Alemayehu Zenebe

Alemayehu Zenebe በመኖር ውስጥ ...

💚 💛 ❤ ኢትዮጵያዬ 💚 💛 ❤
17/04/2024

💚 💛 ❤ ኢትዮጵያዬ 💚 💛 ❤

ንዝረት አለው .... 💚 💛 ❤
16/03/2024

ንዝረት አለው .... 💚 💛 ❤

14/03/2024
❤
10/03/2024




09/03/2024

«ማታ ወደ አልጋሽ ሄደሽ ጓደኞችሽ የተሻለ ቦታ ደርሰው አንቺ አሁንም እየታገልሽ እንደሆነ ስታውቂ ይፈትንሻል። ፈተና የሌለው ምንም ነገር የለም ስኬት እንደተለያየ ሰው ይለያያል፣
ለአንዳንድ ሰው ስኬት አግብቶ ልጅ መውለድ ሊሆን ይችላል፣ ለአንዳንድ ሰው ደግሞ ተምሮ ዲግሪውን መያዝ ሊሆን ይችላል፣ ለአንዳንዱ ደግሞ ደግሞ ሚሊዮን ብር ባንክ ማስቀመጥ ሊሆን ይችላል፣
ለእኔ ስኬቴ በየቀኑ ራሴን ማሸነፌ ነው፣ ወደ አልጋዬ ስሄድ ህሊናዬ ዛሬ ምን ሰርተሻል ብሎ ለጠየቀኝ ጥያቄ መልስ መስጠት ነው። በዛ ረገድ ደስተኛ ነሽ ወይ ከተባልኩ አዎ ስኬት ግን መንገድ ነው ብትሄጂበት ጥግ የለውም፣ ደግሞ ደስ የሚለው መንገዱ ነው።»

ተወዳጇ አርቲስት ሳያት ደምሴ

Halyo Media ኀልዮ ሚዲያ

29/07/2023

ለብቻ የመቆም ማሳያ፥ ከግርሻውያን ኀልዮት የማፈንገጫ፤ የእውነት አምድ፥ የጽናት ጉልላት ... አቡነ ጴጥሮስ።

"ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት" በተሰኘው፥ በሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅን ቲያትር ላይ፥ ግርሻ የተሰኘ የዘመኑን አጎብዳጆች እሚወክል ገጸባህሪ አለ። ለጥልያን እጅ እንስጥ እሚልበት አመክንዮ የዋዛ እሚባል አይደለም። ለአቡነ ጴጥሮስ የኢትዮጵያን ፍጹም ሞት እሚያትትበት መንገድ አጀብ ነው። በቃላት አሽሞንሙኖ የኢትዮጵያን ሞት ያረዳቸዋል። አቡነ ጴጥሮስ ኢትዮጵያን ከድተው በፋሽስት እንዲጠመቁ ሲያብል። አቡኑም እንዲህ ይሉታል፦ "እኔ በኢትዮጵያ ስለማምን፥ እኔ እስካመንኩ እሷ አትሞትም።"

አቡነ ጴጥሮስ የዛሬ 87 ዓመት ነበር ሰማዕትነትን የተቀበሉት!

Halyo Media ኀልዮ ሚዲያ

15/07/2023

ቀን ጎድሎብህ ሁሉንም ብታጣ፤ ሁሉም ቢከዳህ፤ሁሉን ነገር እንደነበር መመለስ የሚያስችልህ አንድ ነገር ብቻ አለ«በራስህ ልቦና ውስጥ የምትፈጥረው የአይበገሬነት እልህ!»

📓 ያልታበሱ እንባዎች

HHalyo Media ኀልዮ ሚዲያMHalyo Media ኀልዮ ሚዲያኀHalyo Media ኀልዮ ሚዲያሚHalyo Media ኀልዮ ሚዲያ

10/06/2023

. አንዳዴ #ከሁካታው ገለል ማለት እንዴት ሰላም ይሰጣል ! በዚህ ላይ ደሞ የገሀዱን አለም መስታወት እያዩ አረፍ ማለትን የመሰለ ሀሴት! ዋው.....

