Cush*te brave son

  • Home
  • Cush*te brave son

Cush*te brave son Kashfin mu'ujizadha abbaa shiraa qofa nyaatii kan ittin beekamu ruumicha fugug oroti

06/02/2024

"Abadan aangoon karaa afaan qawwee argamu hin jiru. Aangoon kan argamu karaa nagaa sagantaa ofii uummata amansiisuun qofaani"

MMI Dr Abiy Ahimad

06/02/2024

“Seenaa kaleessaatiin osoo wal nyaannuu egereen keenya akka hin diigamneef of eeggannoo taasisuu qabna!”

Ministeera Muummee Dr. Abiyyi Ahimad

12/01/2024
12/01/2024



Ethiopia to recognize Republic of Somaliland for sea access

The federal government is reportedly willing to become the first African nation to recognize the sovereignty of the Republic of Somaliland, a breakaway Somali territory, in exchange for a lease on a 20 kilometer stretch of the Somaliland coast and access to Berbera Port.

Stakes in state-owned Ethiopian Airlines and Ethio telecom are also on the table in the Somaliland deal, according to Ambassador Redwan Hussein, security advisor to the Prime Minister.

An MoU signed with Somaliland President Muse Bihi will also enable Ethiopia to operate a military base and commercial port in Somaliland, according to Redwan.

12/01/2024

Our force on the port
The only peace and treaty bought me

20/09/2023
Kantiibaan Magaalaa Maayaa Dr.Ifrahaa Waziir Bara haaraaya 2016 Sababeeffachuun ergaa Baga geessani dabarsaan.Barri 2016...
11/09/2023

Kantiibaan Magaalaa Maayaa Dr.Ifrahaa Waziir Bara haaraaya 2016 Sababeeffachuun ergaa Baga geessani dabarsaan.

Barri 2016 Bara tokkummaa, jaalalaa, nageenyaa fi Milkii akka isiniif tahuun hawwa. Barri 2016 bara tokkummaan imala badhaadhinaa jalqabame itti milkeessinuufi boqonnaa seenaa haaraa Naannoon teenyaa fi biyyi keenyaa Itoophiyaan galmeessaa jirtuun galma akka geenyuuf tokkummaan cimnee itti hojjanuudha.

Ummanni Magaalaa teenya Magaalaa Maayaas Bara 2016 kana keessa Magaalaan Maayaa Roga Dinaagdee, Siyaasaa fi Hawaasummaan fakkeenyummaa gaarii akka taatuuf Miira tokkummaa fi Jaalalaan gonfateen akka hojjattaan ergaa koo dabarsa.

Ayyaana Bara Haaraaya kana yeroo kabaajnu Kan daare Uwwisaa kan beelawe nyaachiisa Obbolummaan gammachuu waliin qooddachuun akka dabarsaan Dr.Ifrahaan ergaa dabarsaan.
Barri Bara Nageenyaa fi Badhaadhina isiniif haa tahu.

Dr.Ifrahaa Waziir
Kantiibaa Magaalaa Maayaa

04/09/2023
20/08/2023

የማህበራዊ ሚዲያ መረጃ መታወክ ምንድን ነው?

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተለያዩ መረጃዎችን ማጋራት የሚቻል ሲሆን መረጃዎቹ ጠቃሚና አወንታዊ ተፅዕኖም ሊኖራቸዉ ይችላል፤ ነገር ግን በዚሁ ማህበራዊ ሚዲያ ጠቃሚ ያልሆኑ ሀሰተኛ እና ጎጂ የሆኑ መረጃዎችም ይተላለፋሉ፤ ጉዳትም ሲያደርሱ ይስተዋላል፡፡

በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚተላለፉ ሀሰተኛ እና የተበረዙ መረጃዎች ተለያዩ አላማ ሊኖራቸው ይችላል፤ ከነዚህም ዉስጥ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማግኘት፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ጫና ለመፍጠር እንዲሁም ስነ ልቦናዊ ጫና ለመፍጠር እና ለበቀል ሊሆን ይችላል፡፡

በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቀቁ እዉነተኛ ያልሆኑ መረጃዎች ወይም የማህበራዊ ሚዲያ መረጃ መታዎኮች የራሳቸዉ ደረጃ ያላቸዉ ሲሆን በሶስት ደረጃዎች ከፍሎ ማየት ይቻላል፡

• ሚስ ኢንፎርሜሽን (Misinformation)፡- ይህኛዉ የመረጃ መታዎክ አይነት
o መረጃን ያሰራጨዉ አካል የአጥቂነት ፍላጎት የሌለዉ እና የመረጃ ስህተት ችግር ብቻ ያለበት የመረጃ መታዎክ ነዉ፤
o ይህ አይነቱ የመረጃ መታዎክ የሚፈጠረዉ ትክክለኛ ያልሆነ የመረጃ እና የምስል ቅንጅት፣ቁጥሮች እና አሃዞች ተሳስተዉ ሲቀመጡ አልያም ትርጓሜዎች እና አዉዶች በተሳሳተ ሁኔታ ሲቀርቡ ነዉ፡፡

