Biqu Set ብቁ ሴት Empowered Woman Radio Program

Biqu Set ብቁ ሴት Empowered Woman Radio Program በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጾታዊ ጥቃቅን የሚጸየፍ እና ለሴቶች ከ?

27/10/2024

በኒዮርክ በተካሄደ ዓለም አቀፍ የሴቶች ስብሰባ ላይ ሶማሊያዊን በወንድ መወከላቸውን ተቃወሙ
በተመድ አዘጋጅነት በተካሄደው የሴቶች ጉባኤ ላይ ሶማሊያ በቤተሰብ እና ሰብዓዊ ሚኒስትሩ በጀነራል ባሽር መሀመድ ተወክላለች።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሴቶች ጉዳይ በኒዮርክ ከተማ የአባል ሀገራት ጉባኤውን አካሂዷል፡፡
57 ሀገራት በተሳተፉበት በዚህ ጉባኤ ላይ ከተሳተፉ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ነች፡፡
የሶማሊያ ቤተሰብ እና ሰብዓዊ መብት ሚኒስትሩ ጀነራል ባሽር መሀመድ ስለ ሴቶች በሚመክረው በዚህ ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ መሆናቸውን የሚያሳይ ምስል በኤክስ ወይም በቀድሞ ስሙ ትዊተር ገጽ ላይ ማጋራታቸውን ተከትሎ ጉዳዩ በመላው ሶማሊያ ትኩረት ስቧል፡፡
ሶማሊያዊያን በሴቶች ጉባኤ ላይ እንዴት በወንድ እንወከላለን ሲሉ ክስተቱን የተቹ ሲሆን ወትሮም ቢሆን የሶማሊያ መንግስት ለሴቶች ግድ የለውም ብለዋል፡፡
የሶማሊያ መንግስት ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ላይ የሴቶች ሚኒስቴርን በማፍረስ ወደ ቤተሰብ እና ሰብዓዊ መብት ሚኒስቴር ቀይሯል፡
ይህን ተከትሎ በርካታ ሶማሊያዊያን የአሁኑን ክስተት ካለፈው ጋር በማያያዝ መንግስታችን ሴቶች የሚለውን ቃል መጥራትም አይፈልግም ሲሉ ከሰዋል፡፡
የሀገሪቱ መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ እስካሁን ያለው ነገር ባይኖርም ሁለት ሴቶች ለዚሁ ጉባኤ ሲባል ወደ ኒዮርክ ከሄደው የሶማሊያ ልዑክ ጋር ማቅናቸውን የሚሳዩ ፎቶዎች ቀስ በቀስ መውጣት ጀምረዋል፡፡
በተመድ የሴቶች ጉባኤ ላይ ከ57 ሀገራት የተውጣቱ 197 ሰዎች እየተሳተፉ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 21 ወንዶች እንደሆኑ ተገልጿል፡፡

21/10/2024

#ፍትሕለኩሾቦናያ (የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር)
(Ethiopian Women lawyers’ Association (EWLA)

ማንኛውም ባህላዊም ሆነ ሀይማኖታዊ ስርዓት ተቀባይነት የሚኖረው የሰዎችን ሰብዓዊ መብት እንዲሁም በህግ የተደነገጉ መብቶቻቸውን እስካልጣሰ ድረስ ነው፡፡ ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ቦረና ዋጪሌ ወረዳ “የሽማግሌዎችን ትእዛዝ አላከበርሽም” በማለት ተጠቂን ከዛፍ ላይ በማሰር በባለቤቷ በአሰቃቂ ሁኔታ የግርፋት እና ድብደባ ወንጀል ተፈፅሞባት በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል በከፍተኛ ክትትል ላይ ለምትገኘው ኩሹ ቦናያ ፍትህ እንሻለን፡፡

ባህላዊ የሽምግልና ስርዓት ሰውን ከሰው የሚያቀራርብ፣ የሰውን ስነ ምግባር በመልካም የሚገራ፣ ማህበረሰብን ከማህበረሰብ የሚያስተሳስር እንዲሁም ክቡር የሆነውን የሰውን ህይወት፣ ሰብዓዊ መብትና የደህንነት ጥያቄ ሊያከብር የሚገባ እንጂ ወደበለጠ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል መሆን የለበትም፡፡ ባህላዊ የሽምግልናና የዳኝነት ስርዓት በሁለቱም ፆታዎች መካከል ፆታን መሰረት አድርጎ መድሎ እና መገለል ሳይደረግ እኩል የዳኝነት ሥራ ሊያከናውን የሚገባ እንጂ ሴቶችን ለጥቃት የሚዳርግና ህይወታቸውን ለአደጋ የሚያጋልጥ እንዲሁም ኢ-ፍትሃዊነት የሰፈነበት የዳኝነት ስርዓት ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም፡፡

