Offa media network OMN

Offa media network OMN To provide news,events and performance of offa zonal areas as well as national and global context.

04/11/2023
04/11/2023
04/11/2023

ከዕዳ ወደ ዕዳ አሰባሰብ ይሆናል ምንዳ
ተዘዋዋሪ ብድርና ኦሞ ሲሰበሰብም=ምንዳ
እያንዳንድሽ ዕዳ እየመለስሽ የማይመለስ ዕዳ የለም!
የሚታለፉ ግለሰቦችንና ማህበራትን አንታገስም።

  በገሡባ ኦርጋኒክ ቡና ግብይት ማዕከል የቡና ግብይት በይፋ ጀምሯል ።የገሡባ አካባቢ ገበሬዎች ሁለገብ ኅብረት ሥራ ማህበር (ኃ.የተወሰነ ) በዛሬው ዕለት ከንቅናቄው መልስ 1ኛ ደረጃ የእሸ...
16/10/2023


በገሡባ ኦርጋኒክ ቡና ግብይት ማዕከል የቡና ግብይት በይፋ ጀምሯል ።
የገሡባ አካባቢ ገበሬዎች ሁለገብ ኅብረት ሥራ ማህበር (ኃ.የተወሰነ ) በዛሬው ዕለት ከንቅናቄው መልስ 1ኛ ደረጃ የእሸት ቡና በኪሎ 35 ብር 2ኛ ደረጃ 31-34 ብር ሲገበያይ ዉሏል።የዳቀያ አካባቢ ገበሬዎች ሁለገብ ኅብረት ሥራ ማህበር እና ለሎች ፍቃድ ያላቸው የግል ባለሃብቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ ገደብ በንቃት እንድሳተፉና ጥራቱን የጠበቀ ቡና በመግዛትና በማቅረብ የወላይታ ብራንድ ቡና ለዓለም ገበያ እንድያሰተዋዉቁ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።
©የኦፋ ወረዳ እና ገሡባ ከተማ አስ/ር ግብርና ጽ/ቤት

17/09/2023
10/09/2023
28/08/2023


📝ዛሬን በእንቅልፍ ካሳለፋቹ... ነገም ቅዠትን ነው የምታተርፉት

📝ዛሬን ጠንክራችሁ መስራት ከቻላችሁ... ነገ የተሻለ ይሆናል።

📝ጠንክረን በሰራን ቁጥር... ዕድለኛነታችን ይጨምራል።

ለስኬት 7 ነገሮች ያስፈልጋሉ...
በዚህ ሊንክ በመግባት ይማሩበት!!!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/5ziL0Gv7E-E?si=ogj3LSlZo5D-uHp9
https://youtu.be/5ziL0Gv7E-E?si=ogj3LSlZo5D-uHp9
https://youtu.be/5ziL0Gv7E-E?si=ogj3LSlZo5D-uHp9

21/08/2023

በ40 ዓመቷ በጨጓራ ካንሰር ከመሞቷ በፊት በዓለም ታዋቂው ዲዛይነር እና ደራሲ “ክሪስዳ ሮድሪጌዝ” እንዲህ ስትል ፅፋለች።

1. ጋራዥ ውስጥ የአለማችን ውድ መኪና ነበረኝ፣ አሁን ግን በዊልቸር መንቀሳቀስ አለብኝ።

2. ቤቴ ሁሉንም አይነት ብራንድ ያላቸው ልብሶች፣ ጫማዎች እና ውድ እቃዎች ይሸጣል፣ አሁን ግን ሰውነቴ በሆስፒታሉ በተዘጋጀ ትንሽ ጨርቅ ተጠቅልሏል።

3. በባንክ ውስጥ ብዙ ገንዘብ አለኝ። አሁን ግን ከዚህ መጠን ምንም አልጠቀመኝም።

4. ቤቴ እንደ ቤተ መንግስት ነበር አሁን ግን በሆስፒታል ውስጥ በሁለት አልጋዎች ተኝቻለሁ።

5. ከባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ወደ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል. አሁን ግን በሆስፒታል ውስጥ ከአንድ ላብራቶሪ ወደ ሌላ በመንቀሳቀስ ጊዜዬን አሳልፋለሁ

🦋 በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ፊርማ ሰጥቻለሁ ነገርግን በዚህ ጊዜ የሕክምና መዝገቦች የእኔ ፊርማ ናቸው።

እ.ኤ.አ. . ፀጉሬን ለመስራት ሰባት ፀጉር አስተካካዮች ነበሩኝ ፣ አሁን ግን - በራሴ ላይ አንድ ፀጉር የለኝም።

፨ በግል ጄት ላይ፣ የትኛውም ቦታ መብረር እችላለሁ፣ አሁን ግን ወደ ሆስፒታል በር ለመራመድ ሁለት እርዳታዎች ያስፈልጉኛል።

፨ ምንም እንኳን ብዙ ምግቦች ቢኖሩም, አሁን የእኔ አመጋገብ በቀን ሁለት ጽላቶች እና ምሽት ላይ ጥቂት የጨው ውሃ ጠብታዎች ናቸው.

