የሌተ/ጄኔራል ይልማ መርዳሳ አድናቂ

የሌተ/ጄኔራል ይልማ መርዳሳ አድናቂ ምን ግዜም ስለፍትሕ፣ እውነት፣ ነፃነት፣ እኩልነት፣ ሳልሰለች በታማኝነት እናገራለሁ!!!!

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳድር እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር ገለፀ‼️“ህዝባችን ወደ አመፅ እና ግርግር እንዲገባ ሌትና ቀን እየሰራ ያለው ቡድን ፥  ከዚህ ፀረ ሰላም ተግባሩ ካልተቆጠበ የትግራይ...
22/12/2024

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳድር እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር ገለፀ‼️

“ህዝባችን ወደ አመፅ እና ግርግር እንዲገባ ሌትና ቀን እየሰራ ያለው ቡድን ፥ ከዚህ ፀረ ሰላም ተግባሩ ካልተቆጠበ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳድር ከእንግዲህ ቦኃላ እንደማይታገሰው” ገለፀ።

ለክልሉ የሚያስፈልገው ጦርነት ሳይኾን ሰላም እንደኾነ የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ገለጹበደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር "ለሰላም ዘብ እንቁም"በሚል መሪ መልዕክት ...
18/12/2024

ለክልሉ የሚያስፈልገው ጦርነት ሳይኾን ሰላም እንደኾነ የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ገለጹ

በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር "ለሰላም ዘብ እንቁም"በሚል መሪ መልዕክት ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

በሰልፉ ላይ የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው።

ሰልፈኞቹ በመፈክሮቻቸው ባስተላለፉት መልዕክት መንግሥት ለሰላም መስፈን የሚወስደውን ርምጃ እንደሚደግፉ ተናግረዋል።

ሰላም የጋራ ሃብት ነው ያሉት ሰልፈኞቹ በጋራ እንደሚያለሙት እና በጋራ እንደሚጠብቁትም መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል።

መንግሥት ለሰላም መስፈን የሚወስዳቸውን ርምጃዎች እንደሚደግፉም ነው ያብራሩት።
ሰልፈኞቹ ለክልሉ የሚያስፈልገው ጦርነት ሳይኾን ሰላም እንደኾነ ነው የተናገሩት።

የሩሲያ የኬሚካል የጦር መሳሪዎች ጥበቃ ኃላፊ ጄነራል ሞስኮ ውስጥ ተገደሉ ።የሩሲያ የኬሚካል የጦር መሳሪዎች ጥበቃ የበላይ ኃላፊ ጄነራል ኢጎር ኪሪሎቭ እና ረዳታቸው ዛሬ ሞስኮ ውስጥ በተጠመ...
17/12/2024

የሩሲያ የኬሚካል የጦር መሳሪዎች ጥበቃ ኃላፊ ጄነራል ሞስኮ ውስጥ ተገደሉ ።
የሩሲያ የኬሚካል የጦር መሳሪዎች ጥበቃ የበላይ ኃላፊ ጄነራል ኢጎር ኪሪሎቭ እና ረዳታቸው ዛሬ ሞስኮ ውስጥ በተጠመደ ቦምብ ተገድለዋል። ለጥቃቱ ዩክሬን ኃላፊነት ወስዳለች። የዩክሬን የደህንነት መስሪያ ቤት በጦር ወንጀል የሚፈለጉ «ሁነኛ ዒላማ» የሆኑ ሰውን «በልዩ ዘመቻ» በፈጸመው ጥቃት መግደሉን አስታውቋል። ሩሲያ የጄነራሉን መገደል አረጋግጣለች ። ነገር ግን ክሬምሊን ስለአሟማታቸው ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ከመግለጽ ያለፈ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል። ሶስት ዓመት ባስቆጠረው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ዩክሬን ሞስኮ ድረስ ዘልቃ በመግባት አንድ የሩስያ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ ስትገድል ይህ የመጀመሪያው መሆኑን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
ኢጎር ኪርሎቭ እና ረዳታቸውን ለሞት ያበቃው የቦምብ ጥቃት የተፈጸመው በደቡብ ምስራቃዊ የሞስኮ ክፍል ከአንድ የመኖሪያ ህንጻ ውጭ ነው ተብሏል። ቦምቡ ስኩተር በተሰኘ በኤልክትሪክ በሚሰራ ሞተርሳይክል ላይ ተጠምዶ እንደነበር የጠቀሰው ዘገባው በፍንዳታው በአቅራቢያ በነበሩ መኖሪያ ቤቶች ላይም ጉዳት ማድረሱን ገልጿል።
የቦምብ ጥቃቱ የተፈጸመው የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሩስያ ወታደሮች በዩክሬን ባስመዘገቡት ስኬት ካወደሷቸው አንድ ቀን በኋላ ነው።
የሞስኮ ባለስልጣናት ለጄኔራሉ ህልፈት ምክንያት የሆነው ጥቃት «የሽብር« ይሁን ሌላ እናጣራለን ብለዋል።

