ᴀʜʟᴀᴛ ᴍᴇᴅɪᴀ

ᴀʜʟᴀᴛ ᴍᴇᴅɪᴀ ABDUKE MEDIA # VIDEO EDITING TUTORIAL INFO

አረ ለመሆኑ Domain name ምን ይሁን ? 🤔🤔🤔ሶፍትዌር ወይም ድህረ ገጽን ለማግኘት የሚያገለግል የቁጥር (IP) አይፒ አድራሻ የሚይዝ የጽሑፍ ሕብር ነው። የጎራ ስም ማለት አንድ ተጠቃሚ...
12/05/2022

አረ ለመሆኑ Domain name ምን ይሁን ?
🤔🤔🤔
ሶፍትዌር ወይም ድህረ ገጽን ለማግኘት የሚያገለግል የቁጥር (IP) አይፒ አድራሻ የሚይዝ የጽሑፍ ሕብር ነው። የጎራ ስም ማለት አንድ ተጠቃሚ የተወሰነ ድረ-ገጽ ላይ ለመድረስ ወይም ለመጎብኘት የሚተይበው ጽሑፍ ነው። ለምሳሌ የጉግል ጎግል ስም 'google.com' ነው።

ትክክለኛው የድረ-ገጽ አድራሻ ውስብስብ አሃዛዊ አይፒ IP አድራሻ ነው (ለምሳሌ 103.21.244.0) ግን ለዲ ኤን ኤስ ምስጋና ይግባውና ተጠቃሚዎች ለሰዎች ተስማሚ የሆኑ የጎራ ስሞችን አስገብተው ወደ ሚፈልጉዋቸው ድረ-ገጾች እንዲሄዱ ማድረግ ችለዋል። ይህ ሂደት ዲ ኤን ኤስ (DNS) ፍለጋ በመባል ይታወቃል።

የጎራ ስሞችን ማን ያስተዳድራል?

የጎራ ስሞች ሁሉም የሚተዳደሩት በጎራ መዝገብ ቤቶች ነው፣ ይህም የጎራ ስሞችን ማስያዝን ለመዝጋቢዎች በውክልና ይሰጣል። ድህረ ገጽ መፍጠር የሚፈልግ ማንኛውም ሰው የዶሜይን ስም በመዝጋቢ ማስመዝገብ የሚችል ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ከ300 ሚሊዮን በላይ የተመዘገቡ የጎራ ስሞች ወይም domain name አሉ።

በጎራ ስም እና url መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

አንድ ወጥ የሆነ የመረጃ ምንጭ url (ዩአርኤል) ፣ አንዳንድ ጊዜ የድር አድራሻ ተብሎ የሚጠራው፣ የጣቢያውን ስም እና ሌሎች መረጃዎችን ፣ የማስተላለፊያ ፕሮቶኮሉን እና መንገዱን ያካትታል። ለምሳሌ፣ በዩአርኤል 'https:gawtechnology.com./ውስጥ 'gawtechnology.com' የጎራ ስም ሲሆን 'https' ደግሞ ፕሮቶኮል እና '/learning/' ወደ አንድ የተወሰነ ገጽ የሚወስደው መንገድ ነው። ድር ጣቢያው.

የጎራ ስም ክፍሎች ምንድናቸው?

የጎራ ስሞች በተለምዶ በሁለት ወይም በሦስት ክፍሎች የተከፋፈሉ ሲሆን እያንዳንዳቸው በነጥብ ይለያያሉ።
ከቀኝ-ወደ-ግራ ሲነበቡ፣ በጎራ ስሞች ውስጥ ያሉት ለዪዎች ከአብዛኛዎቹ አጠቃላይ ወደ ልዩ ናቸው። በጎራ ስም ከመጨረሻው ነጥብ በስተቀኝ ያለው ክፍል ከፍተኛ ደረጃ ጎራ (TLD) ነው። እነዚህ እንደ ‘.com’፣ ‘.net’ እና ‘.org’ ያሉ ‘አጠቃላይ’ TLDዎችን፣ እንዲሁም እንደ ‘.uk’ እና ‘.jp’ ያሉ አገር-ተኮር TLDዎችን ያካትታሉ።

ከTLD በስተግራ የሁለተኛ ደረጃ ጎራ (2LD) ነው እና ከ 2LD በግራ በኩል የሆነ ነገር ካለ የሶስተኛ ደረጃ ጎራ (3LD) ይባላል።

Search the world's information, including webpages, images, videos and more. Google has many special features to help you find exactly what you're looking for.