ይህ ቤት፣ ይህ መኪና፣ ይህ አውሮፕላን፣ ይህ የቤት ዕቃ፣ ይህ ባንክ፣ ብዙ ዝናና ዝና፣ አንዳቸውም አይመጥኑኝም። ከእነዚህ ውስጥ አንዳቸውም አያዝናኑኝም.

የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቅለው መሰል መረጃዎች በፍጥነት ያግኙ
https://t.me/changeitwow

Youtube subscribe እያደረጋችሁ!
https://youtu.be/kaVoq1_miNs
https://youtu.be/kaVoq1_miNs
https://youtu.be/kaVoq1_miNs


ራስን መለወጥ

መንግስታዊ የሆነ ሃይማኖት እንደሌለ ሁሉ ሃይማኖታዊ የሆነ መንግሥት አይኖርም ህገ መንግስትም አይፈቅደዉም።
11/08/2023

መንግስታዊ የሆነ ሃይማኖት እንደሌለ ሁሉ ሃይማኖታዊ የሆነ መንግሥት አይኖርም ህገ መንግስትም አይፈቅደዉም።

11/08/2023

የትም ቦታ ብንሄድ እዛም ያለነው እኛው ነን!
==========================
ይህ በጆን ካባት-ዚን የተፃፈው ምርጥ መፅሀፍ ርዕስ ነው፡፡ ርዕሱ እንደሚገልፀው የትም ቦታ ብንሄድ ራሳችንን ይዘን ነው፡፡ አስፈላጊነቱ "ሌላ ቦታ በሆንኩኝ!" እያሉ መመኘትን እንድናቆም ነው፡፡ እረፍት ላይ ብሆን፣ ከሌላ ፍቅረኛ /የትዳር አጋር ጋር ብሆን፣ ሌላ ትምህርት ተምሬ ቢሆን፣ ሌላ ስራ ቢኖረኝ፣ ሌላ ቤት ውስጥ ብኖር፣ ሌላ ሁኔታ ውስጥ ብሆን...ደስተኛ እሆን ነበር ብለን እናስባለን፡፡ ደስተኛ አንሆንም!

በእውነታው ጎጂ የሆነ የአስተሳሰብ ልማድ ካለን ማለትም በቀላሉ የምንናደድ ከሆነ፣ ትንንሽ ነገሮች የሚያበሳጩን ከሆነ፣ ነገሮች የተለዩ ቢሆኑ ብለን የምንመኝ ከሆነ የትም ብንሄድ እነዚህ ልማዶች ይከተሉናል፡፡ በተቃራኒውም ደግሞ እውነት ነው፡፡ በአብዛኛው በትንሹ የማይናደድ ደስተኛ ሰው ከሆንን ቦታ ብንለውጥም ከሌላ ሰው ጋር ብናሳልፍም ሳንጨነቅ ጥሩ ጊዜ ይኖረናል፡፡

አንድ ጊዜ አንድ ሰው "እናንተ አካባቢ ያሉ ሰዎች ምን አይነት ናቸው?" ብሎ ጠየቀኝ፡፡ እኔም መልሼ "መጀመሪያ እናንተ አካባቢ ያሉት ሰዎች ምን አይነት ናቸው?" ብዬ ጠየቅሁት፡፡ "ስግብግብና ራስ ወዳድ ናቸው፡፡" ብሎ መለሰልኝ፡፡ "እኛ አካባቢ ያሉትንም ሰዎች እንደዚያው የምታገኛቸው ይመስለኛል፡፡" አልኩት፡፡

ህይወት እንደመኪና ከውስጥ ወደ ውጭ እንደሚሽከረከር ስንገነዘብ አስገራሚ ነገሮች መፈጠር ይጀምራሉ፡፡ ከውጭ ወደ ውስጥ አይሆንም! ሌላ ቦታ፣ ሌላ ሁኔታ ቢሆን የሚለውን ምኞት ትተን አሁን ያለንበትን ቦታ የተሻለ ማድረግ ላይ ስናተኩር አሁን እዚሁ ደስተኛ መሆን እንጀምራለን፡፡ ከዛ ቦታ ብንለውጥም፣ አዲስ ነገር ብንሞክርም፣ አዲስ ሰዎች ስናገኝም ውስጣዊ እርጋታችንን ይዘን ነው፡፡ የትም ቦታ ብንሄድ ራሳችንን ይዘን ነው፡፡

ከ 'ቀላሉን ነገር አታካብ' መፅሀፍ ገፅ 133-134 የተተረጎመ

በደስተኝነታችንን እና በኛ መካከል ጣልቃ ሊገባ የሚችለው ሌላኛው ብቸኛ ሰው መስታወት ውስጥ የምንመለከተው እኛኑ የሚመስለው ግራኝ ሰው ብቻ ነው፡፡

