ቤተ ማርያም ሚዲያ Bete Mariam Media

  • Home
  • ቤተ ማርያም ሚዲያ Bete Mariam Media

ቤተ ማርያም ሚዲያ Bete Mariam Media Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ቤተ ማርያም ሚዲያ Bete Mariam Media, Media/News Company, .

05/02/2024

መድኃኔዓለም

"እርሱ ግን ስለመተላለፋችን ቆሰለ
ስለ በደላችንም ደቀቀ፤
በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን።"
ትንቢተ ኢሳይያስ 53፤5

17/01/2024

አምላከ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ህዝብህን አድህን💔💔💔💔😭😭😭

የጠረፍቱ ንጉስ አደራህ🙏🙏🙏

07/01/2024

"ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።"
ሉቃ 2፡11

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

መልካም በዓለ ልደት ይሁንላችሁ።

29/12/2023

"እርሱም፦ እነሆ፥ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ ምንም አላቈሰላቸውም፤ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል ብሎ መለሰ።" ዳን 3:25

እንኳን ለሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሠላም አደረሳችሁ! በዚህ ዕለት መልአኩ ሠልስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳነበት መታሰቢያ ነው!

22/12/2023

አንተ ኑ ሚካኤል
ኦ መላከ ልዑል
ባህራን ልጅህ ነኝ ዘወትር ጠብቀኝ 🙌♥

20/12/2023

"ጸሎቴን በፊትህ እንደ ዕጣን ተቀበልልኝ፥ እጅ መንሣቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ትሁን።" መዝ 140፡2

16/12/2023
05/12/2023

"ወሀሎ አሐዱ አሐዱ ብእሲ ዘስሙ ፒሉፓዴር ዘበትርጓሜሁ መርቆሬዎስ ብሂል ነገረ ገድሉ መዓርዒር እጹብ በግብር ለተናግሮ በቤክርስቲያን ፒሉፓዴር የተባለዉን መርቆርዮስ ተጋድሎዉን ለመናገር በቤተክርስቲያን ዘንድ እጅግ ድንቅ ነዉ፡፡"

እንኳን ለታላቁ ሰማእት ቅዱስ መርቆሬዎስ ዓመታዊ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ።

የታላቁን ሰማዕት የቅዱስ መርቆሬዎስ ረድኤት በረከቱ ይድርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፣ የሰማእቱን ገድል እኛም በህይወታችን በመድገም የጽድቅን አክሊል እንድንቀዳጅ አምላከ ቅዱስ መርቆርዮስ ይርዳን: አሜን ፡፡

04/12/2023

ለፃድቁ አባታችን ለአቡነ ተክለሃይማኖት ዓመታዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን !!!

ህዳር 24 ቀን ሃያ አምስተኛ ካህናተ ሰማይ ሆነው በሰማይ የስላሴን መንበር ያጠኑበት እለት ነው፡፡

01/12/2023

ማእበለ ጌጋይ ክቡድ ሶበ ለአስጥሞ በጽሐኒ
ሐመርየኒ ማዕዶትየኒ ሃይማኖትየኒ
ማርያም ዘእንበሌኪ አልብየ ምንትኒ

እመቤቴ ሆይ
ከባድ የበደል ማእበል ሊያሰጥመኝ በደረሰ ጊዜ
መርከቤ፣ መሻገሪያዬ፣ መተማመኛዬም አንቺ ብቻ ነሽ
ማርያም ሆይ ካንቺ በቀር ማንም የለኝም

እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ
የእመቤታችንን ጣዕሟን ፍቅሯን ያሳድርብን !

30/11/2023

እስመ ሐረያ እግዚአብሔር ለጽዮን።
ወአብደራ ከመትኩኖ ማኅደሮ።
ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም።

እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታልና
ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወዷታልና
እንዲህ ብሎ ይህች ለዘላለም ማረፊያየ ናት።

24/11/2023

በቅዱስ ሲኖዶስ ከህዳር 15-21 ለአንድ ሱባኤ ጸሎተ ምኅላ ታውጇል። ሰዓቱም ጠዋት ከ12:00 -1:00 ሰዓትና ሠርክ ከ12:00 -1:00 በመላዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ይሆናል።አምላክ ይለመነን❤🙏

