Sabir Gali

Sabir Gali Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Sabir Gali, News & Media Website, .

06/12/2021

ፀረ ሰላም ኃይሎች በሱዳን ድንበር ሰርገው ለመግባት ያደረጉት ሙከራ ከሸፈ
*******************

ከኢትዮጵያ የውስጥና የውጭ ጠላቶች ተልዕኮ ተቀብለው በድንበር አካባቢ ሰርጎ ለመግባት በሞከሩ የአሸባሪዎቹ ህወሓትና ሸኔ እንዲሁም የቤህነን ታጣቂዎች በጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና በክልሉ ፀጥታ ኃይሎች የጋራ ጥምረት ርምጃ እንደተወሰደባቸው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የታጣቂዎቹ ተልዕኮ የህዳሴ ግድብ ተገንብቶ ስራ ላይ እንዳይውል እና መንግስት የያዘው የብልፅግና ጉዞ እንዳይሳካ ለማደናቀፍ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አብዱልአዚም መሀመድ ገልፀዋል።

በተወሰደው ርምጃም ፀረ ሰላም ኃይሎቹ ይጠቀምባቸው የነበሩ በርካታ ጥይቶች እና ፈንጂዎች እንዲሁም አርፒጂ፣ ሞርታር እና ሌሎች ልዩ ልዩ ከባድ መሳሪያዎች መማረካቸውን ኮሚሽነሩ አክለው ገልጸዋል።

የክልሉን ሰላምን በዘላቂነት ለማስቀጠል በተከናወነው ኦፕሬሽን ህብረተሰቡም ከፍተኛ ሚና እንደነበረው የጠቀሱት ኮሚሽነሩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስተግበር የፀጥታ ስራው ከአጎራባች ክልሎች ጋር የጋራ ጥምረት በመፍጠር በእቅድ እየተመራ ተጠናክሮ መቀሉን ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል አሸባሪው ህወሓት እና ተላላኪው ሸኔ ሀገርን ለማፈራረስ የወጠኑት ሴራ መክሸፉን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል አራርሳ መርዳሳ ገለፁ፡፡

ባለፉት ጊዜያት በሀገሪቱ ብሎም በክልሉ ጠላት ሀገር ለማፈራረስ ጥረት አድርጓል፣ ብዙ ጥፋቶችን አጥፍቷል ያሉት ኮሚሽነሩ ይህንን ለመቀልበስ መላው ህብረተሰብ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የክልሉ የፀጥታ ኃይል ከሌሎች የፀጥታ አካላት እና ከማህበረሰቡ ጋር ባደረገው ቅንጅት በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የሸኔ ቡድን ላይ አስፈላጊውን እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አክለውም ለአሸባሪው ሸኔ አገልግሎት ሊውሉ የነበሩ በርካታ የጦር መስሪያዎች ከመያዝ እና ቡድኑ የጦር ግብዓቶችን እንዳያገኝ የግንኙነት መረቡን ከመበጣጠስ አኳያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለፀጥታ ኃይሉ ተጨማሪ አቅም እና ጉልበት እንደሆነው መግለፃቸውን ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በትግራይ መሪዎቹን  የሚጠብቅ ሃይል  ብቻ ነው የቀረው በቀጣዮቹ ቀናት ደሴና ኮምቦልቻ ያለው ጦርነት ሲጠናቀቅ  ዘጠና ፐርሰንቱ  የትግራይ ወጣት   ከጥቅም ውጪም  ይሆናል   ።በጠቅላይ ሚኒ...
06/12/2021

በትግራይ መሪዎቹን የሚጠብቅ ሃይል ብቻ ነው የቀረው በቀጣዮቹ ቀናት ደሴና ኮምቦልቻ ያለው ጦርነት ሲጠናቀቅ ዘጠና ፐርሰንቱ የትግራይ ወጣት ከጥቅም ውጪም ይሆናል ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ባጭር ግዜ በ"ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት" ባካሄደው ኦፕሬሽን፣ የተለያዩ ከተሞችን ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ የማውጣቱን እና በጥልቀት በመግባት የአሸባሪውን ጀሌዎች የመማረክ እና የመደምሰስ ተግባሩን ቀጥሏል።