ያለ አእምሮ ጤና፤ጤና የለም!!!!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

11/08/2023

✅የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በአማራ ክልል ያለው አለመረጋጋት እንዳሳሰባቸው ገለፁ።
ግጭቶች በህዝቡ ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳሉ ያሉት ዶክተር ቴድሮስ

ሁለቱም ሀይሎች ጦርነቱ ሳይባባስ ወደ ሰላም ስምምነት ሊመጡ ይገባል

W H O office Dr T A
ከደራሲያን አለም ፔጅ

07/07/2023

💚በዓለም ትልቁ ሀብት አመለካከት ነው!💚

-ፈጣሪን አመስጋኝ ብንሆን ህይወታችን ብሩህ ይሆናል። መፍትሄ ፈላጊዎች እንጂ እንከን አሳሾች አንሆንም።

-ብሩህ አመለካከት ብንይዝ ቀናችንም... ህይወታችንም ይስተካከል።

-ተነጫናጭና ብሶተኛ ከሆንን የሚያጋጥመንም እንደዛው ነው።

ጥሩ አመለካከት ካለን ጥሩ እንሆናለን
መጥፍ አመለካከት ካለን መጥፎ ነገሮች ውስጥ እንገኛለን!

-ሁልጊዜም በውስጣችን ስለምንገነባው አመለካከት ጥንቃቄ እናድርግ!

👍ውስጣችን በገነባነው ልክ ነው መልስ የሚሰጠን።

መልካም ቀን!

ራስን መለወጥ

t.me/changeitwow

(ታላቅ ነገር የማሰብ ኃይል) ከሚለው መፅሀፍ የተገኘ ታላላቅ አሳቦች ምን ያህል ህይወታችንን እንደሚቀይሩ የሚሳይ አሳብ ያለው 10 ቁምነገሮች በዚህ ሊንክ ገብተው ያገኛሉ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/ZWD1D0xzFk0

07/07/2023

ስኬትማነት የሶስት ወሳኝ ቁልፎች ውጤት ነው!

1ኛ የተግባር
👉ተግባር የሌለው ህልማ... "ቅዠት ነው" ልንደርስ ያሰብንበት ስኬት ተግባር መነሻ ቁልፍ ነው።

2ኛ የመማር
👉ወደ ተግባር ስንገባ በተደጋጋሚ እንወድቃለን። ውድቀታችን ደግሞ ሊያስተምርን ይገባል። ድጋሚ ስንጀምር ከምን ሳይሆን ከልምድ ነው።

3ኛ የመሻሻል
👉ስኬት የአንድ ቀን ለውጥ ሳይሆን ቀን በቀን የሚደርግ መሻሻል ውጤት ነው። መሻሻሎቻችን ደግሞ ቀስ ቀስ የምንፈልገው ቦታ ያደርሱናል።

ራስን መለወጥ

t.me/changeitwow

እኛ ሰዎች ለምን አይሳካልንም?! ለምንስ በተደጋጋሚ እንወድቃለን?!!!!
በዚህ ሊንክ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/SBN3wItqXL4

11/06/2023

ጤናመረጃ‼️

የአብሽ 10 የጤና ጥቅሞች!

ለልብ ድካም፣ ለደም ግፊት፣ ኮሌስትሮል ለመቀነስ፣ ለጨጓራና በስካር በሽታ ለሚሰቃዩ ፍቱን መድሃኒት ነው::ገና ለወለዱ እናቶችም የጡታቸውን መጠን የተወሰነ ለመጨመር ይጠቅማል።

ጥቅሞቹ በዝርዝር ቀጥሎ ቀርበዋል፦

※የስኳር በሽታን ለመቆጣጠር ይረዳል፦ አብሽ ደም ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠን በመቆጣጠር ኢንሱሊን መቋቋምን ይቀንሳል።

※የልብ በሽታን ያስወግዳል፦ የልብ ጉዳትን ለመከላከልና ኦክሲዳቲቭ ውጥረት ለማስወገድ ይረዳል።

※የወር አበባ ቁርጥማትን ያስታግሳል፦ አብሽ ከቁርጥማት በተጨማሪ ራስ ምታት፣ ማቅለሽለሽና ድካምን ለመቀነስ ይረዳል።

※የጡት ወተት ምርትን ያሻሽላል፦ አብሽን መጠጣት የወተት ምርትን የሚጨምር ውህድ ስላለው፤ ለሚያጠቡ እናቶች ይረዳል።

※የምግብ መፍጨት ችግርን ይረዳል፦ የሆድ ድርቀትንና ከጨጓራ መቆጣት የተነሳ ለሚከሰት የምግብ መፍጨት ችግርን ለመከላከል ይረዳል።

