Abenezere Christian News and Education Page

  • Home
  • Abenezere Christian News and Education Page

Abenezere Christian News and Education Page ለትርፍ ያልተቋቋመ Page

08/03/2021
03/03/2021

የእግዚአብሔርን የድነት (ደኅንነት) ስጦታ የምንቀበለው በሥራ ሳይሆን ክርስቶስ ለእኛ በመሞቱ ነው (ሮሜ 3፡27-31)። የእግዚአብሔርን የድነት (ደኅንነት) ስጦታ ለማግኘት በፍጹም መደገፍ ላይ የተመሠረተ እምነት ያስፈልጋል። እንደ ድነት (ደኅንነት) ተስፋችን ሆኖ ኢየሱስ በምትካችን መሞቱን ስናምን «አላጠፋህም» የሚለውን የእግዚአብሔር አዋጅ መቀበል እንችላለን። ይህም ሕግ ላላቸው አይሁዶችም ሆነ ሕግ ለሌላቸው አሕዛብ ሁሉ የሚሠራ ነው። የድነትን (ደኅንነትን) መንገድ ያዘጋጀው እግዚአብሔር በመሆኑ፥ ማንም ከእግዚአብሔር ጋር ትክክለኛ ግንኙነት ለመመሥረት ባከናወነው ተግባር በእግዚአብሔር ፊትም ሆነ በሌሎች ዘንድ ሊመካ አይችልም።

03/03/2021

ሰላም ለእናንተ ይሁን ።
ወንድማችሁ አቤነዜር ነኝ እስክ የፈለጋችሁትን የመፅሐፍ ቅዱስ ጥያቄ ጠይቁ ለመለስ ዝግጁ ነኝ

01/03/2021

ሰላም ለእናንተ ይሁን

27/02/2021

ዝነኛ ለመሆን ሳይሆን ነፍሳትን ከዘለዓለም ሞት ለማትረፍ እግዚአብሔርን እናገለግል

20/02/2021

በብዙ ሰዎች ጭንቅላት ውስጥ ሰይጣን ነው የምኖረው

መልስ እና ጥያቄ ውድድር ዛሬ ይጀመራልይጠብቁን
07/02/2021

መልስ እና ጥያቄ ውድድር ዛሬ ይጀመራል
ይጠብቁን

02/02/2021

#ማሳሰቢያ

መልእክት

ውድ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ቤተሰቦች
በርካታ አገልጋዮች እና መሪዎች ወደ ካውንስሉ ጽ/ቤት በአካል በመምጣትና ስልክ በመደወል ለአገልጋዮች የመኖሪያ ቤት በማህበር ለማሰራት ገንዘብ እየተሰበሰበ እንዳለ እና እውነት ስለመሆኑ መጠየቃችሁ ይታወቃል።

ሆኖም ካውንስሉ እየሰበሰበ ያለው ምንም አይነት ገንዘብ አለመኖሩን እና በካውንስሉ ስም እየተሰበሰበ ካለም ከጽ/ቤቱ እውቅና ውጪ መሆኑን እየገለጽን ካውንስሉን የማይመለከት መሆኑን እናሳውቃለን።

ለበለጠ መረጃ በማንኛውም የስራ ሰዓት ወደ ካውንስሉ ጽ/ቤት በመደወለም ይሁን በአካል በመገኘት ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ስል መልእክቱን አስተላልፏል

@የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል።

    በመላው አለም የምትገኙ የወንጌል አማኞች በሙሉ ሁላችንም እንደምናውቀው በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በነበረው ጦርነት የትግራይ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ልዩ አጥቢያዎች ኅብረት ውስጥ የ...
01/02/2021




በመላው አለም የምትገኙ የወንጌል አማኞች በሙሉ ሁላችንም እንደምናውቀው በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በነበረው ጦርነት የትግራይ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ልዩ አጥቢያዎች ኅብረት ውስጥ የሚገኙ 28 ያህል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ለከፋ ችግር ተዳርገዋል፡፡

በእነዚሁ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት የሚያገለግሉ 44 የሚደርሱ የወንጌል አገልጋዮች እና ምዕመናንም በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ወድቀዋል፡፡

የደረሱትን ችግሮ ለመግለጽ ያህልም፡
- የመቀሌ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን እና የኅብረቱ ጽሕፈት ቤት ሙሉ ለሙሉ (ኮምፒውተር፣ ላፕቶፕ፣ የቢሮ ጠረጴዛዎችና ወንበሮች፣ የአምልኮ ወንበሮች፣ … ) ተዘርፈዋል፡፡

- የአክሱም እና የአዲግራት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናትም በከፊል ተዘርፈዋል፡፡

