Silte Television - ስልጤ ቴሌቪዥን

  • Home
  • Silte Television - ስልጤ ቴሌቪዥን

Silte Television - ስልጤ ቴሌቪዥን በስልጤ ቴሌቭዥን የፌስቡክ ገፅ ወቅታዊ፣ ሃገራዊ፣ አለም አቀፈዊ ትክክለኛና ሚዛናዊ መረጀዎቸንና መሰጭ ቁምነገሮችን ያገኙበታል። Silte Television

13/06/2022
28/04/2022

የጎንደር ከተማ አሁናዊ ሁኔታና 2 መፍትሄዎች
(በድሩ ሁሴን)

• ከሰሞኑ በባሰና በከፋ ሁኔታ የተደራጀ ጥቃት ሙስሊሙ ላይ እየተፈፀመ ነው።
• የሙስሊም ቤቶች እየተለዩ በመጠቃት ላይ ናቸው።
• ቀበሌ 06 የሃጅ አህመዲን መስጅድ ተቃጥሏል።
• መስጅድ ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ መስሊሞችም እየተደበደቡ መሆኑን ከቦታው መልእክት አስተላልፈዋል።
• ጥቃቱ ወደ ደባርቅ ከተማ ተሸጋግሯል፤ አምባጊዮርጊስም ተመሳሳይ ዜና እየሰማን ነው።
• ያለው የመከላከያ ኃይል ቁጥሩ አናሳ መሆኑንና ጥቃቱን መቆጣጠር አለመቻሉን ነዋሪዎቹ እየገለፁ ነው።
• "እባካችሁ ለሚመለከተው አድርሱልን" የሚሉ የሲቃ ድምፆች ከቦታው እየተላኩ ነው።

ስለዚህም:-
አስከፊውን እልቂት ለመቀነስና ወደሌላ ቦታ እንሳይዛመት ማድረግ ይቻል ዘንድ:-

1.ከተማዋ በአስቸኴይ ጊዜ አዋጅ ስር ሆና ታጣቂ ሽብርተኞችን በቁጥጥር ስር ማዋል የሚያስችል ተጨማሪ የመከላከያ ኃይል እንዲገባ የፌደራል መንግስቱን እጠይቃለሁ።

2. የጎንደር ከተማ የክርስትና ኃይማኖት አባቶች፣ ሰባኪያንና ተፅእኖ ፈጣሪ የሃገር ሽማግሌዎች በጉዳዩ ላይ ጣልቃ በመግባት እልቂት የማስቆም ታሪካዊ ኃላፊነታችሁን ትወጡ ዘንድ በሃያሉ ፈጣሪ ስም እማፀናችኋለሁ።

በተለይም የክርስትና አባቶች የቤተክርስትያን ስፒከሮችን በመጠቀም ቢገዝቱ በአጭር ጊዜ መቆጣጠር ይቻል ይሆናል። በአጭር እርቀት የሚገኙ በርካታ ቤተክርስቲያናት በተመሳሳይ ሰዓት መልእክት ማስተላለፍ ይቻላል።

ተጨማሪ የመከላከያ ኃይልና የኃይማኖት አባቶች አቋም ሲቀናጁ ብቻ ጥቃቱ ሙሉ ለሙሉ ይቆማል።

እባካችሁ! የፌደራል መንግስቱና የክርስትና የኃይማኖት አባቶች እነኝህንና መሰል መፍትሄዎችን በፍጥነት ተግብራችሁ ህዝብን ከእልቂት ታደጉ። ሃገርንም ከአደጋ ጠብቁ።

ጌትዬ ሆይ! አንተ በእዝነት ዓይንህ ተመልከተን፤ የመጣብንን መከራ መልስልን።

መልእክቱን ያድርሱ!

