዎች’ ከሚባሉት ውስጥ አንዱ የሆነው ይህ ሕንጻ በደቡብ አፍሪካ በሕገወጥ መንገድ የሚወሰድ እና በተለይም በአብዛኛው ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸው አፍሪካውያን የሚኖሩበትም እንደሆነ ተገልጿል።

 #በጅግጅጋ  #በደቦ  #ተደፍራ  #በአሰቃቂ  #ሁኔታ  #የተገደለችው  #የ  #አስራ  #አንድ  #ዓመት  #ታዳጊ  #አባት “ #ፍትሕን  #እሻለሁ”  #አሉበሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በደቦ...
31/08/2023

#በጅግጅጋ #በደቦ #ተደፍራ #በአሰቃቂ #ሁኔታ #የተገደለችው #የ #አስራ #አንድ #ዓመት #ታዳጊ #አባት “ #ፍትሕን #እሻለሁ” #አሉ

በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በደቦ ተደፍራ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ የተገኘችው የ11 ዓመት ታዳጊ አባት “ፍትሕን እንደሚሹ” ለቢቢሲ ተናገሩ።በጅግጅጋ ከተማ ወረዳ 13 ተብሎ በሚጠራው ቦታ ነዋሪ የነበረችው የ11 ዓመቷ ታዳጊ ፋጡማ ኡጋስ በደቦ ከተደፈረች በኋላ በገመድ ታንቃ የተገደለችው እሁድ ነሐሴ 21/ 2015 ዓ.ም ነበር።በልጃቸው ግድያ የተሰበሩት አባት ኡጋስ አረብ ፍትሕን አጥብቀው እንደሚሹም ለቢበሲ ሶማሊ ተናግረዋል።የተናገሩት “እኔ ተጎጂ ነኝ። ፍትሕ እፈልጋለሁ። ለኔ ልጅ ብቻ ሳይሆን ከዚህ ቀደም በዚህ መንገድ ሕይወታቸው ለጠፉት ፍትሕ እንዲሰፍን እጠይቃለሁ” ሲሉም አክለዋል።ታዳጊዋ በቤቷ ጥቃት ከተፈጸመባት በኋላ በከተማዋ በሚገኘው ካራማራ አጠቃላይ ሆስፒታል ለምርመራ በተወሰደችበት ወቅት በገመድ ታንቃ ከመገደሏ በፊት መደፈሯንም አረጋግጧል።የሶማሌ ክልል ፖሊስ በፋጡሞ ኡጋስ አረብ ግድያና መደፈር የተጠረጠሩ አራት ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አረጋግጧል።የሶማሌ ክልል ፖሊስ በፌስቡክ ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫም “በጅግጅጋ በቡድን የመድፈርና ግድያ የፈጸሙ አራት ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንና ምርመራ መከፈቱንም" ነው ያተተው።ታዳጊዋ ተደፍራ የተገደለችው በመኖሪያ ቤቷ ውስጥ ሲሆን አባቷ ለቢቢሲ ሶማሊ እንደተናገሩት ጩኸት ሰምተው ከእንቅልፋቸው መንቃታቸውን ነው።“በወቅቱ መኝታ ቤቴ ውስጥ ተኝቼ ነበር። ቤት ውስጥም ከኔ ውጭ ትልልቅ ሰዎች አልነበሩም። ልጄ ጋር ሄጄ ሳየት እየተነፈሰች አልነበረም ደረቷንም በመጫን እንድትተነፍስ ለማድረግ ሞከርኩ። አንገቷንም ሳየው ገመድ ተጠምጥሞባት ታንቃለች። ገመዱን ቆርጩም ወደ ሐኪም ወሰድኳት” ሲሉም አባቷ ኡጋስ አረብ ለቢቢሲ ሶማሊ ተናግረዋል።ለሕክምና ወደ ሆስፒታል አፋፍሰው ቢወስዷትም ታዳጊዋ ሕይወቷ ማለፉ በሕክምና ባለሙያዎች ተረጋግጧል።የታዳጊዋ አባት ለቢቢሲ ሶማሊ እንደተናገሩት ልጃቸውን ደፍረው የገደሏት “ሠራተኞቻቸው” እንደሆኑ ነው።በጅግጅጋ በሚገኘው ሞባይል ጥገና ሱቃቸው ተቀጥረው የሚሠሩ “አራቱ ሠራተኞቻቸው ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለዋል። አንደኛው ሠራተኛዬ ጠፍቷል” ብለዋል።የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ታዳጊዋን በቡድን ደፍረው ግድያ ፈጽመዋል በሚል አራት ተጠርጣሪዎች በሕግ ጥላ ሥር እንደሚገኙ አስታውቋል። ኮሚሽኑ ለልጅቷ ቤተሰብም ፍትሕን እንደሚያስገኝም ነው የተናገረው።የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሜጀር ጄነራል አብዲ አሊ ሲያድ ድርጊቱን የፈጸሙ ሰዎች ሕጉ ተፈጻሚ እንደሚሆንባቸው ገልጸው ቤተሰቡም ፍትሕ እንደሚያገኝ ነው ለቢቢሲ የተናገሩት።ግድያውንም ተከትሎ በያዝነው ሳምንት ሰኞ ነሐሴ 22/ 2015 ዓ.ም. የጅግጅጋ ከተማ ከፍተኛ ቁጣ ተቀስቅሶ ነበር። ግድያውን የፈጸሙት ግለሰቦች "ከሌላ ብሔር የተውጣጡ ናቸው" መባሉንም ተከትሎም ብጥብጦች መነሳታቸውም ተነግሯል።የሟቿ ታዳጊ ቤተሰብ በሚኖርበት ሰፈር በግድያው በተቆጡ ነዋሪዎች እና በፖሊስ መካከል ግጭት መፈጠሩም ተገልጿል።ፖሊስ ቁጣቸውን እና ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ የነበሩ ነዋሪዎችን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ ተጠቅሟል ተብሏል።በጅግጅጋ ከተማ ማዕከልም ከተነሳው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ በርካታ መኪኖች ላይ ጉዳት መድረሱን የተገለጸ ሲሆን በታዳጊዋ መደፈር እና ግድያ ምክንያት በተፈጠረው ብጥብጥ እና ግጭት ሃምሳ ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም ቢቢሲ ሶማሊ ያገኘው መረጃ ያስረዳል።የፖሊስ ኮሚሽነሩ ኅብረተሰቡን ወደአለመረጋጋት ሊመራ የሚችሉ ሁኔታዎችንም እንዲያስወግድ ጠይቀዋል።በአሁኑ ወቅት በከተማዋ ውስጥ ሁኔታዎች ተረጋግተዋል የተባለ ሲሆን በታዳጊዋም ግድያ የሚደረገው ምርመራ እንደቀጠለና ሲጠናቀቅም ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል።