በኢትዮጵያ የውጭ ባንኮች እንዲገቡ ተፈቀደ !የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ የውጭ ባንኮች እንዲሳተፉ የሚፈቅደውን የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅ አፀደቀ። ምክር ቤቱ በ11ኛ መደበኛ ስብሰባ...
17/12/2024

በኢትዮጵያ የውጭ ባንኮች እንዲገቡ ተፈቀደ !

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ የውጭ ባንኮች እንዲሳተፉ የሚፈቅደውን የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅ አፀደቀ።

ምክር ቤቱ በ11ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ለምክር ቤቱ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ አቅርቧል።

በዚሁ ጊዜ የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅ በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፉን ተወዳዳሪነት የሚያሳድግና ለምጣኔ ሀብት ዕድገቱ ቀጣይነት ጉልህ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።

የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ የባንክ ሥራ መሰማራታቸው የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግር ከማምጣት ባለፈ የውጭ ምንዛሬ ክምችትን ለማሳደግ ያግዛልም ነው የተባለው።

የምክር ቤቱ አባላት የአገር ውስጥ ባንኮችን አቅም ሳያሳድጉ ዘርፉን ለውጭ ባንኮች ክፍት ማድረግ ይዞት ሊመጣ የሚችል አሉታዊ ተፅዕኖ የለም ወይ የሚል ጥያቄ አንስተዋል።

በሌላ በኩል የምክር ቤቱ አባላት ከብሔራዊ ባንክ የቁጥጥር አቅም፣ ከአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የብድር አቅርቦት ጋር ሊያጋጥሙ ይችላሉ ያሏቸውን ስጋቶች አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምሕረቱ በሰጡት ምላሽ፣ ረቂቅ አዋጁ የባንክ ዘርፉ ለውጭ ባንኮች ክፍት የሚሆንበትን ስርዓት የሚያስቀምጥ ነው ብለዋል።

የፋይናንስ ዘርፉን ክፍት ማድረግ የአገር ውስጥ ባንኮችን አቅም የሚያጠናክር እንጂ የሚያጠፋ አለመሆኑንም አብራርተዋል።

አሰራሩ የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ ተቀጥላ ኩባንያ እንዲከፍቱና ከአገር ውስጥ ባንኮች ጋር በሽርክና እንዲሰሩ ዕድል የሚፈጥር መሆኑንም ገልፀዋል።

ዘርፉ ለውጭ ባንኮች ክፍት መደረጉ የአገር ውስጥ ባንኮችን የበለጠ በማጠናከር ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የድርሻውን እንዲወጣ ያስችለዋል ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው። ምክር ቤቱ የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅን በሶስት ተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።

በደቡብ ኦሮሚያ በምሥራቅ ቦረና ለኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል!!
16/12/2024

በደቡብ ኦሮሚያ በምሥራቅ ቦረና ለኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል!!

