Dagimawit Girma/ዳግማዊት ግርማ

Dagimawit Girma/ዳግማዊት ግርማ ባንዴ አንድ ርምጃ የምትራመድ

ለመስቀላችን መዘነጫ ይደውሉ ይዘዙ 🙏🖤
21/09/2022

ለመስቀላችን መዘነጫ ይደውሉ ይዘዙ 🙏🖤

ሰዎች ያሉህን ሳይሆን አንተ ነኝ የምትለውን ነህና ነኝ የምትለውን ምረጥ!ዳግማዊት ግርማ ዛሬ ላይ በብዙ ሚልዮን ዶላር የሚቆጠረ ሀብት ባለቤቷ ህንዳዊቷ ተዋናይና ዘፋኝ ፕሪያንካ ቾፕራ (Pri...
19/09/2022

ሰዎች ያሉህን ሳይሆን አንተ ነኝ የምትለውን ነህና ነኝ የምትለውን ምረጥ!

ዳግማዊት ግርማ

ዛሬ ላይ በብዙ ሚልዮን ዶላር የሚቆጠረ ሀብት ባለቤቷ ህንዳዊቷ ተዋናይና ዘፋኝ ፕሪያንካ ቾፕራ (Priyanka Chopra) የህይወቷ ትላንት ላይ ከባድ ወቅቶችን አሳልፋ ነበር፤ በአሜሪካን ሀገር ምትማርበት ትምህርት ቤት ውስጥ አስቀያሚ ሴት ተብላ ተሸማቅቃ እንዲሁም በፍርሀት ምሳዋን በመታጠቢያ ቤት ውስጥ ተደብቃ በልታ ታውቃለች፡፡

ትላንት አሜሪካውያኑ አስቀያሚ እያሉ ያሾፉባት የነበረች ልጅ የሚስ ወርልድ 2000 የቁንጅና ውድድርን አሸናፊ ሆናለች። በርካታ የተለያዩ ሀገር አቀፍ እና አለምአቀፍ የፊልም ሽልማቶችንም ማሸነፍ ችላለች። ለዛሬዋ ዝነኛና ጎበዟ ፕሪያንካ የእናቷ መልካምና ጠንካራ ስብዕና ከፍተኛውን አስተዋፅኦ እንደሚይዝ በተለያዩ መድረኮች ላይ ስትገልፅ ትደመጣለች፡፡

ፕሪያንካ በህንድ ከፍተኛ ክፍያ ከሚከፈላቸው ባለሙያዎች መሀከል አንዷ ስትሆን ለተከታታይ ዓመታት በ’Time’ እና ‘Forbes’ መፅሄቶች የአለማችን 100 ተፅእኖ ፈጣሪ ሴቶች ዝርዝር ውስጥም ተካትታለች።

ፕሪያንካ ቾፕራ በዲሴምበር 2018 ያገባችው ባሏ(ኒክ ጆንስ) በ10 አመት ታላቁ ስትሆን የአንድ ሴት ልጅ ወላጆች መሆንም ችለዋል፡፡

ፕሪያንካ ቾፕራ ከዓመታት በፊት ከሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ተሰደው ኢትዮጵያ ውስጥ የተጠለሉ እና በዩኒሴፍ እና መንግስት የሚደገፉ ተማሪዎችን በጉብኝቷ ወቅት አግኝታ ማናገሯ የሚታወስ ነው፡፡

ከውዥንብር ተጠበቁ!!የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ  ዛሬ ይፋ በተደረገውና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት  ባዘጋጀው የ4ኛ ክፍል የሂሳብ መፅሃፍ ገፅ 18 ላይ የግእዝ ቁጥርን አስመልክቶ  ወ...
17/09/2022

ከውዥንብር ተጠበቁ!!

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ዛሬ ይፋ በተደረገውና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት ባዘጋጀው የ4ኛ ክፍል የሂሳብ መፅሃፍ ገፅ 18 ላይ የግእዝ ቁጥርን አስመልክቶ ወጥቷል ተብሎ የተገለፀው ሃሳብ በመፅሃፉ ውስጥ የማይገኝና መሆኑንና ሆነ ተብሎ የሃሰት መረጃ የማሰራጨት ተግብር መሆኑን አስታውቋል፡፡

ወደ ስራ ገብተናል ቤተሰብ የተለያዩ MDF እና ላሚኔት  የእንጨት ስራዎች አሉን። ቁም ሳጥን ፣ የTv ማስቀመጫ ፣የሶፋ ጠረጴዛ፣ የኪችን ቁም ሳጥን --- እንሸጣለን ። በትዕዛዝም እንሰራለን...
17/09/2022

