የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን Butajira City Govn.Communication

  • Home
  • Ethiopia
  • Butajira
  • የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን Butajira City Govn.Communication

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን  Butajira City Govn.Communication This is The official Butajira City Gov.t COMM.fb page-ይህ ትክክለኛው የቡታጅራ ከተማ የመንግስት ኮሙኒኬሽን (fb)ፔጅ ነው፦

በቡታጅራ ከተማ የሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ከተማ አቀፍ የግማሽ ዓመት ማጠቃለያ ምዘና እየተሰጠ መሆኑን ጽ/ቤቱ አስታወቀ።(ቡታጅራ ጥር 19/2017 የመንግስት ኮሙኒኬሽን)የትም...
27/01/2025

በቡታጅራ ከተማ የሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ከተማ አቀፍ የግማሽ ዓመት ማጠቃለያ ምዘና እየተሰጠ መሆኑን ጽ/ቤቱ አስታወቀ።

(ቡታጅራ ጥር 19/2017 የመንግስት ኮሙኒኬሽን)
የትምህርት ቤቶች ጽ/ት ዛሬ ከ4ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተና መሰጠት መጀመሩን አስታውቋል።

የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ሀቢብ አብደላ በከተማችን ከሰባት በላይ ከ1ኛ ደረጃ እስከ መሰናዶ የፈተና መስጫ የግልና የመንግስት ማዕከላት መኖራቸውን ገልፀዋል።

በዚህም ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ መምህራንን በመመልመል ከፈተና ማዘጋጀት ጀምሮ ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።

የምዘና ስርዓቱ በተማሪዎች ውጤት ላይ ተወዳዳሪነት ለመጨምር የትምርት ስብራትን ለማሻሻል ተማሪዎችን በክፍል ውጤታቸው በዞን እና በሀገር አቀፍ ፈተና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ወጥነት ያለው የመመዘኛ መስፈርት አሟልተዉ እንዲያልፉና ከኩረጃ በፀዳ መልኩ ተወዳዳሪ ለማድረግ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

በጽ/ቤቱ የአጠቃላይ ፈተናና ምዘና ስራ ሂደት ዳይሬክቶሬት አቶ አህመድ ወደዶ በበኩላቸው በከተማችን የሚገኙ የግልና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ምክትል እና ዋና ርዕሳነ መምህራንን በማወያየት 6ኛ፣8ኛ እና 12ኛ ክፍሎች በክልል አቀፍ እና በሀገር አቀፍ መመዘኛ መስፈርት መሰረት መሆን አለበት በሚል የተጋጀ መሆኑን ገልፀዋል።

ከመማር ማስተማሩ ጋር መምህራን በየክፍል ደረጃ በመመልመል ፈተና መዘጋጀቱና በትላትናው እለት ታሽጎ ወደየትምህርት ቤት መስራጨቱን ለሁሉም የት/ት ደረጃ የመፈተኛ ወጥ የሆነ ሰዓት ወጥቶላቸው እየተሰጠ እንደሚገኝ ገልዖል።

የመቅቾ ከፍተኛና 2ተኛ ደረጃ ት/ት ቤት ዋና ርዕሰ መምህር አቶ ፈቱዲን ኑሪ የፈተና የ2017 የአንደኛ ሴሚሰተር ከጥር 19 እስከ 23 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እንደሚሰጥ እኛም በወጣው መሰረት ከ9ኛ--12ኛ ክፍል ጀምሮ ተማሪዎች በተረጋጋ መልኩ እየወሰዱ እንደሆነ እና ከ9 -11 በከተማ ደረጃ በሁሉም ክላስተሮች እንደሚሰጠው መሆኑን ተናግረዋል። ለ12ኛ ክፍሎች ለሀገር አቀፍ በሚያዘጋጅ ልክ ከሞዴል ባልተናነሰ መልኩ ዝግጅት ተደርጎ እየተሰጠ መገኘቱን ገልፀዋል።

ፈተናውን አስመልክቶ አስተያየት ከሰጡ ተማሪዎች መካከል ተማሪ አምረላ ከማል እና ተማሪ ልደት ነጋ የቡታጅራ ሁለተኛ ደረጃ ት/ት ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው ፈተናው የተማርነው እና እኛም ከመማር ጎን ለጎን ቤተ-መጽሐፍት በመጠቀም የማጠቃሻ መፃሕፍቶችን መሰረት ያደረገ መሆኑን ፤በቂ ዝግጅትም እንዳደረጉ ተናግረዋል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን፦
ቴሌግራም https://t.me/ButajiraCommunication/58
ፌስቡክ https://www.facebook.com/buta1921/
ዩቲዩብ
https://youtube.com/
ትዊተር https://mobile.twitter.com/ButajiraB
ኢንታግራም https://www.instagram.com/butajirab

ኒያ ፋውንዴሽን ኦቲዝም ላለባቸው ልጆች ለቤተሰቦቻቸው የአቅም ግንባታ ስልጠና  እየሰጠ ነው።(ቡታጅራ ጥር 19/2017 የመንግስት ኮሙኒኬሽን)ኒያ ፋውንዴሽን/ጆይ ፎር ኦቲዝም  በቡታጅራና ዙሪ...
27/01/2025

ኒያ ፋውንዴሽን ኦቲዝም ላለባቸው ልጆች ለቤተሰቦቻቸው የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ነው።

(ቡታጅራ ጥር 19/2017 የመንግስት ኮሙኒኬሽን)
ኒያ ፋውንዴሽን/ጆይ ፎር ኦቲዝም በቡታጅራና ዙሪያ በሚገኙ ወረዳዎች፦ ኦቲዝም ላለባቸው ልጆች ለቤተሰቦቻቸው ለ #3 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የአቅም ግንባታ ስልጠና በቡታጅራ ከተማ እየሰጠ ይገኛል።

ማህበራዊ ላይ ችግር ያለባቸው ህፃናት ላይ ብቻ ከመስራት ቤተ-ሰቦቻቸውም ላይ መስራት የተሻለ መሆኑ ተገልጿል።

ኒያ ፋውኔዴሽን በቡታጅራ ከተማ ኦቲዝም ቅርንጫፍ ማዕከል ለመክፈት በ2016 ከከተማ አስተዳደሩ የውል ስምምነት አድርጓል ይህንኑ መሰረት በማድረግ እናቶችን ለመደገፍ ነው ስልጠናው።

የቡታጅራ ከተማ ከንቲባ ተወካይ አቶ ሀይረዲን አህመዲን የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ስራውን ለማጠናከር የሚያስችል ትብብር ለማድረግ አስተዳደሩ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ፋውኔዴሽኑ በውሉ መሰረት ቃልን በመጠበቅ ስለሚሰጠው ስልጠና ምስጋና አቅርበው የተሻለ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በምስራቅ ጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ሜዲካል ሰርቪስ ዳይሬክተር አቶ አየነው በሪሁን ስልጠናው ለቤተሰቦች በጣም አስፈላጊና ጠቃሚ እንደሆነና ልጆችን እንዴት ማስተማርና መንከባከብ እንዳለባቸው ግንዛቤ የሚፈጥር መሆኑን ገልፀዋል።