ይህ ደግሞ እሩቅ አይደለም ለእርሶ ይሆንዎት ዘንድ በጥበብ ቀምረን በ 11 / 10/ 2015 ዓ.ም ከቀኑ 10 : 30 am በጌትቫ ሆቴል ታላቅ የሥነፅሑፍ ምሽት አዘጋጅተናል ይምጡ ይታደሙ ጊዜዎን ያሳምሩ አትርፈው ይመለሱ ፥

#አዘጋጅ ፦ ደብረ-ጥበብ የቲያትር እና የሥነ-ፅሑፍ ቡድን

፦ ሰኔ 11 / 2015 ዓ.ም

#ቦታ ፦ ጌትቫ ሆቴል ደብረብርሃን

፦ VIP 100 ብር ብቻ
ኖርማል ፦ 50 ብር ብቻ

👇

0953982544 ወይም 0703727205 ደውለው መውሰድ ይችላሉ ።

ኑ ከድል ማግስት ፍቅርን እንመስርትከሰዓቶች ሁሉ ሙሉ ቀን ለፍተው የሚዝናኑበትን ሰዓት አይተን፣ከቀናት ቢሉ ሰንበትዎን መርጠን፣ከሳምንታት ቢሉ የውር ማገባደጃ ሳምንትን አስበን፣ከ13 ወራት የ...
03/03/2023

ኑ ከድል ማግስት ፍቅርን እንመስርት
ከሰዓቶች ሁሉ ሙሉ ቀን ለፍተው የሚዝናኑበትን ሰዓት አይተን፣ከቀናት ቢሉ ሰንበትዎን መርጠን፣ከሳምንታት ቢሉ የውር ማገባደጃ ሳምንትን አስበን፣ከ13 ወራት የድል ወርን ፈልገን በኪነ-ጥበባዊ ስራዎች እየተዝናኑ ቁም ነገር የሚጨብጡበትን ስራዎቻችንን ይዘን እሁድ በ26/06/2015 ዓ.ም ከምሽቱ11:00 ሰዓት በህይወት ሆቴል አዳራሽ ከተን እንጠብቆታለን በመሆኑም እርሶ የእሁድ ቀጠሮትን ወደ ህይወት ሆቴል አዳራሽ በማድረግ የጥበብ ድግሳችንን እንዲታደሙ በአክብሮት ተጋብዘዋል።
ቀርተው እንዳያመልጥዎ አልያም ቦታ እንዳይያዝቦ በጊዜ የመግቢያ ትኬቱን በእጅዎ ያስገቡ።
የመግቢያ ዋጋ ኖርማል 50 ብር
ቪአይፒ 100 ብር ይፍጠኑ ትኬቱን ለማግኘት በ 0953982544 ወይም 0703727205 ይደውሉ።

       " ኑ ከድል ማግስት ፍቅርን እንመስርት "    እያልን የካቲት 26 እሁድ ከ11 : 00 ጀምሮ በህይወት ሆቴል አዳራሽ ታላቅ የጥበብ ድግስ አዘጋጅተን እንጠብቆታለን ።     የመግ...
02/03/2023



" ኑ ከድል ማግስት ፍቅርን እንመስርት "
እያልን የካቲት 26 እሁድ ከ11 : 00 ጀምሮ በህይወት ሆቴል አዳራሽ ታላቅ የጥበብ ድግስ አዘጋጅተን እንጠብቆታለን ።

የመግቢያ ትኬት በ50 ብር VIP 100 ብር ብቻ ትኬቱን ለምትፈልጉ ፦

0953982544 (tel )
0703727205 (safari )
በመደወል በፈለጉት ብዛት ጊዜ እና ቦታ እናደርስሎታለን ።

አዘጋጅ ፦ ደብረ ጥበብ የቲያትር እና የስነጽሁፍ ክበብ

04/02/2023

ቅዱስ ሲኖዶስ የካቲት 5 ቀን 2015 ዓም ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል።

በየካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምእመናን ከጠዋቱ 11፡00 ጀምሮ በየአጥብያቸው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት እስከ ጠዋቱ 1:30 ድረስ ሥርዓተ ቅዳሴው ከተፈጸመ በኃላ ከጠዋቱ 2፡00 ላይ ሁሉም ገዳማት፣ አድባራት እና አብያተ ክርስቲያናት በተመሳሳይ ሰዓት ደወል በመደወል ምእመናን በሙሉ እስከ ጠዋቱ 2፡30 ድረስ እንዲሰባሰቡ በማድረግ ከየአጥቢያው በመነሳት የጥምቀተ ባህር ወይም የመስቀል አደባባይ ላይ ታቦተ ሕጉን በማክበር፤ በማጀብ በዝማሬ እና በእልልታ በአንድ ቦታ በመሰባሰብ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

የዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ዝርዝር አፈጻጸም መመሪያን በተመለከተ በአጭር ጊዜ ውስጥ የምናሳውቃችሁ መሆኑን አውቃችሁ ዝግጅት እንድታደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡

ማንኛውም የመንግሥት የጸጥታ ኃይል ቤተ ክርስቲያን ያዘዘችውን ሰላማዊ ጥያቄ በሚከወንበት ማንኛውም የአገልግሎት ጊዜ ተግባራቱ ሰላማዊ መሆናቸውን በመገንዘብ ተገቢውን ጥበቃ የማድረግ ግዴታ እንዳለበት አውቆ እንዲያስፈጽም ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

 #ስለወንዶች…(ከፊያሜታ)•ወንዶችን ፍቅር ማስያዝ ደስ ይለኛል። ወንዶችን ፍቅር ማስያዝ ቀላል ነው። እንዴት መሰለህ? መጀመሪያ ሳገኘው ልክ ስፈልገው የኖርኩት ሰው አስመስዬ የልብ ልብ አሰጠ...
28/10/2022

#ስለወንዶች…
(ከፊያሜታ)

ወንዶችን ፍቅር ማስያዝ ደስ ይለኛል። ወንዶችን ፍቅር ማስያዝ ቀላል ነው። እንዴት መሰለህ? መጀመሪያ ሳገኘው ልክ ስፈልገው የኖርኩት ሰው አስመስዬ የልብ ልብ አሰጠዋለው። ግልፅ እሆንለታለሁ። ፍቅር አሳየዋለሁ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለጥቂት ሳምንታት አልለየውም። ሳላየው ውዬ አላድርም። ሌላ ሴት እንዲያይ ወይም አሳብ እንዲኖረው ጊዜ አልሰጠውም። እንዲለምደኝ አደርገዋለሁ። ደሙ ውስጥ እገባለሁ። ወንድ ሞኝ ነው፥ ውሻ ነው። ቶሎ ይለምዳል። የለመደኝና ደሙ ውስጥ የገባሁ መሆኔን ካወቅሁ በኋላ ገሸሽ ላደርገው እጀምራለሁ፥ ዛሬ አይመቸኝም፥ ነገ አይሆንልኝም ማለት አመጣለሁ፥ ካመረረ እሔድለታለሁ። ብሔድለትም የመንፈስ እረፍት አልሰጠውም። በፊት የማውቃቸውን ወዳጆቼን ስም እየጠራሁና ዝናቸውንና ደግነታቸውን፣ ኃይላቸውንና ወንድነታቸውን እያነሳሁ አስቀናዋለሁ። (355)

፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

#ስለሴቶች…
(ከፀጋዬ)

ሴቶች መቼም ጥሎባቸው ላንድ ሰሞን ቀርቶ ላንድ ቀንም ባጋጣሚ ዝም ካሏቸው ተንቀው የተረሱ ስለሚመስላቸው ያኮርፋሉ። ዘላለም ተንከባከቡን የሚሉ ፍጡራን ናቸው። (151)

መቼም ሴቶች ሲባሉ አስር፣ አስር ጊዜ ካልማሉላቸውና ካልተገዘቱላቸው የተወደዱ አይመስላቸውም። (153)

ናቃቸው ይከተሉሃል። ከመጡ አክብረህ ያዛቸው ይወዱሃል። ውደዳቸው አርካቸው ግን አትመናቸው። (166)