ትላንት እና ከትላንት በስትያ በተደረገ ትግል በጋሸና ግንባር ቀውዝባና ጭላ ከተሞችና አካባቢያቸው ከአሸባሪው ኃይል ነጻ የወጡ ሲሆን፣ በወረኢሉ ግንባር በተደረገው ኦፕሬሽን ደግሞ አጅባር፣ ተንታ እና ዶባ ከተሞች እና አካባቢያቸው ነጻ ወጥተዋል።

በተያያዘም በከሚሴ ግንባር ማጀቴን፣ ጭረቲን፣ ከሚሴን፣ ርቄን፣ ወለዲን፣ አልቡኮ ከተሞችን እና የቃሉ ወረዳን አብዛኛውን ክፍል በመቆጣጠር፣ ጥምር ጦሩ ግዙፍ ሰራዊቱን በማስከተል የኢንዱስትሪ ከተማዋ ኮምቦልቻን ከወራሪው ለማስለቀቅ እጅ አልሰጥ ያለን ጠላትንም ለመቅበር እየገሰገሰም ነው ።

ዛሬ እና ትናንት በተደረጉት ከፍተኛ የማጥቃት ኦፕሬሽኖች አብዛኛው የአሸባሪው ኃይል ከመቼውም ጊዜ በላይ እንዲበተን ተደርጓል።

ጥምር ጦሩ ያገኘውን ድል አስጠብቆ ለመቀጠል እንዲሁም ዘላቂ ሰላም ለማስፈን እንዲረዳ የተበተነውን አሸባሪ በመልቀም ላይ ሲሆን አብዛኞቹ ጀሌዎች ሲደመሰሱ ቀሪዎቹ እጅ በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሉዋል ።

እስካሁንም በነበሩት ኦፕሬሽን "ተደናብሮ የገባው አሸባሪ ኃይል፣ የዘረፈውን ንብረትና ራሱን ይዞ አይወጣም" ተብሎ የተገባው ቃል በተግባር ፈጽሟልም ነው የተባለው ።

አስቀድሞ ነጻ በወጡት በምሥራቅ፣ በምዕራብና በመሐል ግንባር በሚገኙ ከተሞችና አካባቢዎች መንግሥታዊ አስተዳደር ተመልሶ በመደራጀት ሥራውን የጀመረ ሲሆን የከተማውን ሰላም ለማስጠበቅና ህዝቡንም ለማረጋጋት የሚያስችል ሃይል በቦታው እንዲሰፍር በማድረግ ከማህበረሰቡ ጋር ተቀናጅቶ እንዲሰራም እንደሚደረግ ለማወቅ ችለናል።

ከዚህ ጋር በተያያዘም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመከላከያ ሰራዊት በአሁኑ ወቅት የኢንዱስትሪ ከተማ የሆነችውን ኮምቦልቻን ከቦ የሚገኝ እንደሆነ የታወቀ ሲሆን በዚያ ያሉ የጥፋት ቡድኑ ሃይሎች የከፋ ጉዳት ሳይገጥማቸው በአንድ ቀን ውስጥ እጃቸውን እንዲሰጡ ጥሪ የሚያደርግ ወረቀትም በአየር መበተኑ ታውቁዋል ።

ይህ በንዲህ እንዳለ የአፍሪካ ፖለቲካ ተንታኞች የኢትዮጲያ ሰራዊት አማራ እና አፋር ግንባር ያለውን ጦርነት ሙሉ በሙሉ በድል ሲያጠናቅቁ ጦርነቱ የመጨረሻው ምእራፍም ሊሆን ይችላልም ሲሉ የተናገሩ ሲሆን ለዚህም ካነሱዋቸው ዋና ዋና ነጥቦች መሃል