በመሆኑም በኩሾ ቦያና ላይ የተፈፀመባት የወንጀል ድርጊት በህገ መንግስታችን ከአንቀፅ 14 እስከ 18 ድረስ ያለውን የተጠቂዋን የአካል ደህንነት መብት የጣሰ፣ የነፃነት መብቷን የነፈገ እንዲሁም በህገ መንግስቱ አንቀፅ 18 (1) መሰረት ማንኛውም ሰው ጭካኔ ከተሞላበት፣ ኢሰብዓዊ ከሆነ ወይም ክብሩን ከሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት የመጠበቅ መብት አለው፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር በኩሹ ቦናያ ላይ እንደዚህ አይነት አስከፊና ህይወቷን አደጋ ላይ የጣለ ወንጀል የፈፀመባት ባለቤቷ እና በወንጀሉ የተሳተፉት ሰዎች በሙሉ ለፍርድ እንዲቀርቡ እና ኩሹ ቦናያም ለተፈፀመባት ወንጀል አፋጣኝ ፍትህ እንድታገኝ ይጠይቃል፡፡

ወንጀል ሲፈፀም ቆሞ ማየትና ለሚመለከተው አካል ጥቆማ አለመስጠት ከወንጀል ተጠያቂነት አያድንም፡፡ በመሆኑም በዚህ ሁኔታ ማስረጃው የተገኘባቸው ግለሰቦች አስተማሪ ቅጣት እንዲሰጣቸው እንጠይቃለን፡፡ በተጨማሪም በባህላዊ ተፅእኖም ሆነ በማንኛውም ሁኔታ በሴቶች ላይ እንዲህ አይነት ወንጀል ሲፈፀም አይቶ እንዳላዩ መሆን በወንጀል ሊያስቀጣ የሚችል በመሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በሴቶች ላይ ጥቃት ሲፈፀም አይቶ ዝም ከማለት ይልቅ ለሚመለከተው አካል ጥቆማ እንዲያደርግ ጥሪ እያቀረብን የኩሹን ጉዳይ በኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፋችን በኩል የምንከታተለውና አስፈላጊውን ነጻ የህግ ድጋፍ የምናደርግ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

#በሴቶች ላይ ፆታን መሰረት አድርጎ የሚፈፀምን የወንጀል ድርጊት በጋራ እንከላከል!

#ፍትሕለኩሾቦናያ (የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር)
(Ethiopian Women lawyers’ Association (EWLA)

16/09/2024

ዛሬ የሕይወታችሁ የመጀመሪያው ቀን ቢሆን!

እንደምን አደራችሁ የሃገሬ ሰዎች፡፡

“ዛሬ የሕይወታችሁ የመጀመሪያው ቀን ነው!” ብትባሉ . . .

• ምን በማድረግ ቀኑን ትጀምራላችሁ?

• ምንስ በማቆም ቀናችሁን ትጀምራላችሁ?

• የትኛውን ነገር በመርሳትና ወደኋላ በመተው ሕይወታችሁን ትጀምራላችሁ?

• ከየትኛው መርዛማ ግንኙነት በመለየት ወደፊት ለመሄድ ውሳኔን ታስተላልፋላችሁ?

• ለወደፊቱስ ምን አይነት እቅድ ታወጣላችሁ?

• እስካሁን ተጨንቃችሁ ምንም ለውጥ ያላመጣችሁትን የትኛውን ጭንቀት ለመተው ትወስናላችሁ?

በሉ እንግዲያው፣ “ዛሬ ለተቀረው ዘመናችሁ የመጀመሪያው ቀን ነው”!

“Today Is The First Day Of The Rest Of Your Life” - Charles Dederich

መልካም የአዲስ ጅማሬ ቀን ይሁንላችሁ!
ዶ/ር እዮብ ማሞ

አልሃምዱሊላህ🙏ከቀን ወደ ቀን ወራትን አሻግሮንእነሆ አመት ቆጠርን🥰🥰የማያልፉ የሚመስሉ ቀናቶች ,የማይገፉ የሚመስሉ ጊዜያቶች አልፈዋል ሄደዋል,እድሜና ጤና ሰቶን ዛሬን ደርሰናል አልሃምዱሊላህ...
10/09/2024

