ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ትኩስ ዜናዎችን አስተማሪና አዝናኝ መረጃዎችን እናደርሳለን ! (Ethiopia )

"የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ
26/11/2023

"የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ

"አባቴ ክፉህን አያሳየኝ
26/11/2023

"አባቴ ክፉህን አያሳየኝ

Ethiopia - ኢትዮጵያ
25/11/2023

Ethiopia - ኢትዮጵያ

የስኬት ቀላል ህጎች1ኛ በራስህ እመን ግን ደግሞ ደካማ ጎንህን ተረዳ2ኛ ችግሮችን አቅልለህ ተመልከት3ኛ ሁኔታዎችን በወቅቱ አስተውለህ ተመልከት4ኛ ራስህን  በእውቀት ገንባ5ኛ በጎ እይታዎችን...
24/11/2023

የስኬት ቀላል ህጎች
1ኛ በራስህ እመን ግን ደግሞ ደካማ ጎንህን ተረዳ
2ኛ ችግሮችን አቅልለህ ተመልከት
3ኛ ሁኔታዎችን በወቅቱ አስተውለህ ተመልከት
4ኛ ራስህን በእውቀት ገንባ
5ኛ በጎ እይታዎችን አዳብር!

ወዳጄ የምትፈልገውን አይነት የወደፊት ሕይወት መፍጠር የምትችለው እስካሁን ያለውን ሕይወትህን አንተ እንደፈጠርከው ማመን ስትችል ነው ፡፡ "99% የሚሆኑ ውድቀቶች የሚመጡት ስበብ የመፍጠር ል...
23/11/2023

ወዳጄ የምትፈልገውን አይነት የወደፊት ሕይወት መፍጠር የምትችለው እስካሁን ያለውን ሕይወትህን አንተ እንደፈጠርከው ማመን ስትችል ነው ፡፡ "99% የሚሆኑ ውድቀቶች የሚመጡት ስበብ የመፍጠር ልምድ ባላቸው ሰዎች ነው" ጆርጅ ዋሽንግተን ፡፡ ዛሬ የምታልፍበት ነገር ሁሉ የትናቱ ምርጫ ውጤት ነው ፡፡ በሕይወትህ ልትቆጣጠራቸው የምትችላቸው ሶስት ነገሮች ብቻ አሉ፡፡ እነሱም
1 የምታስባቸውን አሳቦች
2 በአምሮህ የምትስላቸውን ምስሎች
3 የምትወስዳቸውን እርምጃዎች፡፡ በተለመደ ተግባር/ባህሪ/ በመቀጠል የተለየ ውጤት ማግኘት የማይታሰብ ነው!!!

የሀገሬ መልክ
21/11/2023

የሀገሬ መልክ

"ሀገሬ ምነው ምጥሽ በረታ ኤሎሔ ኤሎሔ ...
21/11/2023

"ሀገሬ ምነው ምጥሽ በረታ ኤሎሔ ኤሎሔ ...

የቀይ ባህር ጂኦ ፖለቲካዊ ሁኔታ ልዩ ትኩረት በአፋር ሦስት ማዕዘናዊ አቀማመጥ(ክፍል አንድ)በተሾመ ብርሃኑ ከማልመንደርደሪያጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ዓርብ ጥቅምት 2 ቀን 20...
19/11/2023

የቀይ ባህር ጂኦ ፖለቲካዊ ሁኔታ ልዩ ትኩረት በአፋር ሦስት ማዕዘናዊ አቀማመጥ
(ክፍል አንድ)

በተሾመ ብርሃኑ ከማል

መንደርደሪያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ዓርብ ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የቀይ ባህር ጉዳይን በሚመለከት 45 ደቂቃ ያህል የወሰደ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህርና ህንድ ውቅያኖስ ለመውጣት የሚያስችላትን በር መጠየቋ አግባብነት እንዳለው ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ወደ ኤርትራና ሱዳን ተከዜ፣ ወደ ግብፅና ሱዳን ዓባይ፣ ወደ ደቡብ ሱዳን ባሮ፣ ወደ ኬንያ ኦሞ፣ ወደ ሶማሊያ ደግሞ ገናሌ፣ ዳዋና ዋቢ ሸበሌ ወንዞች ከኢትዮጵያ ተነስተው እንደሚጓዙ፣ ወደ ጂቡቲ የውኃ መስመር በኢትዮጵያ ወጪ መገንባቱን አውስተው ኢትዮጵያ ከእነዚህ አገሮች አንዳቸው እንኳን “ለኢትዮጵያ ንፁህ ውኃ የሚሰጥ የለም፣ ሁሉም ተቀባይ ነው፤›› ካሉ በኋላ፣ ‹‹ሀቁ ይህ ሆኖ ሳለ የእናንተን እንካፈል የእኛን አትጠይቁ ማለት ግን ትክክል አይደለም፤” በማለት ተናግረዋል።