• ዲስ ኢንፎርሜሽን (Disinformation)፡- ይህኛዉ የመረጃ መታዎክ አይነት
o መረጃዉን ያሰራጨዉ አካል ሆን ብሎ እና አስቦበት ተደራሾችን ለማሳሳት የሚያደርገዉ መረጃን የማወክ ሂደት ነዉ፤
o ዲስ ኢንፎርሜሽን ሆን ተብለዉ የተፈጠሩ ድምፆች/ምስሎች ወይም ተንቀሳቃሽ ምስሎች፣ ኮንስፓይረሲዎች ወይም አሉባልታዎችን በመጠቀም መረጃን ማዎክ ነዉ፡፡

• ማል ኢንፎርሜሽን (Malinformation)፡- ይህኛዉ የመረጃ መታዎክ አይነት
o እጅግ በጣም ከፍተኛ የአጥቂነት ፍላጎት ወይም መረጃን የማወክ ስሜት የያዘ መረጃን የማዛባት ሂደት ነዉ፤
o ለግል ወይም ለቡድን ጥቅም ሲባል ሆን ተብሎ የብዙሃንን ጥቅም እና ፍላጎት የሚፃረር ድርጊትን መፈፀምን ያካትታል፡፡

እነዚህን የመረጃ መታዎኮች የሚያደርሱትን ተፅዕኖ ለመቀነስ እና ለመከላከል መደረግ ካለባቸዉ ጥንቃቄዎች መካከል የሚከተሉት ተጠቃሾች ናቸዉ
• ሪፖርት ማድረግ፡ በየማህበራዊ ሚዲያዎች ፕላትፎርሞች ያሉ የኮሚዩኒቲ ስታንዳርድ ጋር አብረዉ የማይሄዱ መረጃዎችን ሪፖርት በማድረግ ስርጭቱን መግታት፤

• ዲጂታል ሊትሬሲን ማሳደግ፡ ይህ ማለት ሰዎች የራሳቸዉን በዲጂታል ሚዲያዉ መረጃን የመገምገም እና የመመዘን ብሎም ትክክለኛነቱን የማረጋገጥ ብቃትን ማሳደግ ሲሆን የመረጃን እዉነተኛነትን ለማጣራት የሚደረጉ ቴክኒካል እዉቀቶችንም ጭምር ይይዛል፤ ይህም ከታማኝ ምንጮች ማረጋገጥ እንዲሁም የምስል እና ተንቀሳቃሽ ምስል ፍለጋ “search image’’ የሚያካትት ይሆናል፡፡

ወቅታዊና ተጨማሪ የሳይበር ደህንነት መረጃዎችን ለማግኘት፡-
• ድረ ገጽ፦ https://www.insa.gov.et
• ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/INSA.ETHIOPIA
• ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com//featured
• ቴሌግራም፦ https://t.me/insagovet
• ትዊተር፦ https://twitter.com/INSAEthio
• ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/.gov

18/08/2023

ምክንያታዊ መረጃን የመመርመሪያ መንገዶች

በምንኖርበት የዲጂታል ዓለም ከቴክኖሎጂው ማደግ ጋር ተያይዞ መረጃዎች ከአለማችን አንዱ ጫፍ በሰኮንዶች ሽርፍራፊ ውስጥ ወደ ሌላው ጫፍ ይሰራጫል ይተነተናል፡፡
መረጃዎች በየእለቱ ለምናደርጋቸው እንቅሰቃሴዎቻችን እጅግ አስፈላጊ መሆኑ አያጠያይቅም፤ ነገር ግን እነዚህ መረጃዎች አላማቸውን ሲስቱ እና ላልተፈለገ ጥቅም ላይ ሲውሉ ፓለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ እና የስነ- ልቦና ጉዳቶችን በግለሰብም ሆነ በሀገር ደረጃ ያስከትላሉ ፡፡
በመሆኑም ከማህበራዊ ሚዲያዎች የምናገኛቸውን መረጃዎች መክንያታዊ በሆነ መልክ የመመመርመር ባህልን ልናዳብር ይገባል፡፡
ምክንያታዊ መረጃን የመመርመሪያ መንገዶች
1.የሚዲያ ተጠራጣሪነትን ማዳበር( Media Consciousness) ፤
2.መረጃው ስሜታዊ የማድረግ ዓላማ እንዳለው ማረጋገጥ( Sensationalized) ፤
3 .የመረጃውን ርእስ ብቻ አይቶ አለማመን ፤
4.መረጃው ሊንኩን እንድንከፍት የሚገፋፋ መሆኑን መጤን?
5. የመረጃው አላማ ስርጭት ወይስ መረጃን ማድረስ መሆኑን ማረጋገጥ ፤
6. የመረጃውን የቋንቋ አጠቃቀም ማጤን፤

የመንግስት የሰላም ቁርጠኝነትና የአሸባሪው ህወሀት ጦረኝነት!!አሸባሪው የህወሓት ቡድን ኢትዮጵያን ለማፈራረስና በህዝብ ትግል ያጣውን ስልጣን መልሶ ለመቆናጠጥ በማለም በሰሜን እዝ ላይ የታቀደ...
27/08/2022

የመንግስት የሰላም ቁርጠኝነትና የአሸባሪው ህወሀት ጦረኝነት!!