ወደ ስራ ገብተናል ቤተሰብ

የተለያዩ MDF እና ላሚኔት የእንጨት ስራዎች አሉን። ቁም ሳጥን ፣ የTv ማስቀመጫ ፣የሶፋ ጠረጴዛ፣ የኪችን ቁም ሳጥን --- እንሸጣለን ። በትዕዛዝም እንሰራለን። አዲስ አበባ ውስጥ የትኛውም ቦታ በራሳችን ትራንስፖርት እናደርሳለን ። መለያችን ጥራታችን ነው ።

0910879772 ይደውሉ

Market channel
https://t.me/yet1087

በጎ አድራጊዋ የቤት ሠራተኛ‼️***********ዳግማዊት ግርማየኔነሽ ዳኜ ትባላለች። ሶስት ልጆቿን ለብቻዊ የምታሳድገው በቤት ሰራተኝነት እና በሌሎች ስራዎች ነው። ከቤት ሰራተኝነት በተረፈ ...
03/09/2022

በጎ አድራጊዋ የቤት ሠራተኛ‼️
***********

ዳግማዊት ግርማ

የኔነሽ ዳኜ ትባላለች። ሶስት ልጆቿን ለብቻዊ የምታሳድገው በቤት ሰራተኝነት እና በሌሎች ስራዎች ነው። ከቤት ሰራተኝነት በተረፈ ጊዜዋ በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ትሰማራለች። ለእርሷም የሚያስፈልጋት ብዙ ነገር ቢኖርም ያ ግን በጎ ነገር ከማድረግ ወደኋላ አያስብለኝም በማለት የምሳ ሰዓቷን ሮጣ ሰዎችን ረድታ ትመለሳለች።

ደጎች ይብዙልን 💖🙏

የየኔነሽን ሙሉ ታሪክ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=80577

26/08/2022

ሰላም እንዴት አመሻችሁ
ይህንን የአምስት ቀን ስልጠና እድል በኬንያ ናይሮቢ በሚዲያ ውስጥ በኃላፊነት ያላችሁ እንድታመለክቱ እናበረታለን፡፡ የማመልከቻው መጨረሻ ቀን ነሐሴ 25 ቀን 2014 ነው፡፡
The Aga Khan University – Graduate School of Media and Communications in partnership with The Konrad Adenauer Foundation will be hosting this in-person, 5-day programme whose content will focus on managing newsroom conflict in a way that does not disrupt processes and impact on journalism quality.

This is a great opportunity for newsroom leaders to delve into key conflict resolution concepts relevant to the functions of newsroom leaders.

Please note that all costs associated with attendance of the programme in Nairobi will be catered for, that is, visa, flights and accommodation and participants are NOT required to pay to attend the training.

Participants to this programme will be selected on a first come-first serve basis and upon satisfactorily meeting the set criteria in the document attached.

Kindly apply via this link. If you need any assistance with your application, please feel free to reach out via phone, email, text or WhatsApp (+254 722 52 59 51).

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeX_6e5EPsKV-ggc88u-xby5qVd6ReKY09NWUWcQM6aQtzxPw/viewform

የቡሄ ትዝታዬ በበጌምድሯ እንቁ ደብረታቦርዳግማዊት ግርማያለፈውን ዓመት ክፉ በመልካም ትዝታ ለመተካት ጥሩውን በናፍቆት ለማስታወስ ወጣ ገባ በሚባልባት ነገን በተስፋ በሚጠበቅባት በዓመቱ አስራ...
26/08/2022

የቡሄ ትዝታዬ በበጌምድሯ እንቁ ደብረታቦር

ዳግማዊት ግርማ

ያለፈውን ዓመት ክፉ በመልካም ትዝታ ለመተካት ጥሩውን በናፍቆት ለማስታወስ ወጣ ገባ በሚባልባት ነገን በተስፋ በሚጠበቅባት በዓመቱ አስራ ሁለተኛ ወር በሆነችው ወርሀ ነሀሴ ላይ ነን።

ክረምት ሊወጣ በጋው ሊመጣ ሀገሬው በአዲስ ዓመት “እንቁለጣትሽ” ሊል ልብን በተስፋ ሊሞላ ሲሻ የነሀሴን ወር በቡሄ፣ በሻደይ፣ ሶለልና አሸንድዬ በዓል ድልድይነት ላይ ይረማመዳል።

የቡሄ በዓል ከነ ሙሉ ክብሩ በደብረታቦር ከተማ ላይ አለ። ደበረታቦር የቡሄ በዓል በሚከብርባት ሰሞን ለሰርጓ ብዙ ጥሎሽ እንደተጣለላት አዲስ ሙሽራ ፍንክንክ ስትል ትከርማለች።

በሷ መኖር መልካም የሆነልን እኛ ከብዙ ጋቢዎች አምልጦ በሚጋረፈው ብርድ በምትታወቀው በታቦር ተራራዋ እመቤት ታዛ ስር ተጠልለናል።

ቡሄ ከአሸንድዬ ጋር ተጣምሮ በሚከበርባት ውቧ ከተማ ከሰላሳ በላይ ሚዲያዎች ከደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ በተደረገልን ጥሪ መሰረት እንግዳ ሆነን ተገኝተናል።

