Al meded Islamic media-አል መደድ ኢስላሚክ ሚድያ

Al meded Islamic media-አል መደድ ኢስላሚክ ሚድያ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Al meded Islamic media-አል መደድ ኢስላሚክ ሚድያ, Media/News Company, ቡሌ ሆራ, Hagere Mariam.

ዛሬ  የዐረፋ ቀን ነው ረሱልﷺ  ይህን ዚክር እንድናበዛ አዘውናልበዛሬው ቀን  ይበልጥ ተወዳጅ "❞لا إلهَ إلاَّ اللَّه وحْدهُ لاَ شَرِيكَ لهُ، لَهُ المُلْكُ...
15/06/2024

ዛሬ የዐረፋ ቀን ነው
ረሱልﷺ ይህን ዚክር እንድናበዛ አዘውናል
በዛሬው ቀን ይበልጥ ተወዳጅ
"❞لا إلهَ إلاَّ اللَّه وحْدهُ لاَ شَرِيكَ لهُ، لَهُ المُلْكُ، ولَهُ الحمْدُ، وَهُو عَلَى كُلِّ شَيءٍ قَدِير“❝

 #ነገ የዓረፋ ፆም ነውነገን ማለትም እለት ቅዳሜን/ የዓረፋ ቀንን መፆም የ 2 አመት ወንጀል እንደሚያስምር በሀዲስ መጥቶልና።ሳንዘናጋ ይህን የተከበረ ቀን ፁመን ለማሳለፍ ከአሁኑ ሰአት ጀም...
14/06/2024

#ነገ የዓረፋ ፆም ነው

ነገን ማለትም እለት ቅዳሜን/ የዓረፋ ቀንን መፆም የ 2 አመት ወንጀል እንደሚያስምር በሀዲስ መጥቶልና።
ሳንዘናጋ ይህን የተከበረ ቀን ፁመን ለማሳለፍ ከአሁኑ ሰአት ጀምረን ኒያ እንድናደረግ።

ኒያው👌
ነወይቱ ሶውመ ገغዲን ዐን ሶውሚ የውሚ ዐረፋህ ተጦውዐን ሊላሂ ተዓላ
نويت صوم غد عن صوم يوم عرفة تطوعا لله تعالى

ሼር በማድረግ ተደራሽነት ይኖረው

13/06/2024

ኸሚስ

ሰሉ ዓለ ነቢ💛

ስለ ኡድሂያ ማብራርያ ( በመዝሀብ ሻፊዒይ)ሰይዳችን ﷺ ስለ እርድ እንዲህ ብለውናል :- « የአደም ልጅ የአረፋ ቀን ከማረድ የበለጠ አላህ የሚወደውን ስራ አልሰራም ፤ የታረደችዋም የቂያማ ቀ...
12/06/2024

ስለ ኡድሂያ ማብራርያ ( በመዝሀብ ሻፊዒይ)

ሰይዳችን ﷺ ስለ እርድ እንዲህ ብለውናል :-

« የአደም ልጅ የአረፋ ቀን ከማረድ የበለጠ አላህ የሚወደውን ስራ አልሰራም ፤ የታረደችዋም የቂያማ ቀን ከቀንዶቿ ከጥፍሮቿም ጭምር ትቀርባለች፤ ደሙ መሬት ላይ ከመድረሱ በፊት አላህ ጋር አጅሩ ይደርሳል፤ ተደስታቹ ስሯት »

📗 ኢብኑ ማጀ'ህ (3124)
፡==================

• ኡድሂያ የተባለበት ምክንያት ወቅት ዱሀ (ረፋዱ) ሰዓት ላይ የሚታረድ በመሆኑ ነው ይላሉ ዑለማዎች።

• ኡድሂያ ማረድ በዒዱ ቀናቶች ከሚያስፈልገው ነገር ተጨማሪ ማረድ የሚያስችል ሀብት ላለው ሰው የጠበቀ ሱና ነው።

ኢማሙ ቲርሚዚ'ይ በዘገቡት ሀዲስ ሰይዳችን ﷺ :- « እንዳርድ ታዝዣለው ፤ ለእናንተ ደሞ ሱና ነው » ብለዋል

ነዝር ካደረገው ግን ( ስለት ከገባ) ዋጂብ ይሆናል።

• ለኡድሂያ የሚቀርቡት

1- ግመል (5 አመት የሞላው)
2- በሬ/ላም/ፍየል (2 አመት የሞላው)
3- በግ (1 አመት የሞላው)

