Bole Wereda 15 pp media

  • Home
  • Bole Wereda 15 pp media

Bole Wereda 15 pp media ይውደዱ ሃሳብ ይስቱ

06/12/2021

በህይወት እያላችሁ ይህችን ባንዲራ ጠብቋት! ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

28/11/2020

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹የሀገር መከላከያ ሰራዊት መቐለ ከተማን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ👏🏾👏🏾👏🏾👏🏾👏🏾👏🏾👏🏾👏🏾👏🏾👏🏾👏🏾👏🏾👏🏾👏🏾👏🏾👏🏾እሷናት ክብሬ አረ እኔስ ሀገሬ🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

21/11/2020
17/11/2020
15/11/2020
ደሜን እለግሳለሁ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር እሆናለሁ በሚል መሪ ቃል የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 15 አመራሮች፣ ሰራተኞች እና ነዋሪዎች ዛሬ ህዳር 03/2013 ደም ሲለግሱ  ውለዋል!!!!!
12/11/2020

ደሜን እለግሳለሁ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር እሆናለሁ በሚል መሪ ቃል የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 15 አመራሮች፣ ሰራተኞች እና ነዋሪዎች ዛሬ ህዳር 03/2013 ደም ሲለግሱ ውለዋል!!!!!

10/11/2020
10/11/2020

የተከበራችሁ የቦሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች፣

ከሀዲው የሕወሓት ቡድን በአገራችን የመጣውን ሁሉን አቀፍ ለውጥ ለማደናቀፍ ባለፉት ሁለት ተኩል ዓመታት የትግራይ ሕዝብ ከለውጡ ትሩፋት ተቋዳሽ እንዳይሆን እንቅፋት ከመሆን አልፎ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በሚፈጠሩ ግጭቶችና ጥቃቶችም ውስጥ ተሳታፊ በመሆን በርካታ እኩይ ተግባራትን ሲፈጽም ቆይቷል፡፡

ይህ ከሀዲ ቡድን የእስከዛሬ መሠሪ ሥራው ሳይበቃው አሁን ደግሞ ከሁለት አሥርት ዓመታት በላይ የትግራይን ሕዝብ ሲጠብቅና በተለያዩ መልኮች ሲደግፍ በቆየው የመከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ከጀርባ ጥቃት በመሰንዘር ታሪክ ይቅር የማይለው የክህደት ወንጀል ፈጽሟል፡፡

ይህ አሳፋሪ ተግባር በእጅጉ የሚወገዝ ተግባር በመሆኑ መላው የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎችና አስተዳደሩ ይህንን የክህደት ተግባር በጽኑ እናወግዛለን፡፡ መንግሥት በከሃዲውና የበላበትን እጅ ነካሽ በሆነው የሕወሓት የጥፋት ኃይል ላይ እየወሰደ ያለውን ሕግን የማስከበር እርምጃ የምንደግፍና ዘመቻው ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚጠበቅብንን ማንኛውንም ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናችንን በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ በተለያዩ አካባቢዎች የሕዝባችንን ሰላም ለማወክ የሚንቀሳቀሱ የትሕነግ ተላላኪዎች በክፍለ ከተማችንም የሽብርና የማተራመስ ተግባራት ሊፈጽሙ ስለሚችሉ መላው የክፍለ ከተማችን ነዋሪ ኅብረተሰብ አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ሲመለከት ለጸጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስባለሁ፡፡ ሆቴሎች፣ ፔንሲዮኖች እና ቤት አከራዮች የተከራዮቻቸውን ማንነት በሚገባ ማወቅና አስፈላጊውን መረጃ መያዝ እንደሚኖርባቸውም ለማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡

አሁን በመንግሥት እየተወሰደ ያለው እርምጃ ሕግን የማስከበርና የዜጎችን የመኖርና የመንቀሳቀስ መብት ማረጋገጥ እንዲሁም አገራችንን ከጥፋት ኃይሎች የመታደግ ዘመቻ መሆኑን በመረዳት የትግራይ ሕዝብ ለዚህ ሕገወጥ ቡድን ምሽግ መሆን እንደሌለበት እያሳሰብኩ፣ ኅብረተሰቡ በአካባቢው የተለየ እንቅስቃሴና ጸጉረ ልውጦች ሲያጋጥመው በአቅራቢያው ለሚገኝ የጸጥታ አካል ወይም በስልክ ቁጥር 0118578509 በመደወል እንዲያሳውቅ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡
መኮንን አምባዬ
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ

08/11/2020

ከጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.መ ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተሰጡ ሹመቶች፡

- አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
- ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም
- ሌ/ጄኔራል አበባው ታደሰ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም
- አቶ ተመስገን ጥሩነህ የብሔራዊ መርጃና ድህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር
- ኮሚሽነር ደመላሽ ገ/ሚካኤል የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር
Ebc