የትግራይ ሰራዊት በሰው ሃይል እንዲሁም በጦር መሳርያ ከኢትዮጲያ ሰራዊት በላይ ልቆ ተገኝቶ ሳይሆን እስካሁንም እድሜውን ማርዘም የቻለው

1/ ጦሩን ወደ አማራና አፋር ክልል በማስገባት ጦርነቱን ከራሱ ሜዳ ለማራቅ የሞከረበት ስትራቴጂ
2/ ህዝብ በሚኖርበት አካባቢ እንደ ደሴ እና ኮምቦልቻ የመሳሰሉ የራሱ ወገን ያለበት ቦታዎች ገብቶ እራሱን መሸሸጉ
3/ የውጪ ሃይሎች ከሚያደርጉለት ሁለንተናዊ ድጋፍ በተጨማሪ በኢትዮጲያ በኩል ይህን ቡድን የሚደግፉ የትግራይ ተወላጆች እና በጥቅም የታሰሩ አመራሮች እያደረጉ የነበረው ድጋፍ ለጥቂት ወራትም ቢሆን ተሳክቶም ነበር።

አሁን ግን ይህ ሁሉ መልኩን ቀይሩዋል።
መንግስትም አስቸኩዋይ ግዜ አዋጅ አውጥቶ ባለ በሌለ አቅሙ ሰፊ እርምጃ በመውሰዱ በኢትዮጲያ በኩል ሲያገኙ የነበረውን ድጋፍ አብዛኛ

የትዊተር ርምጃ ያሳደረዉ ቅሬታትዊተር ሕወሓትን የሚነቅፉ አካውንቶችን ሆን ብሎ እያገደ ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ለትዊተር ቅሬታ ማስገባቱን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገበ። የዜና ምንጩ...
01/12/2021

የትዊተር ርምጃ ያሳደረዉ ቅሬታ

ትዊተር ሕወሓትን የሚነቅፉ አካውንቶችን ሆን ብሎ እያገደ ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ለትዊተር ቅሬታ ማስገባቱን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገበ። የዜና ምንጩ የጠቅላይ ሚንሥትር ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ሥዩምን ጠቅሶ እንደዘገበው፦ የኢትዮጵያ መንግሥት ትዊተር ስለ ኢትዮጵያ የሚቆረቆሩ አካውንቶችን ዒላማ አድርጎ እየዘጋ ነው ብሎ ያምናል። የኢትዮጵያ መንግሥት ለትዊተር ፖሊሲ ቡድን ይህንኑ አስመልክቶ የቅሬታ ደብዳቤ ማስገባቱም ተዘግቧል። መንግሥት ባስገባው ቅሬታም «በሌሎች በርካታ ዴሞክራሲያዊ ተቋማት ውስጥ እንደሚታየው የሕወሓት ደጋፊዎች ሰርገው እንደገቡ እናምናለን» ማለቱን ቢልለኔ ሥዩም ተናግረዋል ሲል የዜና ምንጩ ጠቅሷል።

በ ንቅናቄ ጉልኅ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አንዳንድ አካውንቶች ሰሞኑን በተከታታይ ታግደዋል። አካውንቶቹ ለምን እንደሚታገዱ በትዊተር በኩል በይፋ የተባለ ነገር ባይኖርም፤ ንቅናቄውን የሚከታተሉ ሰዎች ትዊተር ሆን ብሎ ተቺ ድምፆችን በማፈን ላይ ነው ሲሉ ይሰማሉ። ሌሎች በተቃራኒው፦ አካውንቶቹ የተዘጉት ጥላቻ እና ግጭቶችን በማስፋፋት ነው ይላሉ።

