አቢሲኒያ የመገናኛ ብዙኃን ሽልማት

  • Home
  • አቢሲኒያ የመገናኛ ብዙኃን ሽልማት

አቢሲኒያ የመገናኛ ብዙኃን ሽልማት Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from አቢሲኒያ የመገናኛ ብዙኃን ሽልማት, Media/News Company, .

 #2009
30/12/2023

#2009

የአቢሲኒያ ሽልማት አሰጣጥ መርሐ ግብርአለምንና ህዝቦቿን የሚታደግ ስራ ለሰሩ ትጉሃን የተሰጠ እውቅናና ሽልማትበሚከተሉት የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከተሉን፡፡Facebook - https://www.facebook....

https://youtu.be/VGVu-2FXmeI?si=KpRbA588aIrDfpRb
25/12/2023

https://youtu.be/VGVu-2FXmeI?si=KpRbA588aIrDfpRb

የአቢሲኒያ ሽልማት አሰጣጥ መርሐ ግብርአለምንና ህዝቦቿን የሚታደግ ስራ ለሰሩ ትጉሃን የተሰጠ እውቅናና ሽልማትበሚከተሉት የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከተሉን፡፡Facebook - https://www.facebook....

https://youtu.be/_WjlifYhoWQ?si=u-zN4uiqv4BqmIED
25/12/2023

https://youtu.be/_WjlifYhoWQ?si=u-zN4uiqv4BqmIED

የአቢሲኒያ ሽልማት አሰጣጥ መርሐ ግብርአለምንና ህዝቦቿን የሚታደግ ስራ ለሰሩ ትጉሃን የተሰጠ እውቅናና ሽልማትበሚከተሉት የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከተሉን፡፡Facebook - https://www.facebook....

26/11/2023

ከ1996-2016 ዓ.ም
የ20 ዓመታት ክብረ በዓል

https://www.youtube.com/
24/09/2023

https://www.youtube.com/

እንኳን ወደ ቀጭኔ ቲዩብ በሰላም መጡ በዚህ ቻናል አዝናኝ እና አስተማሪ ፊልሞች፣ ተከታታይ ድራማዎች፣ ግጥሞች ትረካ እንዲሁም ትምህርታዊ ቪዲዎዎችን ያገኛሉ አዲስ ከሆኑ ሰብስክራይብ ....

አቢሲኒያ ሽልማት የከፍተኛ ክብር የኢንደስትሪ ሽልማት መጋቢት 24 እና ሚያዝያ 1 ቀን በድምቀት ይሸልማል። ይህ ሽልማት በሀገራችን የኢንደስትሪ ታሪክ ትልቅ መልክ እንዲኖረው ላለፉት አምስት ...
29/03/2023

አቢሲኒያ ሽልማት የከፍተኛ ክብር የኢንደስትሪ ሽልማት መጋቢት 24 እና ሚያዝያ 1 ቀን በድምቀት ይሸልማል። ይህ ሽልማት በሀገራችን የኢንደስትሪ ታሪክ ትልቅ መልክ እንዲኖረው ላለፉት አምስት አመታት አብራችሁን ስትሠሩ የቆያችሁትን ሁሉ እናመሰግናለን። ዝግጅቱ በባላገሩና በዋልታ ቴሌቪዢኖች በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል። የጥሪ ካርዶችን በተገቢ መልኩ ያሰራጨን ቢሆንም በተለያየ ምክንያት ያለደረስንላችሁ ተቋማትና ግለሠቦች የጥሪ ካርዱን እንደፕሮቶኮላችሁ የምንልክና የምንሠጣችሁ በመሆኑ እንድትደውሉልን ስንል በትህትና እናሳውቃለን። በዝግጅቱ ላይ መታደም የምትሹ በስልክ ቁጥር0911-52 59 98 ደውላችሁ ቢሮ በመቅረብ የጥሪ ካርድ እንድትወስዱ እንጋብዛለን። ኑና ስለ ልማት ስለ ለውጥ እናውራ። ለሀገር የሠሩ ተቋማትንና ሠራተኞችን እናመስግን።
ትጉኃንን እንሸልማለን!
አቢሲኒያ የከፍተኛ ክብር ሽልማት
እና
አቢሲኒያ የጥራት ሽልማት

