26/06/2023
♦♢19♢♦
⇨ትንቢቱ ሲፈጸም ዘመኑ ሲያበቃ
⇨ከቀናት ሳትዘገይ ሳይጎድል ደቂቃ
⇨ወደ ድንግል መተህ ደስታን አበሰርክ
⇨የዐምላክን ሰው መሆን ለአለሙ ሰበክ (2)
⇨ገብርኤል ገብርኤል መልዓከ ራማ 2x
⇨ስንጠራህ ተሎ ድረስ ድምጽህን እንስማ
ቅዱስ ገብርኤል ረዳት፣ ጠባቂያችን ነው!
ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳን ሰማዕታትን ገድላቸውን እንዲፈጽሙ እሳቱንና ስለቱን ተሳቀው ወደኋላ እንዳይመለሱ ተጋድሏቸውን እንዲጨርሱ ይረዳቸዋል፡፡ (ዳን.፫፥፳፭) ክርስቶስ ሲሰደድም ከስደት ሲመለስም እንዲናገር የተላከ መልአክ ነው። (ማቴ.፪፥፲፱፣ሉቃ.፪፥፰)
ቅዱስ ገብርኤል የእግዚአብሔር ባለሟል ነው፤ "እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነኝ" እንዲል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ማለቱ ...
ለእግዚአብሔር የተወሰነ ፊት ኖሮት ማለትም እንደ ንጉሥ ወታደር በእግዚአብሔር ፊት ተገትሮ የሚቆም መሆኑን ለመግለጽ አይደለም፡፡ ምንጊዜም ከእግዚአብሔር የማይለይ መሆኑን እና አማላጅነቱን ለመግለጽ ነው እንጅ። (ሉቃ.፩፥፲፱)
ቅዱስ ገብርኤል ምእመናንን የሚጠብቅ ጠባቂ መልአክ ነው፤ ስለዚህም ምሥክር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እንመልከት ...
"በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለአንተ ያዛቸዋል፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል" እንዲል። (መዝ.፺፩፥፲፩)
"የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሠፍራል፤ ያድናቸውማል" (መዝ.፴፬፥፩) "በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ፡፡" (ዘጸ.፳፫፥፳)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር 🙏
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ //
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👇👇👇
🔸 t.me/GafatStudio 🔸
🔸🔹🔸 t.me/GafatStudio🔸🔹🔸
🔸 t.me/GafatStudio 🔸
🔸 🔸
✍️Group 👉 t.me/GafatAdvretisement