የኤርትራ መንግሥት የኢንፎርሜሽን ሚንሥትር የማነ ገብረ መስቀል በበኩላቸው፦ ትዊተር ታዋቂ ሰዎችን «በፖለቲካ አድልዎ» አግዷል ብለዋል። በ ንቅናቄ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ የሚታወቁት ዶ/ር ሲሞን ተ/ማሪያም እና ሌሎችም «በመደበኛ የመገናኛ አውታሮች የሚሰራጨውን የሐሰት ዘገባ ለመቋቋም በሚያቀርቡት የተጠና እና ሚዛናዊ ዘገባዎቻቸው ሽልማት ይገባቸዋል» ብለዋል። በአንጻሩ ግን «ትዊተር አካውንቶቹን ማገዱ ተቀባይነት የሌለው እና አስቸኳይ ግምገማ የሚያሻው ነው» ብለዋል ሚንስትሩ፣ በይፋዊ የትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፋቸው።

አንዳንድ የጥላቻ ንግግሮችን ያሰፈሩ የትዊተር አካውንቶች ላይ ትዊተር ርምጃ ሲወስድ ዐይታይም፤ ስለ ኢትዮጵያ የሚቆረቆሩ ድምፆችን ግን ትዊተር «ሆን ብሎ እያፈነ ነው» ሲሉ በርካቶች ቅሬታቸውን እያስተጋቡ ነው።

https://mereja.com/amharic/v2/631517
01/12/2021

https://mereja.com/amharic/v2/631517

ዩናይትድ ስቴትስ በምስራቅ እና በምዕራብ መካከል ያለውን ኮሪደር ለመቆጣጠር ከሞላ ጎደል ሁሉም ዋና ዋና ኃያላን ጋር ከፍተኛ ፉክክር በሆነው በአፍሪካ ቀንድ ላይ ያለውን ጫፍ በእጅጉ አ.....

ሰበር መረጃሩሲያ የአሜሪካ ኤምባሲ ሰራተኞች በአስቸኳይ ከሞስኮ ለቀው እንዲወጡ  አሳሰበች!  ይህን ያሳወቀው የሩሲያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሲሆን ፣ ሰራተኞቹ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከ...
01/12/2021

ሰበር መረጃ

ሩሲያ የአሜሪካ ኤምባሲ ሰራተኞች በአስቸኳይ ከሞስኮ ለቀው እንዲወጡ አሳሰበች! ይህን ያሳወቀው የሩሲያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሲሆን ፣ ሰራተኞቹ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከሩሲያ ምድር እንዲወጡ ታዘዋል።

የአዲስ አበባ ሴቶች ለመከላከያ ሰራዊቱ ከ 20 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ አደረጉ************************የአዲስ አበባ ሴቶች ለመከላከያ ሰራዊቱ ከ 20 ሚሊዮ...
01/12/2021

የአዲስ አበባ ሴቶች ለመከላከያ ሰራዊቱ ከ 20 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ አደረጉ
************************
የአዲስ አበባ ሴቶች ለመከላከያ ሰራዊቱ ከ 20 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ አደረገዋል፡፡

የተለያዩ ሴት አደረጃጅቶች ፣ምገባ ኤጀንሲ ላይ ተቀጥረው የሚሰሩ መጋቢ እናቶች እና ከምገባ ኤጀንሲ ጋር በትብብር የሚሰሩ አካላት በድጋፉ ተሳትፈዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የእናቶች ድጋፍ ምግብ ብቻ ሳይሆን ሞራልም ነው ብለዋል፡፡

"ድሉ ይቀጥላል፣ ኢትዮጵያ ታሽንፋለች፣ ሀቅ እኛ ዘንድ ነውያለው ፣ከነኩን አንመለስም "ብለዋል፡፡

እናቶች በአንድ ሳምንት ጊዜ 83 ሰንጋ አርደው፣ስጋ ዘልዝለው፣ለሰራዊቱ አጋነታቸውን በማሳየታቸው አድናቆታቸውን ገልፀዋል፡፡

ከሳምንት ወዲህ የከተማዋ ሴቶች የበሰለ ምግብ ለሰራዊቱ ግንባር ድረስ ማድረስ መጀመራቸውንም ገልፀዋል ከንቲባዋ፡፡

እየተመዘገበ የሚገኘው ድል የሁሉም በመሆኑ እኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

