DU FM89.0

DU FM89.0 We strive to Disseminate Holistic Knowledge

በሀዋሳ ከተማ በማርበርግ ቫይረስ የተያዘ አንድ ሰው ተገኘ++++++++++++++++++   | በሀዋሳ ከተማ አንድ ግለሰብ በማርበርግ ቫይረስ መያዙ መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።የጤና ...
27/11/2025

በሀዋሳ ከተማ በማርበርግ ቫይረስ የተያዘ አንድ ሰው ተገኘ
++++++++++++++++++

| በሀዋሳ ከተማ አንድ ግለሰብ በማርበርግ ቫይረስ መያዙ መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የጤና ሚኒስቴር የማርበርግ ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታን በሚመለከት ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥቷል።

የጤና ሚኒስትር መቅደስ ዳባ (ዶ/ር) ትናንት በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ ቫይረሱ ባልተገኘባቸው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ቫይረሱ ቢከሰት ህክምና መስጠት የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በትኩረት እየተሰሩ ይገኛል።

ከዚህ አንጻር ከመጀመሪያዎቹ ታማሚዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው እና ከቦታ ቦታ እንቅስቃሴ የነበራቸውን ሰዎችን በመለዬት ክትትል እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም ከጂንካ ከተማ ተመላሽ የነበረ አንድ ግለሰብ በሀዋሳ ከተማ ውስጥ በማርበርግ ቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል ነው ያሉት።

አሁንም ከዚህ ግለሰብ ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎችን የመለየት፣ ህክምና የመስጠት እና መሰል ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አስታውቀዋል።

የበሽታውን ምልክት የሚያሳዩ ሰዎች ሲገኙ በፍጥነት ለጤና ተቋም ማሳወቅ እና ምርመራ ማድረግ ይጠበቃል ያሉት ሚኒስተሯ፤ ህብረተሰቡ የመከላከያ ዘዴዎችን በመጠቀም ራሱን እንዲጠብቅ አሳስበዋል።

ኢትዮጵያ ኬንያን በማሸነፍ ምድቡን በበላይነት አጠናቀቀችከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የሴካፋ ዞን ውድድር የምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ ኬንያን 1 ለ 0 አሸንፋለች፡፡10 ሰዓ...
26/11/2025

ኢትዮጵያ ኬንያን በማሸነፍ ምድቡን በበላይነት አጠናቀቀች

ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የሴካፋ ዞን ውድድር የምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ ኬንያን 1 ለ 0 አሸንፋለች፡፡

10 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ዳዊት ካሳው ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ አስቆጥሯል፡፡ የውድድሩ ክስተት የሆነው ዳዊት ካሳው 7ኛ ግቡን አስቆጥሯል፡፡

ወጣቱ አጥቂ በአራቱም የምድብ ጨዋታዎች ላይ ግብ አስቆጥሯል፡፡

ምድብ አንድ ላይ የነበረው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ምድቡን በ10 ነጥብ በበላይነት አጠናቋል፡፡

አንድ ጨዋታ እየቀረው ለግማሽ ፍጻሜ የደረሰው የኢትዮጵያ ወጣት ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ በትንሹ እስከ 3ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቅቀ ይጠበቅበታል፡፡

የጌዴኦ ዞን አርሶ አደሮችና ላኪዎች ጥራቱን የጠበቀ ቡና በማዘጋጀት ተወዳዳሪ ለመሆን እየሰሩ ነው   ዲላ፣ ኅዳር 17/2018 (ዲዩ ኤፍኤም 89.0) በጌዴኦ ዞን ጥራቱን የጠበቀ ቡና በማዘጋ...
26/11/2025

የጌዴኦ ዞን አርሶ አደሮችና ላኪዎች ጥራቱን የጠበቀ ቡና በማዘጋጀት ተወዳዳሪ ለመሆን እየሰሩ ነው

ዲላ፣ ኅዳር 17/2018 (ዲዩ ኤፍኤም 89.0) በጌዴኦ ዞን ጥራቱን የጠበቀ ቡና በማዘጋጀት በገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን እየሰሩ መሆናቸውን አርሶ አደሮችና ላኪዎች ገለጹ።