መስከረም 10 ቀን 2016 ዓ.ም. ‹‹የቀይ ባህር የደኅንነት ሁኔታ ቀጣናዊ ምክክርና ትብብር መልከዓ ፖለቲካዊ መጠላለፍ በበዛበት ዓለም ወቅት›› በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ጉባዔ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ካደረጉ የተመረጡ የውጭ ዲፕሎማቶች ተወካዮች፣ የዘርፉ ተዋንያን፣ የመንግሥት ተቋማት ተወካዮች፣ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮችና ሌሎች ተጋባዦች በተገኙበት ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱ ከመቶ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላትን አገር ወደብ አልባ ማድረግና በቀይ ባህር ቀጣና ላይ በሚከናወኑ ማናቸውም እንቅስቃሴዎች ማግለልን በዝምታ ማለፍ ለመጪው ትውልድ ፈተና ጥሎ መሄድ ነው ያሉት እንድሪስ መሐመድ (ዶ/ር)ናቸው፡፡ ‹‹ከዚህ በፊት የነበረው የእኔ ትውልድ አገሪቱን ወደብ አልባ ያደረጋትን ስህተት ማናቸውም አማራጮች በመጠቀም መፍትሔ ሊያመጣ የሚችል ሥራ መሥራት ይገባዋል፤›› ብለዋል፡፡ ወደብ የማግኘት ጉዳይ አማራጭ የሌለው በመሆኑ በሰጥቶ በመቀበል፣ ከዚያም ካለፈ የኃይል አማራጮችን የመጨረሻ መንገድ ማድረግ እንደሚያስፈልግ እንድሪስ (ዶ/ር) አስረድተው ነበር፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መሳፍንት ተፈራ፣ ከቀይ ባህር ፖለቲካ ኢትዮጵያን አግልሎ መቆየት የማይቻል በመሆኑ ማናቸውም ቀይ ባህርን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ ሚና ልትጫወት ግድ ይላታል ብለዋል፡፡ ከ120 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት አገር በፀጥታ፣ በንግድና ኢንቨስትመንት፣ በደኅንነት ወይም በሌላ ጉዳይ እያደገ ከሚመጣው ፍላጎት ጋር ከቀይ ባህር ውጪ መንቀሳቀስ የማይቻላት በመሆኑ፣ በዚህ ቀጣና በማንኛውም ኢትዮጵያን ተሳታፊ ሊያደርግ የሚችል ጉዳይ ላይ ተሳታፊ መሆኗን ማረጋገጥ እንደሚገባት አብራርተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይም ሆኑ የውጭ ጉዳይ ባለሥልጣናት ስለቀይ ባህር ወደብ ተጠቃሚነት ሲነግሩን፣ ስለቀይ ባህር ጂኦ ፖሊቲክስ አደገኛ ሁኔታም እየጠቆሙን ነው የሚል ግምት አለኝ፡፡ ለመሆኑ የቀይ ባህር ጂኦ ፖሊቲክስ ማለት ምን ማለት ነው? በቀይ ባህር ጂኦ ፖለቲክስ ዙሪያ የተሰባሰበው ኃይል ምን ያህል ነው? ለምን ስለቀይ ባህር ፖለቲካ እንናገራለን? ኢትዮጵያ ለምንና በምን ሕግ የቀይ ባህር መግቢያ በር ማግኘት ትችላለች? የቀይ ባህር ታሪካችን ምን ይመስላል? በዚህ አምስት ክፍል ያለው ጽሑፍ እነዚህና እነዚህን የመሳሰሉ ዓበይት ጉዳዮች ይቀርባሉ፡፡ በቅድሚያ ጂኦ ፖለቲካ ማለት ምን ማለት ነው?

ጂኦ ፖለቲካ ማለት ምን ማለት ነው? ይቀጥላል ...

"ውብ ሀገሬ ውብ ሀገሬ ባንቺ እኮ ነው መቀበሬውብ ሀገሬ ውብ ሀገሬ
19/11/2023

"ውብ ሀገሬ ውብ ሀገሬ
ባንቺ እኮ ነው መቀበሬ
ውብ ሀገሬ ውብ ሀገሬ

በአማራ ክልል በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት  ንጹሀን ዜጎች የከፋ ጉዳት እያስተናገዱ መሆኑ ተገለፀ። ይህንን የገለፀው የተመድ ሰብዓዊ መብት ጥበቃ ...
18/11/2023

በአማራ ክልል በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት ንጹሀን ዜጎች የከፋ ጉዳት እያስተናገዱ መሆኑ ተገለፀ። ይህንን የገለፀው የተመድ ሰብዓዊ መብት ጥበቃ ቢሮ ሲሆን የሀገር መከላከያ ሰራዊቱ በክልሉ የተለያዩ ቦታዎች በፈፀማቸው የድሮን ጥቃቶች ንፁሃን ሰለባ መሆናቸውን አመልክቷል።

የጅምላ እስር እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀሎች እየተፈጸሙ ነው ያለው ቢሮው ጉዳዩ እንዳሳሰበው ገልጿል።
በተፈፀመው የድሮን ጥቃት
✔ወደራ ወረዳ ባለ አንደኛ ትምህርት ቤት 6 ሰዎች ተገድለዋል
✔ምዕራብ ጎጃም ዋበር መናኸሪያ 13 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
✔በማዕከላዊ ጎንደር ጯሂት 6 ሲገደሉ 14 ቆስለዋል።

✔የፋኖ ታጣቂዎችም በደቡብ ጎንደር አለም በር ባደረሱት ተመሳሳይ ጥቃት ቁጥራቸው 21 የሚሆኑ ሰዎች እንደተገደሉም ቢሮው አስታውቋል።

"የኢትዮጵያን ጀብዱፋሽስቱን ምን አሳበደው? የካቲት 12 ግራዚያኒን በቦንብ ለመግደል የተሞከረው የግድያ ሙከራ የአዲስ አበባ ህዝብን በደም አበላ ያረጠበ ጭፍጨፋን፣ የፋሺስቶችን ሽብርና ግፍ ...
18/11/2023

"የኢትዮጵያን ጀብዱ
ፋሽስቱን ምን አሳበደው?

የካቲት 12 ግራዚያኒን በቦንብ ለመግደል የተሞከረው የግድያ ሙከራ የአዲስ አበባ ህዝብን በደም አበላ ያረጠበ ጭፍጨፋን፣ የፋሺስቶችን ሽብርና ግፍ በአደባባይ ገለጠ።

የሚደንቀው የታሪኩ አካል ይህ ነው።

አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም በፋሺስት ተይዘው ሊሰቀሉ ሲሉ አብርሃ ደቦጭ .
"የወንድሜን ስቅላት አላይም፤ እኔን መጀመሪያ ስቀሉኝ"..