※የጸጉር መሳሳትን ለመከላከልና ለፀጉር እድገት ጠቃሚ ነው። የተፈጨ አብሽን ሳይወፍር በብርጭቆ ውሀ በማዋሀድ መቀባት።

※ አብሽ መጠጣት አቅም ማጣትን ለማከምና የወሲብ ችሎታን ለመጨመር ይረዳል።

※አብሽ መጠጣት ብጉርን ለመከላከል ይረዳል።

※ፀረ-እርጅና ጥቅም አለው፦ለቆዳችን አስደናቂ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን የእርጅና ምልክትን እንደ የቆዳ መጨማደድና ቀጫጭን መስመርን ያስወግዳል።

※ቆዳን ለማርጠብ፦ የአብሽ የሚሙለጨለጨው በሀሪ የደረቁ ቆዳዎችን በማስወገድ ቆዳችን እንዲረጥብ ይረዳናል።

አጠቃቀሙ፣ በ1 ብርጭቆ ውሃ ውስጥ 2 የሾርባ ማንኪያ ነው መጠጣት ያለብዎት። ተፈጥሯዊ ስለሆነ ምንም አይነት ጉዳት የለውም። ክብደት እንዳይጨምሩ በመጠኑ ይጠቀሙ።

ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ!ሼር!

30/05/2023

ኪስህ ገንዘብ ሲኖር ገብተህ የምትመዘው
ከጎንህ ሰው አለ እንደልጅ ምታዘው።
ብዙ አፋሽ አጎንባሽ በዙሪያህ ታያለህ
ገና ሳታስነጥስ ይማርህ የሚልህ።
ጥላ ላይም ቁመህ ጥላ ሚዘረጋ
የቆለፍከውን በር ሩጦ የሚዘጋ፤
በአቧራ ስትሄድ ከፊት ሳር አንጣፊ
ኪስህ ገንዘብ ካለ ሞልተዋል አጣፊ።

አጣሁ ያልክ እለት ግን ኪስህ ሲሆን ባዶ
አንተ በዚህ ስትሄድ እነሱ በማዶ።
አይደለም እንቅፋት ስትውል ብታስነጥስ
ለሞት ብታጣጥር ሰው የለም የሚደርስ።
ነገ ለሚነጋ ዛሬ ቀን ቢጨልም
እንኳን ያበላኸው…..
እንኳን ያጠጣኸው….
የራስህ ጥላ እንኳን ካንተ ጋር አይደለም።

እናማ ወዳጄ ኪስህን ደባብሰው
አለሁ ባይህ ኪስህ....
የወደክ ለታ አለ "ሺህ ገንዘብህ
አደናቅፎህ ብትወድቅ ሟጭሮህ ብትደማ
በማንም አትዘን … ማንንም አትማ።
መንገድ ሁሉ እንቅፋት በሆነበት አለም
መነሳት ነው እንጅ መውደቅ ብርቅ አይደለም።
ሰው ብታጣ ዛሬ አትዘን ወንድሜ
አግኝቶ ማጣትን ያስተምራል እድሜ።
ሲኖርህ የኖረህ ስታጣ ብታጣው
አለኝ ያልከው ወዳጅ ከፊት ባታገኘው፤
የዛሬው ውድቀትህ መማሪያህ ነውና
ባጣኸው ሳይጨንቅህ ባለህ ላይ ተፅናና።
መሙላት ቢቸግርህ ቀን እየጎደለ
አታቀርቅር ተነስ ቀና በል ቀን አለ።

(በአርቲስት ሜሮን ጌትነት)

30/05/2023

1. ለሰዎች መልካም ሁን፦

መልካምነት ለተረጋጋ ህይወት መጀመሪያ ነው። መልካምነት ካንተ ጋር ከሆነ ሁሉም ነገር አብሮህ ይኖራል። ለሰዎች መልካም ነገር ባደረክ ቁጥር የተረጋጋ ህይወትን ለመምራት የሚያስችልህን መንገድ እየጠረክ ትሄዳለህ። የመልካምነትን መንገድ መከተል የጀመረ ሰው ለተሳሳቱና ላልጠሩ አመለካከቶች የሚሆን ቦታ ስለማይኖረው፤ የሚያጋጥሙትን ችግሮች በተለየ አቅጣጫ እየተመለከተ ለመፍታት ይሞክራል።

2.ማገዝ ከሚችሉ ሰዎች ጋር ተወዳጅ፦

አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች በራሳቸው ጥረት ብቻ የሚፈልጉት የስኬት ጫፍ ላይ ለመድረስ ሲታገሉ እንመለከታለን። በተለይ የተሳሳተ አመለካከት ያላቸው ሰዎች የሌሎችን እገዛ መጠየቅ የውድቀት መጀመሪያ መስሎ ይታያቸዋል። በዙሪያ የሚያግዙ ሰዎች መኖር ጥንካሬና ብርታትን ይሰጣል። ስለዚህ የሚያግዝህና ሃሳብህን የምታጋራው አስተዋይ ወዳጅ ይኑሩህ።