ሰልጣኞችም በትኩረት እንዲከታተሉና እንዲሳተፉ የሚቸግራቸውን ነጥብ እንዲያነሱም ጠይቀዋል።
ልጆች ቤተሰቦቻቸውም ድጋፍ እንዲሁም የአቅም ግንባታ ስልጠና እንዲያገኙ ተቋማቸው ከተቋማት ረጂ ድርጅቶችን በማነጋገር በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

#ኦቲዝም የአእምሮ እድገት ውስንነት አይደለም፤አንጎል መረጃ ተቀብሎ ምላሽ የሚሰጥበት እና የሚተነትንበት መንገድ መለየት ነው።
ኦቲዝም ያለባቸው ልጆች ፍላጎታቸውን የሚገልፁበት መንገድ ከሌሎች የተለየ ነው፤የሌሎችን መረጃ ተቀብለው ልምድ እንደማያደርጉ ነው በስልጠናው የተገለፀው፤ እናም ቤተሰቦች ይህንኑ በመረዳት ማስተማርና መንከባከብ እንዳለባቸው ግንዛቤ የሚፈጥር ስልጠና ስለመሆኑም ተመላክቷል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን፦
ቴሌግራም https://t.me/ButajiraCommunication/58
ፌስቡክ https://www.facebook.com/buta1921/
ዩቲዩብ
https://youtube.com/
ትዊተር https://mobile.twitter.com/ButajiraB
ኢንታግራም https://www.instagram.com/butajirab

ምክር ቤቱ የህዝቡን ተጠቃሚነት በማሻሻል ውጤታማ ስራ እያከናወነ መሆኑ ተገለፀ።የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በውጤታማነት እንዲመለሱ  የክትትል እና ቁጥጥር ስራ በቅንጅት እየተሰ...
26/01/2025

ምክር ቤቱ የህዝቡን ተጠቃሚነት በማሻሻል ውጤታማ ስራ እያከናወነ መሆኑ ተገለፀ።

የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በውጤታማነት እንዲመለሱ የክትትል እና ቁጥጥር ስራ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የቡታጅራ ከተማ ምክር ቤት አስታወቀ።

(ቡታጅራ ጥር 18/2017 የመንግስት ኮሙኒኬሽን)
የቡታጅራ ከተማ ምክር ቤት የኢኮኖሚ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ በሴክተር መስሪያ ቤቶች የ2017 የ2ተኛ ሩብ ዓመት የሚያደርገውን የአካል ምልከታን አስመልክት ውይይት አካሂዷል።

ለምልከታውም ያመች ዘንድ የመንገድ ትራንስፖርት የማዘጋጃ ቤት በ2017 2ተኛ ሩብ ዓመት የተሰሩ ስራዎች በመድረኩ ቅኝት ዳሰሳ ተደርጓል።

የቡታጅራ ከተማ ምክር ቤት የኢኮኖሚ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ገረመው ጉራራ የክትትል እና የቁጥጥር ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ማስቻል እንደሚገባ ገልፀዋል።

በቀጣይም በየተቋሙ ክትትል በማድረግ የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ጊዜ ባለመስጠት በተሻለ ሁኔታ እንዲመለሱ በቅንጅት ይሰራል ብለዋል።

በመድረኩ መሰረታዊና ጠንካራ ስራዎች በስፋት ማስቀጠል እንዳለባቸው ተነስቷል።
እዚህ ላይ በዋናነት በክፍተት የታዩ አፈፃፀሞች በተለይ ደግሞ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የማያጠናክሩ ስራዎች ጊዜ ባለመስጠት ማስተካከል እንደሚገባ ተመላክቷል።

በሚደረገው የአካል ምልከታ የተሰሩ ስራዎች ምልከታ ይደረጋል ከቀረበው ክንውን ጋርም የማመሳከርና የመለየት ስራ እንደሚሰራ ከመድረኩ ለማወቅ ተችሏል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን፦
ቴሌግራም https://t.me/ButajiraCommunication/58
ፌስቡክ https://www.facebook.com/buta1921/
ዩቲዩብ
https://youtube.com/
ትዊተር https://mobile.twitter.com/ButajiraB
ኢንታግራም https://www.instagram.com/butajirab

አትሌት ወርቅነሽ ኢዴሳ የኦሳካ ማራቶን ውድድርን አሸነፈችጥር 18/2017 አትሌት ወርቅነሽ ኢዴሳ በጃፓን ኦሳካ በተካሄደ የሴቶች ማራቶን ውድድር አሸናፊ ሆነች።አትሌቷ ርቀቱን ለመጨረስ 2 ሰ...
26/01/2025

አትሌት ወርቅነሽ ኢዴሳ የኦሳካ ማራቶን ውድድርን አሸነፈች

ጥር 18/2017
አትሌት ወርቅነሽ ኢዴሳ በጃፓን ኦሳካ በተካሄደ የሴቶች ማራቶን ውድድር አሸናፊ ሆነች።

አትሌቷ ርቀቱን ለመጨረስ 2 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ከ59 ሴኮንድ የፈጀባት ሲሆን ባለፈው ዓመት በቦታው ውድድሩን ስታሸነፍ ካስመዘገበችው 2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ51 ሰኮንድ ጋር ሲነጻጸር በ2 ደቂቃ ከ51 ሰኮንዶች ዘግይታለች።

አትሌት ወርቅነሽ ከውድድሩ በኋላ በሰጠችው አስተያየት፤ የአምናውን ድሌን በማስጠበቄ ደስተኛ ነኝ፣ የወደፊት ግቤ ብቃቴን የበለጠ ማሻሻል ነው ብላለች።

በውድድሩ ጃፓናውያኑ አትሌቶች ካና ኮባያሺ እና ዩካ ሱዙኪ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነው ማጠናቀቃቸውን ወርልድ አትሌቲክስ ዘግቧል።

የኦሳካ ማራቶን በወርልድ አትሌቲክስ የፕላቲኒዬም ደረጃ ያለው የጎዳና ላይ ውድድር መሆኑ ተመላክቷል።
ከኤፍ ቢ ሲ

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን፦
ቴሌግራም https://t.me/ButajiraCommunication/58
ፌስቡክ https://www.facebook.com/buta1921/
ዩቲዩብ
https://youtube.com/
ትዊተር https://mobile.twitter.com/ButajiraB
ኢንታግራም https://www.instagram.com/butajirab

ርዕሰ መስተዳደር  እንዳሻው ጣሰው ( ዶ/ር )በተገኙበት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች ፎረም በሆሳዕና ከተማ ተመሰረተ። (ቡታጅራ ጥር 18/2017 ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክል...
26/01/2025

ርዕሰ መስተዳደር እንዳሻው ጣሰው ( ዶ/ር )
በተገኙበት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች ፎረም በሆሳዕና ከተማ ተመሰረተ።

(ቡታጅራ ጥር 18/2017 )