አልሃምዱሊላህ🙏ከቀን ወደ ቀን
ወራትን አሻግሮን
እነሆ አመት ቆጠርን🥰🥰
የማያልፉ የሚመስሉ ቀናቶች ,የማይገፉ የሚመስሉ ጊዜያቶች አልፈዋል ሄደዋል,እድሜና ጤና ሰቶን ዛሬን ደርሰናል አልሃምዱሊላህ🙏
ብሩህ ተስፋን የሰነቀ🥰የሰላም🥰የፍቅር🥰የበረካ🥰የብልጽግና🥰የፍትህ🥰ዘመን ይሁንልን🥰🥰
🥰🥰🥰2017🥰🥰🥰

 #ፍትህ ለኛ ለህጻናት #ፍትህ ለኛ ለሴቶች #ፍትህ ለኛ ለሰው ልጆች
06/09/2024

#ፍትህ ለኛ ለህጻናት
#ፍትህ ለኛ ለሴቶች
#ፍትህ ለኛ ለሰው ልጆች

30/08/2024

አሜሪካ በአስገድዶ መድፈር ጥፋተኛ የተባለን ወንጀለኛ በመርዝ ገደለች!!!
አሜሪካ በአስገድዶ ደፋሪዎች ላይ ጥብቅ ቅጣት ከሚያስተላልፉ ሀገራት መካከል አንዷ ናት
አሜሪካ በአስገድዶ መድፈር ጥፋተኛ የተባለን ወንጀለኛ በመርዝ ገደለች፡፡
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ በአስገድዶ ደፋሪዎች ላይ ከባድ ቅጣት ከሚያስተላልፉ ሀገራት መካከል አንዷ ናት፡፡
ሎራን ኮል የተባለው አሜሪካዊ የ57 ዓመት እድሜ ያለው ሲሆን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሶ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
ይህ ወንጀለኛም የሞት ፍርድ የተላለፈበት ሲሆን በዛሬው ዕለት ታስሮ በነበረበት ፍሎሪዳ ማረሚያ ቤት ገዳይ መርዝ በመርፌ ከተወጋ በኋላ ህይወቱ ማለፉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ ግለሰቡ የገዛ እህቱን በመድፈር ወንጀል ከተመሰረተበት ክስ በተጨማሪም የፍሎሪዳ ዩንቨርሲቲ የሆነ የ18 ዓመት ወጣት ግድያም ተከሶ ጥፋተኛ ተብሏል፡፡
አሜሪካ የተያዘው 2024 ዓመት ከገባ ጊዜ ጀምሮ 13 ሰዎች ላይ የሞት ፍርድ የፈጸመች ሲሆን ይህም ሀገሪቱ የሞት ፍርድ በብዛት ከሚፈጸምባቸው የዓለማችን ሀገራት መካከል ከፍተኛዋ አድርጓታል፡፡
አሜሪካ ካሏት 30 ግዛቶች ውስጥ 23ቱ የሞት ፍርድን የሚፈጽሙ ሲሆን ቀሪዎቹ ሰባት ግዛቶች ደግሞ የሞት ፍርዶችን ወደ እድሜ ልክ እስር ይቀይራሉ፡፡
እንደ ዓለም አቀፉ የስነ ህዝብ ፖፑሌሽን ሪቪው ጥናት ከሆነ በዓለም ላይ ካሉ ጠቅላላ ሴቶች መካከል 35 በመቶ ያህሉ ለጾታዊ ጥቃት የተጋለጡ ናቸው፡፡
ይሁንና ጥቃቱን ከሚፈጽሙት ውስጥ 10 በመቶዎቹ ብቻ ህግ ፊት ቀርበው ውሳኔ ሲሰጣቸው ቀሪዎቹ በብዙ ምክንያቶች ተገቢውን ፍትህ አያገኙም፡፡
ከአሜሪካ በተጨማሪም ጥብቅ ህግ ያላቸው ሀገራት ሳውዲ አረቢያ፣ ቻይና፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ቸክ ሪፐብሊክ፣ ሰሜን ኮሪያ እና ፓኪስታን ዋነኞቹ ናቸው።

ኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባለን ወንጀለኛ በስቅላት ቀጣችAugust 21, 2024ወንጀለኛው በጥንቆላ ስራ የሚተዳደር ሲሆን ሴቶችን በማታለል ሲደፍር ነበር ተብሏልኢራን በአስ...
21/08/2024

ኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባለን ወንጀለኛ በስቅላት ቀጣች
August 21, 2024
ወንጀለኛው በጥንቆላ ስራ የሚተዳደር ሲሆን ሴቶችን በማታለል ሲደፍር ነበር ተብሏል
ኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባለን ወንጀለኛ በስቅላት ቀጣች፡፡
የመካከለኛው ምስራቅ ሀገር የሆነችው ኢራን በአስገድዶ መድፈር ትፋተኛ የተባለን ወንጀለኛ በስቅላት ገድላለች፡፡
የሀገሪቱ ብዙሃን መገናኛዎች እንደዘገቡት ከሆነ በማዕከላዊ ኢራን ካሉ ግዛቶች አንዱ በሆነው ዝድ ክልል አስገድዶ መድፈር መፈጸሙ በፍርድ ቤት ቅጣት ተጥሎበታል፡፡
ግለሰቡ በጥንቆላ ይተዳደራል የተባለ ሲሆን ለአገልግሎት የሚመጡ ሴቶችን በማታለል አስገድዶ ሲደፍር እንደነበር ተገልጿል፡፡
ከ12 በላይ የክስ መዝገቦች የተከፈቱበት ይህ ሰው አሱን ጨምሮ ከነ ረዳቱ ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተው በሞት ፍርድ እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡
ኢራን በሞስኮ ለእይታ ያቀረበችው ድሮን - “ሞሃጀር-10”
በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረትም ጥፋተኛ የተባሉት ሰዎች ታንቀው እንዲገደሉ መደረጉን አል አረቢያ ዘግቧል፡፡
ኢራን በአስገድዶ ደፈራ ወንጀል ጥፋተኛ በተባሉ ወንጀለኞች ላይ ከባድ ቅጣት ከሚጥሉ ሀገራት መካከል አንዷ ናት፡፡
በኢራን የሞት ፍርድ ያስቀጣሉ ከተባሉ ወንጀሎች መካከል አስገድዶ መድፈር እና ጾታዊ ጥቃቶች ዋነኞቹ ናቸው፡፡
ሀገሪቱ በየዓመቱ በርካታ ዜጎችን በሞት የምትቀጣ ሲሆን ይህም በመላው ዓለም የሞት ቅጣት ከሚተላለፍባቸው ዜጎች መካከል አብዛኛው በኢራን ይፈጸማል፡፡

ከፅላት ላይ ትፋት ?ታውቃለች እንዳይሏት የፊደላትን ዘር መለየት ያልቻለችለአበባነት ደርሣ ለታይታ ያልበቃችአንዲት ፍሬ ዘር ነች።ብርቱም ናት: እንዳይሏት ከንዷ ጭንቅላቷንመንተራሥ የማይችል: ...
19/08/2024

ከፅላት ላይ ትፋት ?

ታውቃለች እንዳይሏት
የፊደላትን ዘር መለየት ያልቻለች
ለአበባነት ደርሣ ለታይታ ያልበቃች
አንዲት ፍሬ ዘር ነች።
ብርቱም ናት: እንዳይሏት
ከንዷ ጭንቅላቷን
መንተራሥ የማይችል: ሔቨን ህጻን ልጅ ናት::
አልነበራትም አቅም
ትልቅ ሰው ተብየው ከመሬት ሲጥላት
የላትም ነበር ቃል
እንዲህ ያለውን ነውር
ተው እንጂ የማለት
አልነበራትም ድምጽ
አንዳች እንዲያሥጥላት
ጮኾ የመጣራት
ከማየት በሥተቀር
የአሳማውን ጠባይ የአሣማውን ድፍረት
እግሩን ገበታ ላይ
ሢያነሣው ለማርከስ: እንዳልተገኘበት
የላትም ነበር ኃይል
ከመቀበል በቀር የውሻውን ትፋት
ባልጠና ሰውነት በልጅነት ፅላት።