አሸባሪው የህወሓት ቡድን ኢትዮጵያን ለማፈራረስና በህዝብ ትግል ያጣውን ስልጣን መልሶ ለመቆናጠጥ በማለም በሰሜን እዝ ላይ የታቀደና የተደራጀ መጠነ ሰፊ ጥቃት በመፈፀም የክህደት ተግባሩን በገሃድ አሳይቷል፡፡

ከሃዲው የጁንታ ቡድን ግዙፉን የሰሜን ዕዝ ከጀርባው በመምታት ሁሉንም ወታደራዊ ትጥቆች በእጁ በማስገባት ወደ አራት ኪሎ የሚያደርገውን ጉዞ በአጭር ጊዜ ለማሳካት ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ጥቃት በመሰንዘር ለዳግም ስልጣን ቢቋምጥም እንዳሰበውና እንደገመተው ሊሆንለት ግን አልቻለም፡፡

በዕዙ ሠራዊት ላይ አረመኔያዊ ጥቃት በመፈፀም የክህደት ጥጉን ከማሳየት ባሻገር ጨፍጫፊው ህወሓት የሠራዊታችን ህዝባዊ ድጋፍ ክዶ የግፍ በትሩን በዕዙ አባላት ላይ አሳርፏል፡፡ በርካታ አሰቃቂና ሰቅጣጭ የግፍ ድርጊቶችንም ፈፅሟል፡፡

ይህን ተከትሎ በትግራይ ክልል በተካሄደው የህግ ማስከበርና የህልውና ዘመቻ በርካታ አንፀባራቂ ድሎች ተመዝግበዋል፡፡ አንዱና ዋነኛው የጁንታው ሃገር የማፍረስ ህልሙ ሙሉ በሙሉ እንዲከስም ተደርጓል፡፡ የጁንታው ተዋጊ ሃይል አደረጃጀቱንና የዕዝ ሰንሰለቱን በመበጣጠስ የስጋት ደረጃውን ኢምንት ማድረግ ተችሏል፡፡ በጁንታው ታግተው የነበሩ የሰራዊታችን አመራሮችና አባላትን ጥበብ በተሞላበት ኦፕሬሽን በማስለቀቅ አስደናቂ ጀግንነት ተፈጽሟል፡፡ የጁንታው ተዋጊ ሃይል አመራሮችንና አባላትን በቁጥጥር ስር በማዋል ለህግ እንዲቀርቡ ተደርጓል፡፡

መንግስት የተናጥል የተኩስ አቁም አድርጎ ከትግራይ ክልል ጦሩን ቢያወጣም አሸባሪው ህወሓት አጎራባች አካባቢዎችን በመውረር መንግስት ሳይወድ በግድ ወደ ጦርነት ገብቶ የሽብር ቡድኑ በወረራ ከያዘቸው የአፋርና አማራ ክልል አካባቢዎች ተጠራርጎ እንዲወጣ አድጓል፡፡

አሸባሪው የህውሓት ቡድን በህዝብ ትግል ከነበረበት የፌዴራል ስልጣን በሃይል ተሸቀንጥሮ መቀሌ ከመሸገ በኋላ በርካታ የግጭት ሴራዎችን እየጠነሰሰ በሃገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶች እንዲከሰቱና በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስ ያለእረፍት ሲሰራ ቆይቷል፡፡

የሰሜን ዕዝ ጥቃቱን ተከትሎ ህወሓት ካዳረሳቸው ግፎች ጥቂቶቹችን ብናስታውስ እንኳ ዛፍ ላይ አስሮ መረሸን፤ በቢላዋ ማረድ፣ እርቃንን አቁሞ ከገደለ በኋላ አስከሬኑን መጐተትና በአውሬ ማስበላት፣ በአስከሬን ላይ እስከመጨፈር የደረሰ አረመኔያዊ ድርጊት ፈፅሟል፡፡ የሴት ወታደሮችን ጡት መቁረጥ፤ ሰዎች በህይወት እያሉ ሲኖትራክ መኪና በላያቸው ላይ መንዳትና በማንነታቸው እየለየ ማሰቃየትና መግደል የመሳሰሉ በሠራዊታችን ላይ የተፈፀሙ የጁንታው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች ናቸው፡፡

