Esubalew Ayalsew

  • Home
  • Esubalew Ayalsew

Esubalew Ayalsew What I resist persist

31/03/2021

ምዕራብ ወለጋ!

በብሔራዊ ቡድናችን ውጤት ደስታችን ለግማሽ ቀን እንኳን ሳይቆይ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ጋምቤል ወረዳ ቦኔ ቀበሌ ከ130 በላይ የአማራ ተወላጆች በፅንፈኛ የኦሕዴድ/ኦነግ ታጣቂዎች በግፍ ተጨፍጭፈው ተገድለዋል!

21/03/2021

በቀወት እና አካባቢው የፀጥታ ችግር ተከሰተ ፦

በሸዋሮቢትና በቀወት ወረዳ አካባቢ ትላንት የጀመረው በከፍተኛ የጦር መሳሪያ የታጀበ የተኩስ ልውውጥ ዛሬም እንደቀጠለ ተሰምቷል።

የተኩስ ልውውጡ ከፍተኛ እንደሆነ ነው እየተገለፀ ያለው።

የታጠቁ ኃይሎች በሸዋሮቢትና በቀወት ወረዳ አካባቢ በከፍተኛ የጦር መሳሪያ በመታጀበ በማህበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ጉዳት በማድረስ ከተማው ላይ እና ህዝቡ ላይ ጥቃት እያደረሱ መሆኑን ነዋሪዎች አሳውቀዋል።

በአካባቢው በተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስ ንፁሃን እየተገደሉ እና የንብረትም እየወደመ መሆኑ ተገልጿል።

የመንግስት አካላት ሲገልፁት እንደተሰማው ከሆነ ችግሩ ለመከላከል በዞን ፣ በከተማው ፣ በወረዳው እና በአካባቢው የፀጥታ ሀይሎች እንዲሁም ወጣቶች ጥረት እየተደረገ ያለ ቢሆንም ጉዳዮ ስር የሰደደና ከአቅም በላይ በመሆኑ መቆጣጠር አልተቻለም ተብሏል።

የሚመለከተው የፌዴራል መንግስት እና የፀጥታ አካላት በአፋጣኝ ወደ ቦታው በመግባት አካባቢውን እንዲያረጋጉ እየተጠየቀ ይገኛል።

20/03/2021

በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ከአብን የተሰጠ መግለጫ፤

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) በሰሜን ሸዋ ዞን በአጣዬና አጎራባች አካባቢዎች የጥላቻ ኃይሎች በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጦርነት በሕዝባችን ላይ መክፈታቸውን አረጋግጧል። በዚህም ምክንያት የበርካታ ወገኖቻችን ሕይወት ጠፍቷል፣ አካል ጎድሏል እንዲሁም ከፍተኛ ንብረት ወድሟል።

ጥቃቱ የተከፈተውና እየተፈፀመ ያለው በመሀል የአማራ አካባቢዎች ቀደም ሲል በተደጋጋሚ ሲፈፀሙ የነበሩ ጥቃቶች ቀጣይ ክፍል ሆኖ ሲሆን በተለይ የአማራ ልዩ ኃይልና ሚኒሻ የትሕነግን አሸባሪ ኃይል ለመመከት፣ ሕዝቡን፣ ክልሉንና አገሩን ለመከላከል ወደ ክልሉ ምዕራባዊና ደቡባዊ ግዛቶች በሰፊው መንቀሳቀሱን ተከትሎ መሆኑ ብዙ ነገር ይገልጣል።

አብን ቀደም ብሎ መረጃው በደረሰው ወቅት ጉዳዩን በቅርበት በመከታተልና ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በማሳሰብ አጥፊዎቹ ጉዳት ከማድረሳቸው በፊት አፋጣኝ እርምጃ ተወስዶ የሕዝባችን ሰላምና መረጋጋት እንዲረጋገጥ ጠይቋል፤ አሁንም ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ ይገኛል።

ጥቃቱ በተከፈተበትና በሌሎች ቅርበት ባላቸው አካባቢዎች የምትገኙ ወገኖቻችን በተለይም ወጣቶች የተለያዩ የጥፋት አጀንዳ ባላቸው አካላት ሕዝቡን ለማሸበር ታስበው ከሚለቀቁ ሐሰተኛ መረጃዎች በመቆጠብ፣ ከመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመተባበርና ውስጣዊ አንድነታችሁን በማጠናከር ለሕዝባችን ደህንነት መረጋገጥ የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ አብን ያሳስባል።