ደብረታቦር ከተማ ከተለያዩ ስፍራዎች የመጡ እሷን ባይ ወገኖቿን መቀነቷን ታጥቃ ስታስተናግድ ከርማለች።

የቡሄ በዓል በንጋት ኮከብነት ላለችበት ደቡብ ጎንደር ዞን ብቻ ሳይሆን ለመላው የአማራ ክልል ብሎም ለመላው ኢትዮጵያ ኩራትና ክብር ነው።

የቡሄ በዓል መጠሪያ በሆነው ደብረ ታቦር በተሰየመችው በደብረ ታቦር ከተማ ሌላ ውብ መልክ አለው። ሃይማኖታዊውንም ትውፊታዊውንም ሚናውን ይወጣል።

ደብረታቦርን በደብረታቦር የተሰኘው ሰናይ ሃሳብ በደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ሃሳብ ጠንሳሽነት እንዲሁም የበላይ አመራርነት ስር ኗሪ ነው። የድግሱ ባለቤት እንግዶቹን ለመቀበል ሸብረብ ሲያበዛ የከረመው የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ነው።

ቡሄ በመባል የሚታወቀው የደብረታቦር በዓል ደብረታቦርን በእንግዳ ዶፍ አጥለቅልቋታል። የከተማዋ ነዋሪዎች የአምናውን የጠላት ወረራ አሸንፈው ለዛሬ ቀን እንዲደርሱ ያደረጋቸውን አምላካቸውን ከማመስገን አልቦዘኑም።

የቡሄ ወይም የደብረታቦር በዓል መሰረት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ሲሆን በእምነቱ አስተምህሮ መሰረትም ኢየሱስ ክርስቶስ በደቀመዛሙርቱ ፊት ብርሃነ መለኮቱን በደብረ ታቦር ተራራ ላይ ከመግለጡ ጋር ተያይዞ ነው። ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ የሚል ትርጉም አለው፡፡

ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትም ባህሉም ሃይማኖቱም ሀገርን ጠቃሚ ነው ብለው ከጉዳያቸው ፅፈው ከበዓሉም ለመሳተፍ መልእክታቸውንም ለማስተላለፍ በከተማዋ ተገኝተዋል።

የቡሄ በዓል በተከበረበት ደብረታቦር ከተማ በታቦር ተራራ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን በሃይማኖታዊና ትውፊታዊ ስርዓቶች ተከብሯል።

በበዓል አከባበሩ ላይ ከታደሙት የመንግስት ተሿሚዎች መሀል አንዱ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ናቸው። እርሳቸውም በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት የቡሄን እሴት ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስቀጠል ባህልና ቱሪዝም ቢሮዎች ኃላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ የቀደሙ አባቶችና ትውልዶች የቡሄ በዓል ሊከበርባት ትውፊታዊና ሃይማኖታዊ ይዘት ሳይለቅ ዛሬ ላይ ለመድረስ የከፈሉትን ብዙ ዋጋ አላሳጡትም፤ ይልቁንም ባህልና ቱሪዝም ቢሮዎችም እሴቱን ለማቆየት ብዙ የቤት ስራዎች ይጠበቁባቸዋል ሲሉ አደራቸውን ይመለከታቸዋል ላሏቸው አካላት ሰጥተዋል።

ሚኒስትሩ የዘንድሮውን የደብረታቦር በዓል ሲያከብሩ አምና በዚህ ጊዜ በከተማዋ ስለነበረው ውጥንቅጥም አልዘነጉም ነበር። መከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ሀይልና ፋኖ በመተባበር አሸባሪውን ሕወሓት አከርካሪው ተመቶ ከከተማዋ የተመለሰበት ቀን መሆኑን ጭምር ነው ሚኒስትሩ ያወሱት።

የድግሱ ባለቤት የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አነጋግረኝ ጋሻውም በበኩላቸው፤ ሀሳቤን ገላጭ ነው ያሉትን በዓሉንና ህዝቡን የሚመለከት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኢትዮጵያዊ ባህሎች እየጠፉና በውጭና መጤ ባህሎች እየተወረሩ መምጣታቸውን በማሰብ ዩኒቨርሲቲው የቡሄን በዓል ለማክበር ተነሳስቶ አራተኛ ዙር ላይ መድረሱንም ነው ዶክተር አነጋግረኝ ጋሻው የገለፁት።

ዶክተር አነጋግረኝ አምና ከሕወሓት ጋር በነበረው ጦርነት ምክንያት ከተማይቱ የደብረታቦር በዓልን ማክበር አለመቻሏንም በፀፀት አውስተውታል።

የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ በነበረው አስከፊ ሁኔታ ምክንያት መከላከያ ሰራዊት እና ህዝቡ ባይቀለብሱት ኖሮ ከተማችን ላይ ከፍተኛ ውድመት ይፈጠር ነበርም ነው ፕሬዚዳንቱ ያሉት።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ዶክተር ሂሩት ካሳውም በበዓል አከባበሩ ላይ ከታደሙት የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አንዷ ናቸው።

ዶክተር ሂሩት በመልእክታቸው ኢትዮጵያ የታሪክና የሃይማኖት ሀብታም እንደሆነች በመመስከር የቡሄ በዓል ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ ትሩፋቱ ከኢትዮጵያ አልፎ አለማቀፋዊ መሆን እንደሚችልም ጠቁመዋል።

ዶክተር ሂሩት ታሪክን አምጠው ወልደው ለትወልድ ላስተላለፉ እናት አባቶች ምስጋናቸውን አቅርበው ለከርሞ በሰላም በፍቅር እንዲያደርሰን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

ኑ ለአዲስ አመት እናዘንጥዎ ይዘዙን ይደውሉ 0983987174
22/08/2022

ኑ ለአዲስ አመት እናዘንጥዎ ይዘዙን ይደውሉ 0983987174

ከአብን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት መልቀቄን ስለማሳወቅ፤(ክርስቲያን ታደለ ~ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል)የምወዳችሁ የአብን አባላትና ደጋፊዎች ይህን እስከዛሬ ድረስ በግልጽ ባለመናገ...
21/08/2022

ከአብን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት መልቀቄን ስለማሳወቅ፤
(ክርስቲያን ታደለ ~ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል)

የምወዳችሁ የአብን አባላትና ደጋፊዎች ይህን እስከዛሬ ድረስ በግልጽ ባለመናገሬ እጅጉን አዝናለሁ። ይሁንና ጉዳዩን ከዚህ በላይ ማዘግየት ንቅናቄያችን የተሟላ ሁለንተናዊ ሪፎርም እንዳያደርግ እንቅፋት ስለሚፈጥር እና በለውጥ ፈላጊ ብርቱ አባላትና ደጋፊዎቻችን ዘንድ የተሰነቀውን በጎ ተስፋ ጨርሶ እንዳያጨልም ስጋት ስላደረብኝ ዛሬ የግድ ኃቁን መናገር ይኖርብኛል።

በተጨባጭ ከግንቦት 1/ 2014 ዓ/ም ጀምሮ እንደሥራ አስፈፃሚ ተወስነው መሰራት የነበረባቸው ጉዳዮች ለውጥ ፈር በሆኑ ጥቂት ግለሰቦች ምክንያት ከስነስርዓት ውጭ እየተወሰኑ በመሆኑ የእኔ በስም ብቻ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ተብሎ መቀጠል ትክክል አለመሆኑን ተረድቻለሁ። የቤት ኅመማችንን በቤት ተነጋግረን እንቀርፋለን በሚል በዝምታ መቆየቴም በየደረጃው ባሉ የመዋቅራችን አባላትና አመራሮች ዘንድም ለምን ኃቁን አትነግረንም የሚል ወቀሳ አድርሶብኛል። ለተቋም ማዕከላዊነትና ወንድማማችነት እሴት በሚል በዝምታ መቆየቴ ድርጅቱን ከማዳን ይልቅ እንዲፈርስ የመተባበር ያህል በመሆኑ እያደር ስጋት ፈጥሮብኛል።

ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ያስቀመጣቸው ሁኔታዎች ተደማምረውበት በተለይም የለውጡ ሂደት የመደናቀ ከፍተኛ አደጋ የተጋረጠበት በመሆኑ፤ መላው የንቅናቄያችን አባላትና ደጋፊዎችም ይኸንኑ ተገንዝባችሁ፥ አብንን እንደድርጅት ለማስቀጠልና የሚጠበቅበትን ትግል በማድረግ የቆመላቸውን የፖለቲካ ግቦች ያሳካ ዘንድ፥ የሚቻላችሁን በጎ ሚና እንድትወጡም ጥሪዬን አቀርባለሁ። እንደአብንን መስራች፣ ፓርቲውን ወክሎ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባል እንደሆነ ኃላፊነት እንደሚሰማው ግለሰብ እና እንደ አንድ አማራ ንቅናቄያችንን ወደ ቀደመ ሥፍራውና ትክክለኛው የትግል መስመር ለመመለስ በሚደረገው ርብርብ ውስጥ አንዳችስ እንኳን የምቆጥበው ነገር እንደማይኖረኝም ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ።

አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር ጋዜጣዊ መግለጫዎችንም የምንሰጥ ይሆናል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ስር የነበሩ 6 ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች በአንድ ክልል እንዲደራጁ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ተቀበሎ ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ወ...
18/08/2022

የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ስር የነበሩ 6 ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች በአንድ ክልል እንዲደራጁ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ተቀበሎ ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ወስኗል
***************