ስላለ እንደፈለገው ሊሰቅሉት ሲዘጋጁ። መንፈሱ የማይረበሽ፣ ዝምታው የሚያሸብር፣ ቁንን ያለ የወንድ ግንባርን ያሳይ ነበረ።

ፋሺስቶቹ ሊሰቅሉት ሴኮንዶች ሲቀራቸው

እንዲህ አለ
."ለአገሬ በአደረግሁት ነገር ሁሉ እኮራለሁ፤ አሁንም በደስታ ለአገሬ እሞታለሁ...."

ይህን አብረሃ ደቦጭ ንግግር የፋሺስቱ አዛዥ እንደሰማ በንዴት ተበሳጭቶ አብርሃንም ሞገስንም በሽጉጥ ገደላቸውና ሬሳቸውን ሰቀለ።

እብደት የሽብር መጨረሻ..

ፋሺስቱን አዛዥ ምን አሳበደው? ያቺን ጠምዝዞና ጨምቆ፣ ዳምጦና ፈልቅቆ ከውስጣቸው አስወጥቻለሁ ብሎ የገመተው ኢትዮጵያዊነት ፊት ለፊት ገጠመው..

ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ፋሺስቱ አዛዥንም ሞትንም እያዩ በአንድ ላይ ተጋፈጡአቸው።

ኢትዮጵያዊነት የተሸፈነበትን የፋሺስት መንጦልያ ቀዳዶ ወጣ.. ፋሺስቱንም ሞትንም ናቀ..

ለሞት የተዘጋጀ ሰው ሲንቅ፣ ለመግደል ለተዘጋጀው ሰው የመንፈስ ሞት ነው..

በዚያው እለት ከኢትዮጵያዊነት ጋር ተጋፍጦ የአበደው የፋሺስት አዛዥ ቀኛዝማች ወርቁ በሚባሉ አርበኛ ጦር ተመትቶ አብርሃ ደቦጭንና ሞገስ አስገዶምን ተከትሎ ሄዶአል።

የሽብር መጨረሻው ይህ ነው..

የፊልም ሞያ ቢኖረኝ ይህን የመንፈስ ወኔ ለሲኒማው አለም አበቃው ነበረ።

ኢትዮጵያዊነት ሞትን በመናቅ የጠላትን ቅስም መስበር ነው።

ኢትዮጵያ ተዝቆ የማያልቅ የመንፈስ እና የኩራት ታሪክ ሀገር ናት።
መጪው ትውልድ ይዘክረዋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

"አስደሳች ዜና ኢሳያስ አፈወርቂ ስለ ቀይባህር ጉዳይ ዝምታቸውን ሰበሩ❗❗ኢሳይያስ አፈወርቂ ሰሞኑን በሳውዲ አረቢያ በነበራቸው ቆይታ ከአንድ የአረቢኛ ጊዜጣ ጋር ቃለምልልስ አድርገዋል። በዚህ...
16/11/2023

"አስደሳች ዜና
ኢሳያስ አፈወርቂ ስለ ቀይባህር ጉዳይ ዝምታቸውን ሰበሩ❗❗
ኢሳይያስ አፈወርቂ ሰሞኑን በሳውዲ አረቢያ በነበራቸው ቆይታ ከአንድ የአረቢኛ ጊዜጣ ጋር ቃለምልልስ አድርገዋል። በዚህ ቃለምልልሳቸው የተለያዩ ጉዳዮችን ያነሱ ሲሆን ስለቀይባህር ጉዳይ የሚከተለውን ብለዋል❗👇
ቀይባህርን የምንጋራ ሀገራት በጋራ መቆም አለብን ሲሉ ነው የመለሱት።
የቀይባህር ዳርቻ ሀገራትን ሉዓላዊነት ለማስከበር እና የቀይባህርን ደህንነት ለማስጠበቅ በጋራ መቆም አለብን ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ይህ ከሆነ ከሌሎች ጣልቃ ገቦች ለመጠበቅ ያስችለናል ሲሉ ተደምጠዋል።
ለሌሎች ሀገራትን ተጠቃሚነት በተመለከተ ለተነሳላቸው ጥያቄ የቀይባህር ወደብን ለመጠቀም የሚፈልጉ ሌሎች ሀገራት በውይይት እና በምክክር ብቻ ሊሆን እንደሚችል ጠቅሰው ይህን ከማለም በፊት ግን በቀጠናው ያሉብንን የፀጥታ መደፍረስ፣ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን መፍታት ይኖርብናል ብለዋል።

"የኢትዮጵያን ጠ/ሚ አብይ አህመድን በመምሰሌ የደህንነት ስጋት ስላለብኝ ጥበቃ ይደረግልኝ" "የኢትዮጵያውን ጠ/ሚ አብይ አህመድን በመምሰሌ የደህንነት ስጋት ስላለብኝ ጥበቃ ይደረግልኝ" ያሉት...
15/11/2023

"የኢትዮጵያን ጠ/ሚ አብይ አህመድን በመምሰሌ የደህንነት ስጋት ስላለብኝ ጥበቃ ይደረግልኝ"
"የኢትዮጵያውን ጠ/ሚ አብይ አህመድን በመምሰሌ የደህንነት ስጋት ስላለብኝ ጥበቃ ይደረግልኝ" ያሉት በፑንትላንድ ግዛት የዋኢዮ ወረዳ አስተዳዳሪ ኢሳቅ አህመድ ሀሰን በሶማሊያ ሶሻል ሚዲያዎች የእለቱ ሳቅ የሚጭር መነጋገሪያ ሆኗል ሲል ሶማሊ ፈጣን መረጃ ዘገባ ያሳያል።