የአማራ ክልል መንግስትና ገዢው "የአማራ ብልፅግና" የአመራሩን ውስጣዊ አንድነት ከመቸውም ጊዜ በላይ በማጠናከር፣ ለሰርጎ ገቦችና ሴረኞች እንዲሁም አገራችን ኢትዮጵያ እንዳትረጋጋ አበክረው የሚሰሩ የውጭ ኃይሎችና ሚዲያወች በከፈቱት የተቀነባበረ ፕሮፖጋንዳና ወከባ ሳይንበረከክ በሕዝባችን ላይ በየአቅጣጫው የተከፈተውን ዘር ተኮር ጥቃት በብቃት መመከት እንዲችልና ለዚህም ሁሉንም የአማራ ኃይሎች ከጎኑ የማሰለፍ የማስተባበር ሚናውን በቁርጠኝነት እንዲወጣ አብን ታሪካዊ ጥሪውን ያቀርባል።

በአሁኑ ጊዜ የፌደራሉ መንግስት ከበዛ ቸልተኝነት፣ ከታዳሚነት አልፎ አመራሩና መዋቅሩ ለጽንፈኛ ኃይሎቹ በምሽግነትና በድጋፍ ሰጭነት እያገለገለ መሆኑ የተረጋገጠና በራሱ በመንግስት በተደጋጋሚ የታመነ ኃቅ ሆኗል። ስለሆነም መንግስት አገርንና ሕዝብን ወደፊት አንድ እርምጃ ማሻገር ቢሳነው እንኳ ላልተቋረጠ የኋሊዬሽ እንሽርት ዳርጎ ለመቀጠል ያለውን ፍላጎት ደጋግሞ እንዲያጤነው በአፅንኦት እንጠይቃለን።

በተለያዩ አካባቢዎች በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፀሙትን ዘር ተኮር ጥቃቶች በዘላቂነት ማስቆም ካልተቻለና በአጥፊዎቹ ላይ የማያዳግም እርምጃ የማይወሰድ ከሆነ በቀጣይ ግንባር ቀደም የአገር ኅልውናን አደጋ ላይ የሚጥል ችግር መሆኑ እንደማይቀር ያለንን ስጋት ለመግልፅ እንወዳለን።

( አብን )

20/03/2021

የትግራይ የተፈናቃዮች ሁኔታ ፦

• "እስካሁን ከ700 ሺህ በላይ የትግራይ ምዕራባዊ ዞን ነዋሪዎች በኃይል ተፈናቅለዋል። የዞኑ ነዋሪዎች በአማራ ክልል ልዩ ኃይል እና አንዳንድ ሊህቃን በሚፈፅሙት ተግባር ነው እየተፈናቀሉ የሚገኙት" - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን

• "750 ሺ የትግራይ ተወላጅ ተፈናቀለ የተባለው ነጭ ውሸት ነው፤ የዚህን ያህል የትግራይ ተወላጅ ቦታው ላይ አይኖርም፥ የአማራ ተወላጆች ናቸው በብዛት የሚኖሩት፤ ወልቃይት እና ራያ አካባቢን በምዕራብ ትግራይ ስም መጥራት ተገቢና ወቅታዊ አይደለም፤ ጊዜው ያለፈበት ነው" - የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን

14/03/2021

ዋዜማ ራዲዮ- በደቡባዊ ትግራይ ኦፍላ ወረዳ አውሸራ በተባል ስፍራ በትናንትናው እለትና ዛሬ ከ80 በላይ የሚሆኑ የሕወሓት ታጣቂዎች በመከላከያ ሰራዊት እና በአማራ ክልል ልዩ ሀይል መገደላቸውን ያገኘነው መረጃ አመለከተ።

የሕወሓት ታጣቂዎች ኮረም ከተማ አካባቢ ሰፍሮ የነበረው የአማራ ክልል ልዩ ሃይልን ድንገት ለማጥቃት ሙከራ ማድረጋቸውን ተከትሎ የአማራ ክልል ልዩ ሀይል በወሰደው አጸፋ በርካታ ታጥቂዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል

የአገር መከላከያ ሰራዊት በደረሰው መረጃ መሰረት ወደ ስፍራው በመሄድ ከአማራ ክልል ልዩ ሀይል ጋር በጥምረት በወሰዱት እርምጃ ከ80 ያላነሱ የሕወሓት ታጣቂዎች ተገድለዋል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለዋዜማ ገልጸዋል ።

የተቀናጀው የመከላከያ ሰራዊት እና የአማራ ክልል ልዩ ሀይል የሕወሓት ታጣቂዎች ወደ መሸጉበት ተከታትሎ በመግባት ጥቃት መፈጸሙን ስለጉዳዩ የሚያውቁ የመንግስት መስተዳድር አካላት ነግረውናል።

