29/03/2023
ከነገ መጋቢት 21-2015ዓ.ም ጀምሮ ተጥሎ የነበረው የአዲስ መታወቂያ አገልግሎት እገዳ በከፊል የተነሳ መሆኑን የአዲስ ከተማ ክ//ከተማ ወሳኝ ኩነትና መረጃ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
****************************
ጉዳዩን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የጽ/ቤቱ ሃላፊ አቶ አለልኝ ተስፋ እንደ ከተማ አሰተዳደር በተለያዩ ምክንያቶች አዲስ የነዋሪነት ምዝገባ እና የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት ታግዶ የቆየ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ከነገ ጀምሮ አዲስ የነዋሪነት አገልግሎት ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ በከፊል የተነሳ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በዚህም መሰረት
1ኛ. 👉 ለሃገር መከላከያ ሰራዊት አባላት እና ቤተሰቦቻቸው (የትዳር አጋር፣ ልጆች እና የሚያስተዳድሯቸዉ)
2ኛ. 👉 ለህዝብ እንደራሴዎች፣
3ኛ. 👉 በከተማ አስተዳደሩ ወይም በፌደራል ተቋማት እያገለገሉ ላሉ የመንግስት ሰራተኞች እንዲሁም
4ኛ. 👉 አንደኛው የትዳር አጋር በከተማው ነዋሪ ሆነው ሌላኛው የትዳር አጋር በዝዉዉር በከተማው በነዋሪነት ለመመዝገብ የጋብቻ ማስረጃ በማቅረብ ጥያቄ ለሚያቀርቡ የትዳር አጋሮች፤
ከሚሰሩበት ተቋም ሰራተኛ ስለ መሆናቸዉ በአድራሻ ለሚመዘገቡበት ወረዳ ጽ/ቤታችን ማስረጃ እንዲሁም የትዳር አጋር ሆነዉ ሲገኝ የጋብቻ ማስረጃ እንዲያቀርቡ በማድረግ የቆይታ ጊዜ ሳይጠብቁ የመታወቂያ አገልግሎቱን የሚያገኙ መሆኑን አቶ አለልኝ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
ከላይ ከተገለፁት ውጭ አዲስ መታወቂያ ለማውጣት መሸኛ ይዘው ጥያቄ የሚያቀርቡ አመልካቾች አስመዝጋቢዉ ነዋሪ አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ እንዲያሟላለቸዉ በማድረግ እና የግዴታ ፎርም በማስሞላት በነዋሪነት እንዲመዘገቡና ለአገልግሎቱ የቆይታ ጊዜ ቀጠሮ የሚሰጣቸው ይሆናል ብለዋል፡፡
መጋቢት 20-2015ዓ.ም