ኤፍሬም ስዩም ✍

19/08/2024

በአስገድዶ ደፋሪዎች ላይ ከስቅላት እስከ ብልት ማኮላሸት የሚደርስ እርምጃ የሚወስዱ የዓለማችን ሀገራት
አሜሪካንን ጨምሮ ስድስት የዓለማችን ሀገራት በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ወንጀለኞችን ብልት እንዲኮላሽ የሚፈቅድ ህግ አላቸው
በአስገድዶ ደፋሪዎች ላይ ከስቅላት እስከ ብልት ማኮላሸት የሚደርስ እርምጃ የሚወስዱ የዓለማችን ሀገራት
እንደ ዓለም አቀፉ የስነ ህዝብ ትናት ከሆነ በዓለም ላይ ካሉ ጠቅላላ ሴቶች መካከል 35 በመቶ ያህሉ ለጾታዊ ጥቃት የተጋለጡ ናቸው፡፡
ይሁንና ጥቃቱን ከሚፈጽሙት ውስጥ 10 በመቶዎቹ ብቻ ህግ ፊት ቀርበው ውሳኔ ሲሰጣቸው ቀሪዎቹ በብዙ ምክንያቶች ተገቢውን ፍትህ አያገኙም፡፡
የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በመላው ዓለም ያለ ክስተት ቢሆንም የተወሰኑ ሀገራት ወንጀሉን ፈጽመዋል በተባሉ ጥፋተኞች ላይ ከባድ ቅጣት እንዲጥሉ የሚፈቅድ ህግ አዘጋጅተዋል፡፡
በሕፃን ሔቨን ጉዳይ የተጀመረው የሚዲያ ዘመቻ እንዲቆም የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር ጠየቀ
በርካታ ዓለማችን ሀገራት የአስገድዶ መደፈር ወንጀልን ለመከላከል ወንጀለኛ መቅጫ ህጎችን ያዘጋጁ ቢሆንም የተወሰኑ ሀገራት ግን ጥፋተኞች ላይ ከባድ ቅጣትን በመጣል ይታወቃሉ፡፡
ለአብነትም ቻይና፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ግብጽ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ፓኪስታን የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በፈጸሙ ጥፋተኞች ላይ የወንድ ብልትን ከማምከን ጀምሮ በስቅላት እና በእሳት በማቃጠል እንዲገድሉ የሚፈቅድ ህግ አላቸው፡፡
አሜሪካ ካሏት ጠቅላላ ግዛቶች መካከል ሰባቱ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ወንጀለኞችን ብልት ማምከን የሚያስችል ህግ ያላቸው ሲሆን በዚሁ ወንጀል እድሜ ልክ የተፈረደባቸው ወንጀለኞች ቶሎ ከእስር መለቀቅ ከፈለጉ ብልታቸው እንዲመክን መፍቀድ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ሰሜን ኮሪያ በዚሁ ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ወንጀለኞችን በእሳት በማቃጠል ህይወታቸው እንዲያልፍ የምታደርግ ሲሆን ግብጽ አንቆ በመግደል እንዲሁም ሳውዲ አረቢያ ደግሞ አንገታቸውን በሰይፍ በመቅላት የሞት ፍርድ ትፈጽማለች፡፡
ፓኪስታን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ዩክሬን፣ ቸክ ሪፐብሊክ እና ሌሎችም ሀገራት ዜጎቻቸውን ከወንጀል ለመጠበቅ ጥፋተኛ በተባሉ ዜጎች ላይ ጥብቅ ህግ ካላቸው ሀገራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ምንጭ አል አይን ኒውስ

የአማራ ክልል ዳኞች ግን እናት,እህት, ሚስት,ልጅ የላቸውም???በየትኛው የሞራል ልዕልና ነው ግን የሚዲያ ዘመቻው እንዲቆም መግለጫ የሚሰጡት????የተሰጠው ፍርድ አግባብ አይደለም አዎ እንጮሀ...
19/08/2024

የአማራ ክልል ዳኞች ግን እናት,እህት, ሚስት,ልጅ የላቸውም???በየትኛው የሞራል ልዕልና ነው ግን የሚዲያ ዘመቻው እንዲቆም መግለጫ የሚሰጡት????የተሰጠው ፍርድ አግባብ አይደለም አዎ እንጮሀለን ፍትህ ፍትህ እንላለን😭😭እያንዳንህ ዳኛ በልጅህ ይድረስና ህመሙን ስቃዩን ቅመሰው ካልኩህ የእርግማን ሁሉ መጨረሻው ነውና ልቦና ይስጣችሁ

— ሞት ለአስገድዶ ደፋሪ —በ ምስሏ የተለጠፈችው ሴት ማሪያን ባክማየር (Marianne Bachmeier) ትባላለች። የሰባት ዓመት ሴት ልጅ ነበራት። ይህቺን ልጅ ክላውስ ግራቦውስኪ ( Klau...
18/08/2024

— ሞት ለአስገድዶ ደፋሪ —

በ ምስሏ የተለጠፈችው ሴት ማሪያን ባክማየር (Marianne Bachmeier) ትባላለች። የሰባት ዓመት ሴት ልጅ ነበራት። ይህቺን ልጅ ክላውስ ግራቦውስኪ ( Klaus Grabowski ) የተባለ ጎረቤቷ ይደፍራትና ይገድላታል። ግራቦውስኪ የለመደ ደፋሪ (s*x offender) ነው። ይህን ከማድረጉ አስቀድሞም ኹለት ሴቶችን በመድፈር ተጠርጥሮ በተዳከመ የፍትሕ ሥርዓት ምክንያት ተገቢውን ቅጣት ሳይቀበል ሊለቀቅ ችሏል። —ባይለቀቅ ምናልባት የባክማየርንም ልጅ ባልደፈረ ነበር።