የሴቶች ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሀና የሺንጉስ የሀገር ፀር የሆነውን አሸባሪ ቡድን ለመስደምሰስ በሚከፈለው ዋጋ የሴቶችተሳትፎ ትልቅ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በደቡብ ሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለመከላከያ ሠራዊት ከ23 ሺህ ዶላር በላይ ድጋፍ አደረጉ********************በደቡብ ሱዳን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አምባሳደር ነቢል ማሃዲ በደቡብ ሱዳን ...
01/12/2021

በደቡብ ሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለመከላከያ ሠራዊት ከ23 ሺህ ዶላር በላይ ድጋፍ አደረጉ
********************

በደቡብ ሱዳን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አምባሳደር ነቢል ማሃዲ በደቡብ ሱዳን በተለያየ የሥራ መስክ ተሰማርተው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ለሁለተኛ ጊዜ ያዋጡትን 23 ሺህ 655 የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ለመከላከያ ሚኒስቴር አስረክበዋል።

አምባሳደር ነቢል ማሃዲ በዚህ ወቅት በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአገር ቤት እየተካሄደ ያለውን የሕልውና ዘመቻ ጨምሮ ለሕዳሴው ግድብና ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውሉ ተከታታይ ድጋፎችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።

ኢትዮጵያውያኑ መሰል ድጋፎችን አጠናክረው ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆናቸውን አምባሳደር ነቢል አረጋግጠዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ማርታ ሉዊጂ በበኩላቸው በደቡብ ሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላበረከቱት ድጋፍ አመስግነው ድጋፉ በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

የደቡብ ሱዳን ሕዝብና መንግሥት በዚህ ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን በመቆማቸውም ወ/ሮ ማርታ በአምባሳደር ነቢል በኩል ምስጋና ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኀነው መረጃ ያመለክታል።

Sanyii MootiiMagaalaa Jimmaa....Eebbaa Gachaana Sirnaa  suuraadhaanየሥርዓቱ ጋሻ ሰልጣኞች ምረቃ በፎቶ::
01/12/2021

Sanyii Mootii
Magaalaa Jimmaa....

Eebbaa Gachaana Sirnaa suuraadhaan
የሥርዓቱ ጋሻ ሰልጣኞች ምረቃ በፎቶ::

በኢትዮጵያ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጩ ከነበሩ አካውንቶች ውስጥ 49 በመቶ የሚሆኑት በዲጂታል ወያኔ የሽብር ቡድን የተከፈቱ መሆናቸው ተገለጸአዲስ አበባ ፤ ህዳር 22/2014: ባለፉት ሦስት...
01/12/2021

በኢትዮጵያ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጩ ከነበሩ አካውንቶች ውስጥ 49 በመቶ የሚሆኑት በዲጂታል ወያኔ የሽብር ቡድን የተከፈቱ መሆናቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 22/2014: ባለፉት ሦስት አመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዉስጥ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጩ ከነበሩ አካውንቶች ውስጥ 49 በመቶ የሚሆኑት በዲጂታል ወያኔ የሽብር ቡድን የተከፈቱ አካውንቶች መሆናቸው ተገለጸ፡፡

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የግልጽ ምንጭ መረጃ ኦፕሬሽን ማዕከል ኃላፊ የሆኑት አቶ አሸናፊ ኃይሉ እንደገለጹት 122 ሺህ ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ያደርጋሉ ብለዋል፡፡

ከእነዚህ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ከሚያሰራጩ አካውንቶች ውስጥ 49 በመቶ የሚሆኑት በዲጂታል ወያኔ ቡድን የተከፈቱ መሆናቸውን አቶ አሸናፊ አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም የህውሐት አሸባሪ ቡድን በ2013 ዓ.ም ጦርነት በከፈተበት ህዳር ወር ብቻ 17 ሺ የሚሆኑ ሀሰተኛ የቲዊተር አካውንቶችም በዲጂታል ወያኔ የጥፋት ቡድን ተከፍተው ነበር ብለዋል፡፡