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀገር የሽማግሌዎች ፎረም ሰብሳቢ ዳኛ ሞላ ጫኬቦ እንደገለጹት ፎረሙ እንዲመሰረት ለክልሉ መንግስት ያቀረቡትን ጥያቄ ተቀብሎ ፈጣን ምላሽ በመስጠቱ ምስጋና አቅርበዋል።

የፎረሙ መመስረት አብይ ዓላማ የክልሉን ህዝቦች የእርስ በርስ መስተጋብር ከማጠናከሩም በላይ ከመንግስት ጋር በትብብር መስራት የሚያስችል መሆኑን ሰብሳቢው ጠቁመዋል።

ፎረሙ የክልሉን ህዝቦች አንድነት ለማስጠበቅ፣ቱባ ባህሎችና እሴቶች ለማጎልበትና የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ሰብሳቢው አመላክተዋል።

የክልሉ የሀገር ሽማግሌዎች ፎረም አባላት በክልሉ የሚነሱ ጉዳዮችን በውይይትና በምክክር ለማስፈጸም የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ አስታውቀዋል።

የፎረሙ አባላት ሁሉንም የክልሉን ህዝቦች በእኩልነት በፍትሀዊነት እና በታማኝነት ለማገልገል መዘጋጀታቸውንም በቃለ መሐላ አረጋግጠዋል።

የሽማግሌዎቹ ፎረም የክልሉ መንግስት ሰላምን ለማረጋገጥና ልማትን ለማፋጠን የሚያደርገውን ዘርፈ ብዙ ጥረቶች ለማገዝ መዘጋጀታቸውንም አረጋግጠዋል።

ፎረሙ ዛሬ በሆሳዕና ከተማ ሲመሰረት የተለያዩ የስራ አስፈጻሚዎችን በመምረጥ ወደስራ ገብቷል።
ከክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን፦
ቴሌግራም https://t.me/ButajiraCommunication/58
ፌስቡክ https://www.facebook.com/buta1921/
ዩቲዩብ
https://youtube.com/
ትዊተር https://mobile.twitter.com/ButajiraB
ኢንታግራም https://www.instagram.com/butajirab

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በክልሉ ከሁሉም ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ከተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት እያካሔዱ ነው ( ቡታጅራ ፣ጥር 18/2017 ) የማዕከላዊ ኢትዮ...
26/01/2025

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በክልሉ ከሁሉም ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ከተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት እያካሔዱ ነው

( ቡታጅራ ፣ጥር 18/2017 ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) ከሁሉም ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ከተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት እያካሔዱ ነው

ርዕሰ መስተዳድሩ ክልሉ ተመስርቶ ወደ ስራ ከገባባቸው ጊዜያት ወዲህ ያጋጠሙ ፈተናዎች እና መልካም እድሎች ላይ ለሀገር ሽማግሌዎቹ ገለጻ አድርገውላቸዋል።

የክልሉን የመልማት አቅም እና ጸጋዎች ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።

ዘገባው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው
ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን፦
ቴሌግራም https://t.me/ButajiraCommunication/58
ፌስቡክ https://www.facebook.com/buta1921/
ዩቲዩብ
https://youtube.com/
ትዊተር https://mobile.twitter.com/ButajiraB
ኢንታግራም https://www.instagram.com/butajirab

እትሌት ማርታ አለማየሁ የ3 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን በመስበር አሸነፈች ጥር 17፣ 2017 በካዛኪስታን ዋና ከተማ አስታን በተካሄደ የ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር አትሌት ማርታ አለማየሁ...
25/01/2025

እትሌት ማርታ አለማየሁ የ3 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን በመስበር አሸነፈች

ጥር 17፣ 2017 በካዛኪስታን ዋና ከተማ አስታን በተካሄደ የ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር አትሌት ማርታ አለማየሁ ክብረ ወሰን በመስበር አሸንፋለች።

የ16 ዓመቷ አትሌት ማርታ ርቀቱን ለመጨረስ 8 ደቂቃ ከ39 ሰኮንድ ከ80 ማይክሮ ሰኮንድ የወሰደባት ሲሆን ውጤቱም ከ18 ዓመት በታች ባሉ አትሌቶች ፈጣኑ ሰዓት ሆኖ በክብረ ወሰንነት መያዙን የወርልድ አትሌቲክስ መረጃ መለክታል።

እሷን ተከትለው ውድድሩን ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመውጣት ያጠናቀቁት ሌሎቹ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አትሌት ጉሚ ሽቶ እና አምባዬ አክሱማዊት ናቸው።ከኤፍ ቢ ሲ

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን፦
ቴሌግራም https://t.me/ButajiraCommunication/58
ፌስቡክ https://www.facebook.com/buta1921/
ዩቲዩብ
https://youtube.com/
ትዊተር https://mobile.twitter.com/ButajiraB
ኢንታግራም https://www.instagram.com/butajirab

የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሃሰን የቡኢ ከተማ አስተዳደር ቁጥር 2 ከሰንበት እስከሰንበት የገበያ ማዕከልን በይፋ መርቀው ስራ አስጀመሩ(ጥር 17/2017 ቡታጅራ)በቡኢ ከተማ ...
25/01/2025

የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሃሰን የቡኢ ከተማ አስተዳደር ቁጥር 2 ከሰንበት እስከሰንበት የገበያ ማዕከልን በይፋ መርቀው ስራ አስጀመሩ

(ጥር 17/2017 ቡታጅራ)

በቡኢ ከተማ አስተዳደር መንሃሪያ መግቢያ ቁጥር 2 ከሰንበት እስከሰንበት የመገበያያ ማዕከልን በይፋ ተርቆ ስራ ጀምሯል

በምረቃ ፕሮግራሙ የተገኙት የቡኢ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በለጠ ጫካ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት አምራችና ሸማቹን በመገናኘት ረገድ ከሰንበት እሰከሰንበት የመገበያያ ማዕከላት እንዲጠናከሩ በልዩ ትኩረት እየሰራን እንገኛለን ብለዋል ።

ዛሬ የተመረቀው ከሰንበት እስከ ሰንበት የገበያ ማዕከል ቀጥታ አምራቹ ከሸማችሁ ጋር የሚያገናኝ እና ቦታው በርካታ ምልልስ ያለባቸውና ለአካባቢው ማህበረሰብ የገበያ ትስስሩን ማዕከልነት ሊያሳድግ የሚችል ቦታ ነው ሲል አክለዋል ።

በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን ፣ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ እና የብልግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሰለ ጫካ ጨምሮ የዞኑ አመራሮች ፣ የቡኢ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በለጠ ጫካ ፣ የቡኢ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ተጠሪ እና የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደበበ አደና ፣ ሌሎች የከተማው አመራሮች በዞኑ የሚገኙ የወረዳዎች እና የከተማ አስተዳደር አስተዳዳሪዎች እና ተወካዮች ተገኝተዋል ።
ዘገባው የቡዒ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን፦
ቴሌግራም https://t.me/ButajiraCommunication/58
ፌስቡክ https://www.facebook.com/buta1921/
ዩቲዩብ
https://youtube.com/
ትዊተር https://mobile.twitter.com/ButajiraB
ኢንታግራም https://www.instagram.com/butajirab

በምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡኢ ከተማ አስተዳደር ከ8 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ  ተደርጎበት የተገነባው "የቡኢ ክላስተር ማዕከል " ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቆ ጊዜያዊ ርክክብ ተደረገ (ጥር 17/201...
25/01/2025

በምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡኢ ከተማ አስተዳደር ከ8 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበት የተገነባው "የቡኢ ክላስተር ማዕከል " ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቆ ጊዜያዊ ርክክብ ተደረገ

(ጥር 17/2017 የመንግስት ኮሙኒኬሽን)
በምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡኢ ከተማ አስተዳደር ለረዥም ጊዜ ግንባታው ተቋርጦ የነበረውና በአዲሱ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ምስረታ ማግስት ወደ ስራ ተገብቶ እየተገነባ የነበረው "የቡኢ ክላስተር ማዕከል" ግንባታ ተጠናቆ ዛሬ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ስራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት መመሪያ እና የምስራቅ ጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መመሪያ ለቡኢ ከተማ አስተዳደር አስረከበ ።

በማዕከል ርክክብ መርሐ-ግብር ላይ የተገኙት የምስራቅ ጉራጌ ዞን ስራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት መመሪያ ኃላፊ አቶ ታጁ ነስሩ የዚህ ማዕከል ግንባታ ዋነኛ ዓላማ በማኒፋክቸሪንግ ዘርፍ ;ከትላልቅ ማሽነሪዎች ጀምሮ ፣በአግሮ ፕሮሰሲንግ ፣በጨርቃ ጨርቅ እና በሌሎችም ዘርፎች ለተደራጁ ማህበራት ማምረቻ ማዕከል እንደሆነ ገልፀዋል ።

አክለውም አቶ ታጁ ነስሩ ይህ የማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት ለረዥም ጊዜ ተቋርጦ የመልካም አስተዳደር ችግር የነበረ እንደሆነ ገልፀው አዲሱ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ከተመሰረተ በኃላ ካሉ ነባር ፕሮጀክቶች መካከል ቅድሚያ ተሰጥቶት እንዲጠናቀቅ በልዩ ትኩረት የተሰራ ፕሮጀክት እንደሆን ጠቅሰዋል ።

የክላስተር ማዕከሉ ግንባታ ኮንተራክተር ዘውዱ ዘርጋ ፕሮጀክቱ ተጀምሮ ለረዥም ጊዜ ተቋርጦ ስለነበረ የማጠቃለያ ግንባታ ስራው አስቸጋሪ እንዳደረገው እና አሁን ላይ ጥቂት ከፊኒሽንግ ስራዎች በስተቀረ ሙሉ በሙሉ እንደተጠናቀቀ እና አገልግሎት መስጠት እንደሚችል ገልፀዋል።

የቡኢ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በለጠ ጫካ ማዕከሉ ነባሩ ጉራጌ ዞን ላይ ተጀምሮ ሳይጠናቀቅና ለረዥም ጊዜ የግንባታ ምዕራፉ ተቋርጦ እንደነበረ ገልፀው አዲሱ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ከተመሰረተ በኃላ ትኩረት ሰጥቶት እምዲጠናቀቅ የተደረገ ፕሮጀክት መሆኑን አብራርተዋል ።

አክለውም አቶ በለጠ ጫካ የክላስተር ማዕከሉ ግንባታ በሥራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ዘርፍ የከተማ አስተዳደሩ ካለበት የበጀት ውስንነት ምክንያት በማህበር ተደራጅተው ለሚመጡ ሥራ አጥ ዜጎች የማምረቻ ሼድ ችግር በመፍታቱ ረገድ ለከተማችን ትልቅ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተናግረዋል።

የክላስተር ማዕከሉ ከተማችን ካለው ምቹ ሁኔታ አንጻር እና በቂ የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦት በበቂ ደረጃ ለማቅረብ የሚያስችል ሰብስቴሽን ያለው በመሆኑ በማንፋክቸሪንግ ዘርፍ የተደራጁ ከትናንሽ እስከ ትላልቅ ማሽነሪዎች ማስጠቀም የሚችል ማዕከል እንደሆነ ገልፀው በቀጣይም ለዘርፉ ተገቢውን ትኩረት ተሰጥቶት ወደ ሙሉ አገልግሎት ለማስገባት እንደሚሰራ አመላክተዋል።

የቡኢ ከተማ አስተዳደር ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ኢ/ር መስፍን መኩሪያ ክላስተር ማዕከሉ በአንድ ሺህ አንድ መቶ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ህንፃ እንደሆነ እና በማኒፋክቸሪንግ ዘርፉ ለተደራጁ ማህበራት ተጠቃሚ በማድረግ ከ200 በላይ ስራ አጥ ዜጎችን መያዝ የሚችል ተቋም ነው ብለዋል ።

አክለውም ኢ/ር መስፍን መኩሪያ የክላስተር ማዕከሉ ግንባታ መጠናቀቁ ቀድሞ እንደ ከተማ በሼድ እጥረት ችግር ምክንያት ለሚስተዎሉ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ የሚሰጥ እንደሆነ ገልፀዋል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን፦
ቴሌግራም https://t.me/ButajiraCommunication/58
ፌስቡክ https://www.facebook.com/buta1921/
ዩቲዩብ
https://youtube.com/
ትዊተር https://mobile.twitter.com/ButajiraB
ኢንታግራም https://www.instagram.com/butajirab

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኮሚቴ ተለይተው የቀረቡ የውርስ የቀበሌ ቤቶች የሰፈሩባቸው ቦታዎች በኢንቨስትመንት እንዲለሙ ውሳኔ አሳለፈ።(ቡታጅራ ጥር 17/2017 የመንግስት ክሙኒኬሽን)...
25/01/2025

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኮሚቴ ተለይተው የቀረቡ የውርስ የቀበሌ ቤቶች የሰፈሩባቸው ቦታዎች በኢንቨስትመንት እንዲለሙ ውሳኔ አሳለፈ።

(ቡታጅራ ጥር 17/2017 የመንግስት ክሙኒኬሽን)
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኮሚቴ በማዘጋጃ ቤት ለኢንቨስትመንት ተለይተው የቀረቡ #45 የሚሆኑ የውርስ የቀበሌ ቤቶች የሰፈሩባቸው ቦታዎች ከተማውን በሚመጥኑ ኢንቨስትመንት ስራ እንዲለሙ ውሳኔ አሳልፏል።

የቡታጅራ ከተማ ከንቲባ አቶ አብዱ አህመድ በኢንቨስትመንት እንዲለሙ የቀረቡት የውርስ የቀበሌ ቤቶችና ቦታዎች በኢንቨስትመንት እንዲለሙ ሲደረግ ከስራ ዕድል ፈጠራ ጀምሮ ከተማዋ አንድ ደረጃ ከፍ የሚያደርግ በርካታ ፋይዳዎች የሚያስገኝ ከመሆኑም በላይ የከተማው ገፅታ ከመቀየር አንፃር ከፍተኛ ሚና የሚኖረው ስለሆነ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