ሰውዬው በሶሻል ሚዲያ ብቅ ብለው በአፍ ሶማሊ ቋንቋ "አብይን ትመስላለህ እያሉ ህይወቴን አደጋ ውስጥ የከተቱብኝ ሰዎች አሉ። እኔ ሳልሆን አብይ ነው እኔን የሚመሰለው። በዚህ ምክንያት ለህይወቴ ሰለሰጋሁ ያለጠባቂ መንቀሳቀስ አቁሜለሁ። በዛ ላይ የአባቱ እና አባቴ ስም አንድ ነው። ወደ ኢትዮጵያ የሄድኩት በመለስ ዘመን ነው አሁን መሄድ ብፈልግም ለደህንነቴ ስጋት ስላለብኝ ጠባቂ ያስፈልገኛል።" ብለዋል።

በፑንትላንድ ግዛት የዋኢዮ ወረዳ አስተዳዳሪ ይህን መልእክት ያስተላለፉት ለቀልድ ይሁን የምራቸውን ግን የታወቀ ነገር የለም ሲል ሶማሊ ፈጣን መረጃ ዘግቦታል።

ጥፍጥ የምትል ወግ ናት አንብቧት*ልጅ ፡ አባቴ  ባህሪዬ እንዴት ቢሆን ደስ ይልሃል ?አባት: እንደዚህ ሁን ልጄልጅ ፡ እንዴት ? አባት፡ እንደ ውሃ ሁን ባስቸገረ ግዜ እሳትን ቢያጠፋም በተፈ...
14/11/2023

ጥፍጥ የምትል ወግ ናት አንብቧት
*
ልጅ ፡ አባቴ ባህሪዬ እንዴት ቢሆን ደስ ይልሃል ?
አባት: እንደዚህ ሁን ልጄ
ልጅ ፡ እንዴት ?
አባት፡ እንደ ውሃ ሁን ባስቸገረ ግዜ እሳትን ቢያጠፋም በተፈለገ ጊዜ ግን እንዲገኝ ዛፍ ማሳደጉን አይተውምና ፤ እንደጨውም ሁን ለሁሉም ምግብ ቢፈለግም በቀላሉ ይገዛ ዘንድ ግን-ዋጋው ውድ አይደለምና ፤ ከሁሉ ከሁሉ-ግን እንደ ወተት ሁን በተውት ግዜ በሌላ-መልክ ተመልሶ ይመጣል እንጅ አይበላሽምና-በተገፋም ግዜ ከፍ ከፍ ይላልና።
ልጅ: እሽ አባቴ እንዳልሆንስ የምትፈልገው የለም ?
አባት:ልጄ፤ እንደዚህ አትሁን
ልጅ ፡ እንዴት ?
አባት፡ልጄ ሆይ እንደ መርፌ አትሁን የሌሎች ብዙ ቀዳዳ እየደፈነ የራሱን አንዷን መድፈን አይችልምና፤ እንደ መቋሚያም አትሁን ለሌሎች መደገፊያ እየሆነ ለራሱ ግን መቆም አይችልምና ፤ ከሁሉ ግን እንደ ደወል አትሁን ! ከሁሉ ቀድሞ ነቅቶ ሌሎችን ለቅዳሴ ቢቀሰቅስም እርሱ ግን አያስቀድስምና።..............
መልካም ቀን

መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች የማያደርጓቸው ነገሮችን እንከተል!======================= ማንበብ ባትፈልጉም እንኳን አንብቡት ይጠቅማል  መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች ሃሳባቸውንና ባህሪያቸውን በ...
13/11/2023

መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች የማያደርጓቸው ነገሮችን እንከተል!
=======================
ማንበብ ባትፈልጉም እንኳን አንብቡት ይጠቅማል

መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች ሃሳባቸውንና ባህሪያቸውን በመግራት እና ስሜታቸውን በመቆጣጠር ይታወቃሉ፡፡

በአዕምሯዊ ብስለት እና በአስተሳሰብ ከፍ ያለ ደረጃ ላይ የደረሱ ሰዎች የሚከተሉትን ነገሮች አያደርጉም፡፡

✅ ፍርሃት የለባቸውም

መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች ምክንያታዊ አስተሳሰብን ስለሚያጎለብቱ ሰዎች ብዙ ጊዜ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚያዊ ህይወታቸው ወደፊት ሊገጥማቸው ስለሚችሉ ችግሮች አስቀድመው ስጋት ውስጥ ለሚጥል ጭንቀት አይዳረጉም፡፡

✅ በሌሎች ስዎች ስኬታማነት አይቀኑም

አዕምሯቸው ሚዛናዊነትን ያጉለበተ ሰዎች ስኬትን ከተቀዳጁ ሌሎች ሰዎች ትምህርትን ለመውሰድ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ እንደሆኑ ይነገራል፡፡ የስነ ልቦና ባለሙያዎች በሌሎች ሰዎች ድክመት እና ስኬትማነት ላይ ማተኮር የራስን እቅድ ያሳጣል ይላሉ፡፡

✅ ባለፈ ነገር አይፀፀቱም

ስላለፈው ጉዳይ መጨነቅ እና በፀፀት ጊዜን ማሳለፍ ለወደፊቱም እቅድን እንዳይነድፉ መሰናክል ይሆናል፤ መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች ካለፈው ችግራቸው ወይም ውድቀታቸው ትምህርት በመውሰድ አሁን ያለውን የተሻለ በማድረግ ለነገ ስኬታማነታቸው በጥረት ይሰራሉ፡፡

✅ ራሳቸውን አሳልፈው አይሰጡም፤ አይሸነፉም

ብዙ ጊዜ መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች አካላቸው እንኳ ቢደክም በአስተሳሰብ እና በአመለካከታቸው ብርቱ አቋም ይዘው ለስኬት ይበቃሉ፡፡ ራሳቸውንም ለጠላቶቻቸው አንበርክከው አይሰጡም፡፡

✅ ለውጥን አይፈሩም

እነዚህ ሰዎች ነገሮችን አመዛዝነው የሚተነብዩ በመሆናቸው በሚያደርጉት ማንኛውም ነገር ለሚመጣው ውጤት ዝግጁ ናቸው፡፡

አልፈልግም እኮ፣ ግን . . . አንዳንድ ሰዎች ከሌሎች ጋር ባላቸው ግንኙነት የማይፈልጉትን ሲያደርጉ፣ ሲደረግባቸውና ሲያስተናግዱ ራሳቸውን ያገኙትና፣ “አልፈልግም እኮ፣ ግን . . . ” በማ...
12/11/2023

አልፈልግም እኮ፣ ግን . . .