የኤርትራዉ አምባገነን መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ በአሰብ ያልጠበቁት ገጥሟቸዋል‼️ የኤርትራዉ አምባገነን መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ ከ13 ዓመታት ቆይታ በኋላ ከሰሞኑ ወደ አሰብ ብቅ ማለቱ እያነጋገረ ...
15/12/2024

የኤርትራዉ አምባገነን መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ በአሰብ ያልጠበቁት ገጥሟቸዋል‼️

የኤርትራዉ አምባገነን መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ ከ13 ዓመታት ቆይታ በኋላ ከሰሞኑ ወደ አሰብ ብቅ ማለቱ እያነጋገረ ይገኛል ፣ የፕሬዝዳንቱ ጉዞ የኢትዮጵያን እና የሶማሊያን የአንካራ ስምምነት ተከትሎ የተደረገ መሆኑ ከኤርትራ መረጃ ሚንስቴር የተገኙ ፍንጮች ይጠቁማሉ ፡፡ በጉብኝታቸዉም የአካባቢዉን ማህበረሰብ ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የሀይማኖት አባቶችን በማካተት በአንካራ የተደረገዉን የትብብር ስምምነት በማብራራት ኢትዮጵያ ቀጣይ ወደ አሰብ ታደርጋለች ብሎ የፈጠረዉን የወረራ እቅድ ለመግለፅ የሞከረ ሲሆን ነገር ግን ከተወካዮቹ ከባድ ተቋዉሞ ገጥሞታል ፡፡በተለይም ለ 13 አመታት በኤርትራ መንግስት ስር እየተዳደርን የት እንዳለን የማንታወቅ የዚህ አከባቢ ሰዎች ዛሬ ምን ቢገኝ ነዉ ልትጎበኙን የመጣችሁት የሚሉ ድምፆች ሲስተጋቡ ነበር ተብሏል፡፡ አንዲሁም በአከባቢዉ የሚኖሩ የኤርትራ አፋሮች ለጉብኝቱ ያላቸዉን ተቃዉሞ በባህላቸዉ ስርዓት ሲገልፁ ተስተዉሏል፡፡

ሚስት ባሏን ደሀ ነህ ብላ በፈታች በማግስቱ ባል 273 ሚሊዮን ዶላር ሎተሪ አሸነፈ።ሰውዬው ለተወሰነ ጊዜ ሥራ አጥ ነበር እና ሚስቱ በሂደቱ ላይ እምነት መጣል ትዕግስት ስለሌላት ወደ ፊት ለ...
15/12/2024

ሚስት ባሏን ደሀ ነህ ብላ በፈታች በማግስቱ ባል 273 ሚሊዮን ዶላር ሎተሪ አሸነፈ።

ሰውዬው ለተወሰነ ጊዜ ሥራ አጥ ነበር እና ሚስቱ በሂደቱ ላይ እምነት መጣል ትዕግስት ስለሌላት ወደ ፊት ለመቀጠል ወሰነች። ሆኖም የፍቺ ሰነዶችን ከፈረመ ከአንድ ቀን በኋላ ህይወቱን ሙሉ በሙሉ የሚለዉጠውን ሎተሪ አሸንፏል።

ይህም አለ። ገና ሌላም አለ።
07/12/2024

ይህም አለ። ገና ሌላም አለ።

07/12/2024

በመላው ሀገሪቱ ከተቋረጠው ኃይል ከግማሽ በላይ የሚሆነው ወደነበረበት እየተመለሰ ነው.......///.........
በመላው ሀገሪቱ ከተቋረጠው ኃይል ከግማሽ በላይ የሚሆነው ወደነበረበት እየተመለሰ መሆኑን የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታወቀ።

ማዕከሉ እንዳስታወቀው በአዲስ አበባ 85 በመቶ በሚሆነው በአብዛኛዎቹ አካባቢ፣ በአዳማ፣ በሀዋሳ፣ በጅማ፣ አርባምንጭ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሻሸመኔ፣ ወልቂጤ፣ መቀሌ፣ አድዋ፣ አላማጣ፣ ዲላ፣ ቦንጋ፣ ሚዛን እና ሀገረማርያም ኃይል ተመልሶ ተገናኝቷል።

እስካሁን ከ50 በመቶ በላይ በሚሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ኃይል መመለሱን የገለፀው ማዕከሉ በቀሪዎቹ አካባቢዎች መልሶ ለማገናኘት ርብርቡ መቀጠሉን ገልጿል።

የተፈጠረው ችግር ሙሉ በሙሉ እስኪቀረፍ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁም ጠይቋል።

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia
ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/
ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et
ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም

ጃውሳ ማለት ይኼ ነው። ይህ ዘር ማጥፋት ካልተባለ ምን ሊባል ነው? ከታች የተዘረዘሩት ጃውሳው በጎጃም በጅምላ የፈጃቸው የደጋ ዳሞት ወረዳ አመራሮች ናቸው። እና ይህ ምን ሊባል ነው?1• አቶ...
06/12/2024

ጃውሳ ማለት ይኼ ነው። ይህ ዘር ማጥፋት ካልተባለ ምን ሊባል ነው?
ከታች የተዘረዘሩት ጃውሳው በጎጃም በጅምላ የፈጃቸው የደጋ ዳሞት ወረዳ አመራሮች ናቸው። እና ይህ ምን ሊባል ነው?

