ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore Yoftahie book shop locate at the center of Bahir Dar city .kebele 04 ቋሪት(ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል

ዮፍታሔ ማለት እግዚአብሔር ይከፍታል ማለት ሲሆን እንድገናም የአገራችን ታላቁና ታዋቂው ባለቅኔ፣ ደራሲ፣ ጸሐፊ ተውኔት ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤን ለማስታወስ የተሰየመ ነው። እኛም የተለያዩ መጻሕፍትን፣ መጽሔትና ጋዜጣን በችርቻሮና በጅምላ ማቅረብና መሸጥ ነው። የተመሠረተውም በ2004 ዓመተ ምህረት ነው። ዓላማችን ንባብን ማስፋፋት እና መጽሐፍ በእያንዳንዱ ሰው እጅ ገብቶ እንዲነበብ ማድረግ ነው።

ገድለ አቡነ እስትንፋስ ክርስቶስ #ዘጠኝ ዓመት ዓባይ ባሕር ውስጥ በራሳቸው ተዘቅዝቀው በመቆም ለኢትዮጵያ  የጸለዩዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore            አድ...
17/01/2025

ገድለ አቡነ እስትንፋስ ክርስቶስ
#ዘጠኝ ዓመት ዓባይ ባሕር ውስጥ በራሳቸው ተዘቅዝቀው በመቆም ለኢትዮጵያ የጸለዩ
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore

አድራሻችን👇
🇪🇹 ባሕር ዳር ቀበሌ 04
➠ ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል
+251918004191 +251902093535
Contact -
https://t.me/yoftahiebooks

" የትምህርት ሥርዓታችን ባለ ጥሩ ስብዕናም፥ ጥሩ ባለሙያም አያደርግም። "  ዓለማየሁ ዋሴ (ዶክተር)
16/01/2025

" የትምህርት ሥርዓታችን ባለ ጥሩ ስብዕናም፥ ጥሩ ባለሙያም አያደርግም። " ዓለማየሁ ዋሴ (ዶክተር)

ከእቴጌ ዕሌኒ እስከ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ       የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ግንኙነት            በዲያቆን ዳንኤል ክብረት ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore    ...
15/01/2025

ከእቴጌ ዕሌኒ እስከ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ
የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ግንኙነት
በዲያቆን ዳንኤል ክብረት
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
አድራሻችን👇
🇪🇹 ባሕር ዳር ቀበሌ 04
➠ ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል
+251918004191 +251902093535
Contact -
https://t.me/yoftahiebooks

መጽሐፈ ሳዊሮስ ዘእስሙናይን ትርጉም በመምህር ኤፍሬም ክንዱዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore    አድራሻችን👇🇪🇹 ባሕር ዳር ቀበሌ 04  ➠ ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገ...
15/01/2025

መጽሐፈ ሳዊሮስ ዘእስሙናይን
ትርጉም በመምህር ኤፍሬም ክንዱ
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
አድራሻችን👇
🇪🇹 ባሕር ዳር ቀበሌ 04
➠ ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል
+251918004191 +251902093535
Contact -
https://t.me/yoftahiebooks

መጽሐፈ ዜና ሥላሴ  የደብረ ሊባኖስ ተክለሃይማኖት አንድነት ገዳም እትም  ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
15/01/2025

መጽሐፈ ዜና ሥላሴ
የደብረ ሊባኖስ ተክለሃይማኖት አንድነት ገዳም እትም
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore

14/01/2025

-ኦርቶዶክሳውያን የነበሩ ግን "የቤተክርስቲያን በዓላት የሥራ ባህልን የሚያዳክም ነው" በማለት የሚያምኑ ቀደምት ጸሐፊያንና ደራሲያን መካከል
Yosef Fiseha Sewunet
1.)ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም (1875-1969 ዓ.ም.) “ኦቶባዮግራፊ (የሕይወቴ ታሪክ)” በተሰኘ መጽሐፋቻው ላይ ተጽፏል፡፡

-ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ዲያቆን ነበሩ፡፡ ከዳዊት ከፍ ያለ ትምህርት