Universthiopia

  • Home
  • Universthiopia

Universthiopia works on university

🔥Genuine parts, Reliable supply chain!
30/06/2023

🔥Genuine parts, Reliable supply chain!

Genuine parts,Reliable supply chain
05/06/2023

Genuine parts,Reliable supply chain

አዲሱን አመት የሰላምና የጤና ያድርግልን።
11/09/2022

አዲሱን አመት የሰላምና የጤና ያድርግልን።

የዩኒቨርስቲ መምህራን ማህበር ባለ6 ነጥብ የአቋም መግለጫ  ለኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር አቀረቡ።በመግለጫው ላይ የመምህራን ጥቅማ ጥቅም ጉዳይ በዝርዝር ተገልጧል።
04/08/2022

የዩኒቨርስቲ መምህራን ማህበር ባለ6 ነጥብ የአቋም መግለጫ ለኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር አቀረቡ።በመግለጫው ላይ የመምህራን ጥቅማ ጥቅም ጉዳይ በዝርዝር ተገልጧል።

በሼህ ሙሃመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን ስታዲየም በነገው ዕለት የሚካሄደው የምረቃ ፕሮግራሙ ቅድመ ዝግጅት በከፊል ይሄን ይመስላል ። ተማሪዎቻችንና የተማሪ ወላጆች እንኳን ደስ አላችሁ!
29/07/2022

በሼህ ሙሃመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን ስታዲየም በነገው ዕለት የሚካሄደው የምረቃ ፕሮግራሙ ቅድመ ዝግጅት በከፊል ይሄን ይመስላል ። ተማሪዎቻችንና የተማሪ ወላጆች እንኳን ደስ አላችሁ!

 #ጠቃሚ መረጃ‼ በዩኒቨርሲቲው መማክርት ጉባኤ (ሴኔት) በ2014 ዓ.ም አዲስ የጸደቁ እና በ2015 ዓ.ም የሚጀመሩ የድህረ ምረቃ የትምህርት ፕሮግራሞች ዝርዝር:°°°°°°°°°°°°°°°°°°...
25/07/2022

#ጠቃሚ መረጃ‼

በዩኒቨርሲቲው መማክርት ጉባኤ (ሴኔት) በ2014 ዓ.ም አዲስ የጸደቁ እና በ2015 ዓ.ም የሚጀመሩ የድህረ ምረቃ የትምህርት ፕሮግራሞች ዝርዝር:

°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

መማክርት ጉባኤው ካጸደቃቸው 22 አዳዲስ የድህረ ምረቃ የትምህርት ፕሮግራሞች 4ቱ የፒ.ኤች.ዲ እና 18ቱ የማስትሬት ድግሪ የትምህርት ፕሮግራሞች ናቸው።

እነሆ ዝርዝር ፕሮግራሞቹን ይመልከቷቸው👇

1. Ph.D. in Agronomy

2.Ph.D. in Horticulture (with streams)

3. Ph.D. in Soil Science (with streams)

4. Ph.D.in Animal Production (with
streams)

5. Master of Arts Degree in Marketing Management

6. Master of Arts Degree in Project Management

7. MSc in Chemistry (Organic Chemistry and Inorganic chemistry)

8. MSc in Mathematics (Mathematical Modeling,Numerical Analysis, and Fluid Dynamics)

9. Master of Science in Environmental Science

10. M.Sc. in Biostatistics

11. MA in Linguistics

12. MA in Literature in English

13. M.Sc. in Artificial Intelligence

14.M.Sc. in Computer Science

15. MSc in Urban planning and Development

16. MA in Adult Education and Community Development

17. MA in Social Psychology

18. MSc in Plant Protection

19. MSc in Sustainable Forest and Nature Management

20. Masters of Public Health in Health System Management

21. M.Sc. in Geotechnical Engineering

22. Master of Science in Botanical Sciences

ኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃን ይዛ ውድድሩ ተጠናቋል!!!======ኢትዮጵያ 10 ሜዳሊያ በማግኘት ውድድሩን አጠናቃለች። ከተገኘው 10 ሜዳሊያ ሰባቱ በሴቶች የተገኘ ነው፤ የቀረው 3 ሜዳሊያ ደግሞ በወ...
25/07/2022

ኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃን ይዛ ውድድሩ ተጠናቋል!!!
======
ኢትዮጵያ 10 ሜዳሊያ በማግኘት ውድድሩን አጠናቃለች። ከተገኘው 10 ሜዳሊያ ሰባቱ በሴቶች የተገኘ ነው፤ የቀረው 3 ሜዳሊያ ደግሞ በወንዶች የተገኘ ነው።

በዛሬው ንጋት የ5 ሺህ ሜትር ውጤት አልተገኘም። ምክንያቱም አልተጠበቀም።

_ዩሚፍ ቀጀልቻ 8ኛ
_ ሰለሞን ባረጋ 12ኛ
_ ሙክታር እድሪስ 13ኛ ሆነው አጠናቀዋል።

በ800 ሜትር የሴቶች ፍፃሜ ብቸኛዋ የሀገራችን ተወካይ ድርቤ ወልተጂ አራተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።

ወርቅ 🥇

🇪🇹 ለተሰንበት ግደይ
🇪🇹 ጉዳፍ ፀጋይ
🇪🇹 ጎተይቶም ገ/ስላሴ
🇪🇹 ታምራት ቶላ

ብር🥈

🇪🇹 ወርቅውሀ ጌታቸው
🇪🇹 ሞስነት ገረመው
🇪🇹 ለሜቻ ግርማ
🇪🇹 ጉዳፍ ፀጋይ

ነሐስ🥉

🇪🇹 ዳዊት ስዩም
🇪🇹 መቅደስ አበበ

አጠቃላይ
🇪🇹 10 ሜዳሊያ፥ ደረጃ ሁለተኛ!!!

በድጋሚ እኳን ደስ አለን💚💛❤️ በኦሪገን ያለም አትሌቲክ ሻፒዮኑን 5ሽ ሜትር ፍጻሜ ውድድር ✔️ጉዳፍ ጸጋዬ  ወርቅ✔️ዳዊት ስዩም የነሀስ ሚዳሊያ  ለኢትዮጵያ 💚💛❤አስገኝተዋል ።
24/07/2022

በድጋሚ እኳን ደስ አለን💚💛❤️
በኦሪገን ያለም አትሌቲክ ሻፒዮኑን 5ሽ ሜትር ፍጻሜ ውድድር
✔️ጉዳፍ ጸጋዬ ወርቅ
✔️ዳዊት ስዩም የነሀስ ሚዳሊያ ለኢትዮጵያ 💚💛❤አስገኝተዋል ።

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች  #በመደበኛው  #በተከታታይ #በማታው ፕሮግራም  ሲያሰለጥናቸው የነበሩ ተማሪዎችን በዋናው ግቢ አሁን እያስመረቀ ይገኛል!💐💐💐ውድ ተመራቂ...
23/07/2022

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች
#በመደበኛው
#በተከታታይ
#በማታው
ፕሮግራም

ሲያሰለጥናቸው የነበሩ ተማሪዎችን በዋናው ግቢ አሁን እያስመረቀ ይገኛል!💐💐💐
ውድ ተመራቂ ተማሪዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ!💐💐💐💐

ማስታወቂያ የትርፍ ሰዓት ሥራ ፈላጊዎች በሙሉ፦
22/07/2022

ማስታወቂያ
የትርፍ ሰዓት ሥራ ፈላጊዎች በሙሉ፦

The marathon belongs to Ethiopia! 🇪🇹Gotytom Gebreslase is the world marathon champion!She breaks the   championship reco...
18/07/2022

The marathon belongs to Ethiopia! 🇪🇹

Gotytom Gebreslase is the world marathon champion!

She breaks the championship record clocking 2:18:11 to win 🥇 – much to the delight of the roaring crowds in Eugene!