የመንግስት ቤቶች የሰፈሩባቸው ቦታዎችን ለኢንቨስትመንት ስራ ለማዋል የወጣው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ደንብ ቁጥር 10/2016 መሠረት ለኢንቨስትመንት የቀረቡት የውርስ የቀበሌ ቤቶች የሰፈሩባቸው ቦታዎችን እንዲለሙ ሲደረግ የነዋሪዎቹን መብት ጠብቆና ተግባብቶ መሆኑ ጥሩና ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው።

እነዚህና ቀጣይም ተለይተው የሚቀርቡ የውርስ የቀበሌ ቤቶች የሰፈሩባቸው ቦታዎች ከተማውን በሚመጥን መልኩ እንዲለሙ የሚመለከታቸው ተቋማት ልዩ ትኩረት በመስጠት ተፈፃሚነቱን ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልፀዋል።

መልሶ ማልማቱን በታሰበው ሁኔታ ለማስቀጠል ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀው ደረጃውን የጠበቀ ግንባታና ስራ እንዲኖር ያደርጋል ብለዋል።

መመሪያውም ለነዋሪው ትኩረት የሰጠ መሆኑ የተሻለ እንደሆነና ይህንኑ ተግባራዊ በማድረግ ይሰራል ብለዋል።

የማዘጋጃ ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ተስፋዬ አህመድ (ኢንጂነር) የኢንቨስትመንት እና የንግድ ቦታዎች መልሶ ማልማት አካል የሆኑ አካባቢ ከሚመለከታቸው ነዋሪዎች ጋር በመወያየት ስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል።

በዚህም የተሻለ አስተያየት እና ተቀባይነት እንዳላቸው ተናግረዋል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን፦
ቴሌግራም https://t.me/ButajiraCommunication/58
ፌስቡክ https://www.facebook.com/buta1921/
ዩቲዩብ
https://youtube.com/
ትዊተር https://mobile.twitter.com/ButajiraB
ኢንታግራም https://www.instagram.com/butajirab

ከውሃ ስራዎች በተጨማሪ የሌማት ትሩፋት ስራዎችን በስፋት እያከናወነ እንደሆነ የቡታጅራ ውሃ ስራዎች ድርጅት አስታወቀ።(ቡታጅራ ጥር 17/2017 የመንግስት ኮሙኒኬሽን)በዛሬው እለትም የከተማዋ...
25/01/2025

ከውሃ ስራዎች በተጨማሪ የሌማት ትሩፋት ስራዎችን በስፋት እያከናወነ እንደሆነ የቡታጅራ ውሃ ስራዎች ድርጅት አስታወቀ።

(ቡታጅራ ጥር 17/2017 የመንግስት ኮሙኒኬሽን)
በዛሬው እለትም የከተማዋ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ሳሙኤል ማርቆስ የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ሰይድ አማን (ኢንጂነር) በተገኙበት በዘቢዳር ቀበሌ ውሃ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ክፍት ቦታ በዘር የመሸፈን ስራ ተከናውኗል።

የቡታጅራ ውሃ ስራዎች ድርጅት ከከተማ ግብርና በመተባበር ከውሃ ስራዎች በተጨማሪ የሌማት ትሩፋት ስራዎችን በተቋሙ #5 ሳይቶች እያከናወነ እንደሆነ ዋና ስራ አስኪያጁ ሰይድ አማን (ኢ/ር) ገልፀዋል።

የቡታጅራ ከተማ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ሳሙኤል ማርቆስ የሌማት ትሩፋት ስራዎችን በሰፊው ትኩረት ሰጥቶ መስራትና ለአገልግሎት ማቅረብ እንደሚገባ ገልፀዋል።

ህዝቡ አገልግሎት የሚያገኝባቸው ተቋሞች በሚኖራቸው ክፍት ቦታ የሌማት ትሩፋት ልማት እና ፍራፍሬ በመዝራትና በመትከል ለማህበረሰቡ አገልግሎት ማቅረብ ያስፈልጋል።

የውሃ ስራዎች በተሻለ ሁኔታ እየሰራበት መሆኑን አንስተው በሌሎችም አገልግሎት ሰጪ ተቋሞች አካባቢ የጀሩ ትኩረት ሰጥተው መስራት ማፀደቅ እና ለአገልግሎት ማቅረብን አቅደው መስራት እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል።

የቡታጅራ ውሃ ስራዎች ዋና ስራ አስኪያጅ ሰይድ አማን (ኢ/ር) ድርጅቱ ከከተማ ግብርና በመተባበር ከውሃ ስራዎች በተጨማሪ የሌማት ትሩፋት ስራዎችን በስፋት በተቋሙ #5 ሳይቶች እያከናወነ እንደሆነ ገልፀዋል።

በድርጅቱ የተጀመሩ የሌማት ትሩፋት ስራዎች ፀድቆ ለአገልግሎት ለማብቃት ትኩረት በመስጠት እየሰሩ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ልማቱንም በቀላል የመስኖ ዘዴ እያለሙ እንደሆነ ገልፀው ለሌሎችም ማገዝ እንደሚፈልጉ ዝግጁነታቸውን አረጋግጠዋል።

የከተማዋ ረዳት የመንግስት ተጠሪና የብልፅግና ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ መኮንን አሰፋ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ማሩፍ ኢላሉ ፣የድርጅቱና የግብርና ጽ/ቤት ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን፦
ቴሌግራም https://t.me/ButajiraCommunication/58
ፌስቡክ https://www.facebook.com/buta1921/
ዩቲዩብ
https://youtube.com/
ትዊተር https://mobile.twitter.com/ButajiraB
ኢንታግራም https://www.instagram.com/butajirab

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት የከተማዋን ውበትና ጽዳት ለማስጠበቅ እንደሚሰራ ገለፀ።ቡታጅራ ጥር 17/2017 ጽ/ቤቱ (ከCASPW) የወጣቶች "የማህበረሰብ አቀፍ አገ...
25/01/2025

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት የከተማዋን ውበትና ጽዳት ለማስጠበቅ እንደሚሰራ ገለፀ።

ቡታጅራ ጥር 17/2017
ጽ/ቤቱ (ከCASPW) የወጣቶች "የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ለስራ ሽግግር"መሪ ሀሳብ በ #3ቱም ቀበሌ እንደሚሰራ አስታወቀ።

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ምክትልና የስራ እድል ፈጠራ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከበደ አድብብ ከተማዋን ለመኖሪያ ምቹ ለማድረግ ወጣቶችንና የህበረተሰብ ክፍል በማሳተፍ በ3ቱም ቀበሌያት በበጎ ተግባራት በጽዳት ዘመቻ አቀመ ደካሞች እና አረጋውያንን መደገፍ ከሁሉም የሚጠበቅ እንደሆነ ገልፀዋል።