- ካሉት 44 አገልጋዮች 8 ያህሉ ከኮሮና ወረርሺኝ መከሰት ወቅት ጀምሮ ድጋፍ የተቋረጠባቸው ሲሆን የተቀሩት ደግሞ በባንኮች መዘጋት፣ በአካባቢው ባለው ዘረፋ፣ እጅግ ያሻቀበ የኑሮ ውድነት፣ ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ የወቅታዊ ሁኔታዎች አመቺ አለመሆን የተነሳ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ለከፋ ችግር ተዳርገዋል፡፡

ስለሆነም ሁላችንም የወንጌል አማኞች የሆንን ለእነዚሁ ወገኖቻችን አጥብቀን እንድንጸልይ እና የምንችለውን ድጋፍም እንድናደርግላቸው እንጠይቃለን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ የኅብረቱ የባንክ ቁጥሮች
1000152464918 E/K/B T/LU/B/M Office (ብርሃን ባንክ )
1000290295185 E/K/T/L/A/B/T/B (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)

25/01/2021

ሰላም ለኢትዮጵያ ለአገራችን ይሁን

17/12/2020

እግዚአብሔር ይመስገን ሰላም ነን።

24/11/2020

ከሁሉ በፊት ማስተዋል ይኑረን

19/11/2020

1 ተሰሎንቄ 5:1
1፤ ፥ ስለ ዘመናትና ስለ ወራት ምንም እንዲጻፍላችሁ አያስፈልጋችሁም፤
2፤ የጌታ ቀን፥ ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ፥ እንዲሁ ይመጣ ዘንድ ራሳችሁ አጥብቃችሁ አውቃችኋልና።
3፤ ነው ሲሉ ያን ጊዜ ምጥ እርጕዝን እንደሚይዛት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል ከቶም አያመልጡም።
4፤ እናንተ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ቀኑ እንደ ሌባ ይደርስባችሁ ዘንድ በጨለማ አይደላችሁም፥
5፤ ሁላችሁ የብርሃን ልጆች የቀንም ልጆች ናችሁና። እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ አይደለንም፤
6፤ እንግዲያስ እንንቃ በመጠንም እንኑር እንጂ እንደ ሌሎች አናንቀላፋ።
7፤ የሚያንቀላፉ በሌሊት ያንቀላፋሉና፥ የሚሰክሩም በሌሊት ይሰክራሉና፤
8፤ እኛ ግን ከቀን ስለ ሆንን፥ የእምነትንና የፍቅርን ጥሩር የመዳንንም ተስፋ እንደ ራስ ቁር እየለበስን በመጠን እንኑር፤
9፤ እግዚአብሔር ለቍጣ አልመረጠንምና፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መዳንን ለማግኘት ነው እንጂ።
10፤ የምንነቃም ብንሆን፥ የምናንቀላፋም ብንሆን፥ ከእርሱ ጋር አብረን በሕይወት እንኖር ዘንድ ስለ እኛ ሞተ።
11፤ ስለዚህ እናንተ ደግሞ እንደምታደርጉ፥ እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ አንዱም አንዱም ሌላውን ያንጸው።

19/11/2020

የክርስቶስ ስም ከስሞች ሁሉ የበላይ ስም ነው።
ስሙ ሀይል አለው

19/11/2020

ይህ ፔጅ ዘወትር የክርስቲያን ትምህርትና ዜና የሚቀርብበት ነው Pageን ላይክ አድርጋችሁ ቤተሰብ ይሁኑ።

10/11/2020

መስበክ

የዕለቱ ዜናዎች🇪🇹🙏 ለሀገሬ 🙏🇪🇹ወቅታዊውን የሃገራችን ሁኔታ በማስመልከት ግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ ከ ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ እና ዛብሎን የፀሎት አገልግሎት እንዲሁም ሌሎች አጋር ድ...
08/11/2020

የዕለቱ ዜናዎች
🇪🇹🙏 ለሀገሬ 🙏🇪🇹

ወቅታዊውን የሃገራችን ሁኔታ በማስመልከት ግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ ከ ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ እና ዛብሎን የፀሎት አገልግሎት እንዲሁም ሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር “ለሃገሬ ” በሚል ርዕስ ከጥቅምት 28 - ሕዳር 6
ለ9 ቀናት የሚቆይ የፀሎት እና የ ምልጃ ፕሮግራም አዘጋጅቶእል ።
በዚህም በኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያም ውጭ የምትኖሩ ክርስቲያኖች በሙሉ በአንድ ሃሳብ እና ልብ ወደ እግዚአብሄር በመቅረብ እግዚእብሄር በምድራችን ጣልቃ እንዲገባ ለህዝባችንም ሰላምን እንዲያወርድ አብረን እንድንጸልይ እንጋብዛችኋለን!!