የክልሉ ላኪዎችና አርሶ አደሮች ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ቀይ ቡናን በመሰብሰብና በጥራት በማዘጋጀት በገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን በትኩረት እየሰሩ ናቸው፡፡

የይርጋጨፌ ወረዳ ነዋሪ ወይዘሮ ወርቅዬ ሻሎ መንግስት ባመቻቸላቸው እድል የላኪ አርሶ አደር ፍቃድ በማውጣት ለውጭ ገበያ በቀጥታ እያቀረቡ መሆናቸውን አንስተዋል።

በምርት ዘመኑ ካለሙት ከ4 ነጥብ 5 ሄክታር ማሳ ከ70 ኩንታል በላይ ጥራቱን የጠበቀ የልዩ ጣዕም ቡና በማዘጋጀት የተሻለ ዋጋ ለማግኘት እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችን በማልማት ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ መስራታቸውን ያነሱት ደግሞ የዲላ ዙሪያ ወረዳ አርሶ አደር ዳዊት ሌጌ ናቸው።

ምርታቸውን በጥራት በማዘጋጀት በገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን እየሰሩ መሆናቸውን ጠቅስዋል።

የእሸት ቡና መፈልፈያ ኢንዱስትሪ ባለቤት የሆኑት አቶ አበራ አሰፋ በበኩላቸው፤ የልዩ ጣዕም የይርጋጨፌ ቡናን በጥራት ለማዘጋጀት እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ለዚህም ከአርሶ አደሩ ቀይ ቡና ብቻ በመረከብ ለጥራት መረጋገጥ ትኩረት መስጠታቸውን አክለዋል።

የይርጋጨፌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ቡኔ በበኩላቸው፤ በወረዳው በግብይት ማዕከላት ብቻ የእሸት ቡና ግብይት እንዲፈጸም በማድረግ ጥራት እንዳይጓደል እየተሰራ ነው ብለዋል።

በተለይ በወረዳው ከ400 በላይ ላኪ አርሶ አደሮች ልዩ ጣዕም ቡና እንዲያዘጋጁና የተሻለ የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ወረዳው ትልቁ የግብርና አቅሙ ቡና ነው ያሉት አስተዳዳሪው በተያዘው አመት በተለያዩ አማራጮች ከ12 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በክልሉ በቡና ከተሸፈነ 235 ሺህ ሄክታር ማሳ ውስጥ ከ201 ሺህ ቶን በላይ እሸት ቡና ለመሰብስብ ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን ያነሱት ደግሞ የክልሉ ቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ሃላፊ ተወካይ አቶ አብርሃም አስታጥቀኝ ናቸው።

እስካሁንም ከ26 ሺህ ቶን በላይ ቡና መሰብሰቡን አንስተው እስክ ጥር አጋማሽ የቡና ምርት የማሰባሰብ ስራው እንደሚዘልቅ ገልጸዋል።

የአርሶ አደር የልምድ ልውውጥና የምርት ጥራት ማስጠበቂያ የግንዛቤ ስራዎች በምርት አሰባሰብ ወቅት ይገጥም የነበረን የጥራት መጓደል ማሻሻሉንም ተናግረዋል።

Ethiopian News Agency

Karnixxe baajetetixxe wogga'n 46 kuma toone buno odditte dikko'a shiqisate'e herrengeexxi hujete'n he'neexxa bita'i Itop...
25/11/2025

Karnixxe baajetetixxe wogga'n 46 kuma toone buno odditte dikko'a shiqisate'e herrengeexxi hujete'n he'neexxa bita'i Itophphixxi gabalendeexxe galchaxxi bunonna Shuutta Shufuroti baalloomi ifise'en