25/02/2023

የአቢሲኒያ ሽልማት አጭር ፕሮፋይል
አቢሲኒያ ሽልማት በዋና ምዝገባ ቁጥር MT/AA/2/0007938/2004 በፈቃድ ቁጥር BL/AA/14/668/636589/2009 በቀን 19/05/2009 ዓ.ም. የመደበኛ ሽልማቶች ፈቃድ አግኝቶ በመስራት ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡ በተጨማሪም በተጨማሪም አቢሲኒያ የጥራት ሽልማት በዋና ምዝገባ ቁጥር MT/AA/2/0049077/2011 በፈቃድ ቁጥር BL/AA/14/673/1673080/2014 በቀን 09/06/2014 ዓ.ም. እና በዋና ምዝገባ ቁጥር BL/AA/2/0031409/2015 በቀን 15/03/2015 ዓ.ም. በፈቃድ ቁጥር BL/AA/14/673/4199503/2015 በቀን 21/03/2015 ዓ.ም. የጥራት ሽልማት ፈቃድ አግኝቶ በመስራት ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡
ድርጅታችን በአለም ላይ የላቀ ስራ ለሰሩ ትጉኃን ሽልማት ፣ ማበረታቻና እውቅና ለመስጠት የተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡ ይህንንም ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለመስራት 1986 ገፅ ያለው የመደበኛ ሽልማት የመሸለሚያ ሰነድ ሳይንሳዊ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ አዘጋጅቷል፡፡ የጥራት ሽልማት የመለኪያ ሰነዱን በአለም ላይ ስመጥር የጥራት ሽልማት መለኪያ ያላቸውን ታላላቅ ተቋማት አሰራር መነሻ በማድረግና ለሀገራችን ተቋማት የሚመጥንና የሚጠቅም መለኪያ ሰነድና የጥራት አዘጋጅቷል፡፡ የድርጅታችን የጥራት ሽልማት የጥራት መለኪያ ሞዴል በዘርፉ በሀገራችንና በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ልምድ ፣ ተሞክሮና ተዛማጅ የትምህርት ዝግጅት ባላቸው ሙያተኞች የተዘጋጀ ሲሆን በልዩነትም ከእንግሊዝኛ ቋንቋ ጎን ለጎን በአማርኛ ፣ በኦሮምኛና በትግርኛ ቋንቋዎች ጭምር የተዘጋጀ ነው፡፡ በቀጣይም በሌሎች ቋንቋዎች ጭምር በማዘጋጀት የጥራት መለኪያዎች አገልግሎት ሰጪም ሆነ ለአምራች ተቋማት ቅርብ እንዲሆኑ በትጋት እንሰራለን፡፡ የዘርፉ አሰሰሮችና ዳኞችም አለም አቀፍ የአሰሰርነት ሰርቲፊኬት ያላቸውና ተዛማጅነት ያላቸው የትምህርት ዝግጅት ያላቸው ናቸው፡፡
የሽልማት ድርጅታችን 144 የምክር ቤት አባላት እና 600 የዳኞች ህብረት እንዲኖረው ተደርጎ የተዋቀረ ነው፡፡ በትምህርት ዝግጅታቸው እና ኃላፊነት የመሸከም ብቃታቸው አንቱ የተባሉ 9 የቦርድ አባላት አሉት፡፡ የቀድሞ የኢፌዴሪ መንግስት ፕሬዝዳንት ሎሬት ግርማ ወልደጊዮርጊስ እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. የሽልማት ድርጅቱ የበላይ ጠባቂና የምስረታው ባለውለታ ነበሩ፡፡
የሽልማት ድርጅታችን "ዓለምንና ህዝቦቿን የሚታደግ የላቀ ስራ ለሰሩ ትጉኃን እንሸልማለን" በሚል መሪ ቃል ላይ በመመስረት በግለሰብ ደረጃ ፣ በህብረትና በተቋማት ደረጃ የተሰሩ ስራዎችን በመመዘን የሚሸልም ተቋም ነው፡፡ ዓላማውም "የላቀ ስራ ለሰሩና ዘመናዊ የአሰራር ስርአት ለሚከተሉ ተቋማት በመሸለም ጥራት ያለው ምርት እና አገልግሎት ለማህበረሰብ የሚያቀርቡ ሙያተኞች እና ተቋማት በመፍጠር ሀገራችንን ሁለንተናዊ ስልጣኔና እድገት እንድታመጣ ማድረግ ነው፡፡"የሽልማት ድርጅቱ መዋቅር በሚፈቅደው መሰረት የብቃት ሽልማት የከፍተኛ ክብር ሽልማት HIGHER HONOR LAUREATE AWARD እና የጥራት ስራ አመራር ሽልማት QUALITY MANAGEMENT AWARD እንሸልማለን፡፡ በመደበኛ ሽልማት መስኮች በየደረጃው 1ኛ. የከፍተኛ ክብር የላቀ የወርቅ ኮርዶን ኒሻን ከነፕላኩ ፣ 2ኛ. የከፍተኛ ክብር የወርቅ ኒሻን ፣ 3ኛ. የከፍተኛ ክብር የብር ኒሻን ፣ 4ኛ. የከፍተኛ ክብር የነሐስ ኒሻን ፣ 5ኛ. ዋንጫ ፣ 6ኛ. የሜዳሊያ 