Gashaw Shiferaw

Gashaw Shiferaw Limitless

😂😂
12/01/2025

😂😂

Strategist 👏👏👏
12/01/2025

Strategist 👏👏👏

🔥🔥🔥👏👏👏
12/01/2025

🔥🔥🔥👏👏👏

Done
12/01/2025

Done

12/01/2025
12/01/2025

Woganimma❤

ከእንግሊዝ ከሚገኙ ዝነኛ ክለቦች አንድም ክለብ በእርስ በእርስ ግንኙነት ከማንችስተር ዩናይትድ ባደረገው አጠቃላይ ጨዋታ ያ ቡድን ማንችስተር ዩናይትድን በቁጥር የበለጠ ጨዋታ ማሸነፍ አልቻለም...
12/01/2025

ከእንግሊዝ ከሚገኙ ዝነኛ ክለቦች አንድም ክለብ በእርስ በእርስ ግንኙነት ከማንችስተር ዩናይትድ ባደረገው አጠቃላይ ጨዋታ ያ ቡድን ማንችስተር ዩናይትድን በቁጥር የበለጠ ጨዋታ ማሸነፍ አልቻለም ።

ማንችስተር ዩናይትድ ከ ሊቨርፑል
ማንችስተር ዩናይትድ ከ ቼልሲ
ማንችስተር ዩናይትድ ከ አርሰናል
ማንችስተር ዩናይትድ ከ ማን ሲቲ
ማንችስተር ዩናይትድ ከ ቶትንሃም
ማንችስተር ዩናይትድ ከ ዌስተሃም
ማንችስተር ዩናይትድ ኒውካስትል

አንዳቸውም ከተመሰረቱ ጀምሮ ከማንችስተር ዩናይትድ ባደረጉት አጠቃላይ ግጥሚያ ማንችስተር ዩናይትድ ካሸነፋቸው በላይ ሊያሸንፉት አልቻሉም !!

ይሰመርበት አንዳቸውም.....!
Source: 4:3:3.

የሁለት ብር የደመወዝ ጭማሪ 😂
11/01/2025

የሁለት ብር የደመወዝ ጭማሪ 😂

🍰🍦     🍥🍡 🍧🍬🍬🍨🍬🍬🍇🍨🍬   ጣፋጭ   🍬🍦🍰🍬🍬🍬🍬🍬🍧     🍥🍬🍬🍬🍰          🍡🍬🍧                    🍇
11/01/2025

🍰🍦 🍥🍡
🍧🍬🍬🍨🍬🍬🍇
🍨🍬 ጣፋጭ 🍬🍦
🍰🍬🍬🍬🍬🍬🍧
🍥🍬🍬🍬🍰
🍡🍬🍧
🍇

🕺
10/01/2025

🕺

09/01/2025
04/01/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Misganu Lemma, Sara Alaro, Abduu Alii, TradeEthiopia Sales Officer

የሀድያ ብሔር ባህላዊ የከብቶች ቆጠራ ሥርዓትባህላዊ የከብቶች ቆጠራ (ወገና) ማለት አንድ ከብት አርቢ ከብቶቹ ከመቶ በላይ ሲሆኑለት ድግስ በመደገስ ሰዎች አውቀውለት ከሀብቱ ጋር በተያያዘ የ...
01/01/2025

የሀድያ ብሔር ባህላዊ የከብቶች ቆጠራ ሥርዓት

ባህላዊ የከብቶች ቆጠራ (ወገና) ማለት አንድ ከብት አርቢ ከብቶቹ ከመቶ በላይ ሲሆኑለት ድግስ በመደገስ ሰዎች አውቀውለት ከሀብቱ ጋር በተያያዘ የክብር ማዕረግ የሆኑትን አበጋዝ ወይም ጋራድ የሚሉትን ስያሜ የሚያገኝበት ሥርዓት ነው፡፡