Dilla, Sadaasa 16/2018 G.w (DY FM 89.0)

Bita'i Itophphixxe gabalendeexxe galcha'n 2dhibbanna 35 kumi hekitaare buttin buniinxe karranni haanjedheeke kadeexxa ifinse'eki gabalendeexxe galchaki bunonna shuutta shufurotixxe baalloomi illichchi dayirekiteerichchi aaddi Amaanu'eeli Birru buniinxa karranna karrooma nossate'e ayyeretike jeejinni weli qabbaaxxa haaroonsendeexxa sanne qo'netixxe wirto'n qo'nisat latto faqisat wiisalluwwake'e qoqqoodat towenna kipha assina'neexxe kaddeexxa haasonne'en.

‎Ca'inne heqqeeka buno odditte dikko'a shiqisate'e wiisalluwwakenna buno shiqisaake mittoomi'a edile karra bukkassate'e hubanno dadatixxa barachcho uuneexxa ke'issineeki aaddi Amaanu'eeli 2018 baajetetixxe wogga'n 46 kuma toone buno odditte dikko'a shiqisate'e herrengeexxi hujete'n he'neexxa ege'inshe'en.

‎Karrooma nossitaaxxa buniinxa sanne faqise ba'lisatinna cimeeka buno haaroonsat Gede'inxe zoone'n hedheeka eloka fakkeenna gabalendeexxe galcha'n affendaaxxe wele zoonuwwa'n ba'lissate'e herrengeexxi hunja'neexxa ifinse'eki illichchi dayirekiteerichchi bunonna shuutta shufuroti karrooma heddissenna ca'inniki karrooma nossat bogiinxa gadhi maallaqixxe jijjiirraxxa hunna nossate'e lumoxxa wo'laancho assate'n he'neexxe kaddeexxa haasonne'en.

‎Ta'a hedheeke jeeja'n butta duuchchixxi buniinxe dokkoxxi halcha lebba'n daga Itophphiinke bogi'a eloxxa anjire daddaaxxen hineeki illichchi dayirekiteerichchi dokkotika seera daddaqisate'e lele'mita'neexxe seeribeloxxa daddaltoinna otokisano faachcheeffachchot darre'n koobbo koobbonge'n hexxeexxi akeekano ifi iimixxa maganne fu'litaashsha ye'injo shiqinse'en.

‎Buniinxe invetimmente'n bobbaateexxi dureeyye wodi'inxa karra battoossatenaa'n heqqat ardummatixxa maganne fu'linaashsha aaddi Amaanu'eeli yaadachchiinse'en.

Wendimmu Kiphe

https://www.facebook.com/dufm89.0 𝒌𝒐𝒏𝒏𝒆 𝑭𝑩 𝒇𝒖𝒖𝒍𝒂 𝒏𝒐'𝒐𝒌𝒂 𝑭𝒐𝒍𝒍𝒐𝒘,𝒍𝒊𝒌𝒆,𝒔𝒉𝒂𝒓𝒆 𝒂𝒔𝒔𝒂𝒕𝒊 𝒎𝒂𝒂𝒕𝒆 𝒌𝒂𝒅𝒅𝒆.

#𝑫𝑼 𝑭𝑴 89.0 𝑯𝒖𝒏𝒅𝒂𝒂𝒚𝒚𝒆 𝑬𝒈𝒆'𝒏𝒂 𝒃𝒐𝒐𝒕𝒆𝒆𝒔𝒔𝒂𝒕𝒆'𝒆 𝑴𝒆'𝒍𝒄𝒉𝒄𝒉𝒂𝒐𝒕𝒊 𝑯𝒖𝒏𝒋𝒂𝒏𝒏𝒐𝒏 !

