11/08/2023
የሐዋሳ ከተማ ሰላምና ጸጥታ መምሪያ በኑሮ ደረጃቸው ዝቅተኛ ለሆኑ አረጋዊያን ያሰራውን ቤት አስረከበ።
ነሐሴ 4/2015 ዓ/ም
ሐዋሳ
በስፍራው ተገኝተው ርክክብ ያደረጉት የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ኘ/ ጸጋዬ ቱኬ ናቸው።
ረ/ኘሮፌሰር ጸጋዬ ቱኬ በአስተዳደሩ ስር ለሚገኙ መምሪያዎች መሰል ተግባራትን እንዲተገብሩ በገለጹት መሰረት ዛሬ በሰላምና ጸጥታ መምሪያ ተሰርቶ የተጠናቀቀ ቤት ለርክክብ መብቃቱን ተናግረዋል።
ይህ ቤት በጥሬ ገንዘብ ብቻ ከ3 መቶ ሺህ ብር በላይ እንደፈጀ ገልጸው በከተማዋ ባለሀብቶችና ወጣቶች የተጀመሩ በጎ ተግባራት በሁሉም አካባቢ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።
በዚህ ዓመትም ከ2መቶ በላይ ቤቶችን ለመጠገን በዕቅድ መያዙን ነው ከንቲባ ጸጋዬ የገለጹት።
የሐዋሳ ከተማ ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ሀላፊ አቶ መኩሪያ መኒሳ በመምሪው ኮሚቴ በማወቀርና 38 ሰራተኞች 120 ሽህ ብር በማዋጣት በባህል አዳራሽ ክ/ከተማ ተለይቶ የተሰጣቸውን ቤት በሁለት ወር ውስጥ ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቅ እንደተቻለ ገልጸዋል።
ለዚህ ተግባር በርካታ ሰዎች በአይነትና በቁሳቁስ ድጋፍና ትብብር ማድጋቸውን አቶ መኩሪያ በማመስገን ጭምር ገልጸዋል።
የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ ፍሬህይወት ወ/ጻዲቅ በክረምት ከታቀዱ 17 ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የአረጋዊያን ቤት ጥገና በተለያዩ ክ/ከተማ ከ20 ቤት በላይ ለመጠገን ታቅዷል ብለዋል።
ወ/ሮ ፍሬህይወት አልቀው ያስረከብናቸው እየተጠናቀቁና በመሰራት ላይ ያሉ ቤቶች መኖራቸውን ገልጸዋል።
ቅን ልቦችን ፈጣሪ ይባርክ ያሉት ወ/ሮ ፍሬህይወት እነዚህ አረጋዊያን ሲደሰቱ ከማየት በላይ ትልቅ ደስታ የለም ብለዋል።
የቤት ርክክብ የተደረገላቸው አረጋዊያን አቶ ክብረት አሻግሬ እና ወ/ሮ አስናቀች ሀይሉ የ6 ልጆች ወላጅ ሲሆኑ ከዚህ ቀደም ባሉ ዓመታት በሚያፈስ፣ጎርፍ በሚገባበትና በፈራረሰ ቤት ውስጥ በችግር እየኖሩ እንደነበረ ገልጸው ይህንን ቤት ሰርተው ለሰጡን ሁሉ ፈጣሪ ይባርካቸው ሲሉ መርቀዋል አመስግነዋልም።
የመምው ም/ሀላፊና የወጣቶች ዘርፍ ሀላፊ አቶ አደራ ሀርቃ በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት 130 ሺህ ወጣቶች ተሳትፈው ለ270 ማህበረሰብ በመድረስ 110 ሚሊየን የመንግስት ወጪን የማስቀረት እቅድ መያዙን ገልጸዋል።
ከዚህም አንዱ በሆነው ቤት ጥገና ተግባር ዛሬ በአዲስ መልክ በመገንባት ርክክብ መደረጉን ገልጸው ሌሎችም ይህንን ተግባር እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።
Mereja media