ይህ ሥርዓት ወገና ይባላል።

ወገና የሚለው ቃል ትርጉም ውኃ መርጨት ማለት ሲሆን፤ ይህም ሥርዓቱ ሲፈጸም ውኃ፣ ማር እና ወተት ተቀላቅለው በከብቶቹ ላይ ስለሚረጭ ነው፡፡

የወገና ሥርዓት መቼ እንደተጀመረ ቁርጥ ያለ መልስ ማግኘት አይቻልም፡፡

የቀንድ ከብቶችን በብዛት የማርባቱ ልማድ የቆየ ነው። ከብቶችን በብዛት ማርባት ደግሞ በወቅቱ የሀብታምነት መለኪያና መገለጫ ሲሆን ታዋቂነትንም ያስገኝ ነበር። ስለዚህም ብዙ ከብቶችን ያረባ ባለ ብዙ ከብት፣ ሀብታም ተብሎ ሲታወቅ፤ በሌሎቹ አርቢዎች ዘንድም ፉክክር እንዲኖር ያደርጋል፡፡ ፉክክሩ ባለብዙ ከብት፣ ሀብታም ተብሎ ለመታወቅ ከፍተኛ ምኞትንና ጉጉትን ይፈጥርባቸዋል። እንዲህ እያለ እስካሁን ድረስ ይህ የቆጠራ ሥርዓት ቀጥሏል፡፡

በከብቶቹ ብዛት የታወቀውና ሀብታም የሆነው አርቢ ከሌሎቹ አርቢዎች ተለይቶ ለግጦሽ የሚሆኑ ቦታዎችን በመከለል ግዛቱ ያደርጋል፡፡

በዚህም የተነሳ በከብት አርቢዎች ዘንድ የእርስ በርስ ፉክክሩ ቀጠለ።

ከብቶችን በማርባት ሀብታም፣ ባለብዙ ከብት የሚባለው የሚጠቡ ጥጆችና ያልደረሱትን ሳይጨምር የትልልቆቹን ከብቶች ብቻ በመቁጠር ሲሆን የከብት ሀብታም ለመባልም የከብቶች ቁጥር 100 ወይም ጥቤ መሆን አለበት።

በሀድያ ከብቶችን ሲያረቡ 10 በማለት የሚጀመር ሲሆን 10 ቁጥር ሙሉ ተደርጎ ነው የሚታሰበው፤ 10 አሥሮች ሲደርሱ መቶ ይሆናሉ፡፡ 100 አሥሮችም አንድ ሺህ ይሆናሉ፡፡

እነዚህ ሁሉ ቁጥሮች ሙሉ ተደርገው ስለሚታሰቡና ስለሚታመንባቸው የከብቶቹ ቆጠራ በዚህ መልኩ ነው የሚካሄደው።

በድሮ ጊዜ ከብቶቹን በማሳየት እና እውቅና ለማግኘት የሚፈልግ ብዙ ከብት ያለው አርቢ ጥሪ አድርጎላቸው ለሚመጡት እንግዶች ቡሎ የተሰኘ ከገብስ ዱቄትና ከቅቤ የሚዘጋጅ ለተከበረ እንግዳ፣ ለአባወራ ፣ ለሽማግሌዎች፣ ለሙሽሮች እና ለጠንካራ ጀግኖች የሚቀርብ ባህላዊ ምግብ ማቅረብም ግዴታው ነው።

(ባህላዊ የከብቶች ቆጠራ (ወገና) ሥርዓተ ክዋኔ በሀድያ ብሔር) ጥናት

🇪🇹 ከየት ወዴት?
31/12/2024

🇪🇹 ከየት ወዴት?

