12/04/2024
ዛሬ ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ በነበረ ተኩስ የፋኖ አመራር ናሁሰናይ ተገደለ
የተኩሱ መነሻ የጎንደር ፋኖ መሪ የነበረው ናሁሰናይ በመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች በመያዙ ምክንያት ነው ተብሏል።
ናሁሰናይን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ሊያውለው ሲሞክር ከፀጥታ ኃይሎች ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርጓል ያሉ ሲሆን አብረውት ከነበሩት ሁለት ሰዎች ውስጥ አንዱ ወዲያውኑ የሞተ ሲሆን ናሁሰናይ ቆስሎ ቢያዝም ህይወቱ አልፏል ተብሏል። አንደኛው ምንም ሳይሆን ተይዟል ተብሏል።
ከፀጥታ ኃይሎች በኩል አንድ የሞተ ሲሆን የቆሰሉም መኖራቸውን ነው የመረጃ ምንጮቹ የገለፁት።
ይህን ተከትሎ ከቦሌ snap plaza እስከ ቦሌ መድሃኒያለም ያለው መንገድ ዝግ ተደርጓል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ መግለጫ የሚከተለው ነው 👇
"
የጽንፈኛው ቡድን አባላት የሆኑት ናሁሰናይ አንድአርጌ ታረቀኝ ፣ አቤኔዜር ጋሻው አባተ እና ሀብታሙ አንዳርጌ ተሰማ የተባሉት የጽንፈኛው ቡድን አባላት በአዲስ አበባ ከተማ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ተልዕኮ ይዘው እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የጸጥታ አካላት ባደረጉ ክትትል ደርሰዉበት የሽብር ተግባራቸውን ሳይፈፅሙ በቁጥጥር ስር ለማዋል የፖሊስ አባላት እንቅስቃሴ እያደረጉ ባለበት ሁኔታ ሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ/ም ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ሚሊኒዬም አዳራሽ አካባቢ ጽንፈኞቸ እጃቸውን እንዲሰጡ ቢጠየቁም ፍቃደኛ ባለመሆናቸዉ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2C 14373 አ/አ አይነቷ አይሱዙ ዲዛዬር መኪናን በመጠቀም ከፖሊስ አባላት ጋር በተደረገ የተኩስ ልዉዉጥ የጽንፈኛው ቡድን መሪ ናሁሰናይ አንዳርጌ ታረቀኝ ቆስሎ ወደ ህክምና ከተላከ በኋላ ሲሞት ሀብታሙ አንዳርጌ ተሰማ በተኩስ ልውውጡ መሃል ተገድሏል፡፡
አቤኔዘር ጋሻው አባት የተባለው የቡድኑ አባል ሳይቆስል በቁጥጥር ስር መዋሉን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ጽንፈኞቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገ እንቅስቃሴ ሳጅን አራርሳ ተሾመ እና ኮንስታብል ማቲያስ ጴጥሮስ ሲቆስሉ አቶ እንዳሻው ጌትነት የተባሉ ግለሰብ ፅንፈኞቹ በመኪናቸው እንዲጭኗቸው ቢያስገድዷቸውም ግለሰቡ አልተባበር በማለታቸው በፅንፈኛው አባላት ተገድለዋል፡፡
አቶ እንደሻው ሲያሽከርክሯት የነበረቸው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ 80457 በጥይት ጉዳት እንደረሰባት አዲስ አበባ ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል ፡፡ በቀጣይ ፖሊስ የደረሰበትን ዝርዝር መረጃ እንደሚገልፅ አስታውቋል፡፡
ምንጭ:-ኢትዮ ቲዩብ