 #ኢትዮጵያን  #በአባልነት  #የተቀበለው  #ብሪክስ  #የአሜሪካን  #ልዕለ  #ኃያልነት  #ይገዳደር  #ይሆን?በፈጣን ዕድገት የሚገኙ የአምስት አገራት ጥምረት የሆነው ብሪክስ በቅርቡ ስድስ...
31/08/2023

#ኢትዮጵያን #በአባልነት #የተቀበለው #ብሪክስ #የአሜሪካን #ልዕለ #ኃያልነት #ይገዳደር #ይሆን?

በፈጣን ዕድገት የሚገኙ የአምስት አገራት ጥምረት የሆነው ብሪክስ በቅርቡ ስድስት አገራትን በአባልነት ለመቀበል ወስኗል።ብሪክስ በቅርቡ በደቡብ አፍሪካዋ የንግድ ከተማ ጆሃንስበርግ በነበረው 15ኛው ጉባዔው ኢትዮጵያ እና ሰሜን አፍሪካዊቷ ግብፅ ከአፍሪካ ያቀረቡት የአባልነት ጥያቄ ተቀባይነት እንዳገኘ ተገልጿል።ከሁለቱ አገራት በተጨማሪም አርጀንቲና፣ ኢራን፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና ሳዑዲ አረቢያ በመጪው የአውሮፓውያን አዲስ ዓመት በአባልነት ብሪክስን ይቀላቀላሉ።ኢትዮጵያ ብሪክስን በአባልነት ለመቀላቀል ያቀረበችውን ጥያቄ እንደ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ድል የቆጠረችው ሲሆን፣ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በማስገኘቱ ረገድ የጎላ እመርታ ያስገኛል ብላለች።“በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ተሰሚነት ከማሳደግ በላይ የተለያዩ የመሠረተ-ልማት ፕሮጀክቶቿ በቡድኑ የልማት ባንክ በኩል ፋይናንስ እንዲያገኙ በር ይከፍታል፡፡ በብሪክስ አባል አገራት መካከል የሚኖረው የንግድ፣ የባህል እና የፖለቲካ ቁርኝት የላቀ ደረጃ ላይ የሚገኝ በመሆኑ፤ ኢትዮጵያም የዚህ ስብስብ አባል መኾኗ ዲፕሎማሲያዊ ተፅዕኖዋን የበለጠ የሚያሳድግ እንደሚሆን ይጠበቃል” ብሏል የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ባወጣው መግለጫ።ብሪክስ አድማሱን ለማስፋት በማለም አዳዲስ ስድስት አገራትን በአባልነት ለመቀበል መወሰኑን የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ “ታሪካዊ” ሲሉ ጠርተውታል።የብሪክስ አባል አገራት ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ሕንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ ሲሆኑ፣ ፍትሃዊ ዓለም አቀፍ የኃይል አሰላለፍ እንዲኖር በማለም የተመሠረተ እንደሆነም ይነገራል።ጥምረቱም በምዕራቡ የበላይነት የሚመራውን ዓለም የሚገዳደር እንደሆነ ነው የሚቆጠረው።በአሁኑ ወቅት ኅብረቱ አዳዲስ አገራትን በአባልነት ለማካተት የወሰነ ሲሆን፣ ይህንንም በዋነኝነት ስትገፋ የቆየችው ቻይና ናት።ለዚህም የቻይና ምክንያት የምዕራባውያንን የበላይነት ለመመከት የሚል ነው።ለንደን በሚገኘው ‘ስኩል ኦፍ ኦሪየንታል ኤንድ አፍሪካን ስተዲስ’ (ሶዋስ) ዩኒቨርስቲ ውስጥ የቻይና ጥናት ዳይሬክተር ስቲቭ ሳንግ እንደሚያስረዱት የብሪክስ አባል አገራት ከላይ ሲታዩ ምንም እንኳን ብዙ የሚያመሳስላቸው ነገር ባይኖርም ፕሬዝዳንት ዢ ለጥምረቱ አባል አገራት ማሳየት የፈለጉት ጉዳይ ተመሳሳይ መጪ ዘመንን እንደሚሹ ነው።