በአሸባሪዉ ቡድን በተከፈቱ ሀሰተኛ አካውንቶች በአንድ ቀን ብቻ 25ሺ የሚደርሱ መልዕክቶች በቲውተር ምህዳሩ ላይ ይሰራጩ እንደነበርም ነው ሃላፊዉ የገለጹት፡፡

የጥፋት ቡድኑ እነዚህን ሁሉ ዘመቻዎች አድርጎ አልሳካ ሲለው ለሽብር ትግባር ተባባሪ ከሆኑ ሃገራት እገዛ በማግኘት እንዲሁም አስቀድመው አስርገዉ ያስገቧቸዉን ሰዎች በመጠቀም ከእውነታ ውጪ የሆኑ ዘገባዎችን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ እየሰሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

ተዋቂዎቹ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችም ከጥፋት ቡድኑ ጋር የተያያዙ ወይም ለቡድኑ ይጠቅማሉ ያሏቸውን ይዘቶች በፕላትፎርማቸው ላይ እንዲኖሩ ወይም እንዲቆዩ ከመፍቀድ ባለፈ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆኑ ለሌሎች አካላት በስፋት ያሰራጩላቸው /Suggest/ ያደርጉላቸው እንደነበረም አቶ አሸናፊ አስረድተዋል፡፡

በሌላ በኩል የሀገርን አንድነት ወይም ኢትዮጵያዊነትን የሚያቀነቅኑ አካውንቶችን የመዝጋትና መረጃዎቻቸው እንዳይሰራጩ የማድረግ እንዲሁም አንዳንድ አካውንቶችን መረጃ እንዳይለጥፉ ከማድረግም ባለፈ ለተለያየ ጊዜ ሲዘጓቸው እንደነበር አቶ አሸናፊ አብራርተዋል፡፡

እነዚህ ሁሉ ድርጊቶች የሚያሳዩት በጦር መሣሪያ ከሚደረገው ጦርነት በተጨማሪ በመረጃ ጦርነቱ መስክ አስቀድሞ በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ አሽባሪዉ ቡድን ጉልበት ያለዉ በማስመሰል ከፍተኛ የሆን የፕሮፖጋንዳ ስራ ሲሰራባቸው እንደነበረ የሚያመለክቱ መሆናቸውን ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

ይቺን ደፋር  ላመነችበት አላማ እጅ የማትሰጥ የሌቦች የግር እሳት ፣የድሆች እናት ፣ የከንቲባዎች በጎ ተምሳሌት ፣ ለተፈናቀሉ ወገኖች ፈጥኖ ደራሽ  ፣ የሰራዊታችንን የሁዋላ ደጀን መሆን የቻ...
01/12/2021

ይቺን ደፋር ላመነችበት አላማ እጅ የማትሰጥ የሌቦች የግር እሳት ፣የድሆች እናት ፣ የከንቲባዎች በጎ ተምሳሌት ፣ ለተፈናቀሉ ወገኖች ፈጥኖ ደራሽ ፣ የሰራዊታችንን የሁዋላ ደጀን መሆን የቻለች ቆራጥ ሴት አለማመስገን አለማድነቅ ይቻለን ይሆን ?

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ
እናመስግናለን

አሜሪካ አሸባሪን በመደገፍ ኢትዮጵያን ማቀቧን ሴናተር ጂም ኢንሆፌ ተቃወሙኅዳር 22/2014 የኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ወዳጅ የሆኑት የአሜሪካ የኦክላሆማ ግዛት ሴናተር ጂም ኢንሆፌ አሜሪካ በኢት...
01/12/2021