• የሚታረደው ከብት ስጋውን ከሚቀንስ ወይም ከሚያነውር ጉድለት መጥራት አለበት ( በጣም የከሳ ፤ ያበደ ፤ እውር ውይም አንድ አይኑ የጠፋ፤ በሽታ ያለበት ፤ ጆሮው ወይ ምላሱ የተቆረጠ ወይ ሙሉ ጥርሱ የሌለና የመሳሰሉት ነውሮች የሌለበት መሆን አለበት )

• አንድ ቤተሰብ ውስጥ አንዱ ካረደ ይበቃል። ሁሉም ከቻሉና አጅር ለማግኘት ሁሉም ቢያርዱ የተወደደ ነው።

• ግመል ወይም ከብት ለሰባት ሰዎች መሻረክ ይቻላል።

• የሚታረድበት ሰዓት የሚጀምረው የዒዱ ጠዋት ፀሀይ ከወጣችና አጠር ያሉ የሁለት ረክዐ ሰላትና ኹጥባ ጊዜ ካለፈ ቡሀላ ነው። ከዛች ሰዓት ጀምሮ እስከ ሶስተኛው አያም ተሽሪቅ (13 ዙል ሂጃ) መግሪብ ድረስ ይቻላል።

• ቡኻሪና ሙስሊም ከሰይዳችን ﷺ በዘገቡት ሀዲስ :- « በዚህ ቀናችን (የአረፋ ቀን) መጀመርያ የምንጀምርበት ስራ ሰላት እንሰግዳለን ፤ ከዛ ተመልሰን እናርዳለን። ይሄን ያደረገ መንገዳችንን በእርግጥ አግኝቷል ፤ ከዛ በፊት ግን ያረደ ለቤተሰቡ እንደማንኛው ግዜ እንደሚያቀርብላቸው ስጋ ነው ከኢባዳ ( ኡድሂያ) አይቆጠርም..»

• ሱና ከሆነው ኡድሂያ ትንሽም ቢሆን ሰደቃ መስጠት ግዴታ ነው። ትንሽም ቢሆን ሰደቃውን ካወጣ ሙሉ አጅሩን ያገኛል።

- የበለጠው ደሞ አንድ ሶስተኛውን በልቶ ሌላውን ሰደቃ ማውጣት ነው።

- ከዚህም የበለጠ ደሞ ከኡድሂያው ጉበት ትንሽ በልቶ ስጋውን በሙሉ ሰደቃ ማውጣት ነው።

- የኡድሂያን ስጋም ሆነ ቆዳ ሰደቃ መስጠት እንጂ ምንም ነገር መሸጥ ክልክል ነው። ለገፋፊውም ቢሆን ክፍያ ተደርጎ አይሰጥም።

• ኡድሂያ ለማድረግ ነዝር ያደረገ ( ስለት የገባ ) ኡድሂያው ዋጂብ ይሆናል። ዋጂብ ኡድሂያን ደሞ ስጋውን በሙሉ ሰደቃ ማውጣት ግዴታ ይሆንበታል።

• የኡድሂያን ሙሉ አጅር ለማግኘት ከማረዱ በፊት ወይም ሲያርድ ኒያ ማድረግ ይኖርበታል ።
- እራሱ የማያርድ ከሆነ ኡድሂያው ሲታረድ መመልከት ይወደድለታል።

አላህ ይወፍቀን ፣ አላህ ይቀበለን
፡==================

16/05/2024

በድርቅ የተመቱ ቀናቶችም ሆኑ
ልቦች ሁሉ
በሰለዋት ዐለ ነቢ ﷺ ይለመልማሉ።

11/05/2024

ሀቅ ሀቅ ነው💛

09/05/2024

ኸሚስ ሙባረክ!!

