
16/07/2024
ቀን 09/11/2016 ዓ.ም
የሾኔ ከተማ አስ/ር ጤና ጽ/ቤት የ2016 ዓ.ም አፈፃፀምና ወቅታዊ የወባ ወረርሽኝ ሥራዎች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ፤
ሾኔ፤ ሐምሌ 09/2016 ዓ.ም ( የሾኔ የከተማ አስ/ር ጤና ጽ/ቤት የ2016 ዓ.ም አፈፃፀምና ወቅታዊ የወባ ወረርሽኝ ሥራዎች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።
በመድረኩም የተዘጋጀው ሰነድ በጤና ልማት ዕቅድ ተወካይ በአቶ አሸናፍ ዮሴፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።
መድረኩን የመሩት የሾኔ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኤልያስ ዳዊት እና የሾኔ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አበራ በዶሬ ሲሆኑ ከንቲባው ቤቱ በስፋት እንዲወያይ ትኩረት ከሰጡአቸው ጉዳዮች በተለይ በጉድለት የተገመገሙት ነጥቦች ዙሪያ ልዩ ትኩረት በመስጠት ሃሳብ መነሳት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
በውይይቱም ላይ የከተማ አስተባባሪ፣ የጤና ጽ/ቤት ማኔጅመንት፣ የሆስፒታል ማኔጅመንት፣ የቀበሌ ደጋፊ አመራሮች፣ የቀበሌ የፊት አመራሮች፣ የማዞሪያ ጤና ጣቢያ ማኔጅሜንት እና የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የተገኙ ስሆን በሰነዱ ላይ አስተያየት ከሰጡ በኋላ በጉድለት በተነሱ ጉዳዮች ዙሪያ በቀጣይ ጊዜ ኃላፊነት ወስደው የየድርሻቸውን ለመወጣት ቃል ገብተዋል።
የሾኔ ከተማ አስተዳደር ዋና የመንግሥት ተጠሪ አቶ ዳንኤል አየለ እንደተናገሩት በጤናው ዘርፍ በርካታ ተግባራት የተከናወነና ውጤትም እያስመዘገብን የመጣን እንደሆነ ሁሉም ሰው ሊገነዘብ ይገባል ካሉ በኃላ በጉድለት ተለይቶ የቀረቡ ተግባራት፣ ወደ ኋላ የቀሩ ተቋማትና እንዲሁም ቀበሌያት የተለየ ርብርብ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል በማለት የማጠቃለያ ሃሳብ ሰጥተዋል።
አቶ ኤልያስ ዳዊት በተለይ ወቅቱ የወባ ወረረሽኝ ያለበት ወቅት በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትኩረት ልሰሩ እንደሚገባ በማስገንዘብ በየቀበሌው ያለው ፈጣን ምላሽ ሰጪ ኮሚቴ ከመቼውም ጊዜ በላዬ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበው ከስርዓተ ምግብ ፕሮግራም ጋር ተያይዞ የአልሚ ምግብ ከታለመው ውጪ ማዋል ይቅርታ እነደማያሰጥ አሳስበው እንደተቋም ግን በታዩት ክፍተቶች ዙሪያ ኃላፊነት ወስደዉ ለመሥራትና ድጋፍ፣ ክትትልና ቁጥጥር የማድረግ ሥራ ከመቸውም ጊዜ በላይ አጠናክረን እንሰራለን ብለዋል።
አቶ አበራ በዶሬ የማጠቃለያ ሃሳብ ስሰጡና ቀጣይ አቅጣጫ ባስቀመጡበት ወቅት የማዐጤመ አገልግሎት አሰጣጥ እና የወባ ወረረሽኝ ዙሪያ ላይ ትኩረት ሰጥተን ለህዝባችን አገልግሎት መስጠት ባለብን ልክ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሁላችንም ቅንጅት ፈጥረን መስራት አለብን በማለት አቅጣጫ ካስቀመጡ በኋላ የውይይት መድረኩ ተጠናቋል።
ሐምሌ 09/2016 ዓ.ም
ሾኔ