በሌሎችም ዘርፍ ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን በመጠቆም በዚህም በከተማችን በስራ እድል ፈጠራ ከ465 አባላት በላይ በፕሮግራሙ ታቅፈው ጎን ለጎን በዚው የበጎ ተግባራትም ላይ በመሳተፍ ህብረተሰቡን በጉልበታቸው በእውቀታቸው እና በገንዘባቸው ድጋፍ በማድረግ ሰፊ ችግር ፈቺ ተግባራት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

ዛሬ በእሬንዛፍና በእሬሻ ቀበሌ ወጣቶች የቀበሌ አስተዳደር አመራሮች እና የቀበሌ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊዎች በፅዳት ዘመቻ እና በኮሪደር ልማት የተተከሉ የዉበት ተክሎች አበባዎችን በማረም, ዉሃ በማጠጣት, በመንከባከብ ሲሳተፉ መቆየታቸውን ከስፍራው ተገኝተን ተመልክተናል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን፦
ቴሌግራም https://t.me/ButajiraCommunication/58
ፌስቡክ https://www.facebook.com/buta1921/
ዩቲዩብ
https://youtube.com/
ትዊተር https://mobile.twitter.com/ButajiraB
ኢንታግራም https://www.instagram.com/butajirab

በምስራቅ ጉራጌ ዞን የ2017 ዓ.ም ዞናዊ  የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ ይፋዊ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በሶዶ ወረዳ አዳዘር ቀበሌ እየተካሄደ ይገኛል።ጥር  17/2017"የተቀናጀ ግብርና ለ...
25/01/2025

በምስራቅ ጉራጌ ዞን የ2017 ዓ.ም ዞናዊ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ ይፋዊ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በሶዶ ወረዳ አዳዘር ቀበሌ እየተካሄደ ይገኛል።
ጥር 17/2017
"የተቀናጀ ግብርና ለቤተሰብ ብልጽግና"በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄደው የአፈርና የውሃ ጥበቃ ስራ ለ30 ቀን የሚቆይ ሲሆን በዚህም በ93 ተፋሰስ ላይ 17500 ሄክታር መሬት እንደሚለማ ተመላክቷል።

በማብሰሪያ ፕሮግራሙ ላይ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን፣የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሠለ ጫካ ፣የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አፈ ጉባዔ ክቡር አቶ እንዳልካቸው ጌታቸው ጨምሮ የዞኑ አመራሮች ፣ የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር አመራሮች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል ።
መረጃው፦የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን፦
ቴሌግራም https://t.me/ButajiraCommunication/58
ፌስቡክ https://www.facebook.com/buta1921/
ዩቲዩብ
https://youtube.com/
ትዊተር https://mobile.twitter.com/ButajiraB
ኢንታግራም https://www.instagram.com/butajirab

ጥር 16/2017የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ባለሙያዎች ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር አብሮ በመዘመን ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎች ለህብረተሰቡ ማድረስ ይጠበቅባቸዋል-    አቶ ዘሪሁን እሸቱ   የኮሙኒኬሽንና...
24/01/2025

ጥር 16/2017

የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ባለሙያዎች ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር አብሮ በመዘመን ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎች ለህብረተሰቡ ማድረስ ይጠበቅባቸዋል- አቶ ዘሪሁን እሸቱ

የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ባለሙያዎች ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር አብሮ በመዘመን ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎች ለህብረተሰቡ ማድረስ ይጠበቅባቸዋል ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ ዘሪሁን እሸቱ ተናግረዋል ።

ሃላፊው ለዞኖችና ልዩ ወረዳዎች፣ለሴክተር መ/ቤቶች ክላስተር የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሮች በሆሳዕና ከተማ የተዘጋጀው የአቅም ግንባታ ስልጠና ሲጠናቀቅ እንዳሉት የዘርፉ ባለሙያዎች ወቅታዊ፣ታኣማኒና በዘመኑ የቴክኖሎጂ አማራጭ ተደራሽ የሆነ መረጃን የማቅረብ ሃላፊነት አለባቸው።

የስልጠናው ዋናው ዓላማ ይህን አላማ ብቻ ሳይሆን የተቋም ግንባታን ታሳቢ ያደረገ በመሆኑ ሰልጣኞቹ ወደየ መዋቅራቸው በመሄድ ባለሙያዎቹን ማሰልጠን ሲቻል ነው ብለዋል።

ዘመኑ የቴክኖሎጂ ዘመን እንደ መሆኑ መጠን የሚዲያ ባለሙያዎች ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር አብሮ በመዘመን ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎች ለህብረተሰቡ ለማድረስ መረባረብ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

በሀገራችን የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞን እውን ለማድረግ የተዛቡ ትርክቶችን በሀሳብ የበላይነት በማሸነፍ ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን ማጠናከር ላይ ትኩረት ተደርጎ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

ሚዲያ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና እና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ላይ በንቃት በመሳታፍ የህዝቦችን አንድነት ሊያጠናክር በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ነው አቶ ዘሪሁን የገለፁት።

በክልሉ የሚገኙ መልካም ገጽታዎችን እና የተጀመሩ የልማት ስራዎችን በማስታዋወቅ በሁሉም መዋቅር ላይ የሚገኙ ሚዲያዎች የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

ሰልጣኞች በበኩላቸው እንደተናገሩት ትክክለኛ እና ተጨባጭ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው።ባስልጠናው መረጃን በብቃት ማስተዳደርና መጠቀም የሚያስችል አቅም ማግኘታቸውንም ተናግረዋል።

የታችኛው መዋቅሮች በእውቀት እና ክህሎት ላይ የተመሰረተ አገልግሎትን ለማህበረሰቡ ለመስጠትና የክህሎት ክፍተትን ለመሙላት የተሰጠው ስልጠና አጋዥ እንደሆነ ገልፀዋል።

በስልጠናውም የማህበራዊ ሚዲያ ምንነትና አስፈላጊነት ፣የአጀንዳ ቀረጻ ምንነትና የአጀንዳ አቀራረጽ ፣የገጽ ለገጽ ሚዲያ ምንነትና አሰራር፣ የዜና አጻጻፍና ስለ ባለሙያዎች ስነ ምግባር፣ የሚዲያ ሞኒተሪንግ አሰራርና የህዝብ አስተያየት አሰባሰብ ዙሪያ በቂ እውቀት ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

ስልጠናው በቀጣይ በመንግስትና ህዝብ መካከል አወንታዊ ተጽዕኖ በመፍጠርና የሚዲያ ሰራዊትን በመገንባት ገዥ ትርክት በማጎልበት የተጀመሩ የልማት ተግባራትን ለማስቀጠል የሚያስችል ነው ብለዋል።
ከክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን

ጥር 15/2017የቡታጅራ ከተማ ምክር ቤት ለከተማውና ለቀበሌው የሴቶች የምክር ቤት አባላት በውሳኔ ሰጪነትና በአመራር ብቃት ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ስልጠና ሰጥቷል።ስልጠናው ሴቶች በዕለት ከዕ...
23/01/2025