3. ኃላፊነቶችን ለመወጣት ዝግጁ ሁን፦

ኃላፊነትን ለመቀበል ዝግጁ መሆን የተሳሳተ አመለካከትን አሽቀንጥሮ ለመጣልና ቀና አመለካከት ለማካበት ከሚረዱ ነገሮች አንዱ ነው። ኃላፊነትን በተሸከምክ ቁጥር ስለ ሌሎች ሰዎች ማሰብና ራስህን በሌሎች ቦታ አስቀምጦ ፍርድ የመስጠት ልምድ ማግኘት ይቻላል። ለሰዎች ማሰብ መቻል ደግሞ ለቀና አመለካከት እንደ ማሳያነት ይቀርባል። በተጨማሪም ከዚህ በፊት በነገሮች ላይ የነበረህን የተሳሳተ ግንዛቤ እያጠራልህ ይሄዳል። ቀስ በቀስ አመለካከትህ ተቀይሮ ሁኔታዎችን የመለወጥ አቅም እንዳለህ ማመን ትጀምራለህ።

4. ይቅር ባይ ሁን፦

በይቅርታ ማመን መቻል ሌላኛው ቀና አመለካከት ያለው ሰው መገለጫ ባህሪ ነው። አንድን ሰው በሆነ አጋጣሚ ቢያስቀይምህና ከቀናት በኋላ የሠራው ሥራ ትክክል እንዳልነበረ ተረድቶ ይቅርታ ቢጠይቅህ ይቅርታህን አትንፈገው። ቀና አመለካከት ያለው ሰው ይቅርታ ለጠየቁት ሰዎች ምህረት ከማድረግ ባለፈ በጥፋቱ ይቅርታ የመጠየቅ ልምድ አለው።

5. ሙሉነት ይሰማህ፦

የሙሉነት ስሜት በሥነ ልቦና ባለሙያዎች ዘንድ ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው። በህይወትህ ብዙ ነገሮች ሊያጋጥሙህና እንዳልነበሩ ሆነው ልታገኛቸው ትችላለህ። ለራስህ ግን ሁሉም ነገር ሙሉ እንደሆነና ዘወትር መልካም ነገር ላይ እንዳለህ አስብ።

አብዛኛውን ጊዜ የተሳሳተ አመለካከት ያላቸው ሰዎች በራሳቸው ሙሉነት አይሰ ማቸውም። ቀና አመለካከት ያላቸው ሰዎች ግን የተዘበራረቁ የህይወት መስመሮች ውስጥ ቢሆኑም እንኳን እንዳልተዘበራረቁ አድርገው ማሰብ ይችላሉ። የጎደለ ነገር ሁሉ ባዶ አይሆንምና ሁል ጊዜ በራስህ ሙሉነት ይሰማህ። ሰዎች ዛሬ የምታሳልፈው ቀን ደስ የማይል እንደሆነ አስረግጠው ቢነግሩህ እንኳን ፍፁም ደስተኛ ሆነህ ማሳለፍ እንደምትችል ውስጥህን አሳምነው።

6. ከመጠን ያለፈ አታስብ፦

ሁሉም ነገር በተፈቀደለት ጊዜ መሆኑ አይቀሬ ነው። አእምሮህ ከሚችለው በላይ በሃሳቦች መወጠር ቀና አመለካከት እንዳይኖር ያደርጋል። ስለአንድ ነገር አብዝተህ የምትጨነቅ ከሆነ ትኩረትህን ሁሉ ጉዳዩ ላይ ይሆንና በዙሪያህ ስላሉ ሰዎች ማሰብ ታቆማለህ። ያኔ ከሰዎች ጋር አለመግባባት ውስጥ ትገባለህ።

7. ደስታ አይራቅህ፦

አብዛኛውን ጊዜ የተሳሳተ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ፍፁም ደስታ የራቃቸው ናቸው። ነገሮች ላይ አብዝተው ስለሚጨነቁ፣ በይቅርታ ስለማያምኑና ሙሉነት ስለማይሰማቸው ለራሳቸው ደስታን መፍጠር ይሳናቸዋል። ቀና አመለካከት ያላቸው ሰዎች ግን ሁል ጊዜ ሙሉ እንደሆኑ ስለሚሰማቸውና አርቀው ስለሚያስቡ ደስታቸው በእጃቸው ነው።

8. ለዋዛ ፈዛዛ ነገሮች ቦታ አለመስጠት፦

ለሚረባውም ለማይረባውም ነገር ቦታ መስጠት የተዛባ አመለካከት እንዲኖር ከማድረጉም በላይ መንፈስን ላላስፈላጊ ጭንቀት ይዳርጋል። በመሆኑም ትኩረት መስጠት ለሚያስፈልገው ጉዳይ ብቻ ትኩረት በመስጠት የቀና አመለካከት ጎዳናን ማስፋት ይቻላል።

