27/04/2025
የ 10 አገራት የመገበያያ ገንዘብ በአሜሪካው ዶላር የዛሬ ሽያጭ (ምንዛሬ) ዋጋ ከዚህ እንደሚከተለው ነው፦
⩩
1| ኢትዮጵያ ➔ 1 dollar = 133.45 Birr (ብር¹)
2| ቬትናም ➔ 1 dollar = 26,021.47 d**g
3| ኢንዶኔዥያ ➔ 1 dollar = 16,828.56 Rupiah
4| ማሌዥያ ➔ 1 dollar = 3,841.79 Rupiah
5| ኡጋንዳ ➔ 1 dollar = 3,665.60 Shilling
6| ታንዛኒያ ➔ 1 dollar = 2,686.67 Shilling
7| ናይጀሪያ ➔ 1 dollar = 1,608.72 Naira
8| ደቡብ ኮሪያ ➔ 1 dollar = 1,440.83 won
9| ፓኪስታን ➔ 1 dollar = 280.95 Rupee
10| ኬንያ ➔ 1 dollar = 129.50 Shilling
[ወዳጄ ልቤ!...]
➊ የኢትዮጵያ ብር የወደቀ ነው የሚሉህ የወደቁ ናቸው። የኢትዮጵያ ብር ከወደቀ የቬትናም፣ ኢንዶኔዥያ፣ ማሌዥያ፣... ብር ምን ሊባል ነው? አስቀድሜ የጠቀስኳቸውን ሃገራት ጠቅል ሃገራዊ ምርት፣ የኢኮኖሚ ደረጃ፣ የገቢ መጠን፣... ወዘተ ትንሽ Browse አድርገህ አንብብ...
➋ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ምርታማ አይደለም። 85% ህዝባችን በግብርና ላይ ተሰማርቷል ብለን ስናበቃ ከዛሬ ሦስት ዓመት በፊት ስንዴ ስንገዛ ነበር። በአፍሪካ በቀንድ ከብት አንደኛ ነን ብለን ስናበቃ ስጋ ከኬንያ እንገዛለን። ሸራተን ሆቴል እና Sky light hotel ስጋ የሚገዙት ከኬንያ ነው 🤔 መንግስት ምርት እናምርት፣ የከተማ ግብርና፣ የበጋ ስንዴ፣ የሌማት ትሩፋት፣... ወዘተረፈ የሚለው ምርትና ምርታማነታችንን ለማሳደግ የዳቦ ቅርጫታችንን ለመሙላት ነው።
ዛሬም ዘይት ከውጭ ገዝተን እናስገባለን። ጫማ፣ ልብስ፣ የጽሕፈት መሳሪያ፣ የጸጉር ቅባት፣ መድሃኒት፣ የቤት ቁሳቁስ፣ ነዳጅ፣ አትክልትና ፍራፍሬ (ሽንኩርት ሳይቀር 😂)፣ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪ ከእነመለዋወጫው፣ ማሽነሪ፣ ወዘተረፈ በውጭ ምንዛሬ ገዝተን የምናስገባ ጉዶ'ች ነን።
[መፍትሄው]
[ሀ] ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሃገር ውስጥ ማምረት፣
[ለ] የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ ብዙ ምርት ወደውጭ መሸጥ
[ሐ] ማምረት! ማምረት ! አሁንም ማምረት !