ያ ጀመዓ ረሱል (ﷺ) ላይ ሰለዋት
እናውርድ እስቲ❤💛

03/05/2024

ጁምአ ሙባረክ💛

🌹«የኔ ስም ሲጠራ ዝም ያለ ሰው ስስታም ነው»
ብለዋል 👉ውዱ ሰው ነብዩ ሙሐመድ💜ﷺ💜
🍀 #ሶሉ አለ ነቢ🍀صَلُّوا عَلَى النَّبِي🍀
።💜اَللّٰهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ وَبَارِكْ عَلَى سَيِّدِنَا مُحَمَّدْﷺ💜

አዝናለሁ  ያ ረሱለላህ ﷺ ሰው ሁሉ በዱኒያ ቢዚ ሆኗል።ሸረሪቷና እርግቧ ነቢን አልረሱም ነበር ።ራሳቸውን ለነቢ ፊዳእ ለማድረግ ከፊት ነበሩ። 🙏አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላ...
02/05/2024

አዝናለሁ ያ ረሱለላህ ﷺ ሰው ሁሉ በዱኒያ ቢዚ ሆኗል።

ሸረሪቷና እርግቧ ነቢን አልረሱም ነበር ።
ራሳቸውን ለነቢ ፊዳእ ለማድረግ ከፊት ነበሩ። 🙏

አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ወሸፊኢና ﷴﷺ ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!

02/05/2024

ኸሚስ💛

⌚𝐎𝐧𝐥𝐢𝐧𝐞 ከሆናችሁ
በረሱል {ﷺ} ላይ ሰለዋት አውርዱ

የሰይዳችን ሙሉ ስም 💚 ﷺ
27/04/2024

የሰይዳችን ሙሉ ስም 💚 ﷺ

26/04/2024

በውዱ ነብያችንﷺ ላይ በቀን አንድ ሺ ሰለዋት የሚያወርድ ሰው:-
➦ በጀነት መቀመጫውን(የጀነት ቤተመንግስቱን) ሳያይ አይሞትም::
➦ ነቅቶም(ሳይተኛ) እንዲሁም ተኝቶ በመናሙ አላህﷻ በጀነት ሳያበሽረው አይሞትም::
➦ በቀን ወይንም በማታ ሺ ግዜ ሰለዋት የሚያወርድ ሰው ስጋውንም ሆነ አጥንቱን ከአዛብ ሀራም ያደርግለታል::
➦ ከዱንያም ከአኸራም አዛብ(ቅጣት) አላህﷻ ነጃ ያወጣዋል::
➦ ከመሞቱ በፊት በነብዩﷺ ላይ ሺ ግዜ ሰለዋት ያወረደ ሰው አላህﷻ በጀነት ከዱር እና ያቁት(የከበሩ ዲንጋዬች) የተሰሩ ሺ ቤተ መንግስቶችን ይሰጠዋል::

ኢንሻአላህ እንጠቀምበት 🙏

25/04/2024

63 ዓመት 🥰
በዱንያ ኖሩ አንድም ቀን ክፉ ሳይናገሩ

ለዚህ ነቢይ የደቂቃ ሰለዋት ያንሳቸዋልን😥
ሰሉ ዐለ ነቢ💛

25/04/2024

ሲወዱም በሙሀመድ ሲናፍቁም በሙሀመድ
ሙሀመድ ነው ሙሀመድ ቢድኑም ቢታመሙ

ነቢ ሰለዋትህን እየጠበቁ ነው 💚

25/04/2024

ያረቢ🤲 ሀገራችንን ሰላም አርግልን
ምቀኛ ሸረኛውም ከኛ አርቅልን
ማጣትን ከኛ አርቅልን አሏሁመ አሚይን👏

በዱዓችሁ አትርሱኝ🙏

25/04/2024

እኔ በረውዷዬ ሐይ ነኝ የምታወርዱትን ሰለዋት እሰማለሁ ረሱል( ﷺ)

በክቡር ዶክተር ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ መኖርያ ቤት፤በአንዋር መስጂድ ወጣት ጀመዓ አዘጋጅነት.... በረመዷን 28 ልዩ የኢፍጣር ፕሮግራም እጅግ በአማረ መልኩ ተከውኗል።በዚህ የኢፍ...
07/04/2024