በጀግናው ሠራዊታችን በምዕራብ ግንባር የተሰነዘረበትን የፀረ ማጥቃት ርምጃ መቋቋም የተሳነው የጁንታው ቡድን “ሳምሪ” በመባል በሚታወቁ ገዳይ ቡድን በማይካድራ ከተማ የሚኖሩ ከትግራይ ብሔር ውጭ የሆኑ ሰዎችን እጅግ ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ በመጨፍጨፍ የበቀል በትሩን አሳርፏል፡፡ በባል ፊት ሚስት ደፍረዋል፣ ገድለዋል፣ በወላጆቻቸው ፊት ሴት ህፃናትንና ልጃገረዶችን ደፍረዋል፣ ንፁሀንን በገጀራ እየቆራረጡ በዱላና በድንጋይ በመቀጥቀጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ረሽኗል፡፡

አሸባሪ ቡድኑ ወረራውን ቀጥሎ በአማራ ክልል በተለይ በሰሜን ጐንደር ዞን ጭና ቀበሌ ዘግናኝና አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ንፁሐን ዜጎች የተጨፈጨፉ ሲሆን በርካታ ንፁሃን ሰዎችም ደብዛቸው እንዲጠፋ አድርጓል፡፡ ሴቶችን በመንጋ በመድፈርና በብልታቸው ውስጥ ባዕድ ነገር በመጨመር ከሰውነት ያፈነገጠ አስነዋሪ ድርጊቶች የተፈፀሙ ሲሆን በዚህ ምክንያት ለማህፀን ኢንፌክሽን፤ ለፊስቱላ፤ ለኤች.አይ.ቪ/ኤድስ፤ ለአዕምሮ ጤና መታወክና ለሌሎች በሽታዎች ተጠቂ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡

የሽብር ቡድኑ በአፋር ክልል ጋሊኮማ ጤና ጣቢያና ትምህርት ቤት ተጠልለው የነበሩ ዜጎችን የጦር ዒላማ በማድረግ በከባድ መሳሪያ በመደብደብ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ፈጽመዋል፡፡ በዚህ ጥቃት በርካታ ንፁሐን ሰዎች ሞተዋል አካላቸውም ጎሏል፡፡ በጥቅሉ ሲታይ ጁንታው በከፈተው ጦርነት ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያ እንዲኖሩ ተገደዋል፡፡

አሸባሪ የህውሃት ቡድን ትምህርት ቤቶች ባንኮችና ቢሮዎች ዘርፏል አውድሟል። በሚሊየን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው ነበር፤ በሺዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ሰራተኞችም ከስራ ገበታቸው ተፈናቅለዋል፡፡ የግለሰብ ሱቆችን፡ አልባሳትን ገንዘብና የገበሬውን እህልና ከብቶች ሳይቀር በመዝረፍ ህዝቡ በርሃብ እንዲሰቃይ አድርጓል፡፡

ጁንታው የእምነት ተቋማትን የመሳሪያ መከዘኛ፣ የከባድ መሳሪያ መጥመጃ እና ለምሽግነት በመጠቀም የእምነት ስፍራዎችን አርክሷል፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች የእምነት ተቋማትን በከባድ መሳሪያ በመደብደብ ጉዳት እንዲደርስባቸው አድርጓል፡፡ የሃይማኖት መፅሃፍትን የቁርዓንና ኪታቦችን ላልተገባ ጠያፍ ተግባር በመጠቀም እና በማቃጠል ለሃይማኖቶች ያለውን ጥላቻና ሰይጣናዊ ማንነቱን አሳይቷል፡፡

ከሰሞኑ የሽብር ቡድኑ ህወሐት በመቀሌ ከተማ ውስጥ የሚገኘውን የዓለም የምግብ ድርጅት መጋዘን በኃይል ሰብሮ በመግባት ነዳጅ እና ሌሎች ለሰብዓዊ ድጋፍ አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶችን በመዝረፍ ለወታደራዊ ጉዳዮች በማዋል ጦረኝነቱን ዓለም አውቆለታል፡፡ ድርጊቱ ህወሓትን በውል ለማያውቅ እንግዳ ቢመስልም የሽብር ቡድኑ ያደገበት ባህሪው ነው፡፡

አሸባሪው የህውሃት ቡድን ይህን ሁሉ አስከፊ ዘግናኝ ድርጊት እየፈፀመ እንኳን መንግስት ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት የሰሜኑን ጦርነት በሰላም ለመቋጨት ያስችላሉ ያላቸውን በርካታ አዎንታዊ እርምጃዎች ሲወስድ ቆይቷል፡፡ ከነዚህም መካከል መንግስት የኃይል የበላይነትና የሎጂስቲክስ አቅም እያለው ወደ ትግራይ ክልል ከመግባት ተቆጥቧል፡፡ ለትግራይ ህዝብ ተጨማሪ እድል በመስጠት ከችግር እንዲላቀቅ እና በአካባቢው መረጋጋት ተፈጥሮ ወደ ግብርና ስራው እንዲመለስ መንግስት በራሱ ተነሳሽነት የተኩስ አቁም አድርጓል፡፡ በተጨማሪም ከግጭት የሚገኝ ምንም ነገር የለሌ በመሆኑ መንግስት ለትግራይ ሁለተኛ የጥሞና ጊዜ ሰጥቶ ነበር፡፡