በሞባይል ስልክ የምንለዋወጣቸው ቴክስት ሜሴጆች እነዴት መደበቅ እንደሚቻል ልጠቁማችሁበሞባይል ስልካችን የምንለዋወጣቸው ቴክስት መልዕክቶች ሌላ ሰው እንዲያይብን አንፈልግም ፡፡ ምክንያቱም ሁላ...
21/09/2021

በሞባይል ስልክ የምንለዋወጣቸው ቴክስት ሜሴጆች እነዴት መደበቅ እንደሚቻል ልጠቁማችሁ

በሞባይል ስልካችን የምንለዋወጣቸው ቴክስት መልዕክቶች ሌላ ሰው እንዲያይብን አንፈልግም ፡፡ ምክንያቱም ሁላችንም የራሳችን ሚስጥር ስላለን፡፡

ስለዚህ የምንለዋወጣቸው ቴክስት ሜሴጆች ሌላ ሰው እንዳያይብን እንዴት በደበቅ እንደምንችል ልንገራችሁ፡፡

1ኛ SMS Lock app የሚል አፕሊኬሽን ከፕሌይስቶር ላይ ዳውንሎድ ማድረግ፡፡

አፕሊኬሽኑን ዳውንሎድ ለማድረግ ይህንን ሊንከ መጠቀም ትችላላችሁ፦
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.thinkyeah.smslocker

2ኛ አፕሊኬሽኑ ዳውንሎድ አድርጎ ሲጨርስ አስነሱት፣

3ኛ አፕሊኬሽኑ ከተነሳ በኋላ ለቴክስት የምትጠቀሙዋቸው ዝርዝር የሜሴጅ አፖች ይመጣሉ፡፡

አፕሊኬሽኑ አናት ላይ ክብ በተን ታገኛላችሁ፡፡ ከዚህ ክብ በተን ስር “ Tab above to Enable Lock” የሚል ፁሁፍ ታገኛላችሁ፡፡ ስለዚህ ክብ በተኑን ታፕ(ክሊክ) ማድረግ፣

4ኛ ክብ በተኑን ታፕ(ክሊክ) ስታደርጉ ፓስዎርድ በፓተርን መልክ እንድታስገቡ ይጠይቃችኋል፡፡ ስለዚህ የፈለጋችሁትን ፓስዎርድ በፓተርን መልክ ታስገባላችሁ፡፡

በቃ፡፡አለቀ፡፡ ካሁን በኋላ በሞባይል ስልካችሁ የምትለዋወጧቸው ቴክስት መልዕክቶች ከናንተ ውጪ ሌላ ሰው ማየት አይችልም።

28/08/2021

⚡️10 ጠቃሚ የሆኑ አፖች እንጠቁማቹ!
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

1.➡ ትሩኮለር/True Caller/ ይህ አፕ ማንኛውም ሰዉ ወደ ሞባይላችን ሲደውል በሶሻል ሚድያ የተመዘገበው ስሙ ያሳየናል: ማለትም ስልኩ በሞባይላችን ባንመዘግበዉም የደዋዪ ስልክ ስም ለማወቅ ይጠቅመናል!

2➡ ሴክሪቲ 360 /360 Security/
ይህ ጸረ ቫይረስ ስልካችንን ከቫይረስ፣ ማል ዌር እና ትሮጃኖች በመከላከል ረገድ የተዋጣለት አፕ ነው። በዚህም ከስልካችን ቀርፋፋነት እስከ ሙሉ የኦፕሬቲንግ ሲስተም ብልሽት የሚያደርሱ የአንድሮይድ ቫይረሶችን አስቀድሞ በመከላከል ስልካችንን ከችግር ይጠብቅልናል።

3➡ ዋይፋይማፕ/WiFi Map/
በሆቴሎች ወይም በሌሎች ስፍራዎች የምናገኛቸው አብዛኞቹ ዋይ ፋይ ኔትወርኮች በይለፍ ቃል (password) የተዘጉ ናቸው። ይህም ማለት የዋይ ፋዩ ፓስወርድ ከሌለን ዋይ ፋዩን ለመጠቀም አንችልም ማለት ነው። ይህ አፕሊኬሽን በአለማችን የሚገኙትን በሆ ፋዮች ሁሉንም በሚባል መልኩ ፓስወርዳቸውን በቀላሉ ይነግረናል። ከእኛ የሚጠበው አፑን ከጫንን በኋላ ከሚመጣልን የአለም ከርታ ላይ ኢትዮጵያን፤ ከዚያም የምንፈልገውን ከተማ መምረጥ ሲሆን በከተማው ውስጥ ያሉትን ዋይ ፋይ ኔትወርኮችና ፓስወርዳቸውን ያመጣልናል። ዋይ ፋይ ኔትወርክ በአቅራቢያችሁ ኖሮ ፓስወርድ ለገደባችሁ ሁሉ ቀላል መፍትሄ ነው።