1• አቶ ዋለ አለማየሁ...አስተዳዳሪ
2• ቄ/እንዳለ ገበየሁ...ኮሚኒኬሽ ጽ/ቤት ኃላፊ
3• ዘመኑ ይባቤ...እንስሳት ሀብት ጽ/ቤት ኃላፊ
4• አይናለም ስንሻው...ውሃ ጽ/ቤት ኃላፊ
5 • አንቢዛው ጠቅላይ...ትም/ጽ/ቤት ም/ኃላፊ
6• ወንድይፍራው ጌታነህ...አስ/ጽ/ቤት ኃላፊ
7• ጌታሰው ውቤ...ሲቭልሰርቪስ ጽ/ቤት ኃላፊ
8• ተመስገን መኮነን...ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ኃላፊ
9• ሞላ አንተነህ..ስፖርት ጽ/ቤት
10• ይፍረድ ወንድሜነህ...መንገድ ጽ/ቤት ኃላፊ
11• አስፋው ስንሻው...ገንዘብ ጽ/ቤት ኃላፊ
12• ጌታቸው የሽዋስ...ጤና ጽ/ቤት
13• ተከታይ ውድነህ ገቢዎች ሀላፊ
14• ምግባሩ አእምሮ መዘጋጃ ምክትል
15• ማስተዋል አሻግሬ አፈጉባኤ
16• ጎሹ ወርቄ መሬት ሀላፊ
17 • ብናየው ምስጋናው -ንግድ ሀላፊ
18• ከፋለ ንብረት መስኖና ቆላማ ጽ/ቤት
19• አበበ ይስማው ማህበራት ሀላፊ
20• ዘመኑ ሙሉነህ ፖሊስ
21• አሰሜ መኮነን ምሊሻ
22• ምስጋናው ምሊሻ
23• ይላቸው ፈንታ ምሊሻ
24• አንሙት አየነው ምሊሻ ባለሙያ
25• የኔሰው ምሊሻ
26• ሽብሬ አፈንጉስ ግብርና ባለሙያ
27• ማተቤ ተመስገን ገቢ ባለሙያ
28• በላይ ዋለ-ገቢዎች ቡድን መሪ
29• አብርሃም ደነቀው-ሚሊሻ
30• .ይዘንጋው ነዋሪ መረጃ ነህ ተብሎ የታሰረ
31.እንየው አስማረ-ነዋሪ መረጃ ነህ ተብሎ.

ሰሞኑን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እና የኦነሰ አመራሮች የተፈራረሙትን ስምምነት ተከትሎ በርካታ ታጣቂዎች ወደ ተዘጋጀላቸው ካምፖች እየገቡ ነው። ቄለም ወለጋን ጨመሮ በተለያዩ የክልሉ ዞኖች ...
06/12/2024

ሰሞኑን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እና የኦነሰ አመራሮች የተፈራረሙትን ስምምነት ተከትሎ በርካታ ታጣቂዎች ወደ ተዘጋጀላቸው ካምፖች እየገቡ ነው። ቄለም ወለጋን ጨመሮ በተለያዩ የክልሉ ዞኖች መሽገው የነበሩ ታጣቃዎች እየገቡ መሆኑን ለመረዳት ችለናል።

05/12/2024

Watch, follow, and discover more trending content.

    Mariin Araaraa   waliin godhamuu kana booda akka hin jirre dubbatani jiru. Humnoonni Bosonaa jiraan gareen garagaraa...
04/12/2024



Mariin Araaraa waliin godhamuu kana booda akka hin jirre dubbatani jiru. Humnoonni Bosonaa jiraan gareen garagaraa Marii kana bu'uura godhachuudhan galuu akka qabanis dhaamaniru.

