Feta daily Extra

  • Home
  • Feta daily Extra

Feta daily Extra Daily updated news,feta daily news,ethiopia

ሰበር ዜና‼️➖➖ሾዴ የተባለው የሸኔው መሮ ዋና ሰው ተገደለ።ሾዴ እየተባለ የሚጠራው የሸኔው መሮ ዋና ሰው እንደሆነ የሚታወቀው መገደሉ ተገለፀ። የመሮ ዋናው ሰው የነበረው እንዲሁም በታንዛኒያ...
05/04/2025

ሰበር ዜና‼️
➖➖
ሾዴ የተባለው የሸኔው መሮ ዋና ሰው ተገደለ።

ሾዴ እየተባለ የሚጠራው የሸኔው መሮ ዋና ሰው እንደሆነ የሚታወቀው መገደሉ ተገለፀ።

የመሮ ዋናው ሰው የነበረው እንዲሁም በታንዛኒያው ድርድር ከጫካ ወጥቶ ታንዛኒያ ዳሬሰላም ድረስ ከመሮ ጋር ተጉዞ የሸኔ ሽብር ቡድን ተደራዳሪ የነበረው ሾዴ በተወሰደበት እርምጃ ተገድሏል።

ሾዴ የተባለው የሽብር ቡድኑ አመራር ከታንዛኒያ መልስ የአጠቃላይ የወለጋ ዞኖች አዛዥ ተደርጎ በመሮ ተሹሞ የነበረ መሆኑ የሚታወቅ ነው።

ሾዴ የተገደለው ምስራቅ ወለጋ ዞን ሃሮ ሊሙ ወረዳ ገንጂ አካባቢ ከኮርማ ወንዝ ወደ ሱጊ በሚወሰደው መንገድ ላይ በሞተር ሳይክል ተደብቆ ሲጓዝ የፀጥታ ኃይሎች ባገኙት መረጃ መጋቢት 26 ቀን 2017 ዓ.ም አመሻሽ ላይ እርምጃ ተወስዶበታል።

ከሾዴ ጋር አብረው አጅበው ሲጓዙ የነበሩ በርካታ የሸኔ ሽብር ቡድን አባላትም ተደምስሰዋል።

ከሠሞኑ በሰሜን ሸዋ ዞን እና በሌሎችም አካባቢዎች የአሸባሪው ሸኔ ታጣቂዎች ክፉኛ እየተመቱ በቁጥጥር የዋሉ ሲሆን አሁንም ቢሆን የሸኔ ታጣቂዎች የመከላከያ ሠራዊቱን ምት መቋቋም ተስኗቸው እየተፍረከረኩ እጅ እየሠጡ እየተማረኩ እርምጃ እየተወሰደባቸውና እየተበተኑ ይገኛሉ።

Check out and kindly join our telegram
04/04/2025

Check out and kindly join our telegram

TOGETHER, WE SET THE SUN AND GROW STRONG

11/09/2024

በ 2017 ደሞ ምን እንስበር

ፍትህ ለ ሄቨን ሁላችሁም share አድርጉ ,🥺😭
19/08/2024

ፍትህ ለ ሄቨን ሁላችሁም share አድርጉ ,🥺😭

" ባንኮች የገንዘብ እጥረት ላጋጠማቸው ባንኮች ማበደር ይችላሉ " - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ካደረገው አዲሱ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ከወሰዳቸው እርምጃዎች አንዱ...
10/07/2024

" ባንኮች የገንዘብ እጥረት ላጋጠማቸው ባንኮች ማበደር ይችላሉ " - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ካደረገው አዲሱ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ከወሰዳቸው እርምጃዎች አንዱ ፦

" የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባንኮች እርስ በርስ የሚበዳደሩበትን የተነቃቃ የገንዘብ ገበያ ለመመሥረት የሚያስችል የኤሌክትሮኒክ ግብይት ሥርዓት በቅርቡ ለመዘርጋት ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