9. ግርማ ሞገስ መላበስ፦

በሌሎች ዘንድ ተቀባይነትንና ተወዳጅነትን ለማግኘት የሰዎችን ቀልብ መሳብ መቻል ተገቢ ነው። ማድረግ የምትፈልጋቸው ድርጊቶች ሁሉ ግርማ ሞገስን የተላበሱ ቢሆኑ መልካም ነው።

30/05/2023

🧠 ጭንቅላታችሁ እንደማግኔት ነው
💚በረከትን ስታስቡ በረከት ይመጣል።
😭ችግሮችን ካሰባችሁ ችግሮችን ትስባላችሁ።
🌻ሁልጊዜም ጥሩ ነገሮች በውስጣችሁ አሳድጉ።
💐በአስተሳሰባችሁ በጎ እና ውጤታማነትን አስቡ

🙏በዚች ዓለም ላይ በሂደት ወደአሰብነው እና ወደተመኘነው ነገር እንሄዳለን።
😭ጭለምተኝነትን ካሳደግን ጭለምተኛ እንሆናለን...
💚ተስፋንና ውጤታማነትን በውስጣችን ካለማመድን እኛም ወደዛ እንሄዳለን።

መልካም ቀን
ራስን መለወጥ
t.me/changeitwow

ይሄን ቪዲዮ ደግሞ በመመልከት ተጠቀሙበት... ህይወታችሁን ቀይሩ

https://youtu.be/ngBBFzWC3hs

30/03/2023

እራስህ ላይ ሰልጥን!
፨፨፨፨////////፨፨፨፨
ህይወትህ በስሜትህ ጥላ ስር ነው። በሚፈራረቀው ሰሜትህ የህይወትን ገፅ ትመለከታለህ። እያንዳንዱ የህይወት ክስተት ላይ ያለህ ስሜት ሲቀየር ህይወትህ ይቀየራል። የስሜት ብስለትህ፣ ስሜትህ ላይ ያለህ ስልጣን እራስህ ላይ እንድትሰለጥን ያደርግሃል፤ ወደፊት እንድትጓዝ፣ ለተሻለው እንድትበቃ፣ ተምሳሌትነትህን እንድታስመሰክር፣ ግብህን እንድትመታ፣ ህልምህን እንድትኖር ያደርግሃል። ሁን ብለውም ይሁን በአጋጣሚ ለተከሰቱብህ ክስተቶች የምትሰጣቸው ምላሾችህ ላይ መጠንቀቅ ከቻልክ እራስህን መቆጣጠር አይከብድህም። እራስ ላይ መሰልጠን አንድም ብስለት ሌላም እውቀት ነው። መጥፎ ስሜትህ በነዳህ ከመነዳትህ በፊት ጉዳቱን ጠንቅቀህ እወቅ፤ የሚያስከትለውን መጥፎ ሁነት ተገንዘብ።

አዎ! ጀግናዬ..! እራስህ ላይ ሰልጥን! ስሜትህን ግዛው፤ ባህሪህን እወቀው፤ ማንነትህን ተረዳው፤ ፍላጎትህን ተገንዘብ። መኖርህ በስሜት ክልል ይገለፃል፤ ደመነፍስህ የሚታየው ወዶቹ ስሜቶችህ መልክ ነው። ምንም ነገር ይግጠምህ ስለምትሰጠው ምላሽ ደጋግመህ አስብ፤ በምንም ውስጥ ተገኝ ከደረጃህ የሚያንስ ግብረ መልስ አትመልስ። ለእራስህ ከምታደርገው ውድ ነገር አንደኛው እራስህን መግዛት፣ ስሜትህን መቆጣጠር፣ አስተውሎትህን ማስፋት፣ ጥንቃቄህን መጨመር እንደሆነ አስተውል። መጥፎ ስሜቶች መጥፎ የተባሉት በሰዓቱ በሚያመጡት መጥፎ ውጤት ወይም እያደር በሚያስከትሉት ጎጂ ነገር ነው። በሰዓቱ ችግር ባይኖርም ስሜታችን ግን የሚያረጋጋውን የትኛውንም መልስ ለመስጠት ይቸኩላል።

