Molalegn Haile

Molalegn Haile Where is justice? ???

 #አስቸኳይ መረጃ ባህር ዳር‼️የኦህዴድ መራሹ የብልፅግና ፋሽት ስርዓት በመሪያችን ፣በምልክታችን አርበኛ ዘመነ ካሴ ላይ ጥቃት ሊፈፅም እንደሆነ መረጃ ደርሶናል ሲል የአማራ ወጣቶች ማህበር ...
01/08/2023

#አስቸኳይ መረጃ ባህር ዳር‼️
የኦህዴድ መራሹ የብልፅግና ፋሽት ስርዓት በመሪያችን ፣በምልክታችን አርበኛ ዘመነ ካሴ ላይ ጥቃት ሊፈፅም እንደሆነ መረጃ ደርሶናል ሲል የአማራ ወጣቶች ማህበር አስታወቀ‼

ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም
አሻራ ሚዲያ ፣

በአማራ ክልል በጦርነት በተነኮሳቸው አካባቢዎች መራራ ሽንፈትን እየተጎነጨ የሚገኘወው ታዛዢ ሰራዊት ምልክታችን አርበኛ ዘመነ ካሴ እና ሌሎች የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ለመግደል ተልኮ ተሰጦት በዛሬው ዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ እንደሆኑ ከታማኝ ምንጭ ማረጋገጥ ችለናል ።

በመሆኑም መላው የባህር ዳር ከተማና አካባቢው ወጣቶች ፣የጎጃም ቀጠና ፋኖ እንዲሁም መላው ህዝብ ከዚህ ደቂቃ ጀምሮ የምናደርገውን ጥሪ በንቃት ፣በአይነ ቁራኛ ሁሉንም ነገር እንዲከታተል የአማራ ወጣቶች ማህበር ጥሪውን ያስተላልፋል ።

ድል ለአማራ ፋኖ ‼️
ድል ለአማራ ህዝብ‼️

ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-
//
Youtube:- Ashara Tv - https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng

//
https://www.facebook.com/asharamedia24
//
ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

ከቤተ አምሓራ ፋኖ የተሰጠ ማስጠንቀቂያቤተ አምሓራ ፋኖ በደሴየአማራ ህዝብ የህልውና አደጋ በተደቀነበት በዚህ ፈታኝ ወቅት ጥቂት የነቁ ወጣቶች ብቻ አያደረጉት ባለው እልህ አስጨራሽ ትግል እዚ...
01/08/2023

ከቤተ አምሓራ ፋኖ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ

ቤተ አምሓራ ፋኖ በደሴ

የአማራ ህዝብ የህልውና አደጋ በተደቀነበት በዚህ ፈታኝ ወቅት ጥቂት የነቁ ወጣቶች ብቻ አያደረጉት ባለው እልህ አስጨራሽ ትግል እዚህ ደርስናል።ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወጣት ደግሞ በሱስ ተጠምዶ ይገኛል። ስለዚህ በዚህ ታሪካዊ ትግል ላይ እድሜው የሚፈቅድለት የአማራ ህዝብ መታገል እንዳለበት ስለምናምን ህዝቡ በተለይም ወጣቱ የመጣበትን የህልውና አደጋ ተገንዝቦ በአንድ ሀይል ነቅቶና ተግቶ መልስ እንዳይሰጥ የግል ጥቅማችሁን በማሰብ

* በቤቲንግ ቁማር

★ በጫት መቃሚያ ቤቶች

★ በሺሻ ማጨሻ ቤቶች

★ በጭፈራ ቤቶች

★ በጃንቦ ቤቶች

ተጠቃሚና አስጠቃሚዎች ላይ የቤተ አምሓራ ፋኖ በደሴ የማይቋረጥ ተከታታይ እርምጃ ስለ- ሚወስድ በዚህ የማደንዘዝ እና የመደንዘዝ ተግባር ላይ ለምትሳተፉ አካላት ለሚወሰድባችሁ ማንኛውም እርምጃ ሃላፊነቱን እራሳችሁ እንደምትወስዱ እየገለፅን ይሄንን ማስጠንቀቂያ ከዛሬ ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን እናሳስባለን።