✅Ethiopia 💚💛❤has officially the 2nd medal table from Top 5 conversation
18/07/2022

✅Ethiopia 💚💛❤has officially the 2nd medal table from Top 5 conversation

አትሌት ታምራት ቶላ የአለም ሻፒዮናን እሪከርድ በመስበር በማራቶን የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ ሆኗል።እንኳን ደስአላችሁ
17/07/2022

አትሌት ታምራት ቶላ የአለም ሻፒዮናን እሪከርድ በመስበር በማራቶን የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ ሆኗል።
እንኳን ደስአላችሁ

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ 2891 ተማሪዎችን በደማቅ ሥነስርዓት አስመረቀ።************************ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በድህረ ምረቃ፣ በቅ...
17/07/2022

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ 2891 ተማሪዎችን በደማቅ ሥነስርዓት አስመረቀ።
************************
ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በድህረ ምረቃ፣ በቅድመ ምረቃ እና ዲፕሎማ ፕሮግራሞች ያሰለጠናቸውን 2891 ተማሪዎች ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ሐምሌ 10/2014 ዓ.ም በደማቅ ሥነስርዓት አስመርቋል።

የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ብርሃነመስቀል ጠና ለዕለቱ ተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ባሰሙበት ንግግራቸው፣ ነባሩ እና አንጋፋው ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ፣ በማታና በተከታታይ የዲፕሎማ፣ የዲግሪ እና የማስትሬት መርሐግብሮች ትምህርታቸውን በሚገባ አጠናቀው፣ አስፈላጊውን የምረቃ መስፈርት አሟልተው በዛሬው ዕለት ለምረቃ የበቁት የ2014 ዓ.ም ተመራቂዎች 2891 መሆናቸውን ተናግረዋል። ከነዚህም ተመራቂዎች መካከል ወንድ 1409፣ ሴት ደግሞ 1482 ሲሆኑ፣ ይህም የሴት ተመራቂዎች ቁጥር ብልጫ ያለው መሆኑንና ዩኒቨርሲቲውም ለሴቶች ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጥ ያሳያል ሲሉ ዶክተር ብርሃነመስቀል ተናግረዋል። በመጨረሻም ፕሬዝዳንቱ የዕለቱ ተመራቂዎች በዩኒቨርሲቲው አዲሱ ስያሜ፣ ተልዕኮ፣ ሎጎ እና ህብረ ዝማሬ በመመረቃቸው የተቋሙ ታሪክ አካል እንደሚያደርጋቸው አስገንዝበዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር እና የዕለቱ የክብር እንግዳ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአዲስ መልክ እየተዋቀረ ያለው ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሀገሪቱን የትምህርት ችግሮች ለመቅረፍ በከፍተኛ ደረጃ ኃላፊነት የተጣለበት በመሆኑ፣ ይህንን ልዩ ተልዕኮውን ለመወጣት በሚያደርገው ጥረትም የትምህርት ሚኒስቴር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግለት ገልጸዋል።
በሥነስርዓቱ ላይም በትምህርታቸው ብልጫ ላሳዩ ተመራቂዎች የዋንጫ እና ሌሎች ሽልማቶች ተሰጥቷቸዋል። እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው የሽግግር ወቅት ልዩ ልዩ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላትም የዕውቅና ምስክር ወረቀትና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

በድጋሚ የወጣ ማስታወቂያ ለክረምት ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ======================የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በክረምት ፕሮግራም በመጀመሪያ ዲግሪ፤ በ...
17/07/2022

በድጋሚ የወጣ ማስታወቂያ ለክረምት ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
======================
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በክረምት ፕሮግራም በመጀመሪያ ዲግሪ፤ በሁለተኛ ዲግሪ እና በPGDT ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ከሰኔ 15 ቀን 2014 ዓ/ም አስከ ሐምሌ 10 ቀን 2014 ዓ/ም ድረስ የምዝገባ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ የመመዝገቢያ ጊዜውን ለተወሰኑ ቀናት ማራዘም በማስፈለጉ ከዚህ በፊት በማስታወቂያው የተገለጹ መስፈርቶችን የምታሟሉ አመልካቾች እስከ ሐምሌ 22 ቀን 2014 ዓ/ም ድረስ የተራዘመ ስለሆነ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እያስታወቅን የምታመለክቱባቸውን የትምህርት መስኮች ዝርዝር ከዩንቨርስቲው ሬጅስትራር ድረ-ገጽ https://bdu.edu.et/registrar/ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ
ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት

17/07/2022

ወድ የዩንቨርስቲ ተመራቂወች
እኳን ደስ አላችሁ።
✔✔የሰራችሁትን ፕሮጀክትና ጥናታዊ ፅሁፍ በአጭሩ ሳቢና ማራኪ በማድረግ ቀርጻችሁ አጋሩንና እፓሰርድ በመሆን ህልማችሁን እውን አድርጉ።

"እጅ አልባው ባለ ብዙ እጆች...‼️"ተፈጥሮ ሁለት እጅ አልሰጠችውም። ክንድም ነፍጋዋለች፣ ከጫንቃ በስተቀር። ጫንቃው ብዙ መከራን ተሸከመለት። ግን እሱ ሁለት አይደለም፣ ብዙ እጆችን ፈጠረ።...
17/07/2022

"እጅ አልባው ባለ ብዙ እጆች...‼️"

ተፈጥሮ ሁለት እጅ አልሰጠችውም። ክንድም ነፍጋዋለች፣ ከጫንቃ በስተቀር። ጫንቃው ብዙ መከራን ተሸከመለት። ግን እሱ ሁለት አይደለም፣ ብዙ እጆችን ፈጠረ። በፈጠራቸው እጆች የኮምፒውተር ሳይንስ ባለሙያ ሆነ። ወላጅ አልባ መሆን ፈተነው እንጂ ከህልሙ አላስቀረውም። እጅ አልባ መሆን በኮምፒተር ሳይንስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በዲግሪ ለመመረቅ አላገደውም። መቸገር፣ አስቸገረው እንጂ ታግሎ አልጣለውም።

ግርማ! ከአራት አመት በፊት ከወንድሜ ጋር ቤቴ መጣ። ተዋወቅን። ወንድሜ ሆነ። ተፈጥሮን ያሸነፈበት ሚስጢር ገረመኝ። የስልክና የኮምፒውተር ኪቦርዶችን የሚነካካበት ፍጥነት አጀብ አሰኘኝ። ለካስ ይቻላል። ለካስ የመቻል አቅም ያለው "አእምሮ" ውስጥ ነው። ለካስ አአምሮ ካልሰራ እጅና እግር ትርፍ ነገር ነው።

በህይወት ዘመኔ "አይዞህ! በርታ!" ልለው ያልቻልሁት ሰው ግርማ ነው። ምንስ ብዬ አይዞህ ልበለው? ምን ብዬ በርታ ልበለው? ቤቴ በመጣ ቁጥር፣ ባገኘሁት ቁጥር፣ ቁጭ ብለን ሻይ በጠጣን ቁጥር የምበረታው እኔ ነኝ። የምታደሰው እኔ ነኝ። ኃይል የማገኘው እኔ ነኝ። ተፈጥሮንም ራሱንም ያሸነፈን ሰው ምን ብለህ አይዞህ ትለዋለህ?

ትናንት ተመረቀ። "ተመረቀ" የሚለው ቃል ለእሱ በቂ ገላጭ ቃል አይደለም። አንድ ዲግሪም ለእሱ በቂ አይደለም።
በውሃው ውስጥ ራሱን እያዬ ነው። "ልጅነቱን፣ ዛሬውንና ነገውን የሚያይ ይመስለኛል"... ስለመጣበት የችግር መንገድ ሳይሆን፣ ስለ ነገ ህልሙ አዘውትሮ ያወራል። እያንዳንዱ ሰው መፅሐፍ ነው። ይህ ሰው ግን ለትውልዱ ትልቅ መፅሐፍ ነው። አንድ የአፍሪካ ሀገር ውስጥ በቴኳንዶ ተወዳድሮ ውጤት ማምጣቱን ብነግራችሁስ አትገረሙም?

ይሄን ዲግሪ ለመጨረስ ያጋጠሙት አሳዛኝ፣ አዝናኝና አስገራሚ ገጠመኞች በራሱ አንድ መፅሐፍ ይወጣቸዋል።
ወንድሜ ግርማ እንኳን ደስ አለህ❤
ደስ ብሎኛል! ከግርማ ጎን የነበራችሁ ሁሉ ክብር ይግባችሁ!ያሰብኸው እንዲሳካ ሁሌም ከጎንህ አለሁ‼️

Via

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Universthiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share