የተናጠል ተኩስ አቁም በማድረግ ምቹ ሁኔታን ፈጥሮ የተሳለጠና ያልተቋረጠ ያለአንዳች ገደብ በየብስና በአየር ሰብዓዊ እርዳታዎቹ ወደ ትግራይ ክልል እንዲደርሱ አድርጓል፡፡ ለሰላም በር ይከፍታል በሚል እስረኞችን ፈቷል፡፡ መንግስት የሰላም አማራጭንም አሟጦ ለመጠቀም እንዲቻል ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለማደራደር ዝግጁነቱን ከማረጋገጥ በላይ የሰላም አማራጭ አብይ ኮሚቴን በይፋ ወደ ስራ አስገብቶ ግልጽ አቅጣጫንም ማስቀመጡ ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት የሚያመላክት ነው፡፡

ነገር ግን አሸባሪው የህውሃት ጁንታ ቡድን በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት የቀረበለትን የሰላም ጥሪ በርካታ ቅድመ ሁኔታዎችንና መሰናክሎችን በመፍጠር አልቀበልም ማለቱ ጦርነቱን ለመጀመር ካለው ፅኑ ፍላጎት የመነጨ መሆኑ አመላካች ነበር፡፡

ይህ የሽብር ቡድን ከመንግስት በኩል የቀረቡለትን በርካታ የሰላም አማራጮች እንዳይቀበል ስጋት የፈጠረበት ደግሞ የትግራይን ህዝብ ጥያቄ መመለስ እንደማይችልና ከህግ ተጠያቂነት እንደማያመልጥ ስለተገነዘበ ነው፡፡

አሸባሪው የህውሃት ጁንታ ቡድን ጦርነትን እንደ መጨረሻ አማራጭ አድርጎ በመውሰድ ከበባውን እንሰብራለን፣ መተማመኛችን ክንዳችን ነው፣ የትግራይ መሬቶችን እናስለቅቃለን፣ ወዘተ በማለት ባለፉት አምስትና ስድስት ወራት በተለያዩ ግንባሮች በርካታ ትንኮሳዎችን ሲያደረግ ቆይቷል፡፡

መንግስት ከጦርነት ይልቅ የሠላም አማራጩን ቅድሚያ በመስጠት በጁንታው የሚፈፀሙ የጠባ ጫሪነት ትንኮሳዎችን በሆደ ሰፊነት በማለፍ ለሰላም ቁርጠኛ መሆኑን በተደጋጋሚ አረጋግጧል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ የሽብር ቡድን ለሰላም እጁን የዘረጋዉን መንግስት በሃሰት በመወንጀል “ድርድሩ አስቀድሞ ከሽፏል/ቴክኒካሊ ፈርሷል/” በሚል ለተለያዩ ወገኖች ጦርነቱ እንደማይቀር ሲያደርጉ የነበረዉን ቅስቀሳ በማጠናከር የትግራይን ወጣት ዳግም ወደ ጦርነት ለመማገድ በይፋ አውጀው ከዕለት ወደ ዕለት በተለያዩ ግንባሮች ትንኮሳ ማድረጉን ቀጠለ፡፡

በደቡብ ትግራይ በኩልም ተደጋገሚ የጦርነት ሙከራ ቢያደርጉም በቀጠናው ያለው ሠራዊታችን ሙከራቸውን እያከሸፈ ዋናው መፍትሔ መንግስት የያዘው የሰላም መንገድ ነው በሚል መስዋዕትነት ጭምር እየከፈለ ጉዳዩ እንዳይባባስ እያረገ ሰንብቷል፡፡

ሠራዊታችን ምንም አይነት እንቅስቃሴ ሳያደረግ የወያኔ አፈቀላጤው የፌደራል መንግሥቱ ጦር በሰሜን ምዕራብና በምዕራብ ትግራይ ደደቢት አካባቢ ባሉ የትግራይ ኃይሎች ላይ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ድብደባ ፈጽሞብናል፤ የሰብዓዊ እርዳታና የተኩስ አቁም አዋጅ ተጥሷል በማለት የተለመደ የሃሰት ውንጀላውን አሰምቷል፡፡

የሽብር ቡድኑ የኢትዮጵያ ሰራዊት የማያውቀው የደበቀው ተተኳሽ እንዳለውና ጦርነት ለመጀመር ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ በሚልሻ ጥርቅም ጦር አዛዡ ታደሰ ወረደ አማካኝነት ተናግሯል፡፡