አዎ! ስሜቶችህ ያንተ ናቸውና ልትቆጣጠራቸው ትችላለህ፤ መነሻቸው አንተ ነህና የሚያስከትሉትን ጉዳት መቀነስ ትችላለህ። መልካምና አስደሳች በሆኑትም የማትረፉና የማደጉ ምርጫ ያንተው ነው። ገዢ ሃይል ውስጥህ አለ፤ የምታምንበት ትክክለኛ ሰሜት በማንነት መልክ ይገለጣል። በምታምነው ልክ የማስተናገድና በሚጠቅምህ መጠን ስራ ላይ ማዋሉ ያንተ ድርሻ ነው። ሙሉ ሰውነትህ እንዲደሰት በሃዘን ውስጥ እስክታል መጠበቅ አይኖርብህም፤ ሰላምን ለማጣጣም የሰላም ማጣትን ጉዳት መመልከት አይጠበቅብህም፤ በአድናቆት ለመደመም ግዴታ ትቺትና መገፋት ሊገጥምህ አይገባም። እያንዳንዱን ስሜት እንደ አመጣጡ ለማስተናገድና ለማጣጣም ውስጣዊ ንቃትና የመንፈስ ጥንካሬ ያስፈልጋል። ስሜትህን በመግዛት እራስህ ላይ ሰልጥን፤ እራስህን በቀናው መንገድ ምራው፤ በምትፈልገው ልክ ከስሜቱ በላይ እንዲሆን የምትመኘውን ሰው በእውን ሁነው።
ውብ ጊዜ ይሁንልን! 🌅🌞💫✨
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
Telegram: t.me/MentalCounsel

በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ 😊 💪

መልካም የሥራ ጊዜ ብለናል።
30/03/2023

መልካም የሥራ ጊዜ ብለናል።

10/12/2022
17/11/2022
22/09/2022

Robert Lewandowski will show support for Ukraine at the 2022 World Cup 🇺🇦 🤝 🇵🇱

22/09/2022

ሽንፈት የተሸናፊነት ስሜት እንዲሰማህ ያደርግህ ይሆን? ......

❗️ ልብበል ሻምፒዮን መሆን ማለት ማሸነፍ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንስ ከሽንፈት መማር፣ እራስን ማሻሻል እና እንደገና መሞከር እንጂ።

🛠 በሕይወት ትግል፣ በኑሮ ሩጫ ውጣ ውረድ ውስጥ በጥረታችን ልክ አወንታዊ ውጤት መፈለጋችን ጤናማ እሳቤ ነው ። ነገር ግን ሁልጊዜ ይህ እሳቤ ትክክል ነው ብሎ መደምደም ያስቸግራል።

⛔️ በጥረታችን ልክ ተሰፍሮ ከሚሰጠን ስኬት በተፃራሪው እኛው በወጠናቸው ጅምሮች ተደናቅፈን የምንወድቅባቸው ጊዜያቶች አሉ።

👎 በዚህ ጊዜ ደግሞ፣ እራሳችንን ማመን እስኪሳነን ድረስ በውድቀት የቁልቁለት ጉዞ የኋልዮሽ እየተንደረደርን እንደሆነ ሊሰማን ይችላል።

✅ ነገር ግን በሚገባ ነገሮችን ካጤንን ስለሞከርን ብቻ አሸናፊ ለመሆን የሚያስችል ጠቃሚ ልምድ ማካበታችን በራሱ የአሸናፊነታችን ሌላው ገፅታ መሆኑን ልብ ልንለው ይገባል።

👉 ምክናያቱም ወድቆ መቅረት እንጂ መውደቅ መነሳቱ ሽንፈት አይደለምና።

👍 ጠንካራ ከሆንን እና ተስፋ ካልቆረጥን እየወደቅን እየተነሳን ደግሞ በጊዜ ሂደት ሻምፒዮን መሆናችን የማይቀር ይሆናል።
#ጥበብ እና #ማስተዋል ለሰው ልጅ በሙሉ!

-ሣሙኤል ተክለየሱስ
(ዓለም አቀፍ የህይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)
========================
©️ ሙዳዬ ንዋይ - የቢዝነስ ልህቀት

22/09/2022

አለቃ ወይስ መሪ?

መሪ ሁሉ አለቃ ነው፣ አለቃ ሁሉ ግን መሪ አይደለም! መሪ ባለው ቀደም ብሎ የመራመድ ሚና ፈርን የመቅደድ ሃላፊነቱ ስላለው አለቃም ነው ብንል አንሳሳትም፡፡ ሆኖም፣ በተለያዩ የስልጣን ምንጮች አለቃ የሆኑ ሁሉ መሪዎች ናቸው ለማለት አስቸጋሪ ነው፡፡

አለቃ፣ አለቃ ነው፤ በማስፈራት ይገዛል እንጂ አይመራም፡፡ መሪ አለቃ ነው ተብሎ ቢጠራም እንኳ በተለምዶ አለቆች የሚያሳዩትን ባህሪ አያንጸባርቅም፡፡ ስለዚህ መሪ የአለቅነቱ ዝንባሌ በጎላ ቁጥር የመሪነቱ መልክና ተጽእኖ እየደበዘዘና እየጠፋ ይሄዳል፡፡