ግራቦውስኪ ተይዞ ፍርድ ቤት ቀረበ። የፍርድ ሒደቱ በሚካሄድበት በሦስተኛው ቀን ግን ባክማየር በድብቅ ሽጉጥ ይዛ በመግባት ሰባት ጊዜ ግራቦውስኪ ወደተቀመጠበት አቅጣጫ አከታትላ ትተኩሳለች። (ነገሩን ፖየቲክ ሊያደርጉት ሲፈልጉ እያንዳንዱ ጥይት ለእያንዳንዱ የልጇ ዕድሜ ይላሉ።) ከተኮሰችው ውስጥ ስድስቱ ታላሚው ላይ አርፈው እዚያው ፀጥ አለ —የታባቱ። ባክማየርም ያለምንም ማንገራገር እጇን ሰጠች።

ፍርድ ሁሉ ፍትሕ አይደለም። የተበዳዮችን አንጀት የማያደርስ፣ ካቀረቀሩበት ቀና የማያደርግ፣ ዕምባ የማያብስ የፍትሕ ሥርዓት የወንጀለኛ ልብ ያላቸውን ግለሰቦች የልብ ልብ ይሰጣቸዋል። ቁርጠኝነት የሌለው፣ ልፍስፍስ የወንጀለኛ መቅጫ «ብታሠርም ጥቂት ዓመት ነው፤ ምን አላት?» የሚሉ አስገድዶ ደፋሪዎችን የሚያፈራ መደላድል ይሆናል። ከጊዜ ወደ ጊዜ እሥር ቤትን ቤታቸው ያደረጉ፣ መታሰር ብርቃቸው ያልሆኑ ዱርዬዎችና ባለጌዎች የሚፈጠሩት በዚህ ሒደት ነው።

በተለይም ራሳቸውን በምንም መንገድ መከላከል የማችሉ፣ ሕመማቸውን በቅጡ መናገር የማይችሉ ሕፃናትንም ኾነ ሴቶችን አሳድደው፣ አልመውና አቅደው ለዕድሜ ልክ ጾታዊ፣ አካላዊና ሥነ ልቡናዊ ቁስል የሚዳርጉ ሰዎች አንድ ተጨማሪ ቀን በምድር ላይ የሰላምን አየር ሊምጉ አይገባቸውም። ተበዳዮች በኀፍረትና በመሸማቀቅ አቀርቅረው፣ ወንጀለኞች በድፍረትና በልበ ሙሉነት ቀና ቀና የሚሉባት ሀገር ለማንም አትበጅም። ነገ በእያንዳንዳችን ቤት ባሉ ሕፃናትና ሴቶች በደሉ ይደርሳል። ስለዚህም እንደ ወንጀሉ አሰቃቂነት ሁሉ፣ የፍርድ ብይን ዜናውም ምሕረትን የማያውቅ፣ ለቀጣይ ወንጀል እየተዘጋጁና አድብተው ቀን እየጠበቁ ያሉ ነውረኛ ግለሰቦችን ጆሮ ጭው የሚያደርግ፣ ተስፋ የሚያስቆርጥ የሞት ፍርድ መሆን አለበት።

ሳታረጋግጡ የመንግስት ሰራተኛ ደሞዝ ተጨመረ ብላችሁ,የሸቀጥ ዋጋና ሌሎች ላይ ዋጋ የጨማመራችሁ,የቤት ኪራይ የጨመራችሁ አከራዮች እና ሌሎችም አደብ ግዙዙዙዙዙ ጉድ ሆነናል🤔🤔እናፌ ግን ጠቅላይ...
09/08/2024

ሳታረጋግጡ የመንግስት ሰራተኛ ደሞዝ ተጨመረ ብላችሁ,የሸቀጥ ዋጋና ሌሎች ላይ ዋጋ የጨማመራችሁ,የቤት ኪራይ የጨመራችሁ አከራዮች እና ሌሎችም አደብ ግዙዙዙዙዙ ጉድ ሆነናል🤔🤔እናፌ ግን ጠቅላይ ሚኒስተራችን ሲናገሩ ጆሮዬ ላይ ሽውውውውው ያለ መስሎኛል🤔ምንድነው ነገሩ ታዲያ ለምኖ ዶላር አይቀንስልንም🤔

መኩሪያ ሃይሌ (ዶ/ር) የሲቪል ሰርቫንት ደመወዝ ማሻሻያ በሚል የተሰራጨው መረጃ ሃሰተኛ መሆኑን አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲቪል ሰርቫንት ደመወዝ ማሻሻያ በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች የተሰራጨው መረጃ ሃሰተኛና ምንም ዓይነት የመነሻ መሰረት የሌለው መሆኑን የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር መኩሪያ ሃይሌ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡

መኩሪያ ሃይሌ (ዶ/ር) ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት ÷የመንግስት ሰራተኞችን የደመወዝ ስኬል በተመለከተ በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተናፈሱ የሚገኙ መረጃዎች ሃሰተኛ ናቸው፡፡

ማንኛውም ማሻሻያ ወይም የደመወዝ ስኬል ለውጥ ካለ ሕጋዊ ሰውነት ባላቸው እና በሚመለከታቸው አካላት ይፋ እንደሚደረግ አስገንዝበዋል፡፡

ውሳኔዎቹ ሲኖሩም በዝርዝር ጥናቶች እና የበጀት አጸዳደቅ ሥርዓትን ተከትለው የሚካሄዱ መሆኑን ማጤን ጠቃሚ ነው ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ታማኝ እና ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት ሁልጊዜም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ማጣራት እና ማገናዘብ ከስህተት እንደሚታደግም አንስተዋል፡፡

በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚሰራጩ መረጃዎች አንዳንድ ጊዜ እውነታዎችን ሊያዛቡ ይችላሉ ያሉት ኮሚሽነሩ ÷ ይህም ግራ መጋባትን ከማስከተሉ ባለፈ ያልተፈለገ እንድምታ ሊያስከትል ይችላል ብለዋል።

በአሁኑ ጊዜ እየተናፈሱ የሚገኙት አሉባልታዎች እውነተኛ የመረጃ መሠረት እንደሌላቸው ገልጸው ÷ መሰል የሚሊየኖችን ሕይወት የሚነካ ሃሰተኛ መረጃ ማሰራጨት ተገቢነት እንደሌለውም ጠቅሰዋል።

ምንጭ- ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬት

የዲኮሯን ባለሙያ ሊና ወለይኔ እና የኬኩን ማኪ ካፌ ግን አንደኛ ናችሁ👍👍👍ተመራቂዋ ደግሞ ድምቀት አብሪ ኮኮብ ናትየኔ ውድ እህት ዛሬ በከፍተኛ ማእረግ አስመርቀናታል💃💃😍😍የኔ ፍልቅ ልቅ ታና...
02/07/2024

የዲኮሯን ባለሙያ ሊና ወለይኔ እና የኬኩን ማኪ ካፌ ግን አንደኛ ናችሁ👍👍👍ተመራቂዋ ደግሞ ድምቀት አብሪ ኮኮብ ናት
የኔ ውድ እህት ዛሬ በከፍተኛ ማእረግ አስመርቀናታል💃💃😍😍የኔ ፍልቅ ልቅ ታናሼም ጓደኛዬም አማካሪዬም ደራሼም የኔ ሁሉ ነገር አልሃምዱሊላህ አላህ እንኳን ለዛሬዋ ቀን አበቃን🙏

ከዜሮ ድክድክ ከነርሰሪ ምርቃትከ8 ሚኒስትሪከማትሪክ እንቅፋትከ12ቱ ምጥ ከፍሬሽማን ማዕበልአራቱን አመት ውጦ አላምጦ ሰልቅጦከመጣው ኤግዚትያ የዘመናት የልፋት ድካም ውጤትበደስታ እንባ ታጅቦ ...
02/07/2024

ከዜሮ ድክድክ ከነርሰሪ ምርቃት
ከ8 ሚኒስትሪ
ከማትሪክ እንቅፋት
ከ12ቱ ምጥ
ከፍሬሽማን ማዕበል
አራቱን አመት ውጦ
አላምጦ ሰልቅጦ
ከመጣው ኤግዚት
ያ የዘመናት የልፋት ድካም ውጤት
በደስታ እንባ ታጅቦ
ጥቁሩን ደርቦ ጋውን
እንኳን ደስ አለሽ እንኳን ደስ አላችሁ
መባሉ እንዲህ ቀላል መሰላችሁ?
የናት ያባት ጭንቀት
ድካም ተስፋ ልፋት
አይደለም የአንድ ጀንበር
ለመውጣት ከባርነት ቀንበር
ድንቁርናን ሽሽት ለመድረስ ከእውቀት በር
ይኸው አዲስ ምዕራፍ አንድ ከፍታ
ተስፋ ይቻላል የሞላበት ደስታ
ተማረች ተማረች ተማረች
ይኸው ዛሬ ተመረቀች
ተሽቀረቀረች ተዋበች አበራች
የአብዲ ሙሜ ልጅ አኑ

