02/06/2023
በታላቁ አንዋር መስጂድ በሰላማዊ ምእመናን ላይ የደረሰውን ጉዳት ተከትሎ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ ከሚመለከተው የፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን ጋር የተፈጠረውን ቀውስ ለማረጋጋት እና ባስቸኳይ የተጎዱትን ለማትረፍ በሚቻልበት መንገድ ላይ እየተነጋገሩ ቆይተዋል::
በተፈፀመው ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው ወንድሞቻችን የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ ወደ ሆስፒታል እንዲወሰዱ አምቡላስ ወደ ቦታው እንዲደርስ እያደረጉ ይገኛሉ::
ታላቁ ኣንዋር መስጂድ ከውጥረት ነፃ እንዲሆን ፣በመስጂዱ ውስጥ የሚገኙ ምዕመናንም በሰላም ወደቤታቸው እንዲገቡ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሼይኽ ሱልጣን አማንን ጨምሮ ሶስት ከፍተኛ አመራሮች ከመጅሊሱ ተወክለው ወደ ቦታው በማምራት ከፀጥታ ኃይሉ ጋር ይህን ተፈፃሚ እንዲሆን እየሰሩ ይገኛሉ::
ከሁሉም ነገር በፊት ሰብኣዊነት መቅደም ስለሚኖርበት የተጎዱትን ወደ ህክምና ቦታ ለማድረስ እና በመስጂዱ ያሉ ምዕመናን በሰላም ወደቤታቸው እንዲገቡ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት በአንዋር መስጂድ እና በዙርያው ያለው የፀጥታ ኀይሉም ይህ ተፈፃሚ እንዲሆን የበኩሉን ሓላፊነት እንዲወጣ ጥሪ እናቀርባለን::
Ustaz Abubeker Ahmed/ ኡስታዝ አቡበከር