ከተለያየ ወገን “ለምን አታጠቁም? ለምን አትጀምሩም?" የሚሉ ጥያቄዎችና ጉትጎታዎች አሉ “መቼ እንጀምር? እንዴትና የት? የሚለው ወታደራዊ ስራ የኛ ነው እያሉም ሲደነፉ ነበር፡፡ ወደ ኤርትራም ጦርነት እንደሚከፍቱም በግልፅ ተናግረዋል፡፡ ጦርነቱን ለመጀመር ሲንደረደሩ የሕወሓት አመራሮች በተለያዩ የትግራይ ዞኖች ከነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የትግራይ ህዝብ ያለብንን ችግር ለመፍታት ጦርነት ለመጀመር የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሰናል ተዘጋጁ በማለት አውጀዋል፡፡ እነዚህ ተደምረው ሲታዩ ጦርነቱን አሸባሪው ኃይል ስለመጀመሩ በቂ ማሳያ ነው፡፡

የሽብር ቡድኑ የህወሓት ታጣቂ ቡድን ሰሞኑን ሲፈጽም የሰነበተውን ትንኮሳ ገፍቶበት ነሃሴ17/2014 ዓ/ም ንጋት 11 ሰዓት ላይ በምስራቅ ግንባር በቢሶበር፣ በዞብል እና በተኩለሽ አቅጣጫዎች ውጊያ በመክፈት ጥቃት ፈጽሟል፡፡ በዚህ እርምጃውም ተኩስ ማቆሙን በይፋ አፍርሷል፡፡ የፈጸመው ጥቃትም ሆነ እሱን ተከትሎ ያወጣው መግለጫ አስቀድሞ ለውጊያ ሲዘጋጅ እንደነበር ግልጽ ማሳያ ነው፡፡

መግልጫ የሰጠበት ሰዓትና የመግለጫው ይዘት አስቀድም ዝግጅት የተደረገበት መሆኑን በገሃድ የሚያሳይ ነው፡፡ የሽብር ቡድኑ እንደገና ለሶስተኛ ጊዜ በእብሪት የጀመረው ጦርነት ታሪካዊ ከሃዲነቱን እና የባዕዳን ጉዳይ አስፈፃሚ ኃይል መሆኑን በድጋሜ አረጋግጧል፡፡

መንግስት ለአፍሪካ ችግሮች የአፍሪካ መፍትሔ መርህን ለመተግበር የሰላም ጥረት ሲያደርግ ህወሓት የሰላም ውይይቱን ጥረት ሲያደናቅፍ ቆይቶ አሁን ላይ ለይቶለት ጦርነት ከፍቷል፡፡ የቡድኑ ህልውና ግጭት መፍጠር ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ከግጭት፣ ትንኮሳና ከጦርነት አባዜው ዛሬም አለመቆጠቡን የሙጥኝ ብሏል፡፡

አሸባሪው ወያኔ ተዘጋጅቶና አቅዶ ባካሄደው ውጊያ አንድም ነገር ማሳካት ሳይችል ቀርቷል፡፡ በያለበት ተመትቷል፤ ከባድ ኪሳራም ደርሶበታል፤ ቆርጦ የመጣው ተቆርጦ ተመትቷል፣ ፊት ለፊት የመጣው ደግሞ ተደምስሷል፡፡ በግድ እየገፉ ያመጡትን ለጋ ወጣት ቄራ እንደሚገባ እንስሳ እያስገቡ እያስጨረሱት ነው፡፡ ወያኔ ካለፈው ስህተቱ ሳይማር አሁንም የ17ኛውን ክ/ዘመን የውጊያ ስልት ወይም በህዝብ ማዕበል የሚካሄድ ውጊያ በ21ኛው ክ/ዘመን ላይም ተግባራዊ በማድረግ ቆሞ ቀርነቱን እያስመሰከረ ነው፡፡

አሸባሪው የህውሃት ቡድን አሁንም የትግራይን ወጣት በሃሰት ፕሮፖጋንዳ እየቀሰቀሰ ወደ ጦርነት በመማገድ ከፍተኛ የህዝብ እልቂት እንዲፈፀም አበክሮ እየሰራ ይገኛል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ መንግስት እንዲህ አይነት ድርጊት እንዳይፈፀም አሁንም ድረስ የሰላም አጆቹን ዘርግቶ ጁንታው ወደ ሰላማዊ ድርድር እንዲመጣ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ የሽብር ቡድን የሰላም አማራጩን አሻፈረኝ ብሎ ጦርነቱን የሚገፋበት ከሆነ እንደተለመደው ሁሉ ሠራዊታችን አስፈላጊውን መስዋዕተነት ሁሉ እየከፈለ የጁንታውን ሃይል ድባቅ በመምታት ግብዓተ መሬቱን በማፋጣን የሃገራችንን ሉዓላዊነትና ብሄራዊ ጥቅም ማስጠበቁን ይቀጥላል፡፡

ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ አኩር ተጋድሎ ታሸንፋለች!!

የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ተጨባጭ ውጤት አስገኝቶልናል ሲሉ በምስራቅ ሀረርጌ ዞን አርሶ አደሮች ተናገሩሐምሌ 5/2014 (ዋልታ) ካለፉት ሶስት አመታት ወዲህ እየተካሄደ የሚገኘው የአረንጓ...
12/07/2022

የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ተጨባጭ ውጤት አስገኝቶልናል ሲሉ በምስራቅ ሀረርጌ ዞን አርሶ አደሮች ተናገሩ

ሐምሌ 5/2014 (ዋልታ) ካለፉት ሶስት አመታት ወዲህ እየተካሄደ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ተጨባጭ ውጤት አስገኝቶልናል ሲሉ በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በደኖ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮች ተናገሩ፡፡

አራተኛው የአራንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በሚገኙ 24 ወረዳዎችና ከተማ መስተዳድሮች እየተካሄደ ሲሆን በዞን በሚገኘው በደኖ ወረዳም አርሶ አደሮችንና የዞኑ አመራሮችን ባሳተፈ መልኩ የችግኝ ተከላ ተካሂዷል፡፡

አርሶ አደሮቹ ለዋልታ በሰጡት አስተያየትም የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብሩ የአፈር መሸርሸርን በማስቀረት፣ ለከብቶች የሚሆን መኖ እንዲያገኙና በአካባቢው የነበረው የአየር ንብረት እንዲሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ተናግረዋል፡፡

መሬታችን በጎርፍ በመሸርሸሩ ምርታማ አልነበረም፤ ዝናብም አናገኝም ነበር ሆኖም ችግኝ መትከል ከጀመርን ወዲህ ብዙ ጥቅም አግኝተናል ብለዋል።

ፋይዳው በመገንዘባቸውም የተከሏቸውን ችግኞች በዘላቂነት እንዲፀድቁ በኃላፊነት ስሜት እንክብካቤ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የምስራቅ ሀረርጌ ዞን አስተዳዳሪ ሚስኪ መሀመድ በእለቱ የችግኝ ተከላ የተካሄደበት የበደኖ ወረዳ ለም ቢሆንም ለአፈር መሸርሸር የተጋለጠ እና ኅብረተሰቡም በድርቅ ተጎድቶ ቆይቷል ብለዋል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብሩ ይህንን ችግር ከመቅረፍ አንፃር ውጤት እያመጣ መሆኑን አንስተው ኅብረተሰቡም በንቃት እየተሳተፈ እና የተተከሉ ችግኞች እንዲፀድቁም በባለቤትነት መንፈስ እየተንከባከበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም በዞኑ በአንድ ጀምበር 33 ሚሊየን ችግኞች ለመትከል ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል፡፡

የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ ጌታሁን ንጋቱ በዘንድሮው አመት በዞኑ 300 ሚሊየን ችግኞች ለተከላ ዝግጁ ማድረግ መቻሉን ጠቁመው ከተዘጋጁ ችግኞች መካከልም 60 በመቶው ለምግብነት የሚውሉና 40 በመቶው ደግሞ የደን ዛፎች ናቸው ብለዋል፡፡

ከአምስት አመታት በፊት የዞኑ የደን ሽፋን ከ3 በመቶ በታች የነበረ ቢሆንም በተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ወደ 13 በመቶ ማሳደግ ተችሏል ብለዋል፡፡

በተለይም ምርትና ምርታማነት ከማጎልበት አንፃር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ጠቁመው ለዚህም ከሶስት አመታት በፊት በዞኑ የተገኘው ምርት 3 ሚሊየን ኩንታል ብቻ የነበረ ቢሆንም የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብሩ በተለይም በአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራን በማጎልበቱ በየአመቱ የሚገኘው ምርት እየተሻሻለ መምጣቱን እና በዘንድሮው አመትም 9 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን ተናግረዋል፡፡

ተስፋዬ ኃይሉ (ከሀረር)

💞"ሀገራችን ባለ ጽኑ መሠረት እንጂ ማንም የሚንዳት የጨረቃ ቤት አይደለችም።"💞-ኮ/ል ጌትነት አዳነ
12/07/2022

💞"ሀገራችን ባለ ጽኑ መሠረት እንጂ ማንም የሚንዳት የጨረቃ ቤት አይደለችም።"💞
-ኮ/ል ጌትነት አዳነ

ሐምሌ 3 ቀን 2014 ዓ.ምኪነ-ጥበብ ለሠራዊት ሞራል ከመሆን ባለፈ ድልን የሚያጎናፅፍ ነው ሲሉ አርቲስቶች ገለፁ።የምስራቅ ዕዝ ኦርኬስትራ ከተጋባዥ ድምፃውያን ጋር በመሆን በማዕከላዊ ዕዝ የ...
10/07/2022

ሐምሌ 3 ቀን 2014 ዓ.ም

ኪነ-ጥበብ ለሠራዊት ሞራል ከመሆን ባለፈ ድልን የሚያጎናፅፍ ነው ሲሉ አርቲስቶች ገለፁ።

የምስራቅ ዕዝ ኦርኬስትራ ከተጋባዥ ድምፃውያን ጋር በመሆን በማዕከላዊ ዕዝ የግዳጅ ቀጠና ተዘዋውሮ አነቃቂ የኪነ-ጥበብ ስራዎችን አቅርቧል።