አንዳንድ ሰዎች ከሌሎች ጋር ባላቸው ግንኙነት የማይፈልጉትን ሲያደርጉ፣ ሲደረግባቸውና ሲያስተናግዱ ራሳቸውን ያገኙትና፣ “አልፈልግም እኮ፣ ግን . . . ” በማለት የግዳጅ ሕይወት እንደሚኖሩ ያስባሉ አንዳንዴም ይናገራሉ፡፡ ይህ አይነቱ ዝንባሌ የሚመጣው ከተሰበረና ከተቀጠቀጠ ፈቀድ ነው፡፡

የተሰበረ እና የተቀጠቀጠ ፈቃድ ማለት የእኛ ፈቃድ እጅግ ደካማ ከመሆኑ የተነሳ ሁል ጊዜ የሰዎች ፈቃድ በእኛ ላይ ሲሰለጥንና ከዚያም የተነሳ የምንፈልገውን ትክክለኛ ነገር ማድረግ ሲያቅተን እና የማንፈልገውን ጤና-ቢስ ነገር ለማድረግ ስንገደድ ማለት ነው፡፡

ይህንን አትዘንጉ . . .

• እናንተ ካልፈቀዳችሁላቸው በስተቀር ሰዎች በግዳጅ ከእነሱ ጋር እንድትቆዩ ሊያደርጓችሁ አይችሉም፡፡

• እናንተ ካልፈቀዳችሁላቸው በስተቀር ሰዎች የግል መስመራችሁን (personal boundary) አልፈው እንደፈለጉ ሊያደርጓችሁ አይችሉም፡፡

• እናንተ ካልፈቀዳችሁላቸው በስተቀር ሰዎች በአጉል ስሜት ተጽእኖ ስር እንድትቆዩ ሊያደርጓችሁ አይችሉም፡፡

• እናንተ ካልፈቀዳችሁላቸው በስተቀር ሰዎች ሕይወታችሁን ሊያመሳለቅሉት አይችሉም፡፡

መፍትሄው

1. የምትፈልጉትንና የማትፈልጉት ለይታችሁ እወቁ፡፡

2. የምትፈልጉት ነገር የእናንተው ፍላጎት መሆኑንና የሰው ጫና እንደሌለበት አረጋግጡ፡

3. የምትፈልጉት ነገር ጤናማ እና ትክክለኛ መሆኑን አረጋግጡ፡፡

4. ጤናማ እና ትክክለኛ የሆነውን ፍላጎታችሁን ለመናገርም ሆነ ለመተግባረ ፍርሃት ካለባችሁ ፍርሃታችሁን አስወግዱ፡፡

5. በእናነት ፈቃድ ላይ የራሳቸውን ፍጎትና ፈቃድ መከመር የሚወዱ ሰዎችን አይናቸውን እያያችሁ፣ በአክብሮትና በተረጋጋ መልኩ ፍላጎታችሁን መናገር ልመዱ፡፡

6. እውነተኛ ማንነታችሁን ለመኖር ከላይ የተጠቀሱትን በማድረጋችሁ ምክንያት የሚደርስባችሁ ማንኛውም ችግርም ሆነ የሚቀርባችሁ ማንኛውም ነገር እጅግ ውብና ያማረ ሕይወት በፊታችሁ እንደሚያመጣላችሁ ጥርጥር አይግባችሁ፡፡

ሁለቱ የውጥረት ምንጮቸጭንቀትና ውጥረት በሕይወታችን ከመሬት ተነስቶ አይመጣም፡፡ የተለያዩ ምክንያቶችና ምንጮች አሉት፡፡ ሆኖም ለዛሬው እጅግ በጣም የተለመዱትን ሁለቱን መንስኤዎች ላስታውሳችሁ...
12/11/2023

ሁለቱ የውጥረት ምንጮቸ

ጭንቀትና ውጥረት በሕይወታችን ከመሬት ተነስቶ አይመጣም፡፡ የተለያዩ ምክንያቶችና ምንጮች አሉት፡፡ ሆኖም ለዛሬው እጅግ በጣም የተለመዱትን ሁለቱን መንስኤዎች ላስታውሳችሁ፡፡

1. በእናንተ ቁጥጥር ስር የሆኑ ነገሮችን ችላ ማለት

ትናንትና በእናንተ ቁጥር ስር የነበሩትንና ችላ ብላችኋቸው ያለፋችኋቸው ነገሮች ልክ እንደ ዘር ሆነው በቅለውና ፍሬ አፍርተው ዛሬ የጭንቀትና የውጥረት ምንጭ ሆነው ብቅ ብለዋል፡፡ ዛሬም ቢሆን ችላ ያላችሁት ነገር ነገ የውጥረት ምንጭ ሆኖ ብቅ ማለቱ አይቀርም፡፡

ለምሳሌ፣ ሊታረም የሚገባው የሰዎች ባህሪይ፣ መስመር ሊይዝና ትርጉሙ ሊለይ የሚገባው ከሰው ጋር ያላችሁ ግንኙነት፣ ሊቆም ወይም ሊለወጥ የሚገባው የግል ልማድ እና የመሳሰሉት ሁኔታዎች በእናንተ ቁጥጥር ስር ስለሆኑና ትክክለኛው ምርጫና ውሳኔ ሊደረግባቸው ይገባል፡፡ አለዚያ ግን ነገ የውጥረት ምንጭ ሆነ ብቅ ማለቱ አይቀርም፡፡

