Ethio media

Ethio media Ethiopian for ethiopian

ኢትዮጵያዊነት Ethiopiawinetኢትዮጵያዊነት Ethiopiawinet1m󰞋󰟡󰟝 #ደጀን  የወልድያ ዙሪያ ጎላ መቻሬና ደብረብርሃኖች ለመከላከያሠራዊት ድጋፍ አድርገዋል🇪🇹   መጋሌ ስመራ   የ...
24/09/2022

ኢትዮጵያዊነት Ethiopiawinet
ኢትዮጵያዊነት Ethiopiawinet
1m󰞋󰟡
󰟝
#ደጀን የወልድያ ዙሪያ ጎላ መቻሬና ደብረብርሃኖች ለመከላከያ
ሠራዊት ድጋፍ አድርገዋል🇪🇹

መጋሌ ስመራ
የራያው ባቢና...
ሚሌ ወደ ሐራ
አሃይ አሃይ መገና...

እያሉ በአካባቢው ዘዬ ድምጻቸውን እያሰሙ አውራ ጎዳናውን የሞሉት
የወልድያ ዙሪያ ጎላ መቻሬ ነዋሪዎች ናቸው።

የአካባቢው አባቶች እንደሚያስረዱት የጎላ መቻሬዎቹ ነዋሪዎች
በአውራ ጎዳናዎች ያቀረቡት ስነግጥም ቀጥታ ትርጎሙ
መጋሌ የተባለችው ላም ስትመራው የራያው ኮርማ በሬ ይመጣል፤
በሐራ በኩልም አፋር ሚሌ ይገኛል፣ ና ጀግናዬ ና እንደማለት ነው።
ይህን ማለታቸው ጀግናን በማሞገስ ለመከከላከያ ሠራዊት ድጋፍ
ለመስጠት ነው።

በዚህም ለሠራዊቱ ደጀን መሆናቸውን ምግብ በማቅረብ ብቻ ሳይሆን
ሞራል በመስጠትም ጭምር አረጋግጠዋል።

ከወልድያ ከተማ ዙሪያ ቀበሌ ጎላ መቻሬ የተሰባሰበው የማኀበረሰብ
ክፍል በበኩሉ ስንቅ አዘጋጅቶ ግንባር ለሚገኘው መከላከያ ሠራዊት
ያደረሰው በሰልፍ ታጅቦ ነው።

በወሎ አካባቢ "ሙጌራ" እየተባለ የሚጠራውን ትልቅ ድፎ ዳቦ
የተሸከሙ አርሶአደሮች ኢትዮጵያ ያከበረሽ ይክበር እያሉ ለመከላከያ
ሠራዊቱ የያዙትን ድጋፋቸውን አቅርበዋል።
ደጀኑ ሕዝብ ለአገር መከላከያ ሠራዊት የሚያደርገውን ድጋፍ
እንደቀጠለ ነው።
ከጎላ መቻሬ ነዋሪዎች በተጨማሪ የአፄ ዘርዓያዕቆብ ቅርስና የተለያዩ
የታሪክ ማህደሮችን ከሰነደችው ደብረብርሃን ከተማና በዙሪያዋ
ከሚገኙ አካባቢዎች ለአገር መከላከያ ሠራዊት ደጀንነት የሚሆን
ድጋፍ ተበርክቷል።

ከሁለት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ መደረጉን
የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጸጋዬ
በየነ ተናግረዋል።

ደረቅ ሬሽን፣ የታሸገ ውሃ፣ ቴምርና ሌሎች ድጋፎችን የያዙ የጎላ መቻሬ
አርሶአደሮችና የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ለሠራዊቱ
ደጀንነታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

በጌትነት ተስፋማርያም

Address


Telephone

+251946208235

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share