መምህሩ እንደሚሉት ዢ ጂንፒንግ ሁሉም አገራት የምዕራቡ ዓለም የበላይነት በተጫነበት ሁኔታ መኖር እንደማይፈልጉ አሳይተዋል። “ቻይና እያቀረበች ያለው አማራጭ ፈላጭ ቆራጭ መሪዎች በአገራቸው ደኅንነት እንዲሰማቸው እና ያለ ስጋት የሚኖሩበት የዓለም ሥርዓትን ነው” ይላሉ መምህሩ።“አሜሪካ እና አውሮፓ ኃያላን የሚያቀርቡትን የዲሞክራሲ ቅድመ ሁኔታዎች መቀበል ሳያስፈልጋቸው አማራጭ የእድገት እና ልማትን የሚቀይሱበት መንገድን ነው እየተናገሩ ያሉት” በማለትም ዳይሬክተሩ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
#አጋርነትን #መገንባት
የብሪክስ ጉባዔ አስተናጋጅ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ አዲሶቹ አባል አገራትን በተመለከተ መግለጫ ሲሰጡ በደስታ ተውጠው ነበር።“ከብሪክስ ጋር አጋርነትን ለመፍጠር የሌሎች አገራትን ፍላጎት ዋጋ የምንሰጠው ጉዳይ ነው” ሲሉም ፕሬዝዳንት ራማፎሳ ተናግረው ነበር።የብሪክስ መሥራች አገራት፣ አባል ለመሆን የሚያስፈልገው መስፈርት ላይ መስማማት ከተደረሰ በኋላ ሌሎች ተጨማሪ በርካታ አገራትን እንደሚቀበሉ ነው ራማፎሳ የተናገሩት።ሆኖም በዘንድሮው የብሪክስ ጉባኤ ምን ያህል አገራትን በአዲስ አባልነት እንቀበል? እንዲሁም ጊዜውስ መቼ ይሁን? በሚለው ላይ መከፋፈል ነበር።አምስት አዳዲስ አገራት የኅብረቱ አባል እንደሚሆኑ ወሬዎች መናፈሳቸውን ተከትሎ በጉባዔው ሁለተኛ ቀን ረቡዕ፣ ነሐሴ 17/2015 ዓ.ም ሊካሄድ የነበረ ጋዜጣዊ መግለጫ በመጨረሻው ደቂቃ ላይ ተሰርዟል።የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ በዚያኑ ዕለት ተይዞ በነበረው የመሪዎች የእራት ግብዣ ፕሮግራም ላይ አልተገኙም።የብራዚሉ መሪ ለምን እንዳልተገኙ ምክንያታቸው በትክክል ባይታወቅም፣ ነገር ግን ከምዕራባውያን አጋሮች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ማስቀጠልን የማስቀጠል ከፍተኛ ትኩረት የሰጡት መሆኑ እና አዳዲስ አገራትን የመቀበሉን ጉዳይ ላይም ጠንቃቃ ነበሩ።ረቡዕ ምሽት ላይ ጋዜጠኞች ሐሙስ ጠዋት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚኖር መልዕክት የተላከላቸው ሲሆን ሥነ ሥርዓቱ ሁለት ሰዓት ዘግይቶ ነበር የተጀመረው።እነዚህ ጉዳዮችም እስከ መጨረሻው ደቂቃ ድረስ ውይይቶች መደረጋቸውን የሚያሳዩ ምልክቶች እንደሆኑ የጠቆሙ ሲሆን፣ በአባልነት ስድስተኛ አገር መጨመሯም አስገራሚ ሆኗል።በጋዜጣዊ መግለጫው ላይም የብሪክስ አባል አገራት መሪዎች የአዳዲሶቹን አገራት መጨመር በተመለከተ የየራሳቸውን ምላሽ ሰጥተዋል።