የገንዘብ ገበያው በኤሌክትሮኒክ የግብይት ሥርዓት ላይ ተመሥርቶ በሚገባ ሥራ ላይ ሲውል ትርፍ ገንዘብ ያላቸው ባንኮች የገንዘብ እጥረት ላጋጠማቸው ባንኮች ማበደር ይችላሉ፡፡

በመሆኑም፣ ባንኮች የገንዘብ እጥረት ሲገጥማቸው ወይም ትርፍ ገንዘብ ሲኖራቸው እርስ በርስ የመገበያየት ዕድል ይኖራቸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ፣ ይህ አሠራር ሥራ ላይ ሲውል የባንክ ለባንክ የወለድ ተመን ከማዕከላዊ ባንኩ የፖሊሲ-ነከ የወለድ መጣኔ ጋር የሚጣጣም ሲሆን፣ ይህ ካልሆነ ግን ብሔራዊ ባንኩ ሁኔታውን ለማስተካከል ከባንኮች ጋር የግብይት ጨረታን ይጠቀማል፡፡ "

" ከዛሬ ጀምሮ በየትኛውም የፋይናንስ ተቋም ገንዘብ ያስቀመጡ ሰዎች ገንዘባቸው በገንዘብ መድን ፈንድ ዋስትና ያገኛል "በኢትዮጵያ በባንኮች ገንዘብ ከሚያስቀምጡት አብዛኛዎቹ ወይም 95 በመቶ ...
03/11/2023

" ከዛሬ ጀምሮ በየትኛውም የፋይናንስ ተቋም ገንዘብ ያስቀመጡ ሰዎች ገንዘባቸው በገንዘብ መድን ፈንድ ዋስትና ያገኛል "

በኢትዮጵያ በባንኮች ገንዘብ ከሚያስቀምጡት አብዛኛዎቹ ወይም 95 በመቶ የሚሆኑት በባንክ ያለው የገንዘብ መጠን ከ100,000 ብር በታች መሆኑ ተገለፀ።

ይህ የተገለፀው ኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ወደ ሥራ መግባቱን በተነገረበት ጊዜ መሆኑን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

በተለያዩ ገንዘብ ተቋማት ላለ ተቀማጭ ገንዘብ ዋስትና የሚሰጥ የገንዘብ መድን ፈንድ ተቋቁሞ ዛሬ በይፋ ስራ ጀምሯል፡፡

ይህ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ተጠሪነቱ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነው ተብሏል።

ከዛሬ ጀምሮ በየትኛውም የፋይናንስ ተቋም ገንዘብ ያስቀመጡ ሰዎች ገንዘባቸው በዚሁ ፈንድ ዋስትና ያገኛል የተባለ ሲሆን ጥበቃው የሚመለከተው 100,000 ብር እና ከዚያ በላይ የሆነን ብቻ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ መርጋ ዋቆያ ተናግረዋል።

ይህም በፋይናንስ ዘርፍ ላይ ከተፈፀሙ ለውጦች አንዱ ነው ተብሏል።

ፈንዱ አደረጃጀቱ ምን ይመስላል የሚለውን የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደስታ ተናግረዋል። የፈንዱ ስልጣንና ተግባር በክፍያ ካዝናነት የተገደበ ነው ተብሏል።

አላማው ህዝባዊ ነው የተባለ ሲሆን የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ ፈንድ በመንግስት እንደሚተዳደር ተገልጿል።

ምክትል ገዢው አንድ የፋይናንስ ተቋም የሚወድቅ ከሆነ ኮሽታ ሳያሰማ ህዝቡን ሳይረብሽ ኢኮኖሚውንም ሳይረብሸው እንዲወጣ ፈንዱ ይሰራል ብለዋል።

ይህ በሚሆን ጊዜም በመድን የተሸፈነውን ገንዘብ ለአስቀማጩ ከ 7 ቀን እስከ 90 ቀን ባነሰ ጊዜ ውስጥ እንደሚመለስ አስረድተዋል።