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ አቻ ተለያዩበምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) ማጣሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከሶማሊያ ጋር 3 ለ 3 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል፡...
21/11/2025

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ አቻ ተለያዩ

በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) ማጣሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከሶማሊያ ጋር 3 ለ 3 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል፡፡

ቀን 10 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው የምድብ ሶስት ጨዋታ ዳዊት ካሳው በጨዋታ እና በፍፁም ቅጣት ምት ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር አቤኔዘር አለማየሁ ቀሪዋን ግብ አስቆጥሯል፡፡

ኢትዮጵያ የተወሰዱባትን 12 ውድ ቅርሶች ተረከበችዲላ:- ሕዳር 10/2018 በ1920ዎቹ ከኢትዮጵያ የተወሰዱ 12 ውድ ቅርሶችን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት እና ምርምር ተቋም ...
19/11/2025

ኢትዮጵያ የተወሰዱባትን 12 ውድ ቅርሶች ተረከበች

ዲላ:- ሕዳር 10/2018

በ1920ዎቹ ከኢትዮጵያ የተወሰዱ 12 ውድ ቅርሶችን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት እና ምርምር ተቋም ተቀብሏል።

ቅርሶቹ የፕሮፌሰር ራሞን አያት እንዲሁም በ1920ዎቹ በኢትዮጵያ የጀርመን ልዑክ በነበሩት ፍራንዝ ዊስ የአገልግሎት ዘመን ከኢትዮጵያ የተወሰዱ ሲሆን፣ ፍራንዝ እና ባለቤታቸው ሄድዊግ ገንዘብ ከፍለው የሰበሰቧቸው ናቸው።

ለዩኒቨርሲቲው ከተበረከቱት ውድ ቅርሶች ውስጥ ዘውድ፣ ጋሻ፣ ጎራዴ፣ ዝናር፣ ስዕሎች እንዲሁም ከራስ ተፈሪ መኮንን የተበረከቱ ስጦታዎች ይገኙባቸዋል።

የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ቅርሶቹ የኢትዮጵያ ሃብቶች ከመሆናቸው በተጨማሪ ለጥናትና ምርምር በግብዓትነት የሚያገለግሉ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በመላው ዓለም በግለሰቦች እጅ እና በተቋማት ውስጥ የሚገኙና የኢትዮጵያ ታሪክ አስረጂ የሆኑ ጥንታዊ ቅርሶች ወደ ሃገር እንዲመለሱ የማድረጉ ጥረትም ይቀጥላል ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

#ኢዜአ

10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ተጠናቀቀከሕዳር 6 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሰመራ ሎጊያ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም በዛሬው ዕለት ተጠናቅቋል፡፡በማጠቃለያ መርሐ...
19/11/2025

10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ተጠናቀቀ

ከሕዳር 6 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሰመራ ሎጊያ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም በዛሬው ዕለት ተጠናቅቋል፡፡

በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፣ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ጫልቱ ሳኒ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ ፎረሙ ከተሞች በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በመዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥ፣ በኮሪደር ልማት አተገባበር እና በሌሎች ዘርፎች ላይ ተሞክሮ የተለዋወጡበት ነበር፡፡

በከተማ የመሬት አጠቃቀም እና የቤት ልማት አያያዝን ለመቅረፍ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመው ÷ የከተሞች የልምድ ልውውጥን በማጠናከር ወደ ተሻለ ብልጽግና መሻገር ይገባል ብለዋል።

በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚነሳውን ቅሬታ መፍታት እንደሚገባ የተናገሩት ሚኒስተሯ÷ በሰመራ ሎጊያ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 10ኛው የከተሞች ፎረም ስኬታማ እንደነበር አመልክተዋል፡፡

ከ140 በላይ ከተሞች በተሳተፉበት ፎረሙ ከተሞች በ5 ምድቦች ተከፍለው ለየምድቡ በቀረቡ የመወዳደሪያ መስፈርቶች ተመዝነዋል።

በዚህም ከምድብ አንድ 1ኛ አዳማ ፣2ኛ ቢሾፍቱ ፣ 3ኛ ሀዋሳ በመሆን ሲያሸንፉ ÷ በምድብ ሁለት ደግሞ ጅማ ፣ ሆሳዕና እና ዲላ በቅደም ተከተል ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