 #ድሬዳዋ የድሬደዋ አስተዳደር ካቢኔ ትላንት ባካሄደው መደበኛ ስብስባ ከዚህ ቀደም የአየር ንብረቱ ሞቃታማ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ተሻሽሎ የነበረው የመንግስት ተቋማት የመግቢያና የመውጫ ሰዓት ...
28/06/2024

#ድሬዳዋ

የድሬደዋ አስተዳደር ካቢኔ ትላንት ባካሄደው መደበኛ ስብስባ ከዚህ ቀደም የአየር ንብረቱ ሞቃታማ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ተሻሽሎ የነበረው የመንግስት ተቋማት የመግቢያና የመውጫ ሰዓት የአየር ንብረቱ በመስተካከሉ ወደ ነበረበት እንዲመለስ ውሳኔ አስተላልፏል።

በዚህም መሰረት ከሰኞ 24/10/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ነበረበት ማለትም ጠዋት 1 ሰዓት ከ30 የመውጫ ሰአት ከቀኑ 6:00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ የመግቢያ ሰዓት 8:00ሰዓት መውጫ ሰዓት 11 ሰዓት ከ30 የሰዓት እንዲመለስ ውሳኔ ተላልፏል።
ምንጭ ቲክቫህ

31/05/2024

ጠብቅ !

አንዳንዴ ከጓደኞችህ ወይ በዙሪያህ ካሉ ሁሉ ኋላ መቅረትህን አትጥላው፤ ምክንያቱም ረጅም ርቀት ለመወርወር ወደ ኋላ በደምብ መንደርደር ወሳኝ ነው።

እየታሸህ ያለኸው በደምብ እንድትበስል ነው፤ እድል ጓዟን ጠቅልላ እጅህ እስክትገባ ጥረትህን እንዳታቆም! የዚህ አለም እድለኞች አብዝተው የሚለፉ እንጂ አብዝተው የሚመኙ አይደሉም።

መልካም ቀን ይሁንላችሁ

Turtii IbsaDamiina TV Dirreeti
25/05/2024

Turtii IbsaDamiina TV Dirreeti

16/05/2024

ክብርት ፕሬዝዳንት ሆይ 50% የጨዋታ ህጉ ለምን ፈረሰ?በዚህ ደረጃ የበቁ ሴቶች የሉንምን?ወንዶች መሾማቸው አልከፋንም ግን ጾቴን የሴቶች ተሳትፎን ያላማከለ ሹመት ነው።ክብርት ሆይ በርሶ ዘመን ይህ መሆኑ የታሪክ ተወቃሽ ያደርግዎታልና ሹመቱን ድጋሚ ያጢኑት።

ከተሾሙት 14 አምባሳደሮች ሴቶች ሁለት ብቻ ናቸው። የአቶዎች ሀገር ኢትዮጵያ እንደምን ነሽ????

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ለተለያዩ አምባሳደሮች ሹመት ሰጡ

1. አምባሳደር ፍስሐ ሻውል ገብሬ

2. አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን ወልደየስ

3. አምባሳደር ለገሰ ገረመው ሃይሌ

4. አምባሳደር ደሊል ከድር ቡሽራ

5. አቶ እስክንድር ይርጋ አስፋው

6. አቶ ልዑልሰገድ ታደሰ አበበ

7. ወይዘሮ ናርዶስ አያሌው በላይ

8. አቶ ብሩክ መኮንን ደምሴ

9. አቶ ቴዎድሮስ ግርማ አበበ

10. አቶ መኩሪያ ጌታቸው ወርቁ ን በባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደርነት

እንዲሁም፦

1 . አቶ በትረ መንግስቱ ብርሃኑ

2 . አቶ ዮሃንስ ፈንታ ወልደጊዮርጊስ

3. አቶ ኃይለሥላሴ ሱባ ገብሩ

4 . አቶ ንጉስ ከበደ ካሳው

5. አቶ ዘሪሁን አበበ ይግዛው

6. አቶ ተሾመ ሹንዴ ሀሚጦ

7 . አቶ ሌሊሳ ብርሃኑ ገለታ

8 . አቶ ደረጀ በየነ ደምሴ

9 . አቶ ሰብስቤ ባዴ አድባብ

10 . አቶ ነብዩ ተድላ ነጋሽ

11 . አቶ አንተነህ አለሙ ሰንበቴ

12 . ወይዘሪት ለምለም ፍስሃ ምናለ

13 . አቶ አንዋር ሙክታር መሀመድ

14 . አቶ አብርሃም መንግስቱ ገመቹ ን በአምባሳደርነት የሾሙ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Address

Dire Dawa
Dire Dawa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Biqu Set ብቁ ሴት Empowered Woman Radio Program posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category


Other Radio Stations in Dire Dawa

Show All