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በዛሬው የአስቸኳይ ጉባኤ ስብሰባ ውሳኔ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ስር የነበሩ 6 ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች በአንድ ክልል እንዲደራጁ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ተቀብሎ ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ወስኗል።

በጋራ አዲስ ክልል እንዲመሰርቱ የቀረበውን ሀሳብ ተቀብሎ የህዝበ ውሳኔ እንዲያካሂዱ የተወሰነላቸው የወላይታ ዞን፣ የጋሞ ዞን፣ የጎፋ ዞን፣ የደቡብ ኦሞ ዞን፣ የጌዴኦ ዞን፣ የኮንሶ ዞን፣ እንዲሁም የደራሼ ልዩ ወረዳ፣ የአማሮ ልዩ ወረዳ፣ የቡርጂ ልዩ ወረዳ፣ የአሌ ልዩ ወረዳ እና የባስኬቶ ልዩ ወረዳ ናቸው።

ቀሪዎቹ የሀድያ ዞን፣ ሀላባ ዞን፣ ከንባታ ጠንባሮ ዞን፣ ጉራጌ ዞን ስልጤ ዞን እና የም ልዩ ወረዳ በነባሩ ክልል የሚቀጥሉ መሆኑም ታውቋል።

ኢ ፕ ድ

14/08/2022

200 ደርሰናል በቅርቡ ደግሞ አንድ ዜሮ ከኋላ እንጨምራለን 💖🙏

«የህዳሴው ስኬት መከራ የማይበግረን፤ ፕሮፖጋንዳ የማይረታን ጠንካራ ሕዝቦች መሆናችንን ያሳየንበት ነው» ወጣት ሱሌይማን አብደላ የማሕበረሰብ አንቂዳግማዊት ግርማ አዲስ አበባ ፡- በታላቁ ሕዳ...
14/08/2022

«የህዳሴው ስኬት መከራ የማይበግረን፤ ፕሮፖጋንዳ የማይረታን ጠንካራ ሕዝቦች መሆናችንን ያሳየንበት ነው» ወጣት ሱሌይማን አብደላ የማሕበረሰብ አንቂ

ዳግማዊት ግርማ

አዲስ አበባ ፡- በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዩኒት ሃይል እንዲያመነጭ ማድረግ መቻላችንና ሶስተኛውን ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት ማጠናቀቃችን መከራ የማይበግረን ፕሮፖጋንዳ የማይረታን ጠንካራ ሕዝቦች መሆናችንን ያሳየንበት ነው ሲል የማሕበረሰብ አንቂው ወጣት ሱሌይማን አብደላ ገለጸ።

የማሕበረሰብ አንቂው ወጣት ሱሌይማን አብደላ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጸው፤ የግድቡ መሰረት ድንጋይ ከተጣለበት እለት ጀምሮ ኢትዮጵያ ብዙ ውጣ ውረዶችን አሳልፋለች።

ኢትዮጵያ አገር፣ አህጉርና ዓለም አቀፍ ፈተናዎች ተቋቁማ እዚህ መድረሷ፤ ኢትዮጵያውያን መከራ የማይበግራቸው የሐሰት ፕሮፖጋንዳ የማይረታቸው ጠንካራ ሕዝቦች መሆናቸውን ለወዳጅና ጠላቶቻቸው ያስመሰከሩበት አጋጣሚ እንደሆነም ተናግሯል።

ኢትዮጵያ ይሄን ቀን ለማየት ብዙ ፈተናዎችን አሳልፋለች ያለው ወጣት ሱሌይማን፤ የገጠሟትን ፈተናዎች ተቋቁማ ለሁለተኛ ጊዜ ሃይል ማመንጨት መጀመሯና ለሶስተኛ ጊዜ የውሃ ሙሌቱን በስኬት ማጠናቀቋ፣ ለዜጎቿ በራስ መተማመንን የሚጨምር ነው ብሏል።

በግድቡ ግንባታ ወቅት ሥነ ልቦናዊ ማበረታቻ ያደረጉ፣ በገንዘብ የደገፉ፣ በሕይወታቸው ተደራድረው ግድቡን የሚጠብቁ የጸጥታ አካላት፣ በግንባታ ስራ የተሰማሩ ሰራተኞች፣ ከአገራቸው ጎን ለቆሙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የደስታና የመመስገኛ ወቅታቸው መሆኑንም ወጣት ሱሌይማን ተናግሯል።

እንደ ወጣት ሱሌይማን ገለጻ፤ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ተነሳሽነት ግድቡን መገንባት መቻላቸውና የግድቡ ኤሌክትሪክ ማመንጨት መጀመር ራስን ችሎ በራስ ወጪና እውቀት ትልልቅ ፕሮጀክቶችን የመገንባት አቅምና ጉልበት ያላት አገር መሆኗን ያሳየ ነው።