4➡ ዊስትል ፎን ፋይንደር/Whistle Phone Finder/
ለመሆኑ ቤት ውስጥ ወይም ስራ ቦታ ስልክዎን ያስቀመጡበት ቦታ ጠፍቶዎት ያውቃል? የሚያውቅ ከሆነ ፍለጋውንና ከሌሎች ስልክ ተውሶ ወደራስ ስልክ ለመደወል የሚደረገውን ድካም በደንብ ያውቁታል። ይሄንን አፕሊኬሽን ስልክዎት ላይ አስቀድመው ከጫኑ, ስልክዎን ያስቀመጡበት ቦታ ሲጠፋዎት ከእርስዎ የሚጠበቀው ማፏጨት ብቻ ነው። የፉጨትዎ ድምጽ አፕሊኬሽኑን በማንቃት ስልክዎ የመጥሪያ ደወል እንዲያሰማ በማድረግ ስልኩን በቀላሉ በድምጹ ተመርተው እንዲያገኙት ይረዳዎታል።

5.➡ ኔክስትዶር/NextDoor/ ይህ ሞባይል አፕሊኬሽን ከጎረቤቶቻቸን ለማዉራት የሚጠቅመን አፕ ነው ይህንን አፕ ተጠቅመን ከጎረበቶቻቸን ጋር መረጃ ለመለዋወጥ እርዳታ ለመፈለግና ተመሳሳይ ስራዎች ለማደረግ ይጠቅማል! ይህንን ስራ ለመስራት ኢንተርኔት አያስፈልገዎም::

6.➡ ኢንስታፔፐር/Instapaper/ ይህ ገራሚ አፕ በሞባይላችን የምናገኛቸው መረጃዎች ሴቭ ለማድረግና በፈለግነው ጊዜ ለማንበብ ወይም ለመመለከት ይጠቅመናል

7.➡ ዪቱዪብኪድስ/YoutubeKids/ ይህ አፕ የዪቱብ አፕ በጎግል በራሱ የተሰራ ሲሆነ ለልጆች ተብሎ የተሰራ አፕ ነው:: በዚህ አፕ ለልጆች የሚሆኑ ሙዚቃ የትምህርት መረጃዎች ቪድዮዎች ወዘተ ይገኛሉ! ከ18 አመት ለሆኑ ይህንን አፕ ብጨንላቸው ተመራጭነው::

8.➡ ለርንሲፕላስፕላስ/Learn C++/ ይህ አፕ ሲፕላስፕላስ ለመማር ለሚፈልጉ በጣም ምርጥ አፕ ነው! በሞባይልዎ ሁነው ሲፕላስፕላስ በመማር የተሻለ ፕሮግራመር ይሁኑ::

9.➡ IDM download manager
በኮምፒውተራችን ፋይሎችን በፍጥነት ዳውንሎድ ለማድረግ የምንጠቀምበት IDM, በቅርቡ ደግሞ ለአንድሮይድ ስልኮች የሚያገለግል አፕ ለቋል። IDM የስልካችን ብሮውዘር ዳውንሎድ ለማድረግ የሚወስድበትን ጊዜ በእጅጉ በመቀነስ የምንፈልገውን ፍይል በአጭር ጊዜ ያወርድልናል።
ከዚህ አፕ በተሻለ ፍጥነትና በነፃ የምናገኛቸው ዶወንሎድ ማድረግያ ለማየት እዘሁ ይጫኑ

10.➡ ዲስክዲገር/DiskDigger/
ዲስክዲገር ከስልካችን በስህተት ያጠፋናቸውን ፎቶዎች፣ ሙዚቃዎች፣ ቪዲዮዎችና ሌሎች ፋይሎቻችን የስልኩን ጥልቅ ዳታ ስቶሬጅ በማሰስ ይመልስልናል።

ሞባይል ዳታ በሚከፈትበት ጊዜ ካርድ ወይም የተሞላውን የዳታ ጥቅል በቶሎ የሚጨርስበት ምክንያትቶችና መፍትሔዎች:ምክንያቶች :-1.የሞባይል ዳታ ተከፍቶ ሲረሳና ሳይዘጋ ሲቀር2.ኢንተርኔት ክፍት...
16/08/2021

ሞባይል ዳታ በሚከፈትበት ጊዜ ካርድ ወይም የተሞላውን የዳታ ጥቅል በቶሎ የሚጨርስበት ምክንያትቶችና መፍትሔዎች:

ምክንያቶች :-
1.የሞባይል ዳታ ተከፍቶ ሲረሳና ሳይዘጋ ሲቀር
2.ኢንተርኔት ክፍት ሆኖ ከተለያዩ ደህረ ገፆች ላይ ቀጥታ ቪዲዮች ሲታዩ
3.System settings እና Applications በራሳቸው ጊዜ አፕዴት ሲያደርጉ
4.በሞባይሉ ላይ የሚገኙ አፕሊኬሽኖች ተጠቃሚው በማያቸው መንገድ ከበስተጀርባ ሲሰሩ
5.በሞባይል ስልኩ ውስጥ ቫይረስ ሲኖር
---------------------------
መፍትሔዎች :-
👉ሞባይል ዳታ ተከፍቶ ሲረሳና ሲቆይ እንደ ሶሻል ሚዲያና ኦንላይን የሚሰሩ አፕሊኬሽኖች ከተጠቃሚው እይታ ውጪ ስራቸውን ያከናውናሉ። በዚህ ጊዜ በሞባይሉ ላይ የተሞላው ክሬዲት ሰዓት ይቀንሳል ወይም ያልቃል ስለዚህም ኢንተርኔት ተጠቅመው ከጨረሱ በኋላ የሞባይሉን ዳታ ያጥፉ።