የሸገር ከተማ በ10ኛው የከተሞች ፎረም ልዩ ተሸላሚ ሲሆን ÷ አዘጋጇ ከተማ ሠመራ ሎጊያም ሽልማት ተበርክቶላታል።

11ኛውን የከሞች ፎረም የአሶሳ ከተማ እንድታዘጋጅ ተመርጣለች፡፡

ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ማጣርያ 🇸🇸ደቡብ ሱዳን 1-4 ኢትዮጵያ 🇪🇹78' ፓኖም ጁ        13' ዳዊት ካሳው                            17' ዳዊት ካሳ...
18/11/2025

ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ማጣርያ
🇸🇸ደቡብ ሱዳን 1-4 ኢትዮጵያ 🇪🇹
78' ፓኖም ጁ 13' ዳዊት ካሳው
17' ዳዊት ካሳው
52' ዳዊት ካሳው (ፍ)
56' እንየው ስለሺ

🏟 አበበ ቢቂላ ስታዲየም

‎ ‌‎ የምድብ ችሎቶች መስፋፋት የህብረተሰቡን የፍትህ ተጠቃሚነት የበለጠ ያረጋግጣል፦መስፍን ደምሴ (ዶ/ር ) ‎ዲላ፣ ‎ህዳር 9/2018 ዓ.ም‎‎የዲላ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍር...
17/11/2025


‌‎ የምድብ ችሎቶች መስፋፋት የህብረተሰቡን የፍትህ ተጠቃሚነት የበለጠ ያረጋግጣል፦መስፍን ደምሴ (ዶ/ር )

ዲላ፣ ‎ህዳር 9/2018 ዓ.ም

‎የዲላ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥን በተሻለ ተደራሽ ለማድረግ በከተማው የተለያዩ ምድብ ችሎቶችን በማዋቀር ወደ ስራ ገብቷል።

‎ቀደም ሲል የፍትህ አገልግሎት አሰጣጡ በአንድ ማዕከል ብቻ መወሰኑ ተገልጋዮች ላይ ከሚደርሰው እንግልትና የጊዜ ብክነት ከማስቀረት ባለፈ የፍትህ ሂደቱን ፈጣንና ቀልጣፋ እንደሚያደርገው የዲላ ከተማ ከንቲባ መስፍን ደምሴ (ዶክተር) ጠቅሰዋል።

‎ዜጎች የፍትህ ተጠቃሚነታቸውን በሚገባ ለማረጋገጥም ከተማ አስተዳደሩ የተቋሙን አገልግሎት ተደራሽ በሚያደርግ መልኩ በዕቅድ የተደገፈ መዋቅራዊ አደረጃጀት በጥናት ተመስርቶ ሲሰራ መቆየቱንም ተናግረዋል።

‎ከከተማው መስፋት ጋር ተያይዞ በየጊዜው አያደገ ያለውን የተገልጋይ ፍላጎት በሚገባ ለማረጋገጥ የምድብ ችሎት መበራከት ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ከንቲባው ገልፀዋል።

‎በማስጀመርሪያ መድረኩ የተገኙትና የዕለቱ እንግዳ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር አንዱዓለም አምባዬ ተቋማዊ አገልግሎትቱን በተደራጀ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ እንደከተማ አስተዳደሩ የተደረገውን ጥረት አድንቀዋል።

‎አቶ አንዱዓለም አክለውም የፍትህ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ከማስፋፋት ባለፈም የዳኝነት ስርዓቱን አሰራርሩንና ህጉን ተከትሎ በማስፈጸም የህብረተሰቡን የፍትህ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

‎የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሳሙኤል በፍቃዱ በበኩላቸው የፍትህ ተቋማቱ ፈጣን ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ተደራሽ እንዲያደርጉ የምድብ ችሎት መደራጀት የላቀ ድርሻ አለው ብለዋል።