ቤተ አምሓራ ፋኖ በደሴ

 #🔥 በነበልባሉ ሻለቃ እሱባለው ሲሳይ የሚመራው አንድ አማራ ፋኖ አንችን ብርጌድ መቄትን ተቆጣጠረ‼ሐምሌ 21 ቀን 2015 ዓ.ምአሻራ ሚዲያ ፣በሻለቃ እሱባለው ሲሳይ የሚመራው አንድ አማራ ፋ...
28/07/2023

#🔥 በነበልባሉ ሻለቃ እሱባለው ሲሳይ የሚመራው አንድ አማራ ፋኖ አንችን ብርጌድ መቄትን ተቆጣጠረ‼

ሐምሌ 21 ቀን 2015 ዓ.ም
አሻራ ሚዲያ ፣

በሻለቃ እሱባለው ሲሳይ የሚመራው አንድ አማራ ፋኖ አንችን ብርጌድ የሰሜን ወሎ ኮከቦች ፥መቄት ላይ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ነፃነት የራበው ፣ጭቆና የበዛበት ህዝባችን በነቂስ ወጥቶ የቁርጥ ቀን ልጆቹን(ፋኖ) በዚህ መልኩ ተቀብሏል ።

በዛሬው ዕለት በሰሜን ወሎ ዞን የመቄት ወረዳ ፣ የገረገራ ከተማ በአማራ ፋኖ ቁጥጥር ስር ገብተዋል ።የአማራ ፋኖ ገረገራ ክተማ ሲገባ በገረገራ ከተማ የአማራ ህዝብ ደማቅ አቀባበል ሲደረግለት ህዝቡም ይለያል! ይለያል! ይለያል !ዘንድሮ የብልጽግና ኑሮ በማለት እየጨፈረ ፋኖን መቀበሉን ታውቋል ።

በዚህም የህዝቡን ድጋፍና ስሜቱን ያየው የከተማው ፖሊስ እና ሚኒሻ በመበሳጨት ወደ ህዝቡ ለመተኮስ በህንጻወች አናት ላይ ተሰግስገው መቀመጣቸውን የህዝብ ልጅ ለሆነው ፣ለመከታችን ፣አለኝታችን ፣የአማራ የቁርጥ ቀን ልጅ ( ፋኖ) መረጃው ቀድሞ በመድረሱ አናብስቱ ፣ቅንድም የማይስተው ፋኖ ተከታታይ ተኩስ ሲተኩስባቸው ሁሉም ተበታትነው እምጥ ይግቡ ስምጥ አልታወቀም።

የአማራ ፋኖ አሁንም እንደዚህ የምታደርጉ የገዥው ስርዓት ታዛዥ የፀጥታ አካላት አደብ ግዙ !
ብትችሉ የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጅ የሆነውን (ፋኖን) ተቀላቀሉ ፣ካልቻላችሁ አርፋችሁ ቁጭ በሉ በማለት የመጨረሻ ጥሪያችን እናስተላልፋለን ።

በመቄት ወረዳ በፋኖ ላይ ይሄን ያክል ሴራ እያሴረ ያለው የከተማው የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊው አቶ መካሽ መሆኑ ታውቋል ።ሆኖም ግን በአስተዋይነቱ የሚታወቀው የአማራ ፋኖ አደረጃጀት
የሰውየውን ክፋት በምክር መልክ እዳለፈው አውቀናል ።ብታርፍ ይሻላል!!

በዛሬው ዕለትም በምስራቅ አማራ ፋኖ ስር የመቄት ወረዳ አንችም ፋኖ ብሎ ተደራጅቶ ታላቅ ተግባራትን እየሰራ ይገኛል ።

ድል ለአማራ ፋኖ‼️
ድል ለአማራ ህዝብ‼️

"ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።"

ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-
//
Youtube:- Ashara Tv - https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng

//
https://www.facebook.com/asharamedia24
//
ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

ብአዴን እየተመናመነ ነው!የወልድያ ከተማ ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ዋና ኃላፊ ኮማንደር አሻግሬ ተስፋው በራሳቸው ፈቃድ የሥራ የመልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተው ከስራ ለቀዋል፡፡ኮማንደሩ በብዙ የኃላፊ...
28/07/2023

ብአዴን እየተመናመነ ነው!