ትናንት ቅዳሜ ጀምሮ እስከ እሁድ (ዛሬ) ድረስ በከባድ መሳሪያ በታገዘ ተኩስ ከአሽንጌ ሃይቅ በስተ ምዕራብ በኩል 20 ኪሎ ሜትር ገባ ብሎ በሚገኝ ተራራማ አካባቢ በዋሻ ውስጥ ተደብቀው የነበሩ የሕወሓት ታጣቂዎች መደምሰሳቸውን እና የቡድኑ አዝዦች መማረካቸውን ምንጮቻችን ተናግረዋል። በንፁሀን ዜጎች ላይ ስለደረሰ ጉዳት የተነገረ ነገር የለም።

ከተማረኩት ውስጥ ቀደም ሲል የመከላከያ ሰራዊቱን የከዱ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እንደሚገኙበትም ለማወቅ ተችሏል። አካባቢው ተራራ እና ገደላማ በመሆኑ በርካታ የሕወሓት ታጣቂዎች መሽገውበት እንደነበር ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
የፌደራል መንግስቱና የሕወሓት አማፅያን ውጊያ መጀመርን ተከትሎ በራያ ግንባር በኩል ከአላማጣ እስከ ዋጅራት ሒዋነ ድረስ ሰፍሮ የነበረው የሕወሓት ልዩ ሀይል እና ሚሊሻ አብዛሀኛው ሃይል ሸሽቶ የገባው ወደዚሁ ተራራ እና ገደላማ ስፍራ ነበር።

ከአማፂው ሕወሓት በኩል ስለጉዳዩ እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

በዚህ አካባቢ ተቆርጦ የቀረው የሕወሓት ታጥቂ ቡድን ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ በሚወስደው መንገድ ከኮረም እስከ ሒዋነ ባለው መስመር የሚተላለፍውን የትራንስፖርት አገልገሎት ሲያውኩ ቆይተዋል ይላሉ ነዋሪዎቹ ።ከመሸጉበት አውሸራ አካባቢ ወደ ዋናው መስመር በመውጣት ድንገት አጥቅቶ በመመለስ ጉዳት ሲያደርሱ ነበር።

ባሳለፍነው የካቲት 11 /2013 ዓ/ም በዚያው አቅራቢያ አዲ መስኖ ከተባለች የገጠር ከተማ ወጣ ብሎ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ስድስት የአዲግራት ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ተማሪዎች እና ሁለት የፌዴራል ፖሊሶች መገደላቸው ይታውሳል ። [ዋዜማ ራዲዮ]

10/03/2021

በወለጋ አማራዎች ላይ ዛሬም የመንግስት የፀጥታ ሀይል ግድያ ፈፅሞ አድሯል።

(አሻራ ፣መጋቢት 01/2013 ዓ•ም ባሕርዳርር)

በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ዞን ሆሮጉዱሩ አቢደንጎሮ ቱሉጋና ከተማ ትናንት ምሽት ሶስት(3)አማራዎች በኦሮሚያ ፖሊስ በጥይት ተገድለዋል።በዛሬው እለትም የቀብር ስነ-ስርዓታቸው እየተፈፀመ ነው።

ለግድያው መንስኤ የነበረውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአሻራ ሚዲያ እንደገለፁት ትናንት ማክሰኞ ከቀኑ 10:ሰዓት ጀምሮ በአንገር ጉትን ከተማ ቱሉጋና ቀበሌ የኦሮሚያ ፖሊስ እየዞረ ምሽት ከ1:00ሰዓት ጀምሮ ከቤት እንዳትወጡ የጦር መሳሪያም ይሁን ቆንጨራ ይዞ መንቀሳቀስ ክልክል ነው እያለ ሲቀሰቅስ ነበር ህዝቡም እኛን ከልክላችሁ በኦነግ ታጣቂዎች ልታስጠቁን ነው በማለት ተቃውሞውን አሰማ።

ፖሊስም በከተማው ውስጥ የግብርና መሳሪያ ይሸጥ የነበረን አብደላ የተባለ ነጋዴ ለህዝቡ ቆንጨራ ሸጠሀል በሚል አሰሩት ሲሉ በስልክ ያገኘናቸው የመረጃ ምንጮች ነግረውናል።በሁኔታው ግራ የተጋባው የከተማው ነዋሪ ለምን ይደረጋል በማለት ጥያቄ ቢያቀርብም የኦሮሚያ ፖሊስ ህዝቡን ለመበተን ተኩስ ከፈተብን ሲሉም አክለው ገልፀውልናል።