ደቡብ ኮሪያ በአውሮፕላን አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ሰዎች የ7 ቀናት ብሔራዊ ሀዘን አወጀችከታይላንድ ባንኮክ 181 ሰዎችን አሳፍሮ ደቡብ ኮሪያ ሙአን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ መስ...
29/12/2024

ደቡብ ኮሪያ በአውሮፕላን አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ሰዎች የ7 ቀናት ብሔራዊ ሀዘን አወጀች

ከታይላንድ ባንኮክ 181 ሰዎችን አሳፍሮ ደቡብ ኮሪያ ሙአን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ መስመር ስቶ አደጋ በደረሰበት አውሮፕላን 179 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተነግሯል።

ልክ እንደ በዛብህ አርነት ሚያወጣ ፣እንደ ተልባ ቆሎ ሚሳኤል ሚያንጣጣ ፤ጀት ይዞ የሚበር ከህዋ ላይ ወጥቶ ፣ታግሎ ሚያታግለን ከጠላት ተዋግቶ፤ውረድ እንውረድ 'ሚል የሚገጥም ካለ፣ ከወደ ሀዲ...
28/12/2024

ልክ እንደ በዛብህ አርነት ሚያወጣ ፣
እንደ ተልባ ቆሎ ሚሳኤል ሚያንጣጣ ፤
ጀት ይዞ የሚበር ከህዋ ላይ ወጥቶ ፣
ታግሎ ሚያታግለን ከጠላት ተዋግቶ፤

ውረድ እንውረድ 'ሚል የሚገጥም ካለ፣
ከወደ ሀዲያ ብዙ ጀግና አለ ❗️

የጦር ጀት አብራሪ - ተመስገን አብርሃም
( ተተኪው የሰደድ እሳት )
Heni landa
Highlight

ዶናልድ ትራፕም የአሜሪካ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቲክ ቶክን በተመለከተ የሚያሳልፈውን ውሳኔ እንዲያዘገይ ጠየቁ።ተመራጩ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለፖለቲካዊ መፍትሄ እሰራላሁ ብለዋል፡፡የትራምፕ የህግ አ...
28/12/2024

ዶናልድ ትራፕም የአሜሪካ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቲክ ቶክን በተመለከተ የሚያሳልፈውን ውሳኔ እንዲያዘገይ ጠየቁ።

ተመራጩ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለፖለቲካዊ መፍትሄ እሰራላሁ ብለዋል፡፡

የትራምፕ የህግ አማካሪ እና ጠበቃ ህጋዊ ማብራሪያዎችን ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡ ሲሆን "ሪፐብሊካኑ ቲክ ቶክ በአሜሪካ ምድር እንዲከለከል አይፈልጉም" ብለዋል፡፡

ወደ ነጩ ቤተ መንግስት ጥር 20 ሲመለሱ ከቫይናው ባይትዳንስ ኩባንያ እና መሪዎች ጋር በጉዳዩ ላይ መክረው መፍትሄ ያመጡበታል ባይ ናቸው፡፡

ፍርድ ቤቱ በፈረንጆቹ 2025 ጥር 10 ክርክሩን የሚያዳምጥ ሲሆን ትራምፕ ወደ ዋይት ከመግባታቸው ከአንድ ቀን ቀደም ብሎ ከአሜሪካ ምድር ቲክ ቶክ ይከለከላል አሊያም ድርሻውን ለአሜሪካ ኩባንያዎች መሸጥ ይኖርበታል፡፡

በአሜሪካ ባለስልጣናት እና በኮንግረስ ዓባላት ባይትዳንስ ከቻይና መንግስት ጋር ግንኙነት አለው የሚል ክስ ይቀርብበታል፡፡

ቲክ ቶክ ግን ውንጀላውን የተሳሳተ በሚል አይቀበለውም።

ማህበራዊ ሚዲያውን ከ170 ሚሊዮን በላይ አሜሪካውያን እንደሚገለገሉበትም ይታወቃል።

Address

Hossana

Opening Hours

Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 11:00
Sunday 09:00 - 11:00

Telephone

+251941011096

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gashaw Shiferaw posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Gashaw Shiferaw:

Videos

Share