Christian new የዘገበው

እግዚአብሔር ሆይ አገራችን ሰላም አድርግልን😭😭😭😭😭😭😭😭
05/11/2020

እግዚአብሔር ሆይ አገራችን ሰላም አድርግልን😭😭😭😭😭😭😭😭

  #አንተስ? #አንችስ?
05/11/2020



#አንተስ?

#አንችስ?

 ውድ የሀገረ ሕዝብውድ ከአገር ወጭ በአለም ዙሪያ ለምትገኙባልታሰበ ሁኔታ አገራችን ያጋጠማትን አለመረጋጋት በጣም አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ ስለ መሆናችን እያየን ወደ አመላካች በመፀለይ ለአገራችን...
05/11/2020



ውድ የሀገረ ሕዝብ
ውድ ከአገር ወጭ በአለም ዙሪያ ለምትገኙ
ባልታሰበ ሁኔታ አገራችን ያጋጠማትን አለመረጋጋት በጣም አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ ስለ መሆናችን እያየን ወደ አመላካች በመፀለይ ለአገራችን ሰላም እንድንሆን በጣም መጠንከር የግዴታ ግዴታ መሆኑን ማወቅ ግድ ይለናል
ሰላም ለአገራችን ለኢትዮጵያ ይሁን

27/08/2020

ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና።❞
—ሮሜ 13: 11

ብዙ ጊዜ እኛ ሰዎች ስለ አንድ ነገር ትንሽ መረዳት ሲኖረን ለሰዎች ስናወራ "ይኼን ነገር አውቃለሁ" እንላለን ......

በእርግጥ አንድን ነገር ለማወቅ ስለዚያ ነገር በቂ እውቀት፡ መረዳት ሊኖረን ይገባል.......ሐዋርያው ጳውሎስ ብሎ በዚያን ጊዜ ለነበሩ ለሮሜ ሰዎች መልእክቱን ፃፈ.....ዘመኑንስ እንዲያውቁ ፡ ዘመኑን እንዲረዱት ስለምንስ ፈለገ?

በአዲስ ኪዳን " " ከሚል ከትዕዛዝ/መልእክት በስተጀርባ አንድ ትልቅ ምስጢር አለ.............ምስጥሩ አንድ ዘመን እንደሚመጣ ብዙዎች የዘመኑን ምልክት ስለማይረዱ ፡ የልቦናቸው አይኖች ስለማያዩ ፍጻሜያቸው ጥፋት ይሆናል፡ ስለዚህ የዘመኑን ምስጢር ማወቅ ለተገባን ለእኛ ዘመኑን እወቁ የሚል መልእክት መነገሩ ዘመኑን አውቀን ምልክቶችን እያየን ለመጠባበቅ እንዲሆነን የማንቂያ ደወል ስለሚሆነን ልባችንን አስፍተን መቀበል ይኖርብናል ፡፡

❀ {ዘመኑ ምን ይባላል? የዘመኑስ ምልክቶች ምንድር ናቸው?}

☞ዘመኑ የመጨረሻው ዘመን ይባላል.....ይኼን ዘመን ክርስቶስ ኢየሱስ ከኖኅ ዘመን ጋር አመሳስሎታል፡ በዚያች ወራት ከጥፋት ውኃ በፊት፥ ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደ ነበሩ፡ ❝የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል፡ በኖኅ ዘመን.... ኖኀ መርከብ እየቀጠቀጠ ሰዎች ከጥፋት እንዲመለሱ ሲጮኽ እንደነበር የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ እንዳልታዘዙ ሀሳባቸው ሁሉ መብላት፡ መጠጣት፡ መጋባት ስለ ምድራዊ ኑሮ ብቻ ሆኖ ሳለ የጥፋት ውሃ እንደመጣ ሁሉንም እንዳጠፋ.....የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናል ዘመኑ የመጨረሻ ዘመን እንደሆነ ብዙዎች ሳይረዱት ድንገት መምጫው ይሆናል፡፡