ጥር 15/2017

የቡታጅራ ከተማ ምክር ቤት ለከተማውና ለቀበሌው የሴቶች የምክር ቤት አባላት በውሳኔ ሰጪነትና በአመራር ብቃት ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ስልጠና ሰጥቷል።

ስልጠናው ሴቶች በዕለት ከዕለት ኑሮዋቸው የሚያስተላልፉት ውሳኔዎች የበሰለና ትክክለኛ እንዲሆን እንዲሁም በሀገሪቷ ፖለቲካ እንቅስቃሴ የሴቶች የውሳኔ ሰጪነትና ተሳታፊነት ለማሳደግ የሚረዳ ነው መሆኑ በስልጠናው ተገልጿል።

የቡታጅራ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ በድሩ ሻፊ እንደገለፁት፦የቀበሌ ሴቶች ኮከስ አመራሮች የከተማ ምክር ቤት አባላት የአመራር ክህሎታቸውን ለማሳደግና የአመራር ተሳትፏቸውን ለማሳደግ እንዲሁም የሴቶች ኮከስ በህገ-መንግስቱ ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ያሳድጋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ሴቶች በፖለቲካና በልማት ዙርያ ላይ ተሳትፏቸውንና የውሳኔ ሰጪነት አቅማቸውን ለማሳደግ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታልም ብለዋል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን፦
ቴሌግራም https://t.me/ButajiraCommunication/58
ፌስቡክ https://www.facebook.com/buta1921/
ዩቲዩብ
https://youtube.com/
ትዊተር https://mobile.twitter.com/ButajiraB
ኢንታግራም https://www.instagram.com/butajirab

ትውልድ ላይ መስራት አማራጭ የሌለው ሀገርን መታደግ ነው፦ከንቲባ አብዱ አህመድትውልድ ላይ መስራት አማራጭ የሌለው ሀገርን መታደግ ነውና ሕፃናትን ከመንከባከብ የሚበልጥ ፕሮጀክት የለም ሲሉ የ...
23/01/2025

ትውልድ ላይ መስራት አማራጭ የሌለው ሀገርን መታደግ ነው፦ከንቲባ አብዱ አህመድ

ትውልድ ላይ መስራት አማራጭ የሌለው ሀገርን መታደግ ነውና ሕፃናትን ከመንከባከብ የሚበልጥ ፕሮጀክት የለም ሲሉ የቡታጅራ ከተማ ከንቲባ አቶ አብዱ አህመድ ተናገሩ።

( ቡታጅራ ጥር 15/2017 የመንግስት ኮሙኒኬሽን)ህፃናትን መታደግ በኢትዮጲያ እድገትና ልማት ትልቁን አሻራ ማሳረፍ ነውና በከተማችን ቀዳሚ ተግባር አድርገን እንሰራለን።በትምህርት ቤት የህፃናት ምገባን በዘላቂ ለማስቀጠል የሁሉም ርብርብና ቅንጅታዊ ስራ ይጠይቃል።

ይህንን የገለፁት ከንቲባው ከተማ አስተዳደሩ ዛሬ ከ"SNV"የኔዘርላድ የልማት ድርጅት በተማሪዎች የወተት/እርጎ ምገባ የሀብት አሰባሰብ ላይ ባለሀብቶች፣ተቋሞችንና ተጽእኖ ፈጣሪዎችን ባወያዩበት መድረክ ላይ ነው።

በቡታጅራ ከተማ አስተዳደር በ2017 በ #5 ቅድመ 1ኛ ትምህርት ቤቶች የወተት ምገባ ተጀምሯል ከዚህ ቀደም ሲሰጥ የቆየውን በ #2 ትምህርት ቤቶች በማስፋት።

በከተማዋ #1600 ህፃናትን በፕሮግራሙ ማቀፍ ቢቻልም ከአስፈላጊነቱና ከሚፈለገው የህፃናት ቁጥር አንፃር ግን በቂ አይደለም ተደራሽነቱን ልናሳድገው ይገባል።

ከንቲባ አቶ አብዱ ፕሮግራሙን በዘላቂ ለማስቀጠል ያስችል ዘንድ ሁሉም መሳተፍና በኢትዮጲያ እድገትና ልማት አሻራ ማኖር ስለሚኖርበት በጋራ ማስቀጠሉ አስፈላጊ ሆኗል።ትውልድ ላይ መስራት ቁልፍ ስራችን ነው።በዛሬው መድረክ የተሳተፉ የፕሮግራሙ አጋዥነታቸውን አሳይተዋል።

የከተማው ከንቲባ አብዱ አህመድ በምግብ እጥረት ትምህርት ቤት የማይሄዱ ህፃናት በርካታ ናቸው። አንድም ህፃን በዚህ ምክንያት ከትምህርት ቤት እንዳይቀር የእድገት የአእምሮ ብልፅግና ችግር እንዳይገጥመው ማድረግ የሁላችን ኃላፊነት ነው።

የኢትዮጲያን ዘላቂ ተወዳዳሪነት የትምህርት ጥራት ለማምጣት ጅምር ላይ የህፃናት እድገት ብልፅግና ላይ መስራት ነው ወሳኙ። ፕሮግራሙን ማስቀጠል ከሁላችን ይጠበቃል።

መመገብ ብቻ ሰይሆን የተመጣጠነ ሆኖ በጥራት ዘላቂ ሆኖ ማስቀጠል ይገባል።ለዚህ ደግሞ የሁሉም ድጋፍ ያስፈልጋልና ጥሪ አቅርበዋል።
ለድርጅቱ እንዲሁም በመድረኩ ተገኝተው ድጋፍ በማድረግ አጋዥነታቸውን ላረጋገጡ ሁሉ ምስጋና አቅርበው ሁሉም የበኩሉን ኃላፊነት መወጣት እንዳለበትም አሳስበዋል።

የ"SNV" የኔዘርላድ የልማት ድርጅት ተወካዮች የህፃናት ምገባ አስፈላጊነት ርዕሰ ጉዳይ ላይ ገለፃ አቅርበዋል በመድረኩ የተገኙ ሁሉም አካላት በትምህርት ቤት በመገኘት የምገባ ሂደቱን ተመልክተዋል።

ተገቢውን አመጋገብ ለህፃናት መመገብ በትውልድ መካከል የሚኖረውን ክፍተት የሚሸፍን ነው።ህፃናት ላይ መስራት ከምግብነት ያለፈ ነው።

SNV የኔዘርላድ የልማት ድርጅት ነገ ሀገር መረከብ የሚችሉ ቅድመ 1ኛ ተማሪዎች በችግር ምክንያት ቤት መቅረት የለባቸውም በሚል እየሰራ ይገኛል።

የልማት ድርጅቱ ዓለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው በኢትዮጲያ ከ1974 ጀምሮ እየሰራ ያለ 18 ፕሮጀክቶችን በማንቀሳቀስ #6 ሚሊዮን ህዝብ ተጠቃሚ በማድረግ #597 ወረዳዎች ላይ ይሠራል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን፦
ቴሌግራም https://t.me/ButajiraCommunication/58
ፌስቡክ https://www.facebook.com/buta1921/
ዩቲዩብ
https://youtube.com/
ትዊተር https://mobile.twitter.com/ButajiraB
ኢንታግራም https://www.instagram.com/butajirab