👉በሞባይል ዳታ ኢንተርኔት ከፍቶ ከተለያዪ ድህ ገፆች ላይ በቀጥታ ቪዲዮ መመልከት የተሞላውን ካርድ መጠን በጊዜ ከሚያሳጥሩት ነገሮች ወስጥ አንደኛው ሲሆን ለዚህም ዋነኛው
ምክንያት በኢንተርኔት ቪዲዮ ቀጥታ መመልከት የሚቆጥረው የዳታ መጠን ከፍተኛ ስለሆነ ነው ስለዚህ ቪዲዮ ማየቱ ግዴታ ከሆነ በ Vidmate እና በሌሉች ቪዲዮ ዳውሎደር አፕሊኬሽኖች የቪዲዮ ይዘት በመቀነስ ጭኖ መመልከቱ ወጪን
ይቆጥባል።

👉System settings እና Application በራሳቸው ጊዜ አፕዴት ሲያደርጉ የተሞላውን ዳታ(ካርድ) ይወስዳሉ ታዲያ ይህን ለማስቀረት Free wifi ከተገኘ አፕዴት ማድረግ ይህ ማድረግ የማይቻል ከሆነ system settings አፕዴት እንዳያደርግ ማስቆም:
👍Settings ----About----Software Update---
Automatic update የሚለውን ማጥፋት
Applications አፕዴት እንዳያደርጉ ከተፈለገ ደግሞ
-Google Play መክፈት.
- hamburger የሚመስለውን በለ ሶስት ሆሪዞንታል ምልክት ያለበትንም አናት ላይ በስተግራ በኩል Settings በመንካት
Auto-update apps.- disable automatic app updates, የሚለውን በመክፈት እና በመምረጥ መዝጋት
ይቻላል

👉በሞባይሉ ላይ የሚገኙ አፕሊኬሽኖች ተጠቀሚው በማያቸው መንገድ ከበስተጀርባ ሲሰሩ ከእይታ ውጪ በመሆን የክሬዲት መጠን ይቀንሳሉ ታዲያ ይህን ለመከላከል:
👍Settings----
data usage ---Restricted Background data
የሚለውን መክፈት... ከዚህ ይበልጥ ደግሞ Mobile data
saver አፕሊኬሽኖች በመጫን መጠቀም

👉በሞባይል ሰልክ ውስጥ ቫይረስ ሲኖር የተሞላውን ሞባይል
ዳታ ከመቅስፈት እድሜው እንዲያጥር ያደርጋል ብሎም ቫይረሱ በራሱ ጊዜ የሞባይሉን ኦፕሬቲንግ ሲስተም በማዘዝ ያለማንም ትዕዛዝ ዳታ ይከፍታል ዳውንሎድ ያደርጋል አላስፈላጊ ነገሮችና ማስታወቂያዋች ይለቃል ከዚህም የተነሳ በፍጥነት የሞባይል ካርድ( ዳታ ጥቅል) ይጨርሳል ይህ ነገር በሞባይሉ ላይ ቢከሰት አንቲ ቫይረስ በመጫ ሰካን ማድረግ ይህ መፍትሔ የማይሆን ከሆነ ለባለሙያ ማሳየቱ ተገቢ ነው::

Follow me telegram youtube facebook

on telegram
t.me/Abduke_26

Facebook
https://www.facebook.com/103537848621463/posts/114909260817655/?app=fbl

የሞባይል ኮኔክሽን በምትከፍቱበት ጊዜ playstore በራሱ ጊዜ application download እያደረገ ገንዘባቹህን አየቆረጠ ላስቸገራቹህ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።...
31/07/2021

የሞባይል ኮኔክሽን በምትከፍቱበት ጊዜ playstore በራሱ ጊዜ application download እያደረገ ገንዘባቹህን አየቆረጠ ላስቸገራቹህ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

በመጀመሪያ playstore ውስጥ ከገባቹህ በኋላ "ከ playstore ጫፍ ላይ በቀኝ ወይም በግራ በኩል እንደየስልካቹህ ይለያያል play protect ከሚለው ቀጥሎ setting የሚለውን ከመረጣቹህ በኋላ
Network preference የሚለውን ተጫኑauto update app የሚለውን ስትጫኑት

Over any network
Over wifi only
Don't auto update apps

የሚሉ options ይመጣላቹሀል ከዛ
Don't auto update apps የሚለው ላይ አድርጉት

**Auto- play video የሚለውን ተጭናቹህ ከታች

auto-play video at any time
Auto - play video over wifi only
Don't auto-play video