2. ከእናንተ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ነገሮች ላይ ማተኮር

በሕይወታችሁ ልታዳብሩት ከሚገባችሁ ጥበብና ብልሃት ዋነኛው ከእናንተ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ነገሮችን የመለየትን ሁኔታ ነው፡፡ ምንም ብታደርጉ ልትቆጣጠሩትና ልትለውጡት በማትችሉት ነገር ላይ በሃሳብ ውሎ ማደርም ሆነ ይህንና ያንን መሞከር ለከፍተኛ ጭንቀትና ውጥረት አጋልጦ ይሰጣችኋል፡፡

ለምሳሌ፣ በተለያዩ ሰዎች ከዚህም ከዚያም ተቃርመው የሚመጡ ዜናዎችን ማዳመጥን ማዘውተር፣ ከሕይወታችሁ የወጣና በፍጹም ወደሕይወታችሁ ሊመለስ የማይችልን ሰው ሲያስቡ ውሎ ማደር፣ ገና ለገና ይከሰታል ብላችሁ የምታስቡትን ነገር ላይ ማተኮር እና የመሳሰሉት ሁኔታዎች ቀስ በቀስ ጫናን እያሳደሩባችሁ መሄዳቸው አይቀርም፡፡

ትኩረታችሁን ከእናንተ ቁጥጥር ውጪ ከሆኑት ነገሮች ላይ አንሱና መለወጥ በምትችሉት ነገር ላይ ተጠመዱ፡፡ ያን ጊዜ ሰላም ትሆናላችሁ፡፡

መልካም ሰንበት

 ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ
29/10/2023

ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ

Miira Daraartu Tullu figicha har'a irratti💔በዛሬው ውድድር የደራርቱ ቱሉ ስሜት!ምክንያቱም እኛ ኢትዮጵያዊያን ነን ሁሌም አንደኝነትን የለመድን ፅኑ ህዝቦች
20/08/2023

Miira Daraartu Tullu figicha har'a irratti💔
በዛሬው ውድድር የደራርቱ ቱሉ ስሜት!

ምክንያቱም እኛ ኢትዮጵያዊያን ነን ሁሌም አንደኝነትን የለመድን ፅኑ ህዝቦች

አቡሽ ዘለቀ አዲስ የሙዚቃ አልበሜን በቅርብ ቀናት ለአድማጭ ላደርስ ተዘጋጅቻለው አለ።ተወዳጁ ድምፃዊ አቡሽ ዘለቀ “እንደ አባቴ እወድሻለው" ሲል የሰየመውን የሙዚቃ አልበም ሰርቶ መጨረሱን ገ...
20/08/2023

አቡሽ ዘለቀ አዲስ የሙዚቃ አልበሜን በቅርብ ቀናት ለአድማጭ ላደርስ ተዘጋጅቻለው አለ።

ተወዳጁ ድምፃዊ አቡሽ ዘለቀ “እንደ አባቴ እወድሻለው" ሲል የሰየመውን የሙዚቃ አልበም ሰርቶ መጨረሱን ገልፆል። በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ለአድናቂዎቹ ባስተላለፋው መልዕክትም በቅርብ ቀን አዲስ አልበሙ እንደሚያወጣ አስታቋል።

ለምትሰጡኝ ፍቅር እና አድናቆት ክብር አለኝ በማለት የተናገረው አቡሽ የሚወጣውን ሙዚቃዬንም እንደምትወዱት ተስፋ አለኝም ብሏል። አቡሽ ዘለቀ ከሶስት አመት በፊት "ሂድዘይራት" የተስኝ በአማርኛ ቋንቋ የሰራውን አልበም ማስደመጡ ይታወቃል።

አብሽ ከዚህ ባለፋ ባህል ና እሴትን በተለየ መንገድ በሚያስተዋዉቅባቸው ባህላዊ የአፋን ኦሮሞ ዜማዎቹም ከፍተኛ አድናቆትን ያገኝ ድምፃዊዉም ነው። አቡሽ አዲስ አልበሜ በቅርብ ይወጣል ይበል እንጂ ትክክለኛ ቀኑ መቼ ነው ? የሚለውን አልተናገረም።

"ኢትዮጵያ በደማቸው የሚያስከብሯት ብዙ ጀግና ልጆች አሏት! በደም የተገኘ ወርቅ
20/08/2023

"ኢትዮጵያ በደማቸው የሚያስከብሯት ብዙ ጀግና ልጆች አሏት! በደም የተገኘ ወርቅ

ዳግማዊ አረንጓዴ ጎርፍ !!!!
19/08/2023

ዳግማዊ አረንጓዴ ጎርፍ !!!!

መቖሌ ትግራይ ኢትዮጵያ
19/08/2023

መቖሌ ትግራይ ኢትዮጵያ

እኔ ማን ነኝ ብለህ ራስህን  ጠይቀው ማንነትህን ጠንቅቀህ ስታውቅ ዋጋህን ታውቀዋለህ የምትኖርበትን እና የምትኖርለትን ትለያለህ።ወደዚች ምድር የመጣኸው ለምክንያት ነው ፣ ለዓላማም ጭምር። አ...
19/08/2023

እኔ ማን ነኝ ብለህ ራስህን ጠይቀው ማንነትህን ጠንቅቀህ ስታውቅ ዋጋህን ታውቀዋለህ የምትኖርበትን እና የምትኖርለትን ትለያለህ።
ወደዚች ምድር የመጣኸው ለምክንያት ነው ፣ ለዓላማም ጭምር።
አንተ የዚህች ዓለም ገጽ ውብ እና ሙሉ ይሆን ዘንድ እንደ አንዱ ጡብ ነህ።

ዋጋህን በመኖርህ እንጂ ባለመኖርህ አትተምን። የአንተ መኖር ለሌሎቹ ጡቦች ድጋፍ እንዲሁም ለግንባታው ውበት አስፈላጊ ነው።

>>አስታውስ አንተን መሆን የሚችል ምትክ የለህምና ራስህን ጠብቅ።

ድም ድም ድም ድም ወደ ወሎ ግድም !
02/08/2023

ድም ድም ድም ድም ወደ ወሎ ግድም !