የወልድያ ከተማ ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ዋና ኃላፊ ኮማንደር አሻግሬ ተስፋው በራሳቸው ፈቃድ የሥራ የመልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተው ከስራ ለቀዋል፡፡

ኮማንደሩ በብዙ የኃላፊነት ቦታወች ከህዝብ ጎን ሆነው የሠሩ እና በህወሀት ወረራ ጊዜም ግንባር ድረስ በመግባት እስከ መቁሠል ድረስ ዋጋ የከፈሉ ጀግና ናቸው፡፡ የከተማዋ ዲክታተር ከንቲባ አቶ ዱባለ አብራሬ "በፋኖ ላይ ዝመቱ፤ ከፋኖ ጎን ናችሁ፤ እንዲሁም የፋኖ አሸናፊ አለሙ ቤተሠብ ነህ" እያለ ሲያቀረሽ ከዋለ በኋላ ቆራጡ ሰው ወደፋኖ አልዘምትም ከቻልኩ እደግፋለሁ ብለው በኩራት ጥለውት ወጥተዋል፡፡

“እስክንድር የሚያደርገው ትግል፣  ህዝብ ላይ የመጣውን አደጋ የማንቃትና የማሳወቅ እንጂ፣ ጦር አንስቶ አልተዋጋም። እየተዋጋም አይደለም!“የአማራ ህዝብ በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ ከየአብይ አ...
04/06/2023

“እስክንድር የሚያደርገው ትግል፣ ህዝብ ላይ የመጣውን አደጋ የማንቃትና የማሳወቅ እንጂ፣ ጦር አንስቶ አልተዋጋም። እየተዋጋም አይደለም!

“የአማራ ህዝብ በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ ከየአብይ አገዛዝ የተቃጣበትን የዘር ማጥፋት እንዲከላከል የማንቃት ስራ ነው እየሰራ ያለው። ጦር አንስቶ እንደነጃልመሮ መንገድ እየዘጋ ሰላማዊ ህዝብን እየገደለ ባንክ እየዘረፈ አይደለም። ይህንን መንግስት ተብዬው ጠንቅቆ ያውቃል።

“እስክንድር ለስልጣን ወይም ለጥቅም አይደለም የሚንከራተተው። በኑሮው ምንም የጎደለበት ሰው አይደለም። እስክንድር ጭቆናን ይፀየፋል። የአማራ ህዝብና የኢትዮጵያ ህዝብ ልጅህን አሳሳፈህ ለሰው በላው መንግስት እንዳትሰጥ ጥሪ አቀርባለሁ። ልጅህን ጠብቀው። የአብይ ሰራዊት እነ እስክንድር ይገኙበታል ወደተባለው ስፍራ እንዳይደርሱ የምትችሉትን ሁሉ ታደርጉ ዘንድ እጠይቃለሁ።

“እስክንድር አንድ ነገር ቢሆን ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ክብርህ የሚገፈፈው ያንተ እንጅ የእሱ አይደለም። እሱ የጀግና ሞት ነው የሚሞተው። በጀርባው እንጅ ፣ በሆዱ አይወድቅም።
የአማራ ክልል ባለስልጣናት ወንድምህን አሳልፈህ እየሰጠህ ነገ ከማን ጋር እንደምትኖር ቆም ብላችሁ ልታስቡ ይገባል።”

ሠርክዓለም ፋሲል

በስመ አብ፤ ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከጥር ፳፱ እስከ የካቲት ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለ ፫ ተከታታይ ቀናት ...
09/02/2023