‎በተለይም በፍትህ አሰጣጡ የሚታዩት መጓተቶችን በማስቀረትም ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው በመግለጽ።

‎ ዜጎች ፍትህን ፍለጋ በሚያደርጉት ጥረት ለአላስፈላጊ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ማህበራዊ ጉዳቶች እንዳይዳረጉ ተቋሙ የፍትህን ተደራሽነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆህ
‎የገለፁት የዲላ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ታሪኩ ዓለሙ።

‎ አገልግሎት ሰጪው ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኝ መንግስት እያደረገ ካለው ጥረት ባለፈ ምቹ የስራ ሁኔታን በመፍጠርም ዜጎች ፍትህን በአግባበቡ እንዲያገኙም በተለየ ትኩረት ይሰራል ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።

‎ በይፋዊ የምድብ ችሎት የስራ ማስጀመሪያ ፕሮግራሙ የዳኞች ማህበር ጠበቆችና የፍትህ አካላት ተገኝተውበታል።

አብዮት ዳቼ

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ መተላለፊያ መንገዶች እና መከላከያ ዘዴዎችአዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የማርበርግ ቫይረስ በሽታ (Marburg Virus Disease) በወረርሽኝ ...
16/11/2025

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ መተላለፊያ መንገዶች እና መከላከያ ዘዴዎች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የማርበርግ ቫይረስ በሽታ (Marburg Virus Disease) በወረርሽኝ መልክ የሚከሰት የደም መፍሰስና ትኩሳት ህመም ሲሆን በሰዎችም ሆነ በሌሎች እንስሳት ላይ ይከሰታል።

የበሽታው ምልክቶች ለቫይረሱ በተጋለጥን ከ2 እስከ 9 ባሉት ቀናት ውስጥ የሚታዩ ሲሆን፤ ምልክቶቹ:-

👉 ከአፍ፣ ከአፍንጫ ወይም ከቆዳ ስር ደም መፍሰስ፣

👉 ከፍተኛ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት እና ራስ ምታት፣

👉 የጡንቻ እና የጀርባ ህመም፣

👉 ማቅለሽለሽ፣ የሆድ ህመም እና ተቅማጥ፣

👉 ደረት፣ ጀርባ እና ሆድ ላይ በጣም ጎልቶ የሚታይ ሽፍታ ናቸው።

የበሽታው መተላለፊያ መንገዶች

👉 ከበሽተኛ ደም፣ ሽንት፣ እንባ እና ሌሎች ፈሳሾች ጋር የሚፈጠር ቀጥተኛ ንክኪ፣

👉 በታመመ ወይም በሞተ ሰው የሰውነት ፈሳሽ የተበከሉ ቁሶች (እንደ ልብስ፣ አልጋ ልብስ፣ መርፌ እና ሌሎች መገልገያዎች) ጋር በሚኖር ንክኪ፣

👉 በተጨማሪ በበሽታው ከተያዙ የሌሊት ወፎች ወደ ሰዎች ይተላለፋል።

የበሽታው መከላከያ መንገዶች

👉 የተዘረዘሩት ምልክቶች ሲኖሩ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ፣

👉 ከታመመ ሰው ጋር ንክኪ ካለዎት እና ትኩሳት ካለ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም መሄድ፣

👉 ሞት በሚከሰትበት ጊዜ አስከሬኑን በባለሙያ ማዘጋጀት እና መቅበር፤ አላስፈላጊ የቀብር ሥነ ሥርዓቶችን ማስቀረት እና ንክኪ ያላቸውን ቁሶች ማስወገድ፣

👉 ከታመመ ሰው ደም እና ፈሳሽ ንክኪ ራስን መጠበቅ፣

👉 ለታመመ ሰው እንክብካቤ በምናደርግበት ጊዜ የመከላከያ ዘዴዎችን ማለትም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ እና የእጅ ጓንት መጠቀም፣