ህመምህን እወቀው!ለዓመታት አንገት ያስደፋህ ህመም ምን ነበር? ለዘመናት ዋጋ ያስከፈለህ ጉዳይ ምን ነበር? ለረጅም ጊዜ ከሰው በታች እንደሆንክ እንዲሰማህ፣ እራሳህን እንዳታከብር፣ ለውጥን እ...
01/08/2023

ህመምህን እወቀው!

ለዓመታት አንገት ያስደፋህ ህመም ምን ነበር? ለዘመናት ዋጋ ያስከፈለህ ጉዳይ ምን ነበር? ለረጅም ጊዜ ከሰው በታች እንደሆንክ እንዲሰማህ፣ እራሳህን እንዳታከብር፣ ለውጥን እንዳትፈልግ፣ ንቃት እንዳይኖርህ፣ አመለካከትህን እንዳትቀይር አስሮ የያዘህ ብርቱ ችግር፣ ጉምቱ ጠላትህ ምንድነው? ሁሉም ሰው ይታመማል፣ የህመሙን ምንነት፣ ምንጭና አመጣጡን ጠንቅቆ የሚያውቅ ግን እጅግ በጣም ጥቂት ነው። ማንም ሰው በልኩ በሚገጥመው ፈተናና ስቃይ ውስጥ ያልፋል። ወዶና ፈልጎ ባይሆንም ግማሹ ፈተናውን ወድቆ ይገኛል፤ ሌላኛውም በጥረቱና በትጋቱ ልክ አሸንፎት፣ ተሻግሮት ይገኛል። ማንም የማያውቀውን ጠላቱን ሊያሸንፈው አይችልም። የማያወቀው ችግሩንም እንዲሁ ሊፈተና ሊሻገረው አይችልም። የችግሩ መፍትሔ ግማሽ የችግሩ እውቀትና ግንዛቤ ነው። ድክመትህን ለማሻሻል የድክመትህ ምንነትና መንሰዔ በሚገባ መታወቅ ይኖርበታል።

ቆንጅዬ ትንሽዬ ህፃን ልጅ ሁለት አፕሎች በእጇ ይዛለች፡፡ እናትዬ ወደ እሷ ቀረበችና በእርጋታ እንዲህ ብላ ጠየቀቻት… ‹ማርዬ አንዱን አፕል ለእናትሽ ትሰጭያለሽ?› ትንሽዬ ልጅ እናቷ ለሰከን...
31/07/2023

ቆንጅዬ ትንሽዬ ህፃን ልጅ ሁለት አፕሎች በእጇ ይዛለች፡፡ እናትዬ ወደ እሷ ቀረበችና በእርጋታ እንዲህ ብላ ጠየቀቻት… ‹ማርዬ አንዱን አፕል ለእናትሽ ትሰጭያለሽ?›
ትንሽዬ ልጅ እናቷ ለሰከንዶች በዝምታ ተመለከተቻትና በፍጥነት ከአንዱ አፕል ገመጠች በመቀጠል ደግሞ ሌላውንም አፕል ገመጠችለት፡፡
እናትየው ገፅ ላይ ያለው ፈገግታ ባለበት ደረቀ… መናደዷን በልጇ ፊት ላለማሰየት የቻለችው ያህል ጥረት አደረገች፡፡
ትንሽዋ ልጅ አንዱን የተገመጠውን አፕል ወደ እናቷ እየሰጠች… እናቷን እንዲህ አለቻት… ‹ማሚ… ይሄኛው ጣፋጭ ስለሆነ እንኪ ለአንቺ…› እናትየው ይበልጥ በሁኔታው መደነቅ ውስጥ ገባች፡፡
ምንም ውስጥ ብትሆን… ምንም ዓይነት ልምድ ቢኖር እና በጣም እውቀት አለኝ ብትል… ሁልጊዜም ሰዎች ላይ ለመፍረድ ያሳለፋችሁትን ውሳኔያችሁን አዘግዩ፡፡ ለሌሎች ቅድሚያ ስጡ ምክንያታቸውን እንዲገልፁ… ምን እያደረጉ እንደሆነ እንዲያብራሩ፡፡

በፈጣሪ እንዴት አይነት አስደናቂ ሰብአዊነት ነው!ጃኩሊን ኪፕሊሞ ፡ ኬንያዊቷ የማራቶን ሯጭ ፡ በቻይና ዜንካይ ተካሂዶ በነበረው የማራቶን ውድድር ላይ ተፎካካሪዎቿን በብዙ ኪ/ሜትር ርቃ ወደፊ...
30/07/2023

በፈጣሪ እንዴት አይነት አስደናቂ ሰብአዊነት ነው!
ጃኩሊን ኪፕሊሞ ፡ ኬንያዊቷ የማራቶን ሯጭ ፡ በቻይና ዜንካይ ተካሂዶ በነበረው የማራቶን ውድድር ላይ ተፎካካሪዎቿን በብዙ ኪ/ሜትር ርቃ ወደፊት እየገሰገሰች የወርቁን ሜዳልያና ፡ አንደኛ ለወጣው አትሌት የሚሰጠውን የገንዘብ ሽልማት ፡ እንደምትወስድ እርግጠኛ ሆና ፡ እያለ ፡ ከፊት ለፊቷ ሁለት እጆች የሌሉት አካል ጉዳተኛ ፡ ተሳታፊ አትሌት ውሀ ለመጠጣት ሲታገል አየች ።

ትታው ማለፍ አልቻለችም ። ውሀውን ተቀብላ አጠጣችው ፡ ጭንቅላቱ ላይ እንድታፈስላት ጠየቃት ፡ ያላትን አደረገችና የውሀውን ኮዳውን ጥላ ፡ ወደፊት መገስገሷን ቀጠለች ።