147 ሀገራት የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ተቋም አላቸው የተባለ ሲሆን ኢትዮጵያ 148ተኛ ሀገር ሆናለች።

የዚህ መረጃ ባለቤት ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

ከሰሞኑ በወለጋ ከተከሠተው የንፁሃን ኢትዮጵያውያን ግድያ ጋር ተያይዞ የመከላከያ  ወታደራዊ ዩኒፎርም የለበሰና ሰልፊ የሚነሳ ወታደር ምስል በማህበራዊ ሚዲያ የማሠራጨቱ ዘመቻ ሆን ተብሎ የተቀ...
07/12/2022

ከሰሞኑ በወለጋ ከተከሠተው የንፁሃን ኢትዮጵያውያን ግድያ ጋር ተያይዞ የመከላከያ ወታደራዊ ዩኒፎርም የለበሰና ሰልፊ የሚነሳ ወታደር ምስል በማህበራዊ ሚዲያ የማሠራጨቱ ዘመቻ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ በንፁሃን ደም የሚነግዱ የሴረኞች ተግባር መሆኑን በአፅንኦት እንገልፃለን፡፡

ሁሉም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን እንደሚገነዘቡት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ተልዕኮውን እና የቆመለትን ዓለማ ጠንቅቆ የሚያውቅ ፤ መተኪያ የሌላት ህይወቱን ሰውቶ ሀገሩን እና ህዝቡን የሚታደግ መሆኑን የለፈው ሁለት ዓመት በተግባር ያሳየ ነው። በተጨማሪም ሠራዊታችን በህዝባዊ ወገንተኝነቱ ተምሳሌት የሆነ ሃይል መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡

እውነታው ይህ ሆኖ እያለ የሀገራችን ሠላም ዕውን መሆን የሚያንገሸግሻቸው ፤ የህዝባችን በሠላም ወጥቶ መግባት የሚጎረብጣቸው የንፁሃን ሞት ነጋዴዎች፤ በህዝብ ደም የመነገድ አባዜ የተጠናወታቸው ሃይሎች አሁንም በሴራ የተጎነጎነ ተንኮል መሸረባቸውን ቀጥለዋል፡፡

ከሠሞኑ በወለጋ ከተከሠተው የንፁሃን ግድያ ጋር ተያይዞ የመከላከያ ወታደራዊ ዩኒፎርም የለበሰ ምስል በፎቶ ሾፕ የተቀነባበረ ፎቶ በማህበራዊ ሚዲያ በማሰራጨት መከላከያ ሠራዊቱ ላይ ጥላሸት የመቀባት ዘመቻ ከፍተዋል፡፡

አንደኛ መከላከያ ሠራዊቱ ሀገሩንና ህዝቡን በመታደግ የተጎናፀፈውን ክብር: ታማኝነት እና ጀግንነት ለመሸርሸር ታስቦ የተሠራ ነው።

ሁለተኛ በታሪክ በመደጋገፍ: በመከባበር እና በአብሮነት ዘመናትን የተሻገረው ህዝባችን በብሄር ስም አንዱ ከሌላው ጋር ግጭት እንዲፈጥር እና የመተማመኑና የአብሮነቱ መረብ እንዲበጠስ ሆን ተብሎ ታስቦበት የተቀነባበረ የፎቶ ቅንብር መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

ይህ ለሠላም ሳይሆን ለጥላቻ ፤ለመወዳጀት ሳይሆን ለማለያየት ፤ለማሥማማት ሳይሆን ለማነጣጣል ትኩረት ሠጥተው በሠው ደም የሚነግዱ የጥላቻ እና የግጭት ነጋዴዎች ሁለት እና ከዚያ በላይ ፎቶዎችን አቀነባብረው የመከላከያ ሠራዊት በማሥመሠል ኢትዮጵያ የሠላም እና የልማት ሀገር በመሆኗ ፈንታ በየጊዜው የጦርነት ነጋሪት የሚጎሠምባት ሀገር እንድትሆን እንቅልፍ አልባ ቀን ከሌሊት የሚሠሩ የጠላቶቻችን ሴራ ተግባር መሆኑን እናሥገነዝባለን፡፡

ተደራዳሪዎቹ ደቡብ አፍሪካ ገብተዋል!ከህወሓት ተደራዳሪዎች መካከል 👉ጄነራል ፃድቃን ገብረትንሳይ እና 👉አቶ ጌታቸው ረዳ እንደሚገኙበት ተዘግቧል።በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥትና በህወሓት መካከል...
24/10/2022

ተደራዳሪዎቹ ደቡብ አፍሪካ ገብተዋል!

