01/10/2023
ዛሬ መስከረም 20 ቀን 2016 ዓ.ም ንጋት 11 ሰዓት ላይ የሰሌዳ ቁጥሩ 3-B29228 ፒክአፕ ደብል ጋቢና የሆነ ተሽከርካሪ የጉዞ አቅጣጫዉን ወደለገጣፎ አድርጎ ሲጓዝ ጣፎ አደባባይ ጋ ሲደርስ ዋናዉን መንገድ ጥሶ ገደል ዉስጥ በመግባቱ አሽከርካሪዉን ጨምሮ የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ አንድ ሰዉ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የሁለቱን ሰዎች አስከሬንና ተሽከርካሪዉን ከገደል ዉስጥ ያወጡት ሲሆን ይህም ሂደት 1 :20 ሰዓት ፈጅቷል።
በአደጋዉ ጉዳት የደረሰበት ሰዉ ህክምና እየተደረገለት የሚገኝ ሲሆን የአደጋዉ መንስዔ በትራፊክ ፖሊስ እየተጣራ ነው ሲል ኮሚሽኑ አስታውቋል።