☞ ኢየሱስ ስለ መጨረሻው ዘመን በደቀ-መዛሙርት ተጠይቆ ስለ ዘመኑ ምልክቶች ያለውን እንመልከት

✉☞ ሀሰተኛ ክርስቶሶች በየቦታው ይነሣሉ፡ ብዙዎችን ያስታሉ፡
✉☞ ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰማላችሁ ....ልብ እንበል በዚህ ዘመን በየሚዲያው የሚዘከረው የጦር ወሬ ሆኑዋል
✉☞ ህዝብ በህዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና .....ልብ እንበል በአለማችን እንዲሁም በሀገራችን በዚህ ዘመን በብሄርተኝነት ጠንቅ በሽታ ህዝብ ከህዝብ ጋር ጦርነት ሲገጥም፡ ሀገራት ከሀገራት ጋር ጦርነት ሲገጥሙ እየተመለከትን እየሰማን ነን፡፡
✉☞ ራብና ቸነፈር .....በዘመናችን በሶርያ ምድር፡ በተለያዩ አፍሪካ ሀገራት ፡በተለያዩ የደቡብ አሜሪካ ሀገራት በሁሉም ክፍለ አለማት.....በብዙ የምድር መናወጥ፡ በጎርፍ፡ በምድር መንቀጥቀጥ፡ በአለም ሙቀት መጨመር፡ በአውሎ ንፋስ እና ወዘተ....ምድር እየተናወጠች ናት.....ዛሬ በምድራችን ተርበው ፡ መጠልያ አጥተው ፡ ከቀያቸው ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያ የተጠለሉ፡ በርሀብ በጥማት ምክንያት ሸሽተው የሚሰደዱ ቁጥራቸው በሚሊዮን ነው፡፡
✉☞ ብዙዎች ፍቅር ያጣሉ፡ በዓመፃ ብዛት የብዙዎች ፍቅር ይቀዘቅዛል.......አለማችን ከምን ጊዜውም በላይ ፍቅር በማጣት ምክንያት በግፍ ብዙዎች ሞተዋል፡ ተሰደዋል፡ ተጎድተዋል.....
✉☞ ብዙ ሐሰተኛ ነብያት ይነሣሉ፡ ብዙዎችንም ያስታሉ......የእነዚህን ሀሰተኛ ነብያት ቁጥር ለማወቅ ያዳግታል፡፡ In millions ቢሆኑ ነው፡፡
ሀሰተኛ ነብያት የሚባሉት እግዚአብሔር የማያውቃቸው ፡ ያልጠራቸው ነገር ግን በሽንገላ ንግግራቸው ብዙዎችን ከእግዚአብሔር መንግሥት የሚያርቁ ናቸው፡፡

✉☞ ለአህዛብ ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በአለም ሁሉ ይሰበካል ......በዚያን ጊዜ መጨረሻ ይሆናል......እርግጥ ነው በዚህች ምድር ስልጣን ያላት ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ሙሽራ የተቀበለችውን ይኼን የእውነት ወንጌል ከምን ጊዜውም በላይ ለአለም እየሰበከች ትገኛለች፡፡

እኛ ክርስቲያኖች ዘመኑን ጠንቅቀን እንድናውቅ የልቦናችን አይኖች የበሩልን እነዚህን የምጥ ዳር ምልክቶችን ስናያቸው ተዘጋጅተን መጠባበቅ እንዳለብን መልእክቴን ለእናንተ እተዋለሁ፡ እንደነዛ አምስቱ ጎበዛዚቶች ተዘጋጅተን እንኑር ጊዜው የእንቅልፍ ፡ የስንፍና ሰዓት አይደለም፡፡

ሀዋርያው ጳውሎስ ስለመጨረሻው ዘመን በመልእክቱ ያለውን እንመልከት

2ኛ ጢሞቴዎስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
❝¹ ነገር ግን በመጨረሻው ቀን እንዲመጣ ይህን እወቅ።
² ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥
³ ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥
⁴ ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤
⁵ የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ፡፡

በሩጫ ውድድር ደወል ሲደወል የመጨረሻው ዙር ከመጀመርያዎች እጅግ ይከራል ፡ በዛ ውስጥ አሸናፊዎች ለማሸነፍ የሞት ትንቅንቅ ያደርጋሉ.........................
ያለንበት ዘመን የሚያስጨንቅ ስለሆነ እነዚህን ሁሉ ባየን ጊዜ ልብ እንበል ............ጊዜው የመዘጋጀት ፡ የመነቃቃት፡ የጎደለብንን ነገሮች ፈትሸን ሞልተናቸው፡ ታጥቀን ፡ በአይናችን ልናየው የናፈቅነውን ኢየሱስን የምንጠብቅበት ጊዜ ነው፡፡

እርሀብ ቸነፈር እርዛት ጥማቱ
እጅጉን አይሎ ሁከት ጦርነቱ
ምድር ስትናወጥ ሠላሙዋ ሲናጋ
የክፋት አሠራር በርትቶ ሲዋጋ

ተው ልቤ ልብ በል ዘመኑን ጠንቅቀ እወቅ

ያለሁበት ዘመን ሆኑዋል የሰቆቃ
ዘመኔን ልዋጀው ሁሉ እስኪያበቃ
እኔስ ልለምንህ ልብህ እንዲራራ
ወድቄ እንዳልገኝ ከተጣሉት ጎራ
...♥♥.........♥♥.........♥♥.......♥♥...

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abenezere Christian News and Education Page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share