ከህወሓት ተደራዳሪዎች መካከል
👉ጄነራል ፃድቃን ገብረትንሳይ እና
👉አቶ ጌታቸው ረዳ እንደሚገኙበት ተዘግቧል።

በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥትና በህወሓት መካከል ዛሬ፤ ሰኞ ይጀመራል ለተባለው የሠላም ንግግር የሁለቱም ወገኖች ተደራዳሪዎች ደቡብ አፍሪካ መግባታቸው ተሰምቷል!!

ምንም እንኳ ድርድሩ የሚካሄድበት ትክክለኛ ቦታና ሰዓት በጥብቅ ምሥጢር የተያዘና እስካሁንም ያልተገለፀ ቢሆንም የህወሓት ቃል አቀባይ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት ዛሬ ባወጡት ትዊት ተደራዳሪዎቻቸው ደቡብ አፍሪካ መግባታቸውን አስታውቀዋል።

“በአፍሪካ ኅብረት በሚመራው የኢትዮጵያ ትግራይ የሠላም ንግግር ላይ ለመገኘት የትግራይ መንግሥት ልዑካን ቡድን ደቡብ አፍሪካ ገብቷል” ብለዋል። ቃል አቀባዩ በዚሁ ትዊታቸው ላይ አክለውም “እጅግ አንገብጋቢ ጉዳዮች” ሲሉ ባሠፈሩት ዝርዝር “ውጊያ ፈጥኖ እንዲቆም፣ ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦትና የኤርትራ ኃይሎች መውጣት” ብለዋል።ይሁን እንጂ እነዚህ ነጥቦች ቅድመ ሁኔታ ይሁኑ አይሁኑ የጠቆሙት ነገር የለም።

የድርድሩ ነጥቦችና ጭብጦች ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ እስካሁን የወጣ መረጃ የለም።

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ዩናይትድ ስቴትስን በእጅጉ እንደሚያሳስባት የተናገሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አንተኒ ብሊንከን የሰኞው የደቡብ አፍሪካ ድርድር በቅን መንፈስ እንዲካሄድ ጥሪ አድርገው ተኩስ በአስቸኳይ እንዲቆም፣ ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲኖር፣ የኤርትራ ኃይሎች ከሰሜን ኢትዮጵያ እንዲወጡ ማሳሰባቸውን ቃል አቀባያቸው ኔድ ፕራይስ ገልፀዋል።ከአፍሪካ ኅብረት በይፋ የተሰጠ መግለጫ እስካሁን የለም ሲል ቪኦኤ ዘግቧል።

ተጨማሪ መረጃዎች

ኢትዮጵያና ሱዳን ያጋጠሟቸውን ችግሮች በወንድማማችነትና በመልካም ጉርብትና መንፈስ የመፍታት አቅም አላቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵ...
29/06/2022

