Gospel of Life tv Ethiopia

Gospel of Life tv Ethiopia “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።”
— ሐዋርያት 4፥12

07/08/2023
02/09/2022

#2015

24/06/2022
28/04/2022
03/03/2022

❤️ ❤️
=================================
❤️
( )
✍️ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦
" እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ፤"
(የዮሐንስ ወንጌል 5: 39)
✍️ ሉቃስ 24 (ኢየሱስም)....
27፤ ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ #ተረጐመላቸው።
📌 መጽሐፍ ቅዱስ በዘፍጥረት ምዕራፍ 4 ስለ አቤልና ቃየን ምን ያስተምረናል ፦
✍️ዘፍጥረት 4 (Genesis)
2፤ ደግሞም ወንድሙን አቤልን ወለደች። አቤልም በግ ጠባቂ ነበረ፤ ቃየንም ምድርን የሚያርስ ነበረ።
3፤ ከብዙ ቀን በኋላም ቃየን ከምድር ፍሬ ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን አቀረበ፤
4፤ አቤልም ደግሞ ከበጎቹ በኵራትና ከስቡ አቀረበ። እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ፤
5፤ ወደ ቃየንና ወደ መሥዋዕቱ ግን አልተመለከተም። ቃየንም እጅግ ተናደደ ፊቱም ጠቆረ።
✍️መጽሐፍ አቤል የበግ እረኛ እንዲሁም ወንድሙ ቃየን ደግም ምድርን የሚያርስ እንደነበሩ ይነግረናል። ሁለቱም ሰዎች በዚህች ምድር ላይ የሚኖሩትን ሁለት አይነት ሰዎች በምሳሌ መልኩ የሚያሳዩ ናቸው።
👉 የበግ ጠባቂውና ለእግዚአብሔር ከበጎች መካከል በኩሩን የሰዋው አቤል የእግዚአብሔር በግ የሆነውን ክርስቶስንና የክርስቶስን የመስዋዕትነት ስራ በማመን የሚጸድቁትን እውነተኛ አማኞችን የሚወክል ሲሆን። እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መስዋዕቱ ተመለከተ አቤል በእምነት በቀረበው መስዋዕት በኩል ተቀባይነትን አገኘ። እግዚአብሔርም መሰከረለት
ዕብራውያን 11፡4
አቤል ከቃየል ይልቅ የሚበልጥን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በእምነት አቀረበ፥ በዚህም፥ እግዚአብሔር ስለ ስጦታው ሲመሰክር፥ እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ ተመሰከረለት፤ ሞቶም ሳለ በመሥዋዕቱ እስከ አሁን ይናገራል።
👉 ቃየን ግን በራሴ መልካም ስራ በላቤ ፥ በልፋቴ እጸድቃለሁ የሚሉትን ሐይማኖተኛ ሰዎችን የሚወክል ነው። ከዚህም የተነሳ የተረገመችውን ምድር የሚያርስ በላቡና በወዙ በጥረትና በትግል የሚያመጣውን የላቡን ውጤት ለእግዚአብሔር የሚያቀርብን ሀይማኖተኛ ሰው ይመስላል። እግዚአብሔር ግን ወደ ቃየንና ወደ መስዋዕቱ አልተመለከተም ቃየን በላቡና በጥረቱ ያቀረበውን መስዋዕት እግዚአብሔር ከልተቀበለውም።
✍️ሀጥያተኛ የሆነው የሰው ልጅ የትኛውንም መልካም ስራ ቢሰራ ሀይማኖታዊ ስርአቶችን ቢጠብቅ በአምላክ ፊት ተቀባይነትን በማግኝት ሊጸድቅ አይችልም።
✍️ሐዋርያው ጳውሎስ በገላትያ መልዕክቱ ላይ እንዳስጠነቀቀን መልካም ስራን በመስራት ሐይማኖታዊ ስርዓት በመፈጸም እንጸድቃለን ብለን የምናስብ ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ
የክርስቶስ ሞት አስፈላጊ አልነበረም ማለት ነው። ነገር ግን በክርስቶስ የቤዛነት ስራ በማመን እንጸድቅ ዘንድ ክርስቶስ ስለሀጥያታችንና ስለበደላችን ሞቷል ተሰውቷል አቤል በእምነት ያቀረበውና ተቀባይነትን ያገኘው አማናዊው የበግ መስዋዕታችን የእግዚአብሔር በግ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
✍️ገላትያ 2፡16
ነገር ግን ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲጸድቅ እንጂ በሕግ ሥራ እንዳይሆን አውቀን፥ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በሕግ ሥራ ስለማይጸድቅ፥ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት እንጸድቅ ዘንድ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል።
✍️ሮሜ 10፡8-11
ነገር ግን ምን ይላል? በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል፤ ይህም የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው።
ይቀጥላል...........
Naol.

21/02/2022

Like & follow

20/02/2022
13/02/2022
08/02/2022

Address

Goba
01

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gospel of Life tv Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Gospel of Life tv Ethiopia:

Videos

Share

Category


Other Goba media companies

Show All