ማንኛውም አለቃ መሪ ለመሆን በተከታዮቹ ወይም በሰራተኞቹ ላይ የአብሮ ሰራተኝነትን ስሜት ሊያሳድር ይገባዋል፡፡ “አለቃ ስለሆንኩኝ ብቻ ሊታዘዙኝና ሊያከብሩኝ ይገባል” ከሚል አመለካከት ወጥቶ በሚያስፈልጋቸው ሁኔታ ሁሉ ለመገኘት ራሱን በማቅረብ፣ ብቃቱን በማዳበርና በምሳሌነት በመምራት ተጽእኖን ማሳደር ይጠበቅበታል፡፡

ስለዚህም ሰዎች፣ መሪን በናፍቆትና በአክብሮት ሲታዘዙት፣ አለቃን ግን በፍርሃት ይታዘዙታል፡፡ የሚከተሉትን ንጽጽሮች እንመልከት፡፡

• አለቃ ሰዎችን በኃይል ይነዳል፤ መሪ ሰዎችን በመልካም ተጽእኖ ያነሳሳል፡፡
• አለቃ በስልጣኑ ላይ ይደገፋል፤ መሪ ባዳበረው ተቀባይነት ላይ ይደገፋል፡፡
• አለቃ ፍርሃትን ይለቅቃል፤ መሪ ፍቅርንና አክብሮትን ያስፋፋል፡፡
• አለቃ “እኔ” ማለት ያበዛል፤ መሪ “እኛ” ይላል፡፡
• አለቃ ስህተተኛው ማን እንደሆነ ያውጣጣል፤ መሪ ስህተቱን ፈልጎ ለማረም ይፈጥናል፡፡
• አለቃ ትኩረቱ ስራው መሰራቱ ላይ ብቻ ነው፤ መሪ ስራውን የሚሰሩት ሰዎች ላይም ትኩረቱን ይጥላል፡፡
• አለቃ ካላከበራችሁኝ ይላል፤ መሪ በሁኔታው መከበርን ያነሳሳል፡፡

የአለቃ አመለካከት
አለቅነት ተገቢና አስፈላጊ ጉዳይ የመሆኑን እውነት መዘንጋት የለብንም፡፡ ሆኖም፣ አለቅነት በተከታዮች ዘንድ ከተገኘ ተቀባይነት ሲመነጭ ትክክለኛና ጤናማ ተጽእኖ ያመጣል፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው አለቃ ከመሆኑ በፊት ተቀባይነት ያገኘ መሪ ወደ መሆን ማደግ አለበት፡፡ ስልጣንን ብቻ የሚጠቀም አለቅነት ወደ ጭፍን አገዛዝ ያመራልና፡፡

የተጽእኖ-ቢስ አለቃ አመለካከት ይህንን ይመስላል፡-
• ሰራተኛው ብዙ ጊዜ ሲወስድ ቀርፋፋ ነው፤ እኔ ብዙ ጊዜ ስወስድ ግን ጠንቃቃ ነኝ፡፡
• ሰራተኛው ሳይሰራ ሲቀር ሰንፎ ነው፤ እኔ ካልሰራሁ ግን ስራ በዝቶ ነው፡፡
• ሰራተኛው ከተሰጠው የስራ ድርሻ አልፎ ሲሰራ ቀልቃላ ነው፤ እኔ ስሰራ ግን የተነሳሳሁ ነኝ፡፡
• ሰራተኛው የራሱ መነሳሳትና አቋም ሲኖረው ሕገ-ወጥ ነው፤ እኔ ሲኖረኝ ግን አዲስ ነገር እየጀመርኩ ነው፡፡
• ሰራተኛው አለቃን ለማስደሰት ሲሞክር አሽቃባጭ ነው፤ እኔ አለቃዬን ለማስደሰት ስሞክር ግን ትብብርን እያሳየሁ ነው፡፡

“ያላቸውን ነገር ሁሉ እስካልወሰድክባቸው ድረስ በሰዎች ላይ ስልጣንን ልትለማመድ ትችላለህ፡፡ አንድን ሰው ያለውን ሁሉ ከወሰድክበት በኋላ ግን በስልጣንህ ስር አይቆይልህም” - Aleksandr Solzhnitsyn

በነገው ፖሰቴ ተጨማሪ የአመራር እውነታዎችን ይዤ እሰከምመለስ ይህንን በዚህ ጥያቄ ላይ ያላችሁን የግል ግንዛቤ ፖስት በማድረግ አጋሩን፡-

“አንዳንድ መሪዎች አጉል የበላይነትና ስልጣንን ካለአግባብ የመጠቀም ዝንባሌ የሚያዳብሩት ለምንድን ይመስላችኋል?”

(ራስንም ሆነ ሌሎችን በመምራት ለማደግ “አመራር A to Z” የተሰኘውን መጽሐፌን አንብቡት)

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

ለተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው !!
21/09/2022

ለተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው !!

16/09/2022

Address

180mi. Gesuba
Gesuba
320

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Offa media network OMN posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share


You may also like