ኢትዮጵያና ሱዳን ያጋጠሟቸውን ችግሮች በወንድማማችነትና በመልካም ጉርብትና መንፈስ የመፍታት አቅም አላቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ እና ሱዳንን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ የሱዳንና የኢትዮጵያ ህዝቦች ወንድማማቾች መሆናቸውን ገልጸዋል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል ችግር መኖሩ ግልፅ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ነገር ግን ሁለቱ ሀገራት እነዚያን ችግሮች ለመፍታት ሊጥሩ እና ሊተባበሩ ነው የሚገባው ብለዋል።
የሀገራቱን መጋጨት የሚፈልጉ መንግስታት ወይም ሌሎች ወገኖች ቢኖሩም እነዚህ አካላት ከሁለቱ ሀገራት ህዝቦች ግጭት የሚያተርፉት አይኖርም ሲሉ አስረድተዋል።
በውጭ ሀይል ግፊት በሁለቱ ሀገራት መካከል ውዝግብ ሊኖር እንደማይግባ በማንሳትም ራሳችንን ልንቆጣጠር እና ከግጭት ልንቆጠብ ይግባል ሲሉም አሳስበዋል።
በመካከላችን የጠላትነት መንፈስ ሊኖር አይግባም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ ይልቁንም በልማት ልንተባበር እና አብረን ልናድግ ይገባናል ነው ያሉት።
ለሱዳን ህዝብ ክብር አለን በማለትም የሁለቱ ሀገራት ህዝቦች ያጋጠማቸውን ችግር በወንድማማችነትና በመልካም ጉርብትና መንፈስ የመፍታት አቅም እንዳላቸው አብራርተዋል።

የጠሚ አቢይ አህመድ ጉዞ በናይጄሪያ ጠሚ አቢይ በናይጄሪ በነበራቸው የ14 ሰዓታት ቆይታን በተመለከተ በሶሻል ሚዲያ ላይ ብዙ ነገሮችን ሲጻፍ ተመልክቻለሁ በተለይ የህወሓት ደጋፊዎችን ብሎም የ...
01/06/2022

የጠሚ አቢይ አህመድ ጉዞ በናይጄሪያ

ጠሚ አቢይ በናይጄሪ በነበራቸው የ14 ሰዓታት ቆይታን በተመለከተ በሶሻል ሚዲያ ላይ ብዙ ነገሮችን ሲጻፍ ተመልክቻለሁ በተለይ የህወሓት ደጋፊዎችን ብሎም የህወሓቱ ብርሃነ ገ/ክስቶስን አግኝተውት ተነጋግረዋል የወልቃይት መሬትን ለህወሓት ሊሰጡ ነው... እሚሉ በሬ ወለደ ፍጹም እማይመስል ነገሮች ተጽፎ ተመልክቻለሁ ይህን ለማጣራት ጠሚ አቢይ ይዘዋቸው ከሄዱትና አብረዋቸው ከነበሩት ልዑካን ቡድን ውስጥ ያወራዋቸው ነበሩ ስለ ጠሚ አቢይ ጉዞ በዝርዝር ጠይቂያቸዋለሁ ይህን ብለውኛል 👇

ጠቅላይሚንስትሩ እና ልዑካቸው አቡጃ የደረሱት ጥዋት በናይጀርያ ሰዓት ሶስት ሰዓት በሁላ ነው በኢትዮጵያ አምስት ሰዓት ማለት ነው። ከዛ ከኤርፖርት እስከ አቡጃ የአንድ ስዓት ጉዞ አለ። ሆቴል በግምት አንድ ሰዓት ባልበለጠ ቆይታ አድርገው ቀጥታ ከፕሬዘዳንት ቡሀሪ ጋር ነው የተገናኙት። እዛም እስከ ቀኑ 9:00 ቆይተዋል። ከዚህ በሁላም እስከ ምሽት 12:00 ድረስ በአቡጃ የተለያዩ ቦታዎች ጉብኝት ላይ ነበሩ። በቀጣይ ቀን ጥዋት ወድ ማላቦ ነው የተጓዙት። እንግዲህ በተጣበበ ፕሮግራማቸው ነው ከትግራይ ዲያስፖራዎች ጋር ተወያይተዋል የሚሉት። ፍጹም ውሸት ብቻ ሳይሆን ሆን ብሎ በጠቅላይሚንስትሩ ላይ የአማራ ህዝብ ጥርጣሬ እንዲኖር የማድረግ ሰሞናዊ የሸፍጥ ፖለቲካ ውጤት ነው።

Address


Telephone

+251913358017

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Feta daily Extra posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share