👉 እጅን በሳኒታይዘር ወይም በሳሙናና በውሃ በአግባቡ መታጠብ እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

‎ፍርድ ቤቱ የአገልግሎት አሰጣጡን ተደራሽነት ለማስፋት ተጨማሪ ምድብ ችሎት ሥራ ሊያስጀምር መሆኑን አስታወቀ‎ዲላ፣ ‎ህዳር 8/2018 (ዲዩ ኤፍኤም 89.0) ‎የዲላ ከተማ አስተዳደር የመጀመ...
16/11/2025

‎ፍርድ ቤቱ የአገልግሎት አሰጣጡን ተደራሽነት ለማስፋት ተጨማሪ ምድብ ችሎት ሥራ ሊያስጀምር መሆኑን አስታወቀ

ዲላ፣ ‎ህዳር 8/2018 (ዲዩ ኤፍኤም 89.0) ‎የዲላ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አገልግሎት አሰጣጡን ፈጣንና ቀልጣፋ በማድረግ ተደራሽነቱን ለማስፋት ከዋናው የአገልግሎት ማዕከል ባለፈ በኦዳያኣና ጪጩ ቀበሌዎች ተጨማሪ የምድብ ችሎትን ወደ ስራ እንደሚገቡ የፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት አቶ ታሪኩ አለሙ ገልጸዋል።

‎የከተማዋን መስፋፋት ተከትሎ እያደገ የመጣውን የተገልጋይ ቁጥር ፍላጎት በአግባቡ ለማርካትና ፍትህን በተቀላጠፈ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ መዋቅሩ አስፈላጊነቱን አቶ ታሪኩ አክለውም ጠቅሰዋል።

‎ማህበረሰቡ ፍትህን በአግባቡ ማግኘት እንዲችል ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ፍርድ ቤቱ የበለጠ ወደ ተጠቃሚው በመቅረብ ተገልጋዩን ከአላስፈላጊ ወጪና የጊዜ ብክነት ለመታደግ ምድብ ችሎቶች መቋቋማቸው ፋይዳቸው የላቀ መሆኑም ተጠቅሷል።

‎ቀደም ሲል በአንድ ማዕከል ሲሰጥ የነበሩት አገልግሎቶች አሁን ወደስራ በሚገቡት የምድብ ችሎት በማስፋት የፍትህ ተደራሽነቱን የበለጠ ለማስፈን አጋዥ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ በመግለጫቸው አመላክቷል።

‎በምድብ ችሎቶ ቹም ህዳር 9/2018 ዓ.ም. ወደ ስራ እንደሚገቡ የገለጹት አቶ ታሪኩ አለሙ በቀጣይም በአንዲዳ ቀበሌ ተዘዋዋሪ ችሎት በቅርቡ እንደሚሰየም ተናግሯል።

‎ተገልጋዩ ህብረተሰብም ይህንኑ በመገንዘብ ወደሚቀርቡት የምድብ ችሎት በመቅረብ የአገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪ ቀርቧልም።

‎ከአዲሶቹ ምድብ ችሎት በተለይም የኦዳያኣ ም/ ችሎት በዞኑ ፍ/ቤቶች ደረጃ የመጀመሪያዉ የአንድ መስኮት አገልግሎትን ተግባራዊ በማድረግ የተገልጋዮችን ፍላጎት ለማርካት የተዋቀረ መሆኑም ተገልጿል።

‎የምድብ ችሎት መዋቅሩ ወደ ስራ እንዲገባ በማድረጉም የዲላ ከተማ ምክር ቤትና ከተማ አስተዳደሩ ለነበራቸው የላቀ ሚና ፕሬዚዳንቱ ምስጋናቸውን ችረዋል።

በአብዮት ዳቼ

14/11/2025

በወቅታዊ ጉዳይ የጤና ሚኒሰቴር መልዕክት

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when DU FM89.0 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to DU FM89.0:

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share