በተጨማሪም ስኬቱ ኢትዮጵያ ከምዕራባውያን እርዳታና ምፅዋት ነፃ ሆነው የቱን ያሕል መጓዝ እንደሚችሉ ትልቅ ማሳያ ነው ሲል ወጣት ተናግሯል።

ወጣት ሱሌይማን ለአገሩ ጥብቅና ቆሞ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ላይ አስተዋፅኦ በማበርከቱና የዚህ ታሪክ አካል መሆኑ እንደሚያኮራው የገለጸ ሲሆን ሌሎች ወጣቶችም እውቀታቸውን፣ ገንዘባቸውንና ጉልበታቸውን ሳይቆጥቡ አገራቸውን ሊያገለግሉ እንደሚገባቸው ጠቁሟል።

መንግሥት የሕዝብን አንድነት አስጠብቆ በምስራቅ አፍሪካ ብሎም በመላው ዓለም ጠንካራ ኢኮኖሚን ለመገንባት ፊቱን ወደ ልማት ስራዎች ማዞር እንደሚጠበቅበት የጠቆመው ወጣት ሱሌይማን ሕብረተሰቡም የሚመራውን መንግሥት የልማት ጥያቄዎች በመጠየቅ ለዚያ ምላሽ የራሱን አስተዋፅኦ ሊያበረክት እንደሚገባው ተናግሯል።

የግድቡ ኤሌክትሪክ ማመንጨት ኢትዮጵያን ወደ ኢኮኖሚዊ ከፍታ እንደሚያሸጋግራት የገለጸው ወጣት ሱሌይማን ኢኮኖሚዋን በተሻለ መንገድ ለመገንባት የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነም ጠቁሟል።

ሱሌይማን አብደላ ለቀና ትብብርህ አመሰግናለሁ🙏

ሱሌይማን አብደላ 😘💖
13/08/2022

ሱሌይማን አብደላ 😘💖

በዕድሜ ትንሿ ባለ ትልቅ ልብ- ሲፈን ዳግማዊት ግርማ በዚህች መከራና ግፍ በሚስተዋልባት ምድር፤ ሰዎች ክፋትን እንደ ክብር ቆጥረው በሚኖሩባት ዓለም ላይ መኖር የማይሰለቸው ቅን ልቦናን በታደ...
10/08/2022

በዕድሜ ትንሿ ባለ ትልቅ ልብ- ሲፈን

ዳግማዊት ግርማ

በዚህች መከራና ግፍ በሚስተዋልባት ምድር፤ ሰዎች ክፋትን እንደ ክብር ቆጥረው በሚኖሩባት ዓለም ላይ መኖር የማይሰለቸው ቅን ልቦናን በታደሉ ሰዎች ምክንያት ነው። ብዙዎች ሮጠው ባልጠገቧት ዓለም ላይ የሚያኖራቸው የደግነት ዓለም ከብዙ መከራ ሰውሮ የሚያቆያቸውም የመልካሞች ተስፋ የራሳቸውም መልካም የመሆን ዋሻ ነው።

በአብዛኛው ሕዝብ ዘንድ የምትታወቅ አንድ የክቡር ዶክተር ከበደ ሚካኤል «ፅድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም» የምትል ስንኝ አለች። ይህቺ ስንኝ ምናልባት ልንል የምንፈልገውን ብዙ ቃላት በአንድ ስንኝ የመግለፅን ጥበብ ታሳይልናለች። እውነት ነው ሃይማኖተኛ ሰው ተስፋ የሚያደርገው የሰማዩ የፅድቅና ኩነኔ ታሪክ ኖረም አልኖረም ከክፋት ደግነት በብዙ እጥፍ ይሻላል።

አንዳንድ ሰዎች አሉ ለመስጠት ተሰጥተው በመልካምነት ኖረው ከጥሩ ሽቶ በበለጠ የሚያውደውን መልካም ስማቸው ሲጠራ ለብዙዎች ፈገግ ማለት ምክንያት መሆን የሚችሉ፤ አንዳንዶች አሉ እነሱ እንደ ሻማ እየቀለጡ ለሌላው እንጀራ ማብሰያ ማገዶ የሚሆኑ፤ አንዳንዶች አሉ ስለሚያደርጉት መልካምነት ምላሽና ሽልማት ሳይሹ በየትኛውም ስፍራ መልካም መሆንን የተሰጡ፤ ምስጋና ለእነዚያ ሰዎች።

ይሄው ቅንነት በማህበራዊ ሚዲያው ብቻ የሚያውቋቸውን ሰዎች እንኳን ባይኔ ካላየሁ ሳይሉ ሰዎችን በመደገፍ የሚዝናኑ፤ ብቸኛ ሱሳቸው ሰውን መርዳት የሆነ ከሰውም ሰው የሆኑ እልፍ አእላፍ ሰዎች አሉ። ምስጋና ሰው በሌለበት ሰው ፈላጊ በበዛበት ዘመን ሰው መሆን ለቻሉ ደጎች።
ሰውን መርዳት በብዙ የዓለም አገራት የሚኖሩ በብዙ ቢሊዮኖች ዘንድ የሚደነቁ ሰዎች መለያ ነው። ትናንታቸውን እንደ መሰላል ሆነው ለዛሬ ድልድይ ሆነው ያሻገሯቸውን ሰዎች ማግኘት ባይችሉ እንኳን እነሱም ሌሎች መኖር ምክንያት ለመሆን ብዙዎች ሌሎችን በማኖር ሕይወት ውስጥ ሲመላለሱ ማስተዋል የተለመደ ነገር ነው።