21/11/2023

እንኳን ለቅድስት ሐና (እመ ማርያም) ዓመታዊ የዕረፍት በዓል አደረሳችሁ ።

♥️ህዳር 11♥️
ብጽዕት ሐና ለሰማይና ለምድር ንግስት ለድንግል ማርያም ወላጅ እናቷ ናትና:: ከዓለም ሴቶች ሁሉ የቅድስት ሐና ማሕጸን እንደ ምን ይከብር! በፍጥረት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥንተ አብሶ (የአዳም በደል) መተላለፍ የቀረው በማሕጸነ ሐና ውስጥ ነውና:: ለዚህ አንክሮ ይገባል።

ይስሐቅን የተሸከመ የሣራ ማሕጸን ቡሩክ ከተባለ የቅድስት ሐናማ እንደምን አይባል! ከፍጥረታት ሁሉ እግዚአብሔር ድንግል ማርያምን እንደ መረጠ ሁሉ ቅድስት ሐናንም ለአያትነት መርጧታል::

ከቅድስት ሐና በረከት ያድለኝ።

17/11/2023

አምላኮሙ ለክርስቲያን ተመሲሎ ሰብዐ መጽአ ሀቤየ ወይቤላ ቅዱስ ጊዮርጊስ፤
አንሰ ኢኮንኩ አምላክ አላ ገብረ አምላክ አነ

የክርስቲያን አምላካቸው ሰውን ተመስሎ መጣ ወደ እኔ
ቅዱስ ጊዮርጊስ አላት
እኔስ አምላክ አይደለሁም የአምላክ አገልጋይ ነኝ እንጂ

16/11/2023

"ልጄን ከግብጽ ጠራሁት!" ሆሴ 11

ተመየጢ ማርያም ሀገረኪ ናዝሬተ፣ በላዕሌኪ አልቦ ዘያበጽሕ ሁከተ፣ ወኢትጎንድዪ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፣ ዘየኀሥሦ ለወልድኪ ይእዜሰ ሞተ፣ በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ

ማርያም ሆይ! ወደ ሀገርሽ ወደ ናዝሬት ተመለሺ፡፡ በአንቺ ላይ ሁከት የሚያመጣ ማንም የለም፡፡ ቤት እንደሌለሽ ሁሉ በግብጽ አትቆይ፡፡ ለዮሴፍ በሕልሙ መልአክ እንደ ነገረው የሕፃኑን ነፍስ የፈለገው (ጠላት ሄሮድስ) ሞቷልና።

16/11/2023

“የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ አለ።” ማቴ 2፥20

12/11/2023

ናሁ ተፈጸመ ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር ተፈጸመ ናሁ
አስምኪ ቦቱ አስምኪ ቦቱ ንግስተ ሰማይ።

12/11/2023

‹‹ተመየጢ ማርያም ሀገረኪ ናዝሬተ፣ በላዕሌኪ አልቦ ዘያበጽሕ ሁከተ፣ ወኢትጎንድዪ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፣ ዘየኀሥሦ ለወልድኪ ይእዜሰ ሞተ፣ በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ›› እያሉ ከስደት መመለሷን ያበሥራሉ፡፡ ትርጉሙም፡- ‹‹ማርያም ሆይ! ወደ ሀገርሽ ወደ ናዝሬት ተመለሺ፡፡ በአንቺ ላይ ሁከት የሚያመጣ ማንም የለም፡፡ ቤት እንደሌለሽ ሁሉ በግብጽ አትቆይ፡፡ ለዮሴፍ በሕልሙ መልአክ እንደ ነገረው የሕፃኑን ነፍስ የፈለገው (ጠላት ሄሮድስ) ሞቷልና››።

10/11/2023

10/11/2023

ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ
ጥቅምት 30 በዚህች ቀን ለእስክንድርያ ሊቃነ ጳጳሳት አለቃ የሆነ ወንጌልን የጻፈ ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ የተወለደበት ነው።

09/11/2023

"የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ፤ የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ።" ዕምባ ፫፥፯

08/11/2023

አማኑኤል🙏

08/11/2023

"ይህ ስፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይደለም፤ ይህም የሰማይ ደጅ ነው።" ዘፍ ፴፰፥፲፯

07/11/2023

እስመ ውእቱ ክብሮሙ ለቅዱሳን መድኃኒቶሙ ለጻድቃን አሠርገዋ ለምድር በጽጌ ሮማን ስብሐተ ዋሕድ ዘምስለ ምህረት በመስቀሉ ወበቃሉ አዕበዮሙ ለአበዊነ።

እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ !

04/11/2023

እኔ ግን በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ አንተን በመፍራት ወደ ቅድስናህ መቅደስ እሰግዳለሁ፡፡ መዝ ፭÷፯

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቤተ ማርያም ሚዲያ Bete Mariam Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ቤተ ማርያም ሚዲያ Bete Mariam Media:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share