ወዲያውኑ ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ለህዝቡ ቆንጨራ ሸጠሀል ተብሎ የታሰረው አብደላ ተገደለ ሁኔታዎች ሁሉ ተቀያየሩ የተኩስ እሩምታ በህዝቡ ላይ ተከፈተ ለምን ብለው የጠየቁ የከተማው ሁለት ተጨማሪ ወጣቶች ህይወት ተቀጠፈ ።

በዛሬው እለት የሶስቱ አማራዎች የቀብር ስነስርዓት ተፈፀመ ።በመንግስት በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም ።አንገር ጉትን ከተማ ፀጥ ረጭ እንዳለች ናት።

18/12/2020

The surprising thing is still we trust them!
What a deceptive government!!!

ወልቃይት ጠገዴ ወፋርግፍ  ለነገ መሬት አቀጥቅጥ ሰላማዊ ሰልፍ እየተዘጋጀች ነው።
12/12/2020

ወልቃይት ጠገዴ ወፋርግፍ ለነገ መሬት አቀጥቅጥ ሰላማዊ ሰልፍ እየተዘጋጀች ነው።

24/11/2020

#ሰበር ዜና !!

ጠለምት እና ማይጸብሪ በአማራ ልዩ ሀይል፤ በአማራ ሚሊሻ እና በፋኖ ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ
አሻራ ሚዲያ
ህዳር 15/ 2013 ዓ ም ባህር ዳር
የጠለምት አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ መምህር ጸጋዬ ለአሻራ ሚዲያ በስልክ እንደገለጹት ዛሬ ህዳር 15 /2013 ዓ.ም በተደረገ ከፍተኛ ውጊያ ጠለምት እናመ ማይጸብሪ ላይ የህወሃት ልዩ ሀይሎችን በመደምሰስ ጠለምትንና ማይተብሪን ሙሉ በሙሉ ነጻ ማድረግ መቻሉን በስልክ ነግረውናል፡፡

ጠለምት እና ማይጸብሪ ከአሁን በፊት የህወሃት ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚደረግበት የአማራ መሬት ሲሆን የአማራ ልዩ ሀይል፤ የአማራ ሚሊሻ እና ፋኖ በጋራ ባደረጉት ከፍተኛ ተጋድሎ ጠለምትና ማይጸብሪን ሙሉ በሙሉ ነጻ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡

መምህር ጸጋዬ ጨምረውም ከጠለምት ማይጸብሪ ስንደርስ የአካባቢው ማህበረሰብ በከፍተኛ ድምቀት አቀባበል አድርጎልናል ሲሉ ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም የጠለምት አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ መምህር ጸጋዬ የአማራ ልዩ ሀይል ፤ የአማራ ሚሊሻ እና ፋኖ እየታገሉ እና መስዕዋትነት እየከፈሉ የሚገኙት ለአማራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለመላው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በመሆኑ ጠለምት እና ማይጸብሪ ከህወሃት ነጻ በመሆናቸው ከፍተኛ ደስታ የተሰማን በመሆኑ ሁላችሁም በያላችሁበት እንኳን ደስ አላችሁ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመጨረሻ ምከጠለምት እና ማይጸብሪ ምድር ላይመለስ የተሰናበተው የህወሃት ጁንታ በአማራ ልዩ ሀይል፤ በአማራ ሚሊሻ እና በፋኖ ከፍተኛ ተጋድሎ እና መስዕዋትነት በመሆኑ ዘለዓለማዊ ክብር ለአማራ ልዩ
ሀይል ፤ለአማራ ሚሊሻ እና ለፋኖ እንሰጣለን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ማርሸት ጽሀው

24/11/2020
24/11/2020

‹‹የማይካድራ ሲቪል ሰዎች ጭፍጨፋ የግፍና ጭካኔ ወንጀል ነው›› ኢሰመኮ

በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን በምትገኘው የማይካድራ ከተማ ጥቅምት 30/ 2013 በወቅቱ በስልጣን ላይ በነበረው የአካባቢው መስተዳድር የጸጥታ መዋቅርና ሳምሪ በተባለ ኢ-መደበኛ የወጣቶች ቡድን የተፈጸመው ጥቃት፤ ግድያ፣ ጉዳትና ውድመት፤ ጠቅላላ ድርጊቱና ውጤቱ ግፍና ጭካኔ የተሞላበት በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸመ የጭፍጨፋ ወንጀል (atrocious crime of massacre against civilians) መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ፡፡

Address


Telephone

+251931889274

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Esubalew Ayalsew posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Esubalew Ayalsew:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share