ከእነዚህ ዝርዝሮች ውስጥ
Don't auto -play video የሚለው ላይ አድርጉት
auto downlode preference የሚለውን ስትጫኑት
over any network
Over wifi only
Ask me every time

ከሚሉት ዝርዝሮች ውስጥ
over wifi only ላይ አድርጉት

ሌሎች ፓስቶች እንዲደርሷቹህ
ፔጁን LIKE ድርጉት
ለሌሎችም አጋሩት ወይም share አድርጉ

t.me/Abduke_26

Facebook
https://www.facebook.com/103537848621463/posts/114909260817655/?app=fbl

info tips tutorials

30/07/2021

የምለቃቸውን ጹሁፎች ሸር እና ላይክ በማድረግ ይተባበሩ share and like may posts

29/07/2021

ስልካችን ወሀ ውስጥ ሲገባ
በቻርጀር ኬብል መሰኪያ እና በድምፅ ማውጫው በኩል ውሀ ይገባል

#ስለዚህ መፍትሄው ምንድነው?
በመጀመሪያ ውሀ በገባበት በኩል ስልኩን በእጃችን መታ መታ አድርገን ውሀውን ካወጣነው በኋላ
ቀሪውን ውስጥ ያለውን ውሀ ለማውጣት
መለጠጥ የሚችል የፕላስክ ፔስታል ፈልገን
ካገኘን በኋላ በቀጭኑ በመጠቅለል ውሀው በገባበት ቀዳዳ እናስገባዋለን ፕላስኩን ስናወጣው ውሀውን ወደራሱ በመሳብ ይዞት ይወጣል
#ሌላኛው መፍትሄ ሁላቹሁም እንደምታውቁት ሩዝ ውስጥ ስልኣችንን ለ2 ሰአት ያክል መተው ነው

24/07/2021

አዲስ Smart ስልክ ከመግዛታችን በፊት ማወቅ የሚገቡን 10 ወሳኝ ነገሮች!

~ መግዛት ያሰቡት Smart ሞባይል ስልክ iPhone ወይም Samsung ወይም ሌላ ሊሆን ይችላል። ማንኛውም Smart ሞባይል ሲገዙ መመዘኛዎችን ማሟላቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል.... ➩ ለምሳሌ:-

1~ ፕሮሰሰር(Processor)
▣ ብዙ ግዜ ጌም የሚጫወቱ ከሆነ፣ቪድዮ የሚያዩ ከሆነ ወይም የቪድዮ ኤዲቲንግ የሚሰሩ ከሆነ የስልኩ ፕሮሰሰር Qualcom Snapdragon(652/820/821/888) /ቢሆን ይመረጣል።
- ለመካከለኛ ተጠቃሚ ፕሮሰሰሩ MedaTek ከሆነ በቂ ነው።

2 ~ ካሜራ
▣ ፎቶ የማንሳት ልምድ ያለው ሰው የስልኩ ካሜራ 16MP (Megapixels) #በላይ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
- ለመካከለኛ ተጠቃሚ ግን 13MP በቂ ነው።

3 ~ ባትሪ
▣ ብዙ ሰዓት ቪድዮ ለሚያይ፣ጌም ለሚጫወት ሰው ባትሪው 4000mAh በላይ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። - ለመካከለኛ ተጠቃሚ 3000mAh/3500mAh በቂ ነው።

4 ~ ኦፐሬቲንግ ሲስተም(OS)
▣ የተለያዩ ኦፐሬቲንግ ሲስተም(OS) ቨርዥኖች
አሉ።
- ለምሳሌ:- ኪትካት፣ሎሊፓፕ፣ማርሽሜሎ፣...ወዘተ የተባሉ ቨርዥኖች አሉ። ስለዚህ latest ቨርዥን መምረጥ ይመከራል።

5 ~ ስቶሬጅ
▣ ስልኩ በቂ የማጠራቀሚያ አቅም ቢኖረው ይመረጣል። 16GB/32GB/64GB..ከነዚህ ውስጥ መምረጥ ነው። ስልኩ ኤክስተርናል ሜሞሪ (microSD card) የሚቀበል መሆን አለበት።
- ለመካከለኛ ተጠቃሚ 32GB Storage በቂ ነው።

6 ~ RAM
▣ ከተቻለ ከ3/4GB Ram በላይ ቢሆን ጥሩ ነው የተለያዩ ነገሮችን በፍጥነት እንድንሰራ ይረዳናል ይህም ስልካችን ፈታ ብሎ ስራውን እንዲያከናውን ይረዳዋል።
- ለመካከለኛ ተጠቃሚ 2GB Ram በቂ ነው

7 ~ Headphone Jack
▣ HeadPhone 3.5mm audio jack ቢሆን ይመረጣል።

8 ~ USB File transfer USB 2.0
▣ በአሁኑ ጊዜ ያለ ስለሆነ ይህ ፖርት ያለው ቢሆን ይነረጣል , USB 3.0 ቢሆን ጥሩ ነው።