27/04/2022
20/04/2022

የረመዷን ወርቃማ 10 ቀናቶች

★ T.me/ahmedin99

🔅የወራቶች ሁሉ አለቃ የሆነው ረመዷን የመጨረሻ አስር ቀናቶቹ ደግሞ የወሩ ቀናቶች ቁንጮ ናቸው፡፡በነዚህ ቀናቶች ውስጥ የምትገኘዋ ለይለቱልቀድር ደግሞ የቁንጮዎች ቁንጮ ናት፡፡

🔅አስሩን ቀኖች (ሌሊቶች) በሙሉ ለይለተል-ቀድርን በማሰብ በዒባዳ ያሳለፈ ያለምንም ጥርጥር ለይለተል-ቀድርን ያገኛል።

🔗ቡኻሪይና ሙስሊም ከእናታችን ዓኢሻ
እንደዘገቡት ነቢዩ ﷺ"የረመዷን 10 ቀኖች ሲገቡ መቀነታቸውን ያጠብቁ ነበር፣ ለሊቱንም በሙሉ በዒባዳ (በሰላት) ያሳልፉ ነበር፣ ባለቤቶቻቸውንም (ለዒባዳ) ይቀሰቅሱ ነበር" ብለዋል፡፡

🔅ጅምርና መነሻ ላይ ሁሉም እኩል ሊሆን ይችላል፡፡ ነገሮች የሚለኩት ግን በፍጻሜያቸው ነው፡፡ እስከመጨረሻው ታግሶ ስራውን አሳምሮ ያጠናቀቀ ይሸለማል፡፡ መጨረሻ ላይ የተሳነፈና ያበላሸ ግን ሽልማቱን በማጣት ወይም ከዛም በከፋ ነገር ሊቀጣ ይችላል፡፡

🔅የረመዷን የመጨረሻ 10 ቀናት ላይ ይበልጥ ኸይር ስራ ላይ ልንተጋና መጨረሻችን ያማረ እንዲሆን ጥረት ልናደርግ እንጂ ልንዘናጋና ልንሰላች በጭራሽ አይገባንም፡፡

🔗ኢብኑል-ጀውዚይ እንደሚሉት"ፈረስ እንኳ የእሽቅድድም ሜዳ ላይ የመጨረሻው ዙር ላይ ሲደርስ ኀይሉን አሟጦ ተጠቅሞ ሌሎች ፈረሶችን በመቅደም ከግቡ ላይ ቀድሞ ለመድረስ ይጥራል" ፣እነሆ ከፈረስ በላይ እንጂ በታች ልንሆን ፈፅሞ አይገባምና እኛም ወደ ጀነት በሮች በመልካም ስራ ልንሽቀዳደም ይገባናል፡፡

🔅የረመዷን የመጀመሪያ አስርቶች ላይ ከነበረን የተሻለ ንቃትና ትጋት ሊኖረን ይገባል።

🔅ሰራተኛ ስራውን ሲያጠናቅቅ የሚያገኘውን ደመወዝ በማሰብ የስራውን ድካም ተቋቁሞ የሚጠበቅበትን ሁሉ እንደሚያደርገው ሁሉ እኛም የአላህን ውዴታና ጀነትን በማሰብ ነፍሲያችንን በማሸነፍ መልካም ስራ ላይ ልንበረታ ይገባናል፡፡ ሁኔታዎች ለመልካም ስራ የማያግዙበት ወቅትና ቦታዎች ላይ ሁሉንም ተቋቁሞ ከእኛ የሚጠበቀውን ማድረግና አላህ እንደሚፈልገው ሆኖ መገኘት ደረጃው ለዲን ብሎ ወደ ነቢዩﷺ የመሰደድ ያክል ነው፡፡

💥ኢዕቲካፍ በመግባት ከዓለማዊ ጉዳዮች ርቆ፣ ከዱንያ ግርግርና ወሬዎቿ ተነጥሎ፣ ዒባዳ ታስቦ፣ የተለያዩ የአምልኮ ተግባራትን መፈፀም እዚያው ለመዋልና ለማደር ጠቅሎ መስጊድ መግባት ማለት ነው፡፡ የቻለ አሥርቱን ቀናት ኢዕቲካፍ ማድረግ ይችላል፤ ያልቻለ የተመቸዉን ቀን መርጦ ኢዕቲካፍ ማድረግ ይችላል፡፡ ኢዕቲካፍ ነፍስን ያጠራል፣ ዉስጥን ያፀዳል፡፡ አሥርቱን ቀናት ኢዕቲካፍ ማድረግ የፈለገ ሰው ረመዷን 20 ቀን (ምሽቱ 21) ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት መስጊድ ይገባና ነገ ዒድ ሲባል ከፀሐይ መጥለቅ በኋላ ይወጣል፡፡

💥"የሰው ልጅ ሆይ:- የተወለድከው ብቻህን ነው፣የምትሞተውም ብቻህን ነው፣ ቀብርም የምትገባው ለብቻህ ነው፣ ለምርመራ አላህ ፊት የምትቆመውም ለብቻህ ነው፣ጀነትም ይሁን ጀሀነም የምትገባው ለብቻህ ነው!" ታዲያ ነገ የምትድንበትን ኸይር ስራ ለብቻህ መስራት እንዴት ይከበድሃል?!?

🔅ዛሬ ዱኒያ ላይ መስፈርቱን ያሟላ መልካም ስራ ከሰራን ነገ ኣኺራ ላይ በጀነት ስናርፍ ድካሙን በሙሉ እንረሳዋለን! ከዛም አልፎ የከፈልነውን ዋጋ እንንቃለን!

💥በወርቃማ አስርቱ ቀናት፣

1/ ኢዕቲካፍ በመግባት

2/ ቁርኣን

3/ ለራሳችንም ለሌሎችም የተለያዩ ዱዓዎችን በማድረግ በተለይም (አላህ ሆይ አንተ ይቅር ባይ ነህ ይቅር ማለትንም ትወዳለህ ይቅር በለኝ) የሚለውን ዱዓ ማብዛት

4/ ዚክር በማብዛት

5/ ሰደቃ

6/ ለሊቱን ሙሉውን -እስከ ሱሑር- በሰላት ብቻ ማሳለፍ የቻለ ይህን በማድረግ ይህን ያልቻለ ደግሞ ለሊቱን ከፋፍሎ በዚክር፣በዱዓእና በኢስቲግፋር እንዲሁም የቻልነውን ያክል ረዘም ያሉ 2/2 ረክዓ ሱንና ሰላቶችን በመስገድ ልናሳልፍ ይገባናል፡፡

አላህ ያግዘን ለይለቱል-ቀድርንም ይወፍቀን "ኣሚን"
✍ ኡስታዝ አሕመድ አደም
🔹🔸🔹🔸🔹
የአህመዲን ጀበልን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ። ለሌሎችም ሼር በማድረግ ያጋሩ
T.me/ahmedin99

20/04/2022
19/04/2022
19/04/2022
19/04/2022
16/04/2022
16/04/2022
16/04/2022

የዳሎቻ ከተማ አስተዳደር ህንፃ ንድፍ


ዲዛይን የተደረገ

15/04/2022

🛑ጁምዓ እለት በተደረገ ዱዓ ጠፍቶ የነበረ ዓይኑ ተመለሰ!

📌 T.me/ahmedin99

በ281ዓ.ሂ የሞቱት ታዋቂው ኢብኑ አቢ-ድዱኒያ "ሙጃቡ'ድዱዓእ" በተሰኘው ኪታባቸው፣ እና በ571 ዓ.ሂ የሞቱት ኢብኑ ዐሳኪር "ታሪኹ-ዲመሽቕ ላይ እንደዘገቡት፣

📌 "ሰልት ኢብኑ ቢስጣም አይናቸው ታሞ እንባ እያፈሰሰ ቆይቶ ከዛም ጠፍቶ ነበር። ከእለታት አንድ ቀን ጁሙዓ ላይ ወንድሞቹ/ጓደኞቹ ከዐስር በኋላ መስጂድ ውስጥ ቁጭ ብለው ዱዓእ እያደረጉለት በዱዓቸው ላይ ደጋግመው አይኑን እያሰቡ (እየጠቀሱ) ቆዩና ልክ ጸሃይ ልትጠልቅ ጥቂት ሲቀራት "ሰልት" አስነጠሱ፣ ልክ ሲያስነጥስ ጠፍቶ የነበረው ዓይናቸው ተመለሰ! በ2ቱም ዓይኖች ማየት ጀመሩ! ከዛም ሰዎች ከመስጂድ ሲወጡ በር ላይ ተሰብስበው "ሰልትን" እንኳን ደስ አለህ ይሏቸው ነበር። "

📌 ዱዓእ የችግር ጠላቱ ነው፣ ጁሙዓ ደግሞ ልዩ የዱዓ ቀን ነው፣ ከዐስር በኋላ ያለው ሰዓት ደግሞ አብዛኞች ሰሓባዎችና ታቢዒዮች "ዱዓእ የማይመለስባት የጁሙዓ ልዩ ሰዓት/ ያለችበት ወቅት እሱ ነው" ያሉለት ጊዜ ነውና፤ ለራሳችንም፣ በየቦታው ለታመሙና ለተቸገሩ ወንድም እህቶቻችን፣ ለሀገራችን ሰላምና ደህንነት ከልባችን ዱዓእ እናድርግ!

📌"ጁሙዓ ላይ አንዲት ዱዓእ የማይመለስባት/ተቀባይነት የሚያገኝባት ሰዓት አለች" ብለው ታማኙና እውነተኛው ነቢይ ነግረውናል።ሰሀባዎች ደግሞ "ይህች ሰዓት ከዐስር እስከ መግሪብ ባለው ጊዜ ውስጥ ነው ያለችው" ብለዋል።

📌 ብዙ ችግሮች አሉብን እያልን ዱዓእ ላይ መስነፋችን በጣም ይገርማል! በርካታ ደጋግ ቀደምቶች ጁሙዓ ቀን ላይ ከዐስር እስከ መግሪብ መስጂድ በየጥጉ ሆነው በዱዓእ ነበር የሚያሳልፉት!

📌 እኛም የነሱን ፈለግ እንከተል፤ መስጂድ ውስጥ ብቻ መሆን የግድ አይደለም። በያለንበት ሁሉ ልባችንን ወደ አላህ አዙረን አላህን መማጸን እንችላለን።

📌 ዛሬ እለቱም ጁምዓ ወቅቱም ረመዳን ነውና ሳንዘናጋ ለዱዓ እንጠቀምበት!

አላህ ይቀበለን!

ኡስታዝ አሕመድ አደም

14/04/2022
24/02/2022
24/02/2022
24/02/2022

ፌስቡክ ከቲክቶክ ጋር ለመፎካካር የሚያስችለው የአጫጭር ቪዲዮ ማጋሪያ አገልግሎት ይፋ አደረገ
======================
አፊኒ 17 06 2014 ዓ.ም ሐዋሳ

በፈረንጆቹ 2022 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከተቀናቃኞቹ ቲክቶክ እና ዩትዩብ የገጠመው ፉክክር ምክንያት የተጠቃሚዎቹ መቀነስ እንዳጋጠመው ይታወሳል።

ታዲያ ፌስቡክ አዲሱን የፉክክር መድረክ ለመቀላቀል #ሪልስ የተባለ የተባለ የአጫጭር ቪዲዮ ማጋሪያ አገልግሎት ይፋ አድርጓል።

አዲሱ ሪልስ የቪዲዮ ማጋሪያ አገልግሎት በዓለም ዙሪያ በ150 ሀገራት ለሚገኙ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልቀቁንም ኩባያው አስታውቋል።

አዲሱ የሪል አገልግሎት ተጠቃሚዎች በገጻቸው ላይ እየቀረጹ በሚጭኗቸው ቪዲዮዎች ገንዘብ ማግኘት እንደሚችሉም ነው የተነገረው።

-Ain

24/02/2022
23/02/2022

አሸባሪው ለመሳሪያ ግዥ የሚያወጣው ረብጣ ዶላር

አል-ሻባብ ለጦር መሳሪያ ግዥ 24 ሚሊዮን ዶላር በ2021 ማውጣቱን አንድ ጥናት አመላከተ፡፡

በሞቃድሾ መቀመጫውን ያደረገው ሂራል የጥናት ተቋም ከአል-ቃይዳ ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚነገርለት አልሻባብ ለጦር መሳሪያ ግዥ ረብጣ ዶላር ማውጣቱን አስታውቋል ፡፡

ጽንፈኛው ቡድን 1 መቶ 80 ሚሊዮን ዶላር ዓመታዊ ገቢ እንደሚሰበስብም በሪፖርቱ ላይ ተካቷል ፡፡

ቡድኑ መሳሪያዎችን ለመግዛት የተለያዩ ስልቶችን የሚከተል ሲሆን በጥቁር ገበያ ከአካባቢው ማኅበረሰብ እንዲሁም ከጦር መሳሪያ ነጋዴዎች ይሸምታል ፡፡

የየመን ስም ከዚህ ጉዳይ ጋር አብሮ ተነስቷል፡፡

የተቋሙ መረጃ እንደሚያሳየው አል-ሻባብ በርካታ የሶማሊያ አካባቢዎችን ይዟል ፤በህዝቡም ላይ አስተዳደራዊ እና ጉልበት አዘል ጫና በመፍጠር የማሳመን ስራ ላይ ተጠምዷል፡፡

ከኤደን ባህረ ሰላጤ ጭምር የሚገባውን የጦር መሳሪያ መከላከል አደጋውን ሊቀንሰው እንደሚችልም የቢቢሲ ዘገባ ያሳያል፡፡

ቢንያም ካሴ

23/02/2022
23/02/2022

“የህወሓት ታጣቂዎች በአማራ ክልል ፈፅመዋል የተባለው ወንጀል አሳስቦኛል” - አሜሪካ

የህወሓት ታጣቂዎች በአማራ ክልል ፆታዊ ጥቃትን ጨምሮ አሰቃቂ ድርጊቶችን መፈጸማቸው መገለጹ በእጅጉ እንዳሳሰባት አሜሪካ ገለጸች።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትላንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጉዳዩን በተመለከተ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት የህወሓት ታጣቂዎች በ2013 ዓ.ም ነሐሴ ወር መጨረሻ እና በ2014 ዓ.ም መስከረም መጀመሪያ አካባቢ በአማራ ክልል አሰቃቂ ድርጊቶችን እንደፈፀሙ መግለጹን አስታውሷል።

ሁሉም ወገኖች በሰብአዊነት ላይ የሚፈፀም ጥቃት እና በሲቪሎች ላይ የሚደርሰው በደል እንዲቆም የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ጥሪ አቅርበዋል።

ግጭቱን ለማስቆም እና ለሁሉም ተበዳዮች ፍትሕን ለማረጋገጥ ጊዜው አሁን ነው ብለዋል ቃል አቀባዩ።(EBC)

23/02/2022
22/02/2022
22/02/2022

በአዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ በጫማ ውስጥ ተደብቆ ወደ ሀገር ሊገባ የነበረ 2 ኪ.ግ ወርቅ ተያዘ
**************************

በአዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ በገቢ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በኩል በጫማ ውስጥ ተደብቆ ወደ ሀገር ሊገባ የነበረ 2 ኪ.ግ ወርቅ ተያዘ።

ግምታዊ ዋጋው 6.6 ሚሊዮን ብር የሆነው ወርቅ የተያዘው በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የኢንተለጀንስ እና ኮንትሮባንድ ክትትል አባላት ነው።

የወንጀሉ ሁኔታ በመጣራት ላይ መሆኑን ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

22/02/2022

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Silte Television - ስልጤ ቴሌቪዥን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Silte Television - ስልጤ ቴሌቪዥን:

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share