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በመስቃን እና ማረቆ አዋሳኝ አካባቢዎች በተፈጠረው ግጭት ተፈናቅለው ወደ ቀዬአቸው የተመለሱ የህብረተሰብ ክፍሎችን አነጋገሩ (ሆሳዕና፣ጥር 14/20...
22/01/2025

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በመስቃን እና ማረቆ አዋሳኝ አካባቢዎች በተፈጠረው ግጭት ተፈናቅለው ወደ ቀዬአቸው የተመለሱ የህብረተሰብ ክፍሎችን አነጋገሩ

(ሆሳዕና፣ጥር 14/2017 ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) ከዚህ ቀደም በመስቃን እና ማረቆ አዋሳኝ ቀበሌያት በተፈጠረው ግጭት ተፈናቅለው ወደ ቀዬአቸው የተመለሱ የህብረተሰብ ክፍሎችን አነጋገሩ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በምስራቅ ጉራጌ ዞን ምስራቅ መስቃን ወረዳ እና በማረቆ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ ቀበሌዎች በተፈጠረው ግጭት የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ በማቋቋም ሂደት የክልሉ መንግስት ድጋፍ እያደረገ ነው ብለዋል።

በግጭቱ ለተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘላቂና ጊዜያዊ ድጋፍ ለማድረግ የክልሉ መንግስት ያለውን ዝግጁነት ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

ከግጭቱ ማትረፍ የፈለጉ ሀይሎች የቀጠናውን ሰላም እንዳይረጋጋ ያደረጉት ጥረት በሰላም ወዳዱ ህብረተሰብ፣በሀገር ባህል ሽማግሌዎች፣በሀይማኖት አባቶች፣በአመራሩ እና በጸጥታ ሀይሉ የላቀ ጥረት በአካባቢው አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

በሁለቱም ወገን ተፈናቅለው አሁን ወደ መኖሪያ አካባቢያቸው የተመለሱ የህብረተሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየት እንደገለጹት የክልሉ መንግስት ላደረገላቸው የላቀ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

መንግስት የጀመረው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል።
ከክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን፦
ቴሌግራም https://t.me/ButajiraCommunication/58
ፌስቡክ https://www.facebook.com/buta1921/
ዩቲዩብ
https://youtube.com/
ትዊተር https://mobile.twitter.com/ButajiraB
ኢንታግራም https://www.instagram.com/butajirab

የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ አገልግሎቶችን በማስፋት እየሰራ መሆኑን ዩኒየኑ አስታወቀ።(ቡታጅራ ጥር 14/2017 የመንግስት ኮሙኒኬሽን)የሰብል ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ፤ምርትና ...
22/01/2025

የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ አገልግሎቶችን በማስፋት እየሰራ መሆኑን ዩኒየኑ አስታወቀ።

(ቡታጅራ ጥር 14/2017 የመንግስት ኮሙኒኬሽን)

የሰብል ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ፤ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል የሚያግዙ አቅርቦቶችን እና በበጎ ፈቃድ ስራዎች በመሳተፍ አገልግሎቶቹን በማስፋት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ዋልታ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን አስታወቀ።

አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ማቅረብና ማስተዋወቅ፣የጓሮ አትክልት ዘሮችና ኬሚካሎች በማቅረብ በተመጣጣኝ ዋጋ እያሰራጨ ይገኛል።

በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን የዋልታ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ያሲን ሀሰን የኑሮ ውድነት በማረጋጋት ለማህበረሰቡ የሰብል ምርት በተመጣጠኝ ዋጋ በማቅረብ፤ በእንስሳት ዘርፍ እና የአፈር ማዳበሪያ በማቅረብ ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ዋልታ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን #31 ማህበራት ከ10 ሺህ 6 መቶ በላይ አባላት ያሉት አጠቃላይ 26 ሚሊየን ብር በጀቱን በማሳደግ በምስራቅ ጉራጌ ዞን ወልቂጤ እና ማረቆ ልዩ ወረዳ ተደራሽ በመሆን እየሰራ ይገኛል።

አቶ ያሲን ሀሰን አገልግሎቶችን በማስፋት ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል እየሰራ እንደሆነና የወተት የእንቁላል ምርት እንዲሻሻል የሚያስችል ምጥን መኖ በተመጣጣኝ ዋጋ በጥራት በማዘጋጀት እያቀረበ እንደሆነ ገልፀዋል።

ዩኒየኑ በበጎ ፈቃድ የተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን ለአቅመ ደከሞች ዓመታዊ ክፍያ እና ሌሎች በጎ ተግባር ላይ በመሳተፍም ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል።

የመስቃን ወረዳ ባቀረበላቸው 3500 ካሬ ሜትር ቦታ የዚህ አካል በሆነው ዊጣ ቀበሌ #900 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ግንባታ እና ዝግጅት በማጠናቀቅ 5250 እንቁላል ጣይ ዶሮዎችን ለማስገባት ቀሪ ስራዎችን እያጠናቀቁ እንደሆነ ገልፀዋል።

ማህበሩ ዋጋ ማረጋጋት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ገልፀው አካባቢው ባለው የምርት አቅም ልክ ለመስራት የቅንጅት ስራ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የአርሶ አደሩን ስራ ለማሻሻል ኮምባይነር ለማቅረብ ዝግጅት እየተደረገ እና ወደ ኢንዱስትሪ ለማሳደግ እና በአካባቢው ያለውን አቅም በማየት የፍራፍሬ ምርት ወደ ውጭ ለመላክም ዕቅድ በመያዝ እየተሰራ እንደሆና ተናግረዋል።

የእንስሳት ምጥን መኖ ጥራቱን የጠበቀና በኢትዮጲያ ግብርና ሚኒስቴር እውቅና ከ3 ዓመት በፊት የተሰጠው መሆኑን ገልፀዋል።

በዩኒየኑ የእንስሳት ምጥን መኖ ቅንብር ባለሙያ አቶ ፈቱ ሽፋ እየተቀነባበረ ያለው የእንስሳት ምጥን መኖ በምርት ላይ አመርቂ ውጤት የሚያሳይና ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻልም አስፈላጊ መሆኑን አርቢዎች ምስክርነት ስለመስጠታቸው አንስተዋል።

በዩኒየኑ መሸጫ መደብር እና በየአካባቢዎች ማህበራት ምርቶችን መመገኘት እንደሚችሉም አቶ ፈቱ ጠቁመዋል።

የከብት ድለባ፣የወተት ላም፣የእንቁላል ጣያ ዶሮ፣የቄብና ኮከኔ ዶሮ፣የበግና የፍየል ማሞከት እና የጥጃ የእንስሳት ምጥን መኖ አዘጋጅቶ ያቀርባል።

Address

Butajira

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን Butajira City Govn.Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን Butajira City Govn.Communication:

Videos

Share