9 ~ Physical Size
▣ በኢንች ለናንተ የሚመቸውን መምረጥ አለባችሁ።
- አሪፍ የሚባለው Size ለምሳሌ:- 6.2inch/6.4inch/6.5inch አሪፍ የሚባል ነው።

10 የሚቀበለው የሲም ካርድ አይነት መለየት።
▣ ለምሳሌ:- Dual SIM (Nano-SIM, dual stand-by)

📍 ለምሳሌ ከታች ያለውን Specification ተመልከቱ።

Technology : GSM / CDMA / HSPA / CDMA2000 / LTE / 5G EXPAND ▼
Dimensions: 75.8 x 164 x 8.9 mm
Weight : 205 g
SoC: MediaTek Helio P35 (MT6765)
CPU : 4x 2.3 GHz ARM Cortex-A53, 4x 1.8 GHz ARM Cortex-A53, Cores : 8
GPU : PowerVR GE8320, 680 MHz
RAM : 3 GB, 4 GB, 6 GB
Storage : 32 GB, 64 GB, 128 GB
Camera : 13MP, 16MP, 48MP, 64MP...
Selfie : 8MP, 13MP, 20MP, 32MP...
Memory cards : microSD, microSDHC, microSDXC
Display : 6.5 in, TFT, 720 x 1560 pixels, 24 bit
Battery : 5000 mAh, Li-Ion
OS: Android 10
SIMcard : Dual SIM (Nano-SIM, dual stand-by)
Wi-Fi : a, b, g, n, n 5GHz, ac, Dual band, Wi-Fi Hotspot, Wi-Fi Direct
US

❖ 6 ምርጥ ቦቶች/bots/① ►የምትፈልጉትን ለ"iphone" የሚሆን አፕልኬሽን በቴሌግራም ለማወረድ ከፈለጉ Appstore ከመፈለግ...② ►ቪዶ/video,ሶፍቴር/Software የምትፈልጉትን...
16/07/2021

❖ 6 ምርጥ ቦቶች/bots/



►የምትፈልጉትን ለ"iphone" የሚሆን አፕልኬሽን በቴሌግራም ለማወረድ ከፈለጉ Appstore ከመፈለግ...



►ቪዶ/video,ሶፍቴር/Software የምትፈልጉትን ነገር ከቴሌግራም ላይ ወስደው በምትፈልጉት የዳውንሎ መተግበሪያ ማውረድ ከፈለጉ ለምሳሌ በ (IDM - Internet Download Manager)



►የምትፈልጉትን ለ"Android" የሚሆን አፕልኬሽን በቴሌግራም ለማወረድ ከፈለጉ playstore አልሰራ ላላችሁ...



►የምትፈልጉትን ቦት ለማግኘት ቴሌግራም ላይ ያሉትን ከ>60% ከነጥቅማችው ያገኛሉ።



►በሚያምር ሁኔታ የቻናላችሁን ስም ወይም ስማችሁን በተለያየ ፎንት (🅕🅞🅝🅣,ʇuoɟ,𝓕𝓸𝓷𝓽..) ለመፃፍ ከፈለጉ

t.me/Abduke_26

Facebook
https://www.facebook.com/103537848621463/posts/114909260817655/?app=fbl

info tips tutorials

14/07/2021

Question? አሁን የሚጠቀሙበት የመፃፊያ አፕልኬሽን ምን አይነት ነው ?
fyngeez 2020app
ምርጥ አፕልኬሽን ነው ምርጥ ከሚያስብሉት ፊወቸሮቹ
1.ብዙ የኢሞጅ ምልክቶች አሉት
2.keybordዱን በምትጠቀሙ ጊዜ ንዝረት እና ድምፅ አለው ካልፈለጋቹሁት setting ውስጥ ገብታቹህ ማጥፋት ትችላላቹሀ
keybordዱ ላይ ቁጥሮችን ለብቻ ማምጣት ይችላል
3. letter default አለው
4.የkeybord theme አለው
5.language. 8 አይነት ቋንቋ አለው
6.(ትንበያም አለው)አናንተ ከታች መፃፍ ስትጀምሩ አፕልኬሽኑ ደግሞ ተቀራራቢ ቃላቶችን ከላይ ይደረድርላቹሀል
7.የስፔስ ምልክቱን ሁለት ጊዜ ስትጫኑት ወደ አራት ነጥብ ይቀይረዋል
8. punctuation አለው ማለትም ለፁሁፉ የሚያገለግል ስርኣተ ነጥብ አለው
9.የኬይቦርዱን መጠን እንደፈለጋቹህ ማድረግ ትችላላቹህ

 # #የሞባይል ኮኔክሽን ምልክት ስልካቹህ ላይ አበራ ካላቹህ ወይም ዳታ አልሰራ ላላቹህየሞባይል ዳታ ወይም ኮኔክሽን አብርታቹህ ነገር ግን የሞባይሎ ዳታ ምልክት ካልበራላቹህ step1 የስልካ...
01/07/2021