7ኛ. የክብር ዲፕሎማ እንሸልማለን፡፡ በጥራት ሽልማት ተቋማት ለጥራት ሽልማት ብቁ መሀናቸው ከሚለካበት ደረጃ ጀምሮ በሚያገኙት ውጤት መሰረት የተሸላሚነት ደረጃ ውስጥ የሚገቡት የወርቅ ደረጃ የጥራት ሽልማት /GOLD LEVEL QUALITY AWARD/ ፣ የፕላቲንየም ደረጃ የጥራት ሽልማተ/PLATINUM LEVEL QUALITY AWARD/ እና የዳይመንድ ደረጃ የጥራት ሽልማት /DIAMOND LEVEL QUALITY AWARD/ ደረጃ የጥራት ዋንጫና ዲፕሎማ እንሸልማለን፡፡ የጥራት ሽልማት ዋና ግብ ከሽልማት ባሻገር ተቋማት አለም ከደረሰበት ዘመናዊ የስራ አመራር ሳይንስ ጋር ማስተዋወቅ በመሆኑ ተቋማት በሚኖራቸው ወቅታዊ ቁመና ላይ በመመስረት ግብረመልሶችን አዘጋጅተን እንሰጣለን፡፡ በድርጅታችን አሰራር መሰረት የትኛውም ተቋም ከየትኛውም ተቋም ጋር አይወዳደርም፡፡ ተቋማትን በጥራት መለኪያ መስፈርቱ ተለክተው በሚያገኙት ውጤት ተሸላሚ ይሆናሉ፡፡
አበሲኒያ ሽልማት በመደበኛ ሽልማት ስር 48 ትጉኃንን የከፍተኛ ክብር ሽልማት በተከታታይ ሸልመናል፡፡ ከተሸለሙት መሀከልም ሎሬት ካፒቴን ሽመልስ ከበደ ፣ ሎሬት ሰዓሊ ለማ ጉያ (የክብር ዶ/ር) ፣ ሎሬት ሙላቱ አስታጥቄ (የክብር ዶ/ር) ፣ ሎሬት ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ ፣ ሎሬት ዶ/ር በላይ አበጋዝ ፣ ሎሬት ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ፣ ሎሬት ታማኝ በየነ ፣ ሎሬት ተወልደ ገብረማሪያም ፣ ሎሬት ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌታሁን ፣ ሎሬት ዶ/ር ሰለሞን በላይ ፣ ሎሬት ታምሩ ወንድማገኘሁ ፣ ሎሬት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ፣ ሎሬት ሰውነት ቢሻው ፣ ሎሬት ዶ/ር ጌታቸው ትኩበት ፣ ሎሬት ዶ/ር ሰለሞን ቢኖር ፣ ሎሬት አለሙ መኮንን ፣ ሎሬት ዶ/ር አለማየሁ ተፈራ ፣ ሎሬት ዶ/ር አብይ አህመድ ፣ ሎሬት መስፍን ጣሰው እና ሌሎችም ነበሩ፡፡ ከ2009 ዓ.ም. ጀምሮ በነበረ የተቋማት ሽልማጽ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶችን ፣ የትምህርት ተቋማትን እና የመንግስት አስተዳደር ፅ/ቤቶችን ሸልመናል፡፡ ከነዚህ ተቋማት መሀከልም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነበር፡፡
ድርጅታችን ከ2009 ዓም ጀምሮ ማጣሪያ ሲሰራላቸው የቆዩና ለሀገራችን የላቀ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ተቋማትን መጋቢት 24 ቀን የከፍተኛ ክብር ዋንጫና ዲፕሎማ ሊሸልም ተዘጋጅቷል፡፡ በልዩነት በምናተወቅበት የሽልማት ይዘትም የአንድ ተቋም መሸለም መሰረቱ የድርጅቱ ሰራተኞች በመሆናቸው ሁለት ከፍተኛ የተሸላሚ ድርጅቶች የስራ መሪዎችን የወርቅ ኒሻንና ዲፕሎማ ፣ ሶስት መሀከለኛ አመራሮችን የወርቅ ሜዳሊያናዲፕሎማ እና ለሰባት ሰራተኞቻቸው ደግሞ የወርቅ ሜዳሊያና ዲፕሎማ ለመሸለም ተዘጋጅተናል፡፡
ሀገር ቆማ የምትታየው በትጉኃን ነው፡፡ ትጉኃንን መሸለም ደግሞ የድርጅታችን ግዴታ ነው፡፡ ድርጅታችን በቀጣይም በአሁኑ ሽልማት የተካተቱ ድርጅቶችን በሙሉ በጥራት ሽልማት ስርአት ውስጥ አሰገብቶ አብሮ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ በድርጅታችን አሰራር መሰረትም ለመደበኛ ሽልማት ይበቃሉ የምትሉትን ለሀገር የላቀ የሰሩትን እንድትጠኩሙ ስንጋብዝ በተቋም ደረጃ የጥራት ስርአታችን ውስጥ መግባት የምትፈልጉ ተቋማት ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ እንጋብዛለን፡፡
አድራሻ፡- ቦሌ መድኃኒያለም ኦሮሚያ ህንጻ 2ኛ ፎቅ!
ስልክ 0911-248368 / 0911-242388 /
Email. [email protected]
የፖስታ ሳ ቁ 13981
ትጉኃንን እንሸልማለን!