ስራቸውን ለሠራዊቱ ካቀረቡ ድምፃውያን መካከል አርቲስት ፀጋዬ ደንደና እና አርቲስት ስንዱ አሌ በሰጡት አስተያዬት የሠራዊቱን ሞራል፣ ጥንካሬ፣ ብርታት እና ቁርጠኝነቱን ስናይ ትልቅ ኩራት ተሰምቶናል።

በሰራዊት ውስጥ ብዙ ብሄር፣ ብዙ ሃይማኖት፣ ብዙ ቋንቋ አለ። ሁሉም በኢትዮጵያዊነት አንድ ሆነው ጠላታቸውን ይፋለማሉ። የመከላከያ ሰራዊቱ ለእኛ ህይወቱን አሳልፎ ሰጥቶናልና እናመሰግነዋለን ሁሌም ከጎኑ ነን ብለዋል።

ልመንህ ሻውል
ፎቶግራፍ እምነ ጋሻው

ለተጨማሪ መረጃዎች ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ።

ቴሌግራም 👇
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

ፌስቡክ 👇
https://www.facebook.com/fdredefense.official

Adoolessa 03,2014-“Sabni Goota qabu Seenaa qaba!” - Pireezedaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa Obbo Shimallis Abdiisaa.To...
10/07/2022

Adoolessa 03,2014
-“Sabni Goota qabu Seenaa qaba!” - Pireezedaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa Obbo Shimallis Abdiisaa.

Tokkummaan sabaafi biyyaa wareegama qaalii gootonni kaffalaniin ijaaramee tikfama.

Galmi waloo ol aanaan aarsaa goototaan dhugooma. Seenaafi seenessi aarsaa isaanii irraa madde haphee ta’ee tokkummaa sabaa iticha. Kanaaf, sabni gootota waloo hin qabne dantaa, seenaafi seenessa waloo hin qabaatu.

Akkuma Pireezidaant Shimallis yeroo mara jedhan, Sabni goota hin qabne seenaa hin qabu. Sabni goota qabu seenaa qaba.

Tokkummaan Oromoo aarsaa kitima galma waloo dhugoomsuuf gootonni kaleessaa kaffalaniin ijaarame.

Gootonni Oromoo gootota mandaraa osoo hin taane gootota Oromiyaafi kan biyyaati.

Wareegamniifi aarsaan isaan kaffalan Oromiyaa hundaaf malee kutaan adda qoodee miti.

Biyyaaf asrsaa qaqqaalii isaan kaffalantu bilisummaa har'a argameef bu'ura, guca isaan qabsiisantu har'a biyyaaf ife.

Mootummaan Naannoo Oromiyaa Siidaa gootota kanneenii bakka dhaloota isaaniitti osoo hin taane, kutaawwan Oromiyaa adda addaa keessatti ijaarsisuun, Oromoon dachee gootota gandaan dhaadatanii osoo hin taane, dachee gootota waloo ta'uu ishee mirkaneessa.

'Lammiin barate gaaffii mirgaa gaafata' jechuun Oromoon akka baratuuf qabsaa'aa kan turan Jeneraal Taaddasaa Birruu, wareegamanis mul'atni isaanii dhaloota har'aatiin galma ga'eera.

Barattoonni Oromoo miliyoona 12 ol Manneen Barnootaa Oromiyaa adda addaa keessatti barachaa jiru.

Goota hawwiin isaa dhaloota har'aan dhugoome kana yaadachuuf Siidaan yaadannoo gootummaa isaanii Mana Barumsaa Bultii Addaa Najjoo keessa dhaabatee eebbifameera.

Hayyuu jalqaba qubee Afaan Oromoo boce Sheek Bakirii Saaphaloon "Afaan Ormaa tolcheen kabaja; kan koo kan salphisu ammoo lafa irraa dhabama" jechuun kabaja Afaan Oromoof qaban kan agarsiisan hayyuu jabaa Oromoo kanaaf siidaan yaadannoo Mana Barnootaa Ifa Boruu Bultii Addaa Yaa'aballoo keessa dhaabachuun eebbifamuun dhaloonni har'aa kabaja abbootii isaaf qabu muldhisa

ተራራን ሰንጥቆ በማለፍ ጠላትን መቅበር የሚችል  ክፍል ፈጥረናል ሲሉ የማዕከላዊ ዕዝ የኮር ዋና አዛዥ ብ/ጀኔራል ተስፋዬ ረጋሳ ተናገሩ።
09/07/2022

ተራራን ሰንጥቆ በማለፍ ጠላትን መቅበር የሚችል ክፍል ፈጥረናል ሲሉ የማዕከላዊ ዕዝ የኮር ዋና አዛዥ ብ/ጀኔራል ተስፋዬ ረጋሳ ተናገሩ።

Address


Telephone

+251902582111

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Cush*te brave son posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share