ኢትዮጵያም የነ አበበች ጎበና የነዘሚ የኑስ የነቢኒንያም በለጠ(መቄዶኒያ) አገር ናት። ብዙ በጎ አሳቢ ከራሳቸው አብልጠው ለሌሎች በመኖር ሕይወታቸውን የገፉ ሰዎች ያሉና የሚኖሩባት የደጎች መኖሪያ ናት። አሁን አሁን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ደግሞ መልካምነት በመንግሥት ደረጃ ታምኖበት የተለያዩ የበጎ አድራጎት ተግባራት መከወን መጀመራቸው ይታወቃል።

የዛሬው የቅን ልቦና ባለቤት እንግዳችን ሲፈን ካሳሁን ትሰኛለች። በዚህች ምድር ላይ አስራ ስድስት አመታትን ኖራለች። ካየችው ትናንት የሚበልጥ ነገን በተስፋ የምትጠባበቅ፤ ትንሽ ናት። ልክ እንደ ፅጌሬዳ አበባ ሁሉም አይኑን የሚጥልባት። ውብ ናት በውብ ፈገግታዋ አኩራፊን የምታስቅ ቅን። እናትና አባቷ የሺ ኢብራሂም እና ካሳሁን እሸቱ ይባላሉ፤ ሁለት እህትና ወንድም ያላት ሲፈን አምስት ልጆች ላሉት ቤተሰቧ አምስተኛና የመጨረሻ ልጅ ነች።

ሲፈን መድኃኒዓለም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ናት። የስምንተኛ መልቀቂያ ፈተናን ባጠናቀቅነው ሳምንት የወሰደችው ሲፈን ፈተና ሂደቱ ሰላማዊና ምቹ እንደነበር ገልፃ፤ ወደፊት ተምራ ሕግ ትምህርትን የመከታተል ሀሳብ እንዳላት አውግታናለች።
ሲፈን የፓርላማ ተሳታፊ እንዲሁም የጉለሌ ክፍለከተማ የሕፃናት ፓርላማ አፈጉባኤ በመሆን የሩቅ ጉዞዋን በቅርብ ስኬት ጀምራዋለች።

ሲፈን ዕድሜ በፈቀደላት መጠን በተለያዩ የበጎ ፍቃድ እንቅስቃሴዎች ላይ ትሳተፋለች። በዕድሜዋ ልክ በጎ ብላ የምታስባቸውን መልካም ነገሮች በመከወን ነው ከትምህርት የተረፈ ጊዜዋን የምታሳልፈው።

በአሁኑም የክረምት በጎፍቃድ ላይ በአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ላይ ተሳታፊ የመሆን እንዲሁም ትልልቅ ድርጅቶችን በማናገር በግሏም ሆነ በጉለሌ ክፍለከተማ ስር በመሆን አስር ወላጅ አልባ ሕፃናትን በመሰብሰብ የመርዳት እቅድ ይዛለች።

ሰዎችን በመርዳት ውስጥ ትልቅ ደስታ አለ ትላለች። ገንዘብ ጊዜና ቦታ ተመቻችቶላቸው ሰዎችን ለማይረዱ ሰዎች ሰዎችን ባለመርዳታችሁ የመርዳትን ደስታ አትጡ ስትል መልዕክቷን አስተላልፋች። ሁሉም ሰው ራሱንና የሚወዳቸውን ሰዎች በተቸገሩ ሰዎች ቦታ አስቀምጦ በማየት ማንኛውም ሰው የተቸገረን በመደገፍ ሰውን መርዳት ውስጥ ያለውን ደስታ ሊያይ እንደሚገባውም ገልፃለች።

ሲፈን ለጎዳና ተዳዳሪ ልጆች እርስ በእርሳቸው እንጂ ከሌላው የማህበረሰብ አካል ፍቅር እንደተነፈጋቸው ታስባለች፤ ለመኖር የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች ቀጥታ ብንሰጣቸው እንዲሁም የጎዳና ልጆች በአግባቡ ከተያዙና ከወደቁበት ጎዳና እንዲነሱ ከተደገፉ ለአገርና ወገናቸው ጠቃሚ ዜጎችን ማፍራት እንደሚቻል ትናገራለች።