  ኢንቨስትመንት በኡጋንዳ ኡጋንዳ በ46 ሚሊዮን ብር መነሻ 7F Agro እሚል ስያሜ ያለው ድርጅት መስርቷል ። ድርጅቱን እሚመራው ያርጋል እሚባል የዘመነ የቅርብ ሰው ነው ::የሚከራዩ ገስት...
03/12/2024

ኢንቨስትመንት በኡጋንዳ

ኡጋንዳ በ46 ሚሊዮን ብር መነሻ 7F Agro እሚል ስያሜ ያለው ድርጅት መስርቷል ። ድርጅቱን እሚመራው ያርጋል እሚባል የዘመነ የቅርብ ሰው ነው ::

የሚከራዩ ገስት ሀውሶችን ገዝተዋል:: አሁን ደግሞ ለደቡብ ሱዳንና ሯንዳ ኮካኮላ ለማከፋፈል ኮንትራት እየወሰዱ ነው:: ይህ ቢዝነት እጅግ ግዙፍ ነው በብዙ መቶ ሚሊዮኖች የባንክ ዋስትና ሚሰራ ነው::


1.ጎዛመን ዩኔን (የገበሬዎች ህበረት ስራ ማህበር ) መጋዘን የ80 ሚሊዮን ብር ሰብል ተዘርፎ ተሽጦ ወደ ዘመነ ቤተሶች አካውንት ተላለፈ ።

2. ከ8 ባንክ ከ105 ሚሊዮን ብር በላይ በእነ ዘመነ ፋኖ ተዘርፏል ።

3. ከመከላከያ የተነጠቀ በሚል ከሰከላ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የወጣው 33 ሚሊዮን ብር እንዲሁ ወደ ባንኩ ሳይመለስ ወደ ዘመነ ቤተሰቦች አካውንት እንዲገባ ተደርጓል ። (በአካውንታቸው እሚገባው የዘመነ ቤተሰቦችና የቅርብ ሰዎች ቋሚ ቢዝነስ ያላቸውና በመንግሥት እማይጠረጠሩ ሰዎች ናቸው )

4. የወርቁ አይተነውን ፋብሪካ ሲቆጣጠሩ የነበረው ዘይት ለህዝብ ሰጠነው ብለው ግን 90% በላይ ተሽጧል ። ይሄም 25 ሚሊዮን ብር ነው ።

በአጠቃላይ ዘመነ ካሴ ከህዝብ በተዘረፈ ገንዘብ ምስራቅ አፍሪካ ላይ የተለያዩ ኢንቨስትመቶችን በመክፈት በትግል ስም ቱጃር እየሆነ ነው ። ወደፊት ከመንግሥት ጋር በድርድር ሲገባ ከቢሌነሮች አንዱ ሁኖ በሀገሪቱ የመንቀሳቀስ ሀሳብ ነው ያለው ።

03/12/2024

የሕዝቡን ጥሪ ተቀብለው እንደዚህ እየገቡ ነው። እጅግ ደስ ይላል።

🕊[የሰላም መጥፎ የጦርነት ጥሩ የለውም!]ይሄንን ዕርቀ ሠላም በምንም መልኩ ልታጠለሸው ከቶውንም አይቻልህም። አዳሜ ሞራልም የለህም!!!ለመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ትልቅ ስኬት እና ድል ነው።ሰሞኑ...
03/12/2024

🕊
[የሰላም መጥፎ የጦርነት ጥሩ የለውም!]
ይሄንን ዕርቀ ሠላም በምንም መልኩ ልታጠለሸው ከቶውንም አይቻልህም። አዳሜ ሞራልም የለህም!!!

ለመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ትልቅ ስኬት እና ድል ነው።

ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል መንግስት እና በኦነሰ መሃከል በተደረገው ስምምነት በርካታ የቡድኑ ታጣቃዎች ወደተዘጋጀላቸው ማቆያ እየገቡ ነው።

02/12/2024

የህዝብን ድምፅ ጥሪ ተቀብላቹ
ለሰላም የተሰለፋቹ ከኦሮሞ ህዝብ ምስጋና አላቹ

Address

Adama
Shewa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሌተ/ጄኔራል ይልማ መርዳሳ አድናቂ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to የሌተ/ጄኔራል ይልማ መርዳሳ አድናቂ:

Videos

Share