04/09/2022

/2015

06/08/2022


አቢሲኒያ የሽልማት ድርጅት ከመደበኛ ሽልማት በተጨማሪ የጥራት ሽልማት ድርጅት ከፍቷል።
ይህንኑ መሠረት በማድረግ አለም አቀፍ የጥራት ሽልማት ደረጃን መሠረት በማድረግ አዲስ ሎጎ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት:-
1. የጥራት ምንነትን የሚያሳይ
2. የዘመኑን የዲዛን ደረጃ የጠበቀ
3. የስነ-ውበታዊ አላባዊያንን የጠበቀ
4. አለም አቀፋዊነት ያለው
5. እድገትን ጠቋሚ
6. ኢንደስትሪና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን የሚደርስ
7. በወርቅማ ቀለም ላይ የተመሠረተ
በዚሁ መሠረት መወዳደር የምትሹ እስከ ነሐሴ 10 ቀን 2014 ዓም ስራችሁን እንድታቀርቡ እናስታውቃለን።
+251911248368
አቢሲኒያ ሽልማት
ትጉኃንን እንሸልማለን!

25/07/2022

#በከፍተኛ ጥናትና ዝግጅት ስንደክምበት የነበረው የከፍተኛ ክብር ሎሬቶች ሽልማት ነሐሴ 29 ቀን እንሸልማለን!
#የኢንደስትሪ ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሽልማት ነሐሴ 15 ቀን እንሸልማለን!
#የኪነ-ጥበብ ሙያተኞችና ተቋማት ፣ የመገናኛ ብዙኃን ሙያተኞችና ተቋማት እና የባህል ሙያተኞችና ተቋማት ሽልማት ነሐሴ 8 ቀን እንሸልማለን!

28/02/2022
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 #የሽልማት ድርጅት ብራንድ ሞዴል            በድጋሜ የወጣ!Abyssinia international award🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖የስራ መደበኛ:- የሽልማት ድርጅት ብራንድ ...
24/10/2021

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
#የሽልማት ድርጅት ብራንድ ሞዴል
በድጋሜ የወጣ!
Abyssinia international award
🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖
የስራ መደበኛ:- የሽልማት ድርጅት ብራንድ ሞዴል!
👉 ቁመት:-ከ1.70 በላይ
👉 እድሜ:- ከ28-36
👉 መልካም ስነ-ምግባር ያላት
👉 በአመት ሽልማት በሚካሔድባቸው
ቀናት መገኘት የምትችል
👉 የቢልቀርድና የማስታወቂያ ስራዎችን
በነፃ መስራት የምትችል!
👉 በሀገር ውስጥም በውጪ ሀገር
ለስራ የምትችል
👉 ፖስፖርት ያላት/የምታወጣ
👉 መደበኛ ስራ ጀርባ የምትሠራ ሲሆን
ደሞዝ በወር:- 8,500 ብር
👉 የተስተካከለ የአካል ቁመና ያላት
👉 አልባሳት እና መዋቢያ ድርጅቱ ይሸፍናል!
👉 ህጋዊ ውል መዋዋል የምትችል!
👉 ለመስራት የምትፈልጉ ከታች ያሉትን
በቅደም ተከተል ላኩ:-
👉 ሙሉ ስም እስከ አያት
በአማርኛና በእንግሊዝኛ ላኩ
👉 እድሜ
👉 ቁመት
👉 ክብደት
👉 ፎቶግራፎች
👉 ስራ
👉 የመኖሪያ አድራሻ
ከላይ ያሉትን በቅደም ተከተል እስከ
ጥቅምት 17 ቀን 2014ዓም ላኩ።
🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖
"ዓለምንና ህዝቦቿን የሚታደግ የላቀ ስራ
ለሠሩ ትጉኃን እንሸልማለን!"
🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖
የቴሌግራም መላኪያ ስልክ
+251905-030000
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
መልካም ልብ ያላችሁ ሁሉ
ለሌሎች ሼር አድርጉልን!
https://t.me/Abyssiniainternationalaward

Address


Telephone

+251912644708

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አቢሲኒያ የመገናኛ ብዙኃን ሽልማት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to አቢሲኒያ የመገናኛ ብዙኃን ሽልማት:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share