አሜሪካ አሸባሪን በመደገፍ ኢትዮጵያን ማቀቧን ሴናተር ጂም ኢንሆፌ ተቃወሙ

ኅዳር 22/2014 የኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ወዳጅ የሆኑት የአሜሪካ የኦክላሆማ ግዛት ሴናተር ጂም ኢንሆፌ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችው ማዕቀብ አግባብ አለመሆኑን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አንድነቷ የተጠበቀች፣ ሰላም የሰፈነባት፣ የተረጋጋች ኢትዮጵያን ለመፍጠር እየሰሩት ያለው ሥራ የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡

"መንግሥታችን (የአሜሪካ መንግሥት) በሕዝብ የተመረጠውን መንግሥት እና ያጣውን ሥልጣን በደም አፋሳሽ ግጭት መልሶ ለመያዝ የሚሰራን አሸባሪ ቡድን እኩል ማየቱ ተገቢ አይደለም አኩል ያልሆኑ አካላትን ለማስተካከል መሞከሩም አስደንግጦኛል" ብለዋል።

አሜሪካም በዴሞክራሲያዊ መንገድ በሕዝብ ከተመረጠው መንግሥት ጋር በጋራ ለሰላም መረጋገጥ መስራት እንጂ አሸባሪ ቡድንን በመደገፍ ኢትዮጵያ ላይ የቅጣት እርምጃ መውሰድ እና ማዕቀብ መጣል አግባብ አለመሆኑን ልታምን ይገባል ብለዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር ወደ ግንባር ለሚዘምቱ በጎ ፍቃደኛ ዘማቾች ሽኝት አደረገ። --------------------------------------ከትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የተውጣጡ 32 ...
01/12/2021

የትምህርት ሚኒስቴር ወደ ግንባር ለሚዘምቱ በጎ ፍቃደኛ ዘማቾች ሽኝት አደረገ።
--------------------------------------
ከትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የተውጣጡ 32 በጎ ፍቃደኛ ዘማቾች በዛሬው እለት ሽኝት ተደርጎላቸዋል።

ለመከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ እና የስንቅ ዝግጅትም እየተደረገ ነው።

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) እርስ በእርስ እንዳንተማመን ያደረገን ስርዓት ጊዜው አብቅቶ "ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም" ለማድረስ በሙሉ አቅማችን ወደ ስራ የምንገባበት ጊዜ ተቃርቧል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ወደ ቀደመ ክብሯ እስክትመለስ ድረስ ለመከላከያ ድጋፋችን እንቀጥላለን ያሉት ሚኒስትሩ እስከ አሁን ከ16 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ መሰብሰቡን ተናግረዋል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ፒ ኤች ዲ) ማንኛውም ጠላት ጥቃት ከመክፈቱ በፊት ሁለት ሶስቴ እንዲያስብ አድርገን ለጠላት ትምህርት መስጠት አለብን ብለዋል።

ዘማቾቹ በድል እንዲመለሱ በመመኘት የባንዲራ ርክክብ ተከናውኗል።

አሁን 1983 አይደለም!አሁን መንገድ እየመራ አራት ኪሎ የሚያመጣ ኢትዮጵያዊ የለም፤ አሁን በሃሰት ፕሮፓጋንዳ ተታሎ አገሩን የሚሸጥ ኢትዮጵያዊ የለም(ጥቂት በገንዘብ የተሸጡ ባንዳዎችን ሳይጨ...
01/12/2021

አሁን 1983 አይደለም!
አሁን መንገድ እየመራ አራት ኪሎ የሚያመጣ ኢትዮጵያዊ የለም፤ አሁን በሃሰት ፕሮፓጋንዳ ተታሎ አገሩን የሚሸጥ ኢትዮጵያዊ የለም(ጥቂት በገንዘብ የተሸጡ ባንዳዎችን ሳይጨምር) ፤ በውጪ ሃይሎች ግፊት አሁን ላይ ከሃገር ኮብልሎ የሚወጣ የሃገር መሪ የለም፡፡ በውጪ ሃይሎች ማስፈርራርያ ልቡ የሚሸበር ህዝብ የለም፡፡
አሁን 2014 ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን አሁን ዳግመኛ በህወሓት የቅጥፈት መንገድ ፤በውጪ ሃይሎች ማስፈራርያና ዛቻ እንዲሁም ጫና በፍፁም አይታለሉም!!
ድል ለኢትዮጵያ!

የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን 4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ማስገባቱ ተገለፀ*************በሀገሪቱ ያለውን ገበያ ዋጋ ለማረጋጋት የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን 8 ሚሊዮን ኩንታ...
01/12/2021

የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን 4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ማስገባቱ ተገለፀ
*************

በሀገሪቱ ያለውን ገበያ ዋጋ ለማረጋጋት የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን 8 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ለማስገባት አቅዶ በመጀመሪያው ዙር 4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ማስገባቱ ተገለፀ ።

ከውጭ ሀገር ከ11 ቢሊዮን ብር በላይ ተገዝቶ የገባው ይህ ስንዴ በአምስት ማዕከላት ማለትም በአዲስ አበባ፣ በሻሸመኔ፣ በባህርዳር፣ በአዳማ እና ድሬዳዋ በሚገኙ ማሰራጫ ማዕከላት ይሰራጫልም ሲሉ የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አቻ ደምሴ አስታውቀዋል።

በተለያዩ ዳቦ ቤቶች የሚታየውን የዋጋ ጭማሬ እና የዱቄት እጥረት በመቅረፍ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ይደረጋልም ብለዋል።

በሚቀጥሉት 15 ቀናት ስርጭቱ በማዕከላቶቹ የሚከናወን ሲሆን የሚሰራጨው ስንዴ በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋሉን ቁጥጥር ይደረጋልም ተብሏል።

01/12/2021
Sadaasa 22, 2014 - Gootni Raayyyaa Ittisa biyyaa dawoo gareen shororkeessaa TPLF qopheefate haala kanaan caccabsee Gaash...
01/12/2021

Sadaasa 22, 2014 - Gootni Raayyyaa Ittisa biyyaa dawoo gareen shororkeessaa TPLF qopheefate haala kanaan caccabsee Gaashanaa kan too'atee.

የተሰበሩት የጋሸና ግንባር ምሽጎች በፎቶየጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከትናንት በስትያ ጋሸናን እንይዛለን ማለታቸው ይታወሳል።-አካባቢህን ጠብቅ _ ወደ ግንባር...
01/12/2021

የተሰበሩት የጋሸና ግንባር ምሽጎች በፎቶ

የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከትናንት በስትያ ጋሸናን እንይዛለን ማለታቸው ይታወሳል።

-አካባቢህን ጠብቅ

_ ወደ ግንባር ዝመት

_ መከላከያን ደግፍ

መረጃዎቻችንን ለማግኘት

UUmmanni Ityoophiyaa damee hundaan tumsaan yoo ka’e, bu’aan isaa injifannoodha - MM Abiy AhimdSadaasa 22, 2014  Uummanni...
01/12/2021

UUmmanni Ityoophiyaa damee hundaan tumsaan yoo ka’e, bu’aan isaa injifannoodha - MM Abiy Ahimd

Sadaasa 22, 2014
Uummanni Ityoophiyaa damee hundaan tumsaan yoo ka’e, bu’aan isaa injifannoodha jedhan Muummeen Ministiraa FDRI Abiy Ahimd.

Adda waraanaan, Dippiloomaasiin, Diinagdeen, Kominikeeshiniin, galaa qopheessuun, duultota kunuunsuun, nageenya kabachiisuun, lammiilee qe’ee fi qabeenya isaniirraa buqqa’an deeggaruun addaa waraanaa hundatti kan duultan marti baga gammaddan jedhaniiru ergaa gama miidiyaa hawaasummaa isaaniin dabarsaniin.

Naannoo keessan eegaa!

Gara adda waraanaatti duulaa!

Raayyaa Ittisa Biyyaa deeggaraa!

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sabir Gali posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Sabir Gali:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share