# #የሞባይል ኮኔክሽን ምልክት ስልካቹህ ላይ አበራ ካላቹህ ወይም ዳታ አልሰራ ላላቹህ

የሞባይል ዳታ ወይም ኮኔክሽን አብርታቹህ ነገር ግን የሞባይሎ ዳታ ምልክት ካልበራላቹህ
step1 የስልካቹህ ዋና ሴቲንግ ውስጥ ትገባለቹህ
Step2 ሞባይል ኔትወርክ ውስጥ ከገባቹህ በኋላ
step3 አክሰስ ፖይንት ኔም access point name ወስጥ ገብታቹህ
step4 ETH-MTN የሚለው ተጫኑት
step 5 NAME የሚለው ላይ etc APN የሚለው ላይ etc.com ብላቹህ ከሞላቹህ connection መስራት የጀምራል ማለት ነው

Follow me telegram youtube facebook

on telegram
t.me/Abduke_26

Facebook
https://www.facebook.com/103537848621463/posts/114909260817655/?app=fbl

የኤድቲንግ ክህሎት ከክፍል ሁለት የቀጠለኤድት ለማድረግ በመጀመሪያ የሚያስፈልገን ነገር ቢኖር አፕልኬሽኖቹን ማወቅ ነው ኤድት ለማድረግ ምን ምን አፕልኬሽን ያስፈልጋል ???ለስልክ1ለቪድዮ መስ...
28/06/2021

የኤድቲንግ ክህሎት
ከክፍል ሁለት የቀጠለ
ኤድት ለማድረግ በመጀመሪያ የሚያስፈልገን ነገር ቢኖር አፕልኬሽኖቹን ማወቅ ነው
ኤድት ለማድረግ ምን ምን አፕልኬሽን ያስፈልጋል ???

ለስልክ
1ለቪድዮ መስሪያ _kine master
2 power directory
3 viva video

በስልክ
ለፎቶ ለሎጎ ለባነር ለተምኔል
logo.banner or channel art.thumbnail.
ቁጥር አንድ ተመራጭ 1 pixellab
2Picsart
3Background eraser
4Inshot

record
ለማድረጎ በስልክ
screen recorder
Du recorder all

በcomputer ወይም laptop
ለቪድዮ ቁጥር አንድ ተፈላጊ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዩቱበሮች የሚጠቀሙት
adobe premium pro

ለፎቶ photoshop
ለaudio -odacity

Follow me telegram youtube facebook

on telegram
t.me/Abduke_26

Facebook
https://www.facebook.com/103537848621463/posts/114909260817655/?app=fbl

Youtube
[ ] በዩቱብ ABDU MEDIA አብዱ ሚድያ
https://youtube.com/channel/UCSEK86LVbMDpRJbsjxxz-pg

የኤድቲንግ ክህሎት ከክፍል ሁለት የቀጠለኤድት ለማድረግ በመጀመሪያ የሚያስፈልገን ነገር ቢኖር አፕልኬሽኖቹን ማወቅ ነው ኤድት ለማድረግ ምን ምን አፕልኬሽን ያስፈልጋል ???ለስልክ1ለቪድዮ መስ...
21/06/2021

የኤድቲንግ ክህሎት
ከክፍል ሁለት የቀጠለ
ኤድት ለማድረግ በመጀመሪያ የሚያስፈልገን ነገር ቢኖር አፕልኬሽኖቹን ማወቅ ነው
ኤድት ለማድረግ ምን ምን አፕልኬሽን ያስፈልጋል ???

ለስልክ
1ለቪድዮ መስሪያ _kine master
2 power directory
3 viva video

በስልክ
ለፎቶ ለሎጎ ለባነር ለተምኔል
logo.banner or channel art.thumbnail.
ቁጥር አንድ ተመራጭ 1 pixellab
2Picsart
3Background eraser
4Inshot

record
ለማድረጎ በስልክ
screen recorder
Du recorder all

በcomputer ወይም laptop
ለቪድዮ ቁጥር አንድ ተፈላጊ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዩቱበሮች የሚጠቀሙት
adobe premium pro

ለፎቶ photoshop
ለaudio -odacity

Follow me telegram youtube facebook

on telegram
t.me/Abduke_26

Facebook
https://www.facebook.com/103537848621463/posts/114909260817655/?app=fbl

Youtube
[ ] በዩቱብ ABDU MEDIA አብዱ ሚድያ
https://youtube.com/channel/UCSEK86LVbMDpRJbsjxxz-pg

info tips tutorials

ክፍል ሁለት የኤድቲንግ ክህሎትየኤድቲንግ ችሎታ ሲባል ዝምብሎ አይመጣም ኤድት ማድረግ ከሚችሉ ጓደኞች ጋር መግባባት እና ፈቃደኛ ከሆኑ እንድያሳዩን መጠየቅ የዩቱብ ቱቶሮቹን ማየት ለምሳሌ እኔ...
20/06/2021