በዩክሬኑ ጦርነት የጦር ወንጀሎች ፈጽመዋል በሚል በዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ የወጣባቸው እና ደቡብ አፍሪካ ቢገኙ በቁጥጥር ስር ሊውሉ የሚችሉበት አጋጣሚም ይኖራል በሚል የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዚህ ጉባዔ ላይ በአካል አልተገኙም። የጆሃንስበርጉን ጉባዔ የታደሙትም በቪዲዮ ነው።የፑቲን ንግግር በየምዕራቡ ዓለም ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፣ ‘ኒዮ ሊበራሊዝም’ በማደግ ላይ ባሉ አገራት ላይ ባህላዊ ዕሴቶች ላይ አደጋን ጋርጧል ብለዋል። በተጨማሪም አንድ አገር ወይም ቡድን የማይጫንበት የብዝሃ ዓለም እንዳይፈጠርም ስጋትን ፈጥሯል ብለዋል።ፕሬዝዳንቱ ስለማን እንደተናገሩ ስም ባይጠቅሱም ስለ አሜሪካ መሆኑ ግልጽ ነበር።ምንም እንኳን ልዕለ ኃያሏ አሜሪካ በጉባኤው ላይ ባትሳተፍም ስሟ በተደጋጋሚ ተጠቃሽ ነበር።የዋይት ሐውስ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጃክ ሰሊቫን የብሪክስን የማስፋፊያ ዕቅዶች ለማቃለል ሞክረዋል።የብሪክስ አባል አገራት ወሳኝ እና መሠረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ባላቸው የተለያየ አመለካከት የተነሳ “ጂኦ-ፖለቲካዊ ተገዳዳሪ ቡድን ይሆናሉ ወይም አሜሪካን ይፈታተናል” የሚል እምነት እንደሌላቸው ነው አማካሪው የተናገሩት።ትክክልም ሊሆኑ ይችላሉ።ብሪክስን እንዲቀላቀሉ የተመረጡት ስድስቱ አገራት አንዳቸውም ቢሆን እንደ ፀረ- አሜሪካ እንደማይታዩ የሚናገሩት በዋሽንግተን የሚገኘው የኪዊንሲ ተቋም የግሎባል ሳውዝ አጥኚ ሳራንግ ሺዶር ናቸው።“እኔ እንደማስበው መልዕክቱ ኅብረቱ የተለያዩ አገራት ስብስብ መሆኑ ነው። አንዳቸውም ቢሆን የአሜሪካ የቅርብ አጋሮች አይደሉም። አንዳንዶቹ መደበኛ አጋሮች ናቸው። ሁለቱ ወይም ሦስቱ የአሜሪካ ተቃዋሚዎች ይሆናሉ። ነገር ግን ሰፋ ባለ መልኩ ስናየው ይህ ኅብረት ፀረ-አሜሪካ የሆኑ አገራት ስብስብ አይደለም” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
“ #አሜሪካ #ሁሉንም #ተቋማት #አታሽከረክርም”
መሠረታዊው ነገር የብሪክስ መስፋፋት የሚመጣውን ለውጥ የሚወክል ነው።“ከእንግዲህ በኋላ አሜሪካ ሁሉንም ሕጎች የምታወጣበት፣ ሁሉንም ተቋማት የምታሽከረክርበት ዓለም አይደለም። ለዚህ ምንም ዓይነት ጥያቄ አይነሳበትም። ግን የአሜሪካ ምትክ አይሆንም። ከምትክነት ይልቅ ተደጋጋፊነት ሊሆን እንደሚችል ነው የሚታየኝ” ይላሉ ሺዶር።አንዱ የአንዱን አስተያየት ያከብራል ለሚሉት የብሪክስ አባል አገራት ማንም አሸናፊ ወይም ተሸናፊ አይሮበትም። መስጠት እና መቀበል ያለበት የዲፕሎማሲ ስብስብ ብቻ ነው።በጉባዔው ላይ ያልተገኙት ፕሬዝዳንት ፑቲንም በቁጥጥር ስር አልዋሉም፣ ለቴክኖሎጂ ምስጋና ይግባው እና ሩሲያ አሁንም ተወክላለች።ቻይና ከብሪክስ መስፋፋት አንጻር ትልቅ ዕቅዷን አሳክታለች። የብራዚል የጋራ መገበያያ ገንዘብም በኅብረቱ አባላት ዘንድ በቁም ነገር ተይዟል። ሕንድ ከአሜሪካ ጋር ያላትን የወዳጅነት ሚዛንን ለመጠበቅ ስትሞክር ታይቷል። ደቡብ አፍሪካም የተሳካ ጉባዔን አስተናግዳለች።