በክቡር ዶክተር ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ መኖርያ ቤት፤በአንዋር መስጂድ ወጣት ጀመዓ አዘጋጅነት.... በረመዷን 28 ልዩ የኢፍጣር ፕሮግራም እጅግ በአማረ መልኩ ተከውኗል።
በዚህ የኢፍጣር ፕሮግራም ላይ አምባሳደር ኡስታዝ ሐሰን ታጁን ጨምሮ የአንዋር መስጂድ ወጣት ጀመዓ አባላት የተገኙ ሲሆን፤የኢፍጣር ዝግጅቱ በአማረ መልኩ ከተከወነ ቡኃላ፤ከክቡር ዶክተር ተቀዳሚ ሙፍቲህ፤ጀመዓው ዱአ ተቀብሎ በአሚንታ የደመቀ ሆኖ ተጠናቋል።

የአንዋር መስጂድ ወጣት ጀመዓ ለኸይራት ታጥቃችሁ፣በረካን ሽታችሁ ይህን ዝግጅት አከናውናችኋል እና የዚያራን በረካ የምታፍሱ፣በዚያራችሁ ሁሉን የምታዳርሱ፤በዚሁ በረካ፣ዱንያ አኺራችሁ አምሮ ስትኖሩ የሐያትን በረካ፣የአፍያን በረካ፣የገንዘብ በረካ በጀመዐው አባላት ላይ የሚሰፍር ይሁን።

የታላቁ አንዋር መስጂድ ወጣት ጀመዓ
Ambassador/Ustaz Hasen Taju

05/04/2024

27ለይል🤲
ያጣ ሚያገኝበት የተከፋ ሚደሰትበት
ለይል ያርግልን 🤲

04/04/2024

በኛ በተወዳጁ ነብይﷺ ላይ እልፍ አእላፍ ሶለዋት እናውርድ
ኸሚስ ሙባረክ😍

23/03/2024

ያለንበት ወቅት😎

መውሊድ ቢድዓ ሆኖ የጎዳና ኢፍጣር ሱና የሆነበት ወጭባራ ምእመን ጋር ነው ውለን የምንገባው:: በወንድ ልጅ ላይ አደብ ያለው ጀለበያ ቢድዓ አድርጎ ቁንጣ የሚያክል ጀለብያ ሱና ያደረገ ፌንጣ ጋር ነው ጎን ለጎን የምንስግደው:: ይህ ብቻ ሳይሆን ከሰገዱ በሗላ ቁጭ ብሎ ዱዓ ማድረግ ቢድዓ አድርጎ እየበረጋገዱ እና እየተቆናጠሩ በትከሻ በኩል መዝለል ሱና ነው ይላሉ ወጣት ልጅ አላህን እና ነቢ ፈልጎ ሀድራ ስቀመጥ ጫት ለመቃም ነው ይላሉ :: ባጠቃላይ መረጋጋት ኩነኔ ሲሆን መንቀልቀል በስምንቱም በር ጀና ያስገባል:: ይላሉ::

21/03/2024

ኸሚስ አመሻሹን

አሁን ሰአት⌚✍︎ 𝐎𝐧𝐥𝐢𝐧𝐞 ከሆናቹ
በረሱል{ﷺ} ላይ ሰለዋት አዉርዱ🤍🫶

20/03/2024

Al meded Islamic media-አል መደድ ኢስላሚክ ሚድያ

18/03/2024

ይሰመርበት!!

በብዙ የሃገራችን ክፍሎች ተራዊሕ በአጫጭር ሱራዎች የሚሰገደው ቁርአንን ማኽተም ስላልተፈለገ አይደለም።አዎ ታላቁ ወር ረመዳን የቁርአን ወር ነው።የቁርአን ወር ነው ተብሎ ግን የተራዊሕ ሶላት ላይ ሁሉም ሱራ ካልተቀራ አይባልም።እንደውም ታላላቅ የፊቅህ ዑለሞች የሚሉት ጀማዓው እንዲረዝምለት ካልተስማማ በስተቀረ ኢማሙ ማስረዝም የለበትም ነው። እንደ ሃገራችን ተጨባጭ ከሆነ ደግሞ በረመዳን ወር ተራዊሕ ላይ ባይሆንም ቁርአን ከአንድም ሁለት ሶስቴ ይኸተማል።ሶላት ላይ ግን መሻይኾቻችን ጥንቃቄ ያደርጋሉ!