ክፍል ሁለት
የኤድቲንግ ክህሎት
የኤድቲንግ ችሎታ ሲባል ዝምብሎ አይመጣም ኤድት ማድረግ ከሚችሉ ጓደኞች ጋር መግባባት እና ፈቃደኛ ከሆኑ እንድያሳዩን መጠየቅ የዩቱብ ቱቶሮቹን ማየት ለምሳሌ እኔ ከዚህ ቡኋላ የኤድቲንግ ቪድዮዎችን በዩቱብ ስለምለቅ እሱን እያያቹህ መለማመድ ትችላላቹህ እና ደግሞ ተስፋ አለመቁረጥ ሁሌም መሞከር ነገሮችን በደጋገምናቸው ቁጥር ጥሩ ነገር እያገኘን ከስህተታችን እየተማርን መጨረሻ ላይ ጥሩ ውጤት ማምጣት እንችላለን ማለት ነው
ስንጀምር ከትንሹ መጀመር መቸም በአንድ ጊዜ ትልቅ ስራ መስራት ይከብዳል ጥሩ ነገር መፍጠር የፈለገ ሰው ከትንሽ ነገር መጀመር ነው ያለበት
የኤድቲንግ ቲቶሮቹን ለማግኘት
[ ] በዩቱብ ABDU MEDIA አብዱ ሚድያ
https://youtube.com/channel/UCSEK86LVbMDpRJbsjxxz-pg

info tips tutorial

ዩቱበር ለመሆን ምን ምምን ነገሮችን ማሟላት አለብንክፍል አንድ1 የኤድቲንግ ክህሎት ምክንያቱም የኤድቲንግ ክህሎት ከሌለን አና የምንሰራቸው ቪድዮዎች እንደነገሩ ከሆኑ ጥሩ ኤድቲንግ ካላገኙ ተ...
19/06/2021

ዩቱበር ለመሆን ምን ምምን ነገሮችን ማሟላት አለብን

ክፍል አንድ

1 የኤድቲንግ ክህሎት ምክንያቱም የኤድቲንግ ክህሎት ከሌለን አና የምንሰራቸው ቪድዮዎች እንደነገሩ ከሆኑ ጥሩ ኤድቲንግ ካላገኙ ተመልካች አይኖረነም
2 የዩቱውብ ሴቲንጎቹን በመጀመሪያ ማወቅ
የዩቱብ ሴቲንጎችን ዩቱውብ ከመጀመራችን በፊት ማወቅ ግድ ይለናል
3 ጥሩ ብለር ያለው ካሜራ ወይም ስማርት ስልክ
4 ጥሩ የድምጽ መቅጃ ማይክ
5 የጎግል አካውንት መክፈት
6 ራሱን የዩቱብ አካውንት መክፈት

7 የአድሰንስ አካውነት መክፈት
8 ጥሩ ብርሀን ወይም light
9 posta box ቁጥር መከራየት
10 ጥሩ አፕልኬሽኖች አሉ እነሱን መጠቀም
ከበድ ላለማድረግ ማይክ የመግዛት አቅም የሌለን ሰዎች በስልክ ኤርፎን መጠቀም አንችላለን
ካሜራ የስልካቹሁን ተጠቀሙት የlight መግዣ አቅም ከሌለን ደግሞ በቤት ውስጥ ሁነን በቀላሉ ጥሩ ብርሀን የሚሰጥ የላይት አሰራር በቪድዮ
አሳያቹሀለሁ
አንግዲህ ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ምንም አክብዳቹህ እንዳታዩት
በዝርዝር እተነትንላቹሀለሁ ጎግል አካውንትን ተጠቅመን አንደት የዩቱብ ቻናል እንደምንከፍት
እንደት ቪድዮ አንደምንጭን እና እንደት ኤድት እንደምናደርግ አድሰንስ አካውንት ምን እንደሆነ ለምን እንዳስፈለገ እና አንደት አንደምንከፍተው
እንደት በስልክ ጥሩ ጥሩ ቪድዮዎችን ኤድት አንደት አንደምንሰራ
እና ዩቱብ በየጊዜው የሚያመጣቸውን እና የድሮውን ጨምሮ የዩቱብ ሴቲንጎችን አሳያቹሀለሁ
በዩቱብ ቻናል በቪዲዮ ለመከታተል
youtube ላይ
https://youtube.com/channel/UCSEK86LVbMDpRJbsjxxz-pg

በቴሌግራም ለመከታተል
ABDU MEDIA አብዱ ሚድያ
t.me/Abduke_26

info tips tutorial

04/06/2021

This page is about technology information tips tutorials

Address

Addis
S**o

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ᴀʜʟᴀᴛ ᴍᴇᴅɪᴀ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category