በተለያዩ ስፍራዎች በጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ ሰዎች መንግሥት የሚሰጣቸውን የአንድ ቀን ምግባቸውን ለመስጠት የመድኃኒዓለም አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጥያቄ አቅርበው እናንተ ከተስማማችሁ ምንም ችግር የለውም ብሎ ጥያቄያቸውን በመቀበል ተማሪው ተስማምቶ ወስኖ እንዲመጣ ዕድል እንደተሰጣቸውም ነግራናለች።

አዲስ ዘመን ሀምሌ 4 ቀን 2014 ዓም

“ለሀገር በመቆም ኢትዮጵያን ካስቀደምን ማሸነፍ እንችላለን” -አምባሳደር መስፍን ቸርነት የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ዳግማዊት ግርማ አዲስ አበባ፡- እንደ አትሌቶቻችን ሁሉ ለሀገ...
10/08/2022

“ለሀገር በመቆም ኢትዮጵያን ካስቀደምን ማሸነፍ እንችላለን”
-አምባሳደር መስፍን ቸርነት
የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ

ዳግማዊት ግርማ

አዲስ አበባ፡- እንደ አትሌቶቻችን ሁሉ ለሀገር በመቆም ኢትዮጵያን ካስቀደምን ማሸነፍ እንችላለን ሲሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታው አምባሳደር መስፍን ቸርነት ገለጹ፡፡

አምባሳደሩ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በ19ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ባስመዘገቡት ድል የተሰማቸውን ደስታ በመግለፅ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብም የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

አምባሳደር መስፍን ቸርነት ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ መላው የሀገራችን ህዝብ ከጥቃቅን ጉዳይ ወጥቶ ቅድሚያ ለሀገር በመስጠት ለሀገሩ እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት አለበት፡፡

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከግለኝነት አስተሳሰብ ወጥተው ለሀገር ሰንደቅ ቅድሚያ በመስጠት ያመጡት አንፀባራቂ ድል በሁሉም ዘርፍ ለሚገኝ ዜጋ አስተማሪ እንደሆነም አምባሳደር መስፍን ጠቁመዋል፡፡

እንደ ሚኒስትር ደኤታው ንግግር፤ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሀገርና ህዝብን፣ የሰንደቅ ፍቅርን በማስቀደም የሀገራቸውን ሰንደቅ በዓለም አደባባዮች ላይ ከፍ በማድረግ ለሀገራቸው የከፈሉት ውድ ዋጋም የሚያስመሰግናቸው ሲሆን መላው ኢትዮጵያዊም ለአትሌቶቹ የሚገባቸውን ክብር ሊሰጥ ይገባዋል፡፡

አትሌቶች በተባበረ ክንድ እንዲሁም በጠነከረ ጉልበት ያስገኙትን ድል በሁሉም የስራ መስክ በመድገም እኔ ለእኔ ብቻ ማለትን በመተው እኛ ለእኛ ማለት እንደሚያሻ ያመላከቱት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ሁሉም በየተሰማራበት የስራ ዘርፍ ሊጀግን እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡

ከእኔነት ወጥቶ ለጋራ ህልውና ለሀገር በመቆም ኢትዮጵያን ካስቀደምን ማሸነፍ እንችላለን ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ በዘርፉ ወጣቶችን ማፍራት ላይ ስራዎች መከናወናቸውን በማመላከት በቀጣይም ጠንክሮ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

ስፖርት በየትኛውም ሀገር ላይ ሰላምን፣ ፍቅርን፣ የሀገር እድገትና የገፅታ ግንባታ ስራን እንደሚከውን የጠቆሙት አምባሳደር መስፍን፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰሩትን ፈርጀ ብዙ መልካም ተግባራት ማስተዋወቅ ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚጫወትም ነው የገለፁት፡፡

መንግስት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ያመላከቱት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ከሰባ በመቶ በላይ ወጣት ባላት ሀገር ላይ ለስፖርት ትኩረት መሰጠቱ ዘርፉን ለብዙዎች የሚተርፍ እንደሚያደርገው በመግለፅ፤ በቀጣይ ዘርፉን በማልማት ስፖርትን ለልማት ማዋል ላይ ለመስራት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውንም ነው ያመላከቱት፡፡

በኮሎምቢያ ካሊ ከሀምሌ 25 እስከ 30 በተደረገው 19ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 6 ወርቅ߹ 5 ብር እና አንድ የነሃስ በአጠቃላይ 12 ሜዳልያዎችን በማስመዝገብ ከአፍሪካ ቀዳሚ ከአለም ደግሞ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ማጠናቀቋ የሚታወቅ ነው፡፡

100 ሞልተናት እንደር
08/08/2022

100 ሞልተናት እንደር

ባንዴ አንድ ርምጃ የምትራመድ

08/08/2022

Address

Jijiga

Telephone

+251924588738

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dagimawit Girma/ዳግማዊት ግርማ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Dagimawit Girma/ዳግማዊት ግርማ:

Share