ሴቶች ፈልገውኝ ቢመጡም እኔ ፈልጌ እንዳመጣኋቸው አድርጌ ነው የምይዛቸው። ሴት ልጅ ከኔ ጋር ሆና ኩራትና ክብር እንዲሰማት አፈልጋለሁ። ሴት ልጅ በፍቅር ቀርቶ በጥልም ቢሆን መከበር አለባት የሚል ፅኑ አምነት አለኝ። (255)

ሴቶችን አልለማመጣቸውም። እልክ መግባትም አልወድም። የማታዳምጠኝ ከሆነ ጥያት መሄድ ብቻ ነው የማውቀው። (348)

በቀጠሮ ሴቶችን አምስት ደቂቃ መጠበቅ ግዴታ ነው፣ ይገባል። አስር ደቂቃ መስጠት ጨዋነት ነው። ከዚያ በላይ መቆየት ነው ግን ሞኝነት ነው። (349)

ፊያሜታና ፀጋዬ በበዓሉ ብዕር፣ ኦሮማይ

24/10/2022

ጠርጣረው ባል ከቢሮ ለሚስቱ ይደውላል፦

ባል: ውዴ የት ነሽ?

ሚስት: እቤት!

ባል: እርግጠኛ ነሽ?

ሚስት አዎ!

ባል: እስኪ እርግጠኛ እንድሆን የቡና መፉጫውን አብሪው?

ሚስት: እርርርርርርርርርር

ባል: እሺ ውዴ አምኜሻለው

በሌላ ቀን ይደውላል
ባል: ውዴ የት ነሽ

ሚስት: እቤት

ባል: እርግጠኛ ነሽ

ሚስት: አዎ

ባል: እስኪ እርግጠኛ እንድሆን የቡና መፉጫውን አብሪው?

ሚስት: እርርርርርር

ባል: እሺ ውዴ አምኜሻለው በቀጣይ ቀን አሳቻ ሰዓት ላይ ድንገት ወደ ቤት ለመሄድ ይወስንና ቤት ይሄዳል ቤት ግን ከልጁ በስተቀር ሚስት አልናበርችም።

ባል: ልጁን በቁጣ እናትህ የት ሄዳ ነው በማለት ጠየቀው??





ልጅ: የቡና መፉጫ ይዛ የት እንደሄደች አላውቅም አለው።

አንስታይን - ከአንተ ጥበብ እጅጉን የሚገርመኝ ዓለማቀፋዊ መሆንህ ነው - አንዲት ቃል አትናገርም ግን ሁሉም ይገባዋል፡፡ቻርሊ ቻፕሊን - ያንተው ደግሞ ከዚህም ይልቃል ! ቅንጣት ባይገባውም ...
08/10/2022

አንስታይን - ከአንተ ጥበብ እጅጉን የሚገርመኝ ዓለማቀፋዊ መሆንህ ነው - አንዲት ቃል አትናገርም ግን ሁሉም ይገባዋል፡፡

ቻርሊ ቻፕሊን - ያንተው ደግሞ ከዚህም ይልቃል ! ቅንጣት ባይገባውም ዓለም ያደንቅሃል...

05/02/2022

የልብህን ቁስል ትተው የደረትህን ንቅሳት ያደንቃሉ የጭንቅላትህን ዋጋ በኮፍያህ ይተምኑሃል፤ ጫማ ከሌለህ እግርህ አይታይም መከራ ተሸክሞ ሲኖር ያላዩትን ትክሻ ኮት ሲለብስ ያጨበጭቡለታል ታሪክህን ጨርቅህ ላይ.....ስምህን
ልብስህ ላይ ለማንበብ ይሽቀዳደማሉ እኔ ታናሽነቴን አልረሳም
ማወቄም አያመፃድቀኝም ጀግና ማለት ታግሎ የጣለ ሳይሆን ታግሶ ያለፈ ነው ወንድሜ ሆይ ሁሌም ራስህን ተመልከት!! የምትወድቀው ሌላውን ለመጣል የሞከርክ ቀን ነው ልትጥለው የሞከርከው ሰው ግን ገልብጦህ ከላይ ሁኖ ታገኘዋለህ ።

🌺 መልካም ቀን 🌺

Address

Dabra-Berhan
DABRABERHAN

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Alemayehu Zenebe posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share


Other Dabra-Berhan media companies

Show All