ኢማም ወይም መሪ ማለት የሚመራውን ሰው ሁኔታ የሚያውቅ ነው።
ጀመዓው ምን አይነት ነው የሚለውን ግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል።የሚከተልህ ጀማዓ የሞላለት ነው ወይስ በጾም አንጀት ቤቱን ለመሙላት ቀኑን ሲባክን የሚውል? በጀማዓው መሃል ብዙ ሲቆም የሚያመው የሚከብደው የማይሆንለት አለ ወይስ የለም? ይሄን ታላቅ ወር ሁሉም ሙስሊም እንዲጠቀምበት ምን አይነት መንገዶችን ብከተል ነው የተሻለ የሚሆነው? ትክክለኛ ኢማም ከሆንክ ይሄን ሁሉ ታሳቢ ታደርጋለህ!

ማሰብና ማስተዋል ሲገባህ ጭራሽ
"ሲጀመር የማይችል ከሆነ ማን ና አለው ቤቱ አርፎ አይቀመጥም?"
ወደሚል አቅጣጫ የምታመራ ከሆንክ በጭራሽ አንተ ኢማምነት አይገባህም።

መካና መዲና ተራዊሕ ላይ ቁርአን ይኸተማል።ስለዚህ እዚህም በውድም በግድም መኸተም አለበት የሚሉት አካሄድ ዲንን ካለመረዳት የሚመነጭ ነው።ወንድሜ ኢማም ሆነህ የምትመራውኮ የመካና የመዲና ሰዎችን አይደለም።

ስለሆነም ወንድሜ በተቻለህ አቅምና ቀስ በቀስ ሙስሊሙ ዒባዳ እንዲወድ አድርገው እንጂ ሰልችቶት ከዒባዳ እንዲቀር አታድርገው።
አይደለም ሱና ሶላት ላይ ዋጂብ ላይ እንኳ ሒክማ ግድ ይላል!

18/03/2024

ሐጃጅ ቢን ዩሱፍ በኡመዊያን ነገስታት ዘመን የነበረ በብዙ በደልና ደም ማፍሰስ የታወቀ ባለስልጣን መሆኑ ታሪክ ላይ ተቀምጧል ።

አንድ ግዜ ወንዝ ውስጥ እየታጠበ ባለበት ይባላል ሊሰምጥ ደርሶ አንድ መንገደኛ የነበረ ባላገር ሰው አዳነው ..

ሐጃጅም ወደ ወንዝ ዳርቻው በሱ አጋዥነት ከወጣ ቡኃላ : " የፈለግከውን ነገር ጠይቀኝ ፍላጎትህን አሟላልሀለው " ይለዋል

ባላገሩም : " አንተ ማን ሆነክ ነው የፈለግኩትን ሁሉ የምታሟላልኝ ? " አለው

" እኔ ሐጃጅ ቢን ዩሱፍ ነኝ " አለው ..

ባላገሩም ደነገጠና : " በአላህ ይዤሀለው ብቸኛ ፍላጎቴ.. እንዳዳንኩህ ለማንም እንዳትናገርብኝ ነው " ብሎ አለው ..
***

አንዳንዴ ብቸኛ የምትፈራውና የምታፍርበት ነገር አንዳንድ ሰዎችን ማዳን ሊሆን ይችላል ! አሏሁል ሙስተዓን !

ነገር ግን መልካምን ስራ የማይረሳ የሆነ ጌታ ስላለን አልሐምዱሊላህ ☺️

የመድህ ጥግ?ፉአድ ሸምሱ ስለ መንዙማ ስታስብ ልብህ ላይ ውል ከሚሉ ስሞች መካከል አንዱ ነው። አብዛኛውን የመድህ ስራዎቹን በ "ናፍቆት" ዙሪያ አርጎ በመስራት ታቀዋለህ። አሁንም እንደዛው በ...
17/03/2024

የመድህ ጥግ?