አካል ጉዳተኛው አትሌት ኬንያዊቷን አትሌት አመስግኖ ፡ በአዲስ ጉልበት መሮጥ ጀመረ ፡

ጃኩሊን ኬፕሌሞ ፡ ሩጫዋን እንደቀጠለች ፡ ውሀ የተደረደረበት ጠረጴዛ ጋር ደረሰች ። አንስታ ጠጣች ፡ ፊቷ ላይ አፈሰሰች እና መሮጧን ልትቀጥል ስትል ፡ ያ ቅድም ውሀ እንዲጠጣ ያገዘችው ፡ አካል ጉዳተኛ ተሳታፊ አትሌት ትዝ አላት ፡ እዚህ ጋርስ ማን ያጠጣው ይሆን ብላ ዞር ብላ አየች ። ከሷ በጣም ርቆ እየተከተላት ነው ።

ጃኩሊን መሮጧን ትታ ፡ አካል ጉዳተኛውን አትሌት የውሀው ቦታ እስኪደርስ ቆማ መጠበቅ ጀመረች ።
ደረሰ ።
ውሀውን አንስታ አጠጣችው ። እና ቅድም ትሮጥበት ከነበረው ፍጥነት ቀንሳ ከሱ እኩል እየሮጠች ፡ ውሀ ቦታ ሲደርሱ እያጠጣችው አብራው መሮጥ ጀመረች ። ይህን እያደረገች እያለ ፡ በብዙ ርቀት ቀድማት የነበረች አንድ አትሌት ፡ ጃኩሊንን ቀድማት ሄደች ።....
ጃኩሊን ኬፕሌሞ ፡ አካል ጉዳተኛውን አትሌት ለመርዳት ስትወስን ፡ ዋጋ ሊያስከፍላት እንደሚችል ታውቅ ነበር ። እና ፍጥነቷን ጨምራ ሩጫዋን ቀጠለች ።
ሆኖም ፡ አትሌቱን ለመርዳት ቆማ በነበረችባቸውና ፡ ፍጥነቷን በቀነሰችባቸው በርካታ ደቂቃዎች ፡ ተፎካካሪዋ ፡ ደርሳባት አልፋት ሄዳ ነበርና ፡አንደኛ ወጥታ መቅደም አልቻለችም ። ሁለተኛ ወጣች ። .......
ጃኩሊን በውድድሩ አሸንፋ አንደኛ መውጣት ባትችልም ፡ ስሟ ከፍ ብሎ ተነሳ ፡ ስለ ሰብአዊነት ሲጻፍ ፡ የጃኩሊን ኬፕሌሞ ስምም ፡ እስከዛሬ ይነሳል ።
ኬንያን የሚጎበኙ ቱሪስቶች ፡ ከጀግናዋ አትሌት ጋር ፎቶ ለመነሳት ወዳለችበት ይሄዳሉ ።
ጃኩሊን ፡ ከዚህ መልካም ስራዋ በኋላ በተሳተፈችባቸው ውድድሮች ብዙ ድል አግኝታለች ፡ ለሷ ግን ፡ ይበልጥ ደስታ የሚሰጣት ፡ ማሸነፍ ስትችል ፡ ሁለተኛ የወጣችበት ፡ የቻይናው የዜንካይ ማራቶን ነበር ።

ዋሲሁን ተስፋዬ እንደአጋራን

😥የባከነች ህይወት 💔​​💔             #ክፍል\_➋ሁለት♥️የቤዛዊት አለሙ እዉነተኛ ታሪክ♥️  🖊በጭንቀትና በሀዘን ከመስታወቱ ፊት ለፊት እንደቆምኩ  እናቴ የመኝታ ቤቴን በር ሳታንኳኳ...
29/07/2023

😥የባከነች ህይወት 💔​​💔
#ክፍል\_➋ሁለት
♥️የቤዛዊት አለሙ እዉነተኛ ታሪክ♥️

🖊በጭንቀትና በሀዘን ከመስታወቱ ፊት ለፊት እንደቆምኩ እናቴ የመኝታ ቤቴን በር ሳታንኳኳ ከፍታ ገባች...


የእናቴ ምክርና የማፅናኛ ቃል የእናትነት ፍቅር የታከለበት ቢሆንም እኔ ግን እንኳን እሷ ቀርቶ ፈጣሪ ወደ ምድር ወርዶ አይዞሽ ቢለኝ እንኳን የምፅናና አይመስለኝም። ወላጆቼ በትምህርት ዉጤቴ መበላሸት ክፉኛ ተደናግጠዉ ቢያዝኑም በሀዘኔ ላይ ሀዘን ላለመጨመር ሲሉ ብቻ ላይ ላዩን ደስተኛ መስለዉ ለመታየት ይሞክራሉ

አለችኝ!!
ከአልጋዉ ጠርዝ ላይ እየተቀመጠች። እናቴ ስለ እኔ ያላት ፍቅር በቃላት የማይገለፅ መሆኑን አዉቃለሁ
አለችኝ።

እኔን ለማፅናናት የምታደርገዉ ሙከራ ስላሳዘነኝ ከአጠገቧ ቁጭ አልኩ
መናገር አቃተኝ!!





አለችኝ!!

እናቴ እያለች ስትለምነኝ ልቤ ድንግጥ ይላል ካሰብኩት ከወሰንኩበት ነገር ሳይቀር ምልስ እላለሁ እሷም ይህን ስለምታዉቅ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ስሆን
ትለኛለች

ያለችኝ እናቴን ማሳዘን ስላልፈለኩ እጄን ይዛ ከተቀመጠችበት ስትነሳ ልቃወማት አልቻልኩም...

ይቀጥላል...
[

Address

Kombolcha
Kembolcha

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኢትዮጵያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share


Other Media/News Companies in Kembolcha

Show All