24/08/2021
*******
ፋብሪካዎች የማምረት አቅማቸው እያደገ ሲሄድ ለማምረት የሚያገለግለውን ማሽነሪ ብዛት ከመጨመር ይልቅ ማሽኑ ላይ የሚሰራውን የሰው ሃይል ቁጥር መጨመር ይቀናቸዋል! ምን ያህል ሰራተኛ ቢቀጠር ነው ብዙ ምርት ማምረት የሚቻለው? የዚህ መልስ ባለቤት Law of Variable Proportion ይባላል!
በማምረት ሂደት ውስጥ ብዙ ሰራተኛ ቀጥሮ ማሰራት አጠቃላይ የምርት መጠንን ይጨምራል ነገር ግን ከተወሰነ መጠን በላይ ሰራተኛ መጨመር አጠቃላይ የሚመረተውን ተጨማሪ መጠን (Marginal Product) እንዲቀንስ ሊያደርገው ይችላል!
Law of Variable Proportion:- ለምርት ከሚያገለግሉ ግብዓቶች መካከል ( #ለምሳሌ:- ከግብዓቶች መካከል የሰው ሃይል እና ማሽን ብንወስድ) አንድ ብቻ ግብዓት ( #ለምሳሌ:- የሰው ሃይል ወይም ማሽን ብቻ) እንዲጨምር ሲደረግ ጠቅላላ ምርት ይጨምራል! ነገር ግን ከልክ በላይ የአንድ ግብዓት ብቻ ( #ለምሳሌ:- የሰው ሃይል ወይም ማሽን ብቻ) ጭማሪ ካለ ጠቅላላ ምርት ይቀንሳል የሚል አስተሳሰብ ነው፡፡
#ማብራሪያ1
የትኛውም ምርት በአንድ ግብዓት ብቻ እንደማይመረት ግልጽ ነው! #ለምሳሌ:- ዳቦ ለማምረት ዱቄት፤ ውሃ፤ መጋገሪያ ማሽን፤ ጋጋሪ ሰራተኛ፤ ወዘተ ያስፈልጋል። ነገር ግን በLaw of Variable Proportion ህግ ዱቄት፤ ውሃ፤ መጋገሪያ ማሽን ምንም ሳይለወጡ/ባሉበት ሆነው ጋጋሪ ሰራተኛ ብቻ ቢጨመር የሚመረተው ዳቦ መጠን መጨመሩ አይቀርም፤ ምክንያቱም አንድ ጋጋሪ ከሚጋግረው በላይ ሁለት ሆነው ሲጋግሩ ብዙ ስለሚሆን ነው (Stage 2)። ነገር ግን የሰራተኞቹ ቁጥር ከ2 ወደ 3 ቢያድግ ዱቄት፤ ውሃ፤ መጋገሪያ ማሽን እስካልተጨመረ ድረስ አጠቃላይ የሚጋግሩት መጠን እየቀነሰ ነው የሚሄደው ለማለት ነው (Stage 3)፡፡
#ማብራሪያ2
በዳቦ ፋብሪካው ምሳሌ አማካኝነት በሰራተኛ ብዛት ምርት ይቀንሳል ሲባል ምርት የሚያድግበት ልዩነት ወይም Marginal Product ነው የሚቀንሰው፤ ምን ማለት ነው?
#ለምሳሌ:- አንድ ዳቦ ፋብሪካ 100 ኪሎ ዱቄት፤ 100 ሊትር ውሃ፤ አንድ መጋገሪያ ማሽን እና አንድ ጋጋሪ ሰራተኛ ተጠቅሞ በቀን 1,000 ዳቦ ይጋግራል ብንል (የዳቦ ቤቱ የማምረት አቅም 2,000 ዳቦ ነው ብንል) እና አጠቃላይ ወጪው 100 ኪሎ ዱቄት 2,500 ብር ቢሆን፤ 100 ሊትር ውሃ 50 ብር ቢሆን፤ የአንድ መጋገሪያ ማሽን ኪራይ በቀን 1,000 ብር ቢሆን እና አንድ ጋጋሪ ሰራተኛ ደሞዝ በቀን 200 ብር ቢሆን በድምሩ 3,750 ብር ወጪ አለበት ማለት ነው (Stage 1)።
ነገር ግን ሌሎቹ ግብዓቶች 100 ኪሎ ዱቄት፤ 100 ሊትር ውሃ እና አንድ መጋገሪያ ማሽን ሳይለወጡ ሰራተኞቹ ሁለት ቢሆኑ እና ተረዳድተው 2,000 ዳቦ በቀን ቢጋግሩ ምርቱ በእጥፍ ጨመረ ወጪ ደግሞ በ200 ብር ጨመረ! ይሄ በጣም ጥሩ ለውጥ ነው (Stage 2)፤ ጥያቄው ሰራተኞቹ ወደ 3 ቢያድጉ ምርት ከ 2,000 በላይ ማደግ አይችልም! ወጪ ግን በ200 ብር ያድጋል ምክንያቱም የሰራተኛው የቀን ደሞዝ ስለሆነ በLaw of Variable Proportion ህግ ዳቦ ፋብሪካው የዱቄት፤ የውሃ እና የመጋገሪያ ማሽን እስካልጨመረ ድረስ 2 ሰራተኛ ከፍተኛ ምርት ለማምረት በቂ ነው ይላል፡፡
ምርታማነትን ለማሻሻል ሁሉንም ግብዓቶች በተመጣጠነ መልኩ መጠቀም እና የሚያመጡትን ለውጥ እየመዘኑ መሄድ ያስፈልጋል ( #ለምሳሌ:- ሁለት ሰራተኛ አለ ብሎ ዳቦ መጋገሪያውን ሁለት ማድረግ ውጤታማ ላያደርግ ይችላል ስለዚህ የማሽኑን መጨመር ተከትሎ ጋጋሪ መጨመር ወይም ዱቄቱን መጨመር ግዴታ ነው! ይህንን የሚያመጣጥነው ዘዴ Isoquant curve እና Isocost Line እንደሚባል ከዚህ በፊት አውርተናል)።
https://t.me/wasealpha