![የ45 ትምህርት ቤቶች መምህራን ሥራ አቆሙ !በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሐዲያ ዞን ምሥራቅ ባድዋቾ ወረዳ፣ ለተከታታይ ሦስት ወራት ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው የገለጹ ከ1,600 በላይ የ45 ትም...](https://img3.medioq.com/866/500/801341708665006.jpg)
17/10/2023
የ45 ትምህርት ቤቶች መምህራን ሥራ አቆሙ !
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሐዲያ ዞን ምሥራቅ ባድዋቾ ወረዳ፣ ለተከታታይ ሦስት ወራት ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው የገለጹ ከ1,600 በላይ የ45 ትምህርት ቤቶች መምህራን፣ ሥራ ማቆማቸውን አስታወቁ።
አማራጭ ገቢ እንደሌላቸው የገለጹት መምህራኑ፣ ቤተሰቦቻቸውን ማስተዳደር እንደተሳናቸውና ለረኀብ እንደተጋለጡ አመልክተዋል። በወረዳውም፣ የ2016 ዓ.ም. የትምህርት መርሐ ግብር እስከ አሁን እንዳልተጀመረ፣ መምህራኑ አክለው ተናግረዋል።
የሐዲያ ዞን ትምህርት መምሪያ፣ መምህራኑ ለተከታታይ ወራት ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው አምነው፣ ችግሩ በበጀት እጥረት እንደተፈጠረና ለመፍታትም ጥረት እየተደረገ እንደኾነ አስታውቀዋል።
Via : VOA