 #ፈረንሳይ  #በትምህርት  #ቤቶች  #ውስጥ  #አባያ  #መልበስ  #አገደችፈረንሳይ በመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ በሙስሊም ሴቶች የሚለብሱት አባያን መልበስ እንደምትከለክል የሀገሪቱ የት...
28/08/2023

#ፈረንሳይ #በትምህርት #ቤቶች #ውስጥ #አባያ #መልበስ #አገደች

ፈረንሳይ በመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ በሙስሊም ሴቶች የሚለብሱት አባያን መልበስ እንደምትከለክል የሀገሪቱ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።አባያ መልበስን የሚከለክለው አዲሱ ህግ በፈረንጆቹ መስከረም 4 2023 ከሚጀምረው አዲሱ የትምህርት ዘመን አንስቶ እንደሚተገብርም ተገልጿል።ፈረንሳይ በመንግስት ትምህርት ቤቶች እና በመንግስት ህንጻዎች ውስጥ ሃይማኖታዊ ምልክቶችን መልበስም ይሁን መሳየት በጥብቅ የተከለከለ ነው።በሀገሪቱ ከፈረንጆቹ 2004 ጀምሮ በመንግስት በሚተዳደሩ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ጭንቅላትን እና ፊትን የሚሸፍኑ ሻርፖችና ስካርፎችን መከልከሏ ይታወሳል።አሁን ደግሞ አባያ የተባለውን የሴት ሙስሊሞችን ልብስ የከለከለች ሲሆን፤ በዚህ ዙሪያም የፈረንሳይ ትምህርት ሚኒስቴር ጋብሪዬል አታል አስተያየት ሰጥተዋል።የትምህርተ ሚኒስትሩ በሰጡት አስተያየት “አባያኃይምኖታዊ ምልክት ነው፤ ወደ ትምህርት ክፍል ስትገባ ተማሪዎችን በሚለብሱት ልብስ ኃማኖታቸውን መለየት የለብህም” ብለዋል።በዚህም “ከዚህ በኋላ አባያ በፈረንሳይ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ እንዳይለበስ ውሳኔ አሳልፍያለሁ” ሲሉም ተናግረዋል።በፈረንሳይ አባያን በትምህርት ቤቶች የመከልከል ውሳኔ ላይ የተደረሰው ለወራት ክርክር ከተደረገበት በኋላ እንደሆነም ተነግሯል።ፈረንሳይ በፈረንጆቹ 2024 ጭንቅላትን እና ፊትን የሚሸፍኑ ሻርፖችና ስካርፎችን፤ በ2010 ደግሞ ሙሉ ፊት የሚሸፍኑ ሂጃቦን መልበስን በይፋ መከልከሏ የሚታወስ ሲሆን፤ ይህም በሚሊየን የሚቆጠሩ ፈረሳውያን ሙስሊሞችን አስቆጥቷል።

Address

World

Telephone

+251911548520

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fitsum Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share