ዘመነ ካሴን ይፍቱት።ምን አድርጓል? ምንም አላደረገም።ሰዉንም አልገደለም። ስለዚህ ፍቱት። ሲታሰር በጣም አዘንኩ።
ዘመነ ካሴን እወደዋለሁ።
የህፃኗ መልክት
በህፃናት መንፈስ ሁሉ የሰረፀዉ ዘመነ ነው።
በዛሬው ዕለት የቡሬ ዳሞት ህዝብ የአርበኛ ዘመነ ካሴ እስር ክፉኛ አስቆጥቷቸው ወደ አደባባይ ለተቃውሞ ወጥተዋል።
የህዝብ ሲወድህ እንዲህ ነው።
ሻለቃ አርበኛ መሳፍንት ተስፉ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የጠቅላላ ጉባኤ ዋና ሰብሳቢ ዘመነ ካሴ ባስቸኳይ እንዲፈታ ዛሬ ጠየቁ።
በተጨማሪም ከወሎ፣ከጎጃም፣ከጎንደር እና ከሸዋ የታሰሩ ፋኖዎች እንዲሁም በአዲስ አበባ የታገቱ ጋዜጠኞች፣ማህበረሰብ አንቂዎች እና ሌሎችም እንዲፈቱ ጠይቀዋል።
ጎንደር ጎንደር…
"…የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ድምጻቸውን ማሰማት ጀመሩ። ያኔ የወያኔ መንግሥት በመውደቂያው ዋዜማ ወያኔ በኦሮሚያ ለምትጨፈጭፋቸው ኦሮሞዎች የፍርሃት ወጥመድን ሰባብሮ በመጣል አደባባይ ወጥቶ ለኦሮሞ ወንድሞቹ ድምጹን ያሰማው ጎንደር ነው። "በኦሮሚያ የሚፈሰው ደም የእኔ ደም ነው" በማለት ድምፁን ያሰማና በእለቱም የወያኔ አግአዚ ጦር በስናይፐር ብዙ ጎንደሬዎችን የፈጀበትን ጊዜ እናስታውሳለን። ስብሃት ነጋና ማፍያ ቡድኑ እንደሚበተኑ፣ ኢትዮጵያ ግን እንደምትቀጥል ጎንደር ነበር በፖለቲካ ነቢያቶቿ በኩል ያወጀችው።
"…ለኦሮሞ ብላ በወያኔ የሞተችው ጎንደር ዛሬም ኦሮሞ ለወያኔ መደረቡ ሳያንስ ወያኔም ሄዳ በኦሮሞ መገደል፣ መጨፍጨፉ በዛበት። እናም ዛሬ ጎንደር እምቢ አልታረድም ብላ ድምጿን ሀ ብላ ማሰማት ጀምራለች። ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ በረከት ስምኦንም "እኛን የኦሮሞ ተቃውሞ አላሰጋንም፣ እኛን አንኮታክቶ የጣለን የዐማራ ተቃውሞ ነው፣ ጎንደር ላይ የተነሣውን ተቃውሞ ነው መመከት ያልቻልነው" ነበር ያሉት። ጌታቸው ረዳ እና ሙፈሪያት ካሚልም ያኔ በፋና ቴሌቭዥን ቀርበው "እንዴት የጎንደር ዐማራ የኦሮሞ ወንድሜ ብሎ ሰልፍ ይወጣል? በማለት ነበር ኮሬንቲ ለመጨበጥ ሲንጨረጨር የነበረው።
"…ጎንደር በዐብይ አሕመድ አማችነት ከተያዘች በኋላ ዝምታ አብዝታ ነበር። የጎንደር አክቲቪስቶች እነ ቶማ
“በአማራዎች ላይ እየተፈፀመ ያለው ጥቃት” የምክር ቤቱ አጀንዳ ባለመሆኑ የአብን ተወካዮች ፓርላማውን ረግጠው ወጡ
ሰኔ 14፤ 2014 ዓ.ም.
(አዲስ ዘይቤ፡ አዲስ አበባ) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የሆኑት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) በአማራ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ምክር ቤቱ አጀንዳ እንዲያደርገው ቢጠይቁም በመከልከላቸው የአብን አባላት የምክር ቤቱን ስብሰባ ረግጠው መውጣታቸውን ገለፁ።
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ በ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ፣ 15ኛ መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ሲሆን የ14ተኛውን መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ማፅደቅ እና የፌዴራል መንግስት መሥሪያ ቤቶችን የ2013 በጀት ዓመት ሒሳብ፤ የፋይናንስ ሕጋዊነት ኦዲት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ለማዳመጥ አጀንዳ ተይዘው ነበር።
ይሁን እንጂ የአብን አባላት በምክር ቤቱ የዛሬ አጀንዳ ላይ ከመወያየታቸው አስቀድሞ “በወለጋ እና በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በሚኖሩ አማራዎች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጅምላ ግድያ፣ የዘር ማጽዳትና ፍጅት ምክር ቤቱ ቀዳሚ አጀንዳው አድርጎ እንዲወያይበት” የሚል ጥያቄ ቢያቀርቡም በምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ሳይፈቀድላቸው ቀርቷል።
በመሆኑም የምክር ቤቱ አባላት የሆኑት የአብን ተወካዮች ስብሰባውን አቋርጠው ለመውጣት መገደዳቸውን የአብን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ገልፀዋ