ፉአድ ሸምሱ ስለ መንዙማ ስታስብ ልብህ ላይ ውል ከሚሉ ስሞች መካከል አንዱ ነው። አብዛኛውን የመድህ ስራዎቹን በ "ናፍቆት" ዙሪያ አርጎ በመስራት ታቀዋለህ። አሁንም እንደዛው በ ናፍቆት መድህ "ሠላሜ" ሊልህ መቷል።

" ሲወዱም በሙሀመድ፣ ሲናፍቁም በሙሀመድ
ሙሀመድ ነው ሙሀመድ፣ ቢድኑም ቢታመሙ "

ስለስራው ተዓምራዊነት ልንገርህ... ግጥሙን ታላቁና አንጋፋው ኡስታዝ ሰዒድ ከትበዉታል። ዜማው በተወዳጃችን ማዲህ ሙአዝ ሀቢብ የተቀመረ ሲሆን ተጨማሪ ዜማ ከኸይራቶች አለው። ቅንብሩም በኑር ዑመር እና በሀመር ቅንጅት የተሰናዳ ነው።

" እሩህ የሌለዉን ግንዱን ሲያስለቅሰዉ
እኛ ሩሁን ይዘን ወዴት እንድረሰዉ "

ሌላኛው የዚህ ስራ ጠንካራ ጎን ግጥሙ ነው። ግጥሙ ከዚህ በፊት ተሰምቶህ ማያቅ አይነት የሙሀባ ስሜት ያሰማሀል። ቀስ በቀስ ውስጥህ የተዳፈነው ሙሀባ ሲያጉረመርም ይታወቅሀል። ከምንም በላይ የምቶዳት እናትህን ፍቅር ስታስብ ለአሽረፈል ኸልቅ ካለህ ፍቅር አንፃር ምንም እንዳልሆነ ታስባለህ። ብሎም "ፋሩቅ ማነው? ሲዲቅ ማነው? የ ሙሀመድ አንደኛ አፍቃሪ እኔ ነኝ!" ያስብልሃል።

" ለኔም ኑልኝ እንጂ፣ ማየቱ ይድረሰኝ
እንደዛች ጨረቃ፣ ናፍቆትሁ ሳይገምሰኝ "

ሙስሊም ነህ? ይህን ስራ ስማው!
ሙሀባ በርትቶብሀል? ይህን ስራ ስማው!
ናፍቆት ምን እንደሆነ አታውቅም? ይህን ስራ ስማው!
ስለ ረሱል መስማት ይስደሳሀል? ይህን ስራ ስማው!
መንዙማ ትወዳለህ? ይህን ስራ ስማው!
መንዙማ አትወድም? ይህን ስራ ስማው!
የግጥም ጥልቀት ላሳይህ? ይህን ስራ ስማው!
የድምፅ ስርቅርቅና ያስፈልግሃል? ይህን ስራ ስማው!

ኸሚስ ምሽት በ አልፋሩቅ መልቲሚድያ ፕሮዳክሽን ይለቀቃል ስማውና ትክክለኛ ሀሳብህን ኮመንት አርግልኝ። የ መድህ ጥግ መሆኑ አለመሆኑንም አንተው ወስን።

17/03/2024

"በየተራዊሑ መሃል ዚክር አታድርግ፣አሏህን አትዝከር" ብለው የማይገናኝ ሐዲስ እየጠቀሱ ሲያምታቱህ ግራ የሚገባህ ሰው ከሆንክ
ወንድሜ ልብህን በደንብ ፈትሸው።የትኛውም የቁርአን አንቀጽም ሆነ ትክክለኛ ሐዲስ "አሏህን በብዙ አስታውሰው" ሲልህ እንጂ
"አሏህን አትዝከረው" ሲል አታገኘውም።ከሙስሊሞች ጋር ሆነህ በጀማዓ አሏህን አትዝከር ብሎ የሚከለክል አንድም ማስረጃ ማቅረብ አይቻልም።

እኔምልህ ወንድሜ?!
ይሄ በየመስጅዱ እየዞረ ሙስሊሙን የሚረብሸው ሰውዬ ግን
በጀማዓ ዚክር ማድረግን ከጠላ ለምን በጀመዓ ሶላት ይሰግዳል?
ለመሆኑ ሙስሊሞች በጀማዓ ሆነው ሶላት ሲሰግዱ ምን እያደረጉ ይመስልሃል? አሏህን እየዘከሩ ነው ወይስ ሌላ እኛ የማናውቀው ነገር አለ?

ታዲያ የትኛው ሸሪዓ ነው "በጀማዓ ሶላት ስገዱ ብሎ ሲያበቃ በጀማዓ ግን አሏህን አትዝከሩ" የሚለው?? ሶላትን በጀማዓ መስገድ ዒባዳና የተወደደ ሆኖ፣በጀማዓ ሆኖ ድምጽን ከፍ አድርጎ አሏህን ማስታወስ ግን ከዒባዳ ውጭ እና የተጠላ የሆነው በየትኛው ህግና ቀኖና ነው??

አልረታ ብለህ፣የናንተን አባባል አልቀበልም ብለሃቸው ከጀማዓ ጋር ሆነህ ዚክር እያደረግክ ሳለ ድንገት መከረኛውን የቢድዓ ርእስ አንስተው ሊገርቡህ ከፈለጉ ብዙ ሳትደናገጥ "እንደዛማ ከሆነ ከነጭራሹም ቢሆን በአንድ ኢማም ሆኖ ተራዊሕ መስገድ ትልቁ ቢድዓ ነው።"በላቸው። እስኪ አንገታቸው ላይ ገመድ የሚከቱ እንደሁ እናያለን።ቢድዓ የተባለን ሁሉ እንቃወማለን ያሉህ ሰዎች ናቸው በራሳቸው ጊዜ ቢድዓን ሲያጧጡፉ የምታገኛቸው።

አሁንም አያፍሩም እንደለመዱት "ማነው ቢድዓ ያለው ?" ብለው ጓ ሊሉብህ ይሞክራሉ።፣ረጋ ብለህ [ቢኩሊ ሁዱእ] ቢድዓ ብሎ የጠራውማ ያ ታላቅ ሰው ነው" በላቸው።እግሩን ባሳረፈበት አቅጣጫ ሁሉ ሸይጣን መንገድ ቀይሶ የሚሸሸው፣በምድር ላይ ምርጥ ትውልድ የተባለላቸውን ሱሐባዎች ሰብስቦ ተራዊሕን በአንድ ኢማም እንዲሰግዱ ካደረገ በኋላ "እንዲህ ያለው ሥራ ጥሩ ቢድዓ ይባላል" ብሎ የተናገረው የሙእሚኖች መሪ ሰይዱና ዑመር ይባላል
በላቸው።

ሰይዱና ዑመር ለዚያ ሁሉ ሱሐባ ተራዊሕን "በአንድ ኢማም ሆኖ በጀመዓ መስገድ ጥሩ ቢድዓ ይባላል" ብለው የተነተኑ ጊዜ
አሁን እናንተ በየመስጅዱ እየዞራችሁ በሰላም የሚሰግደውን ሙስሊም እንደምትረብሹት አንድም ሱሐባ አልተቃወመም፣አልረበሽም በላቸው
ለምን? ምክንያቱም አዋቂዎች ነበሩ!ቢድዓ ሲባል ምን ማለት እንደሆነ አሳምረው የሚያውቁ፣በማንም ንግግርና ሽንገላ የማይታለሉ ምርጦች ነበሩና!

አዎ ወዳጄ! ልብህን አጽንተህ ዚክርህን ከጀማዓህ ጋር ቀጥል።ቢድዓ እያለ ሊወርፍህ የሚሞክረው ጀሌ እሱ ራሱ ቢድዓ ነው።ሰለፍያ ነኝ ያለህ እውነቱን ቢሆን ኖሮ የሰለፎችን ስራ "ጥሩ ቢድዓ የሚባል ነገር መኖሩን" አይቃወምም ነበር።ሰለፍያ ነኝ ያለህ በሱሐቦች ስም መስጅድህን ቀምቶ ቢዝነሱን ሊጀምር ነው። "ብርርር ከሌለህ ጀነት ሲያምርህ ይቀራል" ሲልህኮ በዲን ስም ቢዝነስ ለመስራት ቆርጦ የተነሳ መሆኑን እየነገረህ ነው።

ጭራሽ ውሃb መረጃ አለኝ ብላ ልትፎገላብህ? ሃሽሻ!

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን ታላቁ ሸይኽ ሚስባህ የወግዲው ደብሪቱ ሐሪማ ባለቤት ወደ አኼራ ሄዱ፡፡*****በአማራ ክልል በወሎ ወግዲ ከተማ የወግዲው ደብሪቱ ሐሪማ ባለቤት የነበሩት ሸይኽ...
16/03/2024

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን
ታላቁ ሸይኽ ሚስባህ የወግዲው ደብሪቱ ሐሪማ ባለቤት ወደ አኼራ ሄዱ፡፡
*****
በአማራ ክልል በወሎ ወግዲ ከተማ የወግዲው ደብሪቱ ሐሪማ ባለቤት የነበሩት ሸይኽ ሚስባህ በድንገት ወደ አኼራ ሄደዋል፡፡

ሸይኽ ሚስባህ በሺዎች ለሚቆጠሩ ደረሶች ከዒልም አባት የነበሩ ታላቅ ዓሊም የነበሩ ሲሆን እጅግ ለሰዎች አዛኝ፣ ሩህሩኅ እና በሻሻ ዓሊም ነበሩ፡፡
ከጥልቅ ዒልም ባለቤትነታቸው በተጨማሪ ለወንዜው አስታራቂ እና መካሪ አባትም ነበሩ፡፡
******
እኚህን የመሰሉ ዓሊም ድንገት በሞት ማጣት ስብራቱ ከባድ ነው፡፡
ለታላቁ ዓሊም ለሸይኽ ሚስባህ አሏህ ምሕረቱን ይለግሳቸው፣ ማረፊያቸውንም በጀነተል ፊርዶስ ያድርግላቸው!!
****
ለመላው ቤተሰቦቻቸው፣ ለዒልም ተማሪዎቻቸው፣ ለአካባቢው እና ለመላው ህዝበ ሙስሊም አሏህ መፅናናቱን ይወፍቅልን፡፡ እሳቸውንም በፋቲሀ እና በዱአ እናስታውሳቸው!

እናመሰግናለን  post 1ጥሪያችንን አክብራችሁ ሃውድ 3 | ፕሮግራማችን ላይ በአካል ለተገኛችሁ፣ ፕሮግራማችን ይሳካ ዘንድም ከጎናችን ለነበራችሁ በሙሉ "እናመሰግናለን!!!"****
14/03/2024

እናመሰግናለን

post 1
ጥሪያችንን አክብራችሁ ሃውድ 3 | ፕሮግራማችን ላይ በአካል ለተገኛችሁ፣ ፕሮግራማችን ይሳካ ዘንድም ከጎናችን ለነበራችሁ በሙሉ "እናመሰግናለን!!!"
****

ረመዷን ሙባረክ💛እንኳን ለ 1445 ለታላቁ የረመዷን ወር በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ AAl meded Islamic media-አል መደድ ኢስላሚክ ሚድያ
11/03/2024

ረመዷን ሙባረክ💛

እንኳን ለ 1445 ለታላቁ የረመዷን ወር በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ

AAl meded Islamic media-አል መደድ ኢስላሚክ ሚድያ

07/03/2024

ኸሚስ አመሻሹን

ከሌላው ግዜ በበለጠ ሁኔታ ዱአ ያስን ሰለዋት መወጠር ነው እንጂ ሙሂቦች በሙሉ::

Address

ቡሌ ሆራ
Hagere Mariam

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Al meded Islamic media-አል መደድ ኢስላሚክ ሚድያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share


Other Media/News Companies in Hagere Mariam

Show All