በስመ አብ፤ ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከጥር ፳፱ እስከ የካቲት ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለ ፫ ተከታታይ ቀናት በመላው ዓለም የታወጀው የነነዌ ፆም እና ምሕላ መጠናቀቅን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ::
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
በትንቢተ ዮናስ በሰፊው እንደተጠቀሰው የነነዌ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት ላይ ስለአመጹ እና ግብራቸውም በእግዚአብሔር ፊት አጸያፊ በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ዮናስን “ተነስተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ ክፋታቸውም ወደ ፊቴ ወጥቷልና በእርስዋ ላይ ስበክ” በማለት አዘዘው፡፡ ትንቢተ ዮናስ ምዕ ፩ ቁጥር ፪ ዮናስም ድምፁን ከፍ አድርጎ ለነነዌ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ሲሰብክ “የነነዌ ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም አዋጅ ነገሩ፤ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ፡፡ ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እርሱም ከዙፋኑ ተነስቶ መጎናጸፊያውን አወለቀ ማቅም ለበሰ፤ በአመድም ላይ ተቀመጠ፡፡ አዋጅም አስነገረ፤ በነነዌ ውስጥ የንጉሡንና የመኳንንቱን ትእዛዝ አሳወጀ፤ እንዲህም አለ ሰዎችና እንስሶች፤ ላሞችና በጎች አንዳችን አይቅመሱ፣ አይሰማሩ፣ ውኃንም አይጠጡ፤ ሰዎችና እንስሶችም በማቅ ይከደኑ፣ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ጩኸት ይጩኹ፤ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ፡፡ እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደሆነ ማን ያውቃል፡፡ እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውንም አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም” ትንቢተ ዮናስ ፫፡ ፭-፲

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ይህን የነነዌ ሰዎች ፆም መነሻ በማድረግ የነነዌ ሰዎችን በምሕረቱ የጎበኘ አምላክ እኛንም በምሕረቱ ይቅር ይለን ዘንድ በየዓመቱ በአዋጅ በመፆም አምላካችንን ስንማጸንበት ኖረናል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባዔ በጥር ፳፮ ቀን ፳፻፲፭ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በወሰነው መሠረት የካቲት ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም የተጠናቀቀው የነነዌ ፆምና ምሕላ ልዩ በሆነ በመንፈሳዊ የንስሐ ጸሎት በሰላም ተጠናቋል፡፡

በምሕላውም ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ጀምሮ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፤ ካህናት፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ አገልጋዮች እና ምእመናን እንደነነዌ ሰዎች ጥቁር ለብሰን ጠዋትና ማታ በጸሎት ፤ በምሕላ፤ ቀን በቅዳሴ እንዲሁም በሰባቱ የጸሎት ጊዜያት ፈጣሪያችንን ስንለምን እና ስንማጸን የቆየንበት ምክንያት በቤተክርስቲያናችን ላይ የመጣው ፈተና እጅግ በጣም ከባድ በመሆኑ ነው፡፡

በዚህ የጾምና የንስሐ ወቅት ምእመናን ልጆቻችን የአባቶቻችሁን ጥሪ ሰምታችሁ፤ የሹመኞችን ማዋክብና እስር ሳትፈሩ ጥቁር ለብሳችሁ ጠዋትና ማታ በጾምና በምሕላ፣ ቀን በቅዳሴ በቤተክርስቲያን ቅጥር እየተገኛችሁ ለአምላካችን ያቀረባችሁትን ጸሎት እና ምሕላ እግዚአብሔር ሰምቶ ለችግራችን መፍትሄ፣ ለሀገራችን ሰላምን እንደሚሰጠን እምነታችን ጽኑ ነው፡፡ እናንተም ምእመናን የቤተ ክርስቲያንን ጥሪ ሰምታችሁ ለሃይማኖታችሁ፣ ለሀገራችሁ አንድነትና ሰላም ያላችሁን ጥልቅ ፍቅር ስለገለፃችሁም ያገኘነው መንፈሳዊ ብርታት ሳንገልፅላችሁ አናልፍም፡፡

በእግዚአብሔር ቸርነት፣ በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም እና በቅዱሳን አማላጅነት፣ በመላእክት ተራዳኢነት በፍፁም ፍቅርና አንድነት የያዝነውን ጸሎት እና ምሕላ አጠናቀናል፡፡ ችግራችንን ለአምላካችን በለቅሶ እና በጩኸት ነግረናል፡፡ ከዚህ በኋላ መከራው ቢጸና፣ የመከራው ጊዜ እንኳን ቢረዝም እግዚ

ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም...
03/02/2023

ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

Address

Gondar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Molalegn Haile posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Molalegn Haile:

Share