07/11/2020
05/11/2020

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የተሰጠ ማሳሰቢያ፣

በአሁኑ ጊዜ ያጋጠመንን የፀጥታ ሁኔታ እንደ አጋጣሚ በመጠቀም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በማንኛውም ምርትና አገልግሎት ላይ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርግ ምርት የሚደበቁና የሚያከማቹ የመገልገያ ጊዜው ያለፈበትን ምርት ለገበያ የሚያቀርብ ምርት ላይ ባዕድ ነገር በመቀላቀል ለገበያ የሚያቀርብ በአጠቃላይ በሕገ-ወጥ ንግድ ሥራ ላይ ተሰማርቶ የሚገኝ ማንኛውም ነጋዴ ላይ ቢሮው ሕጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑ በጥብቅ ያሳስባል፡፡

ቢሮው ከዚህ በላይ በተገለፀው መሠረት ሕገ-ወጥ የንግድ ሥራ ላይ ተሠማርተው የሚገኙ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ እንዲያስችለው ተቆጣጣሪዎችን በየደረጃው ከማዕከል እስከ ወረዳ ግብረሃይል በማደራጀት ያሰማራ መሆኑን እየገጽን፤ ሸማቹ ሕብረተሰብ በከተማው በቂ አቅርቦት መኖሩን አውቆ ግብይቱን በተረጋጋ ሁኔታ እንዲያከናውኑ እናሳስባለን፡፡

በዚህ ማሳሰቢያ መሠረት ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ያጋጠመው ማንኛውም ሠው በተቸማሪም በነፃ የስልክ መስመራችን 8588 እንዲያሳውቀን እንጠይቃለን፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ

01/11/2020

የተከበሩ አቶ ሽመልስ ዘውዱ በቦሌ ክ/ከተ ወረዳ 15 አስተዳደር በዋ/ስራ አስፈጻሚነት ለአለፉት ሁለት አመታት በጥንካሬ እና በታታሪነት በማገልገል ወረዳው አሁን ያለበት ደረጃ እዲደርስ የበኩሎን /በሰው ሃይልም በግብአትም /ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማመስገን በሄዱበት ቦታ መልካም እዲገጥሞት የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በመላው በአስተዳደሩ ሰራተኞች እና አመራሮች ስም ልባዊ የሆነ ምኞቱን ይገልጻል ። በድጋሚ እናመሰግናለን ። ጥቅምት 22/2013 ዓ/ም

21/10/2020

ለሚ ኩራ የአዲስ አበባ 11ኛ ክፍለከተማ በመሆን በምክር ቤቱ ጸድቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በከሰዓት ውሎው ክፍለ ከተሞችንና ወረዳዎችን እንደገና ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ወሳኔ አስተላልፏል፡፡

አዲሱ አደረጃጀት የነዋሪዎችን ብዛት በማመጣጠን ፣ አዳጊ የሆነውን የአገልግሎት ተደራሽነትና የማስተዳደር አቅምን በማጎልበት ለከተማው ነዋሪዎች ሚዛናዊ በሆነ ርቀትና ተደራሽ በሆነ መልኩ የአገልግሎት አቅርቦት በማመቻቸት ነዋሪው ፍትሃዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚረዳ ይሆናል፡፡

በመድረኩ ላይ ምክትል ከንቲባ አዳነች አዲሱ ክፍለ ከተማ ተጨማሪ ይዞታ ሳይሆን ከዚህ ቀደም ከነበረው
ከቦሌ እና ከየካ ክፍለከተሞች በመክፈል የተዋቀረ ነው ብለዋል፡፡

ምክር ቤቱ በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ያደረገ ሲሆን ክፍለከተሞችን እና ወረዳዎችን ዳግም የማቋቋሚያ አዋጁንም ተቀብሎ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

በዚህም ለሚ ኩራ ክፍለከተማ የአዲስ አበባ 11ኛው ክፍለ ከተማ እንዲሆን ምክር ቤቱ በዛሬ ውሎው ወስኗል፡፡
ጥቅምት 10/2013 ዓ.ም

ቦሌ ወ15 ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ዛሬ  08/02/12 ከአባላቱ ያካሄደው  ጉባኤ
18/10/2020

ቦሌ ወ15 ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ዛሬ 08/02/12 ከአባላቱ ያካሄደው ጉባኤ

Not only the people the cars also decorated to support our leader Abiy!!!!!!!!
10/10/2020

Not only the people the cars also decorated to support our leader Abiy!!!!!!!!

09/10/2020
Intelligence is one of the quality of effective leader
06/10/2020

Intelligence is one of the quality of effective leader

Transformational leader lead with vision
06/10/2020

Transformational leader lead with vision

06/10/2020

ከመስከረም 25 በኋላ 26......ከመስከረም 30 በኋላም ጥቅምት 1....እያለ ይቀጥላል ከጠ/ሚ ዶ/ርአብይ ጋር ብልጽግና ፓርቲ ወደፊት ይራመዳል ይመራል ።

Address


Telephone

+251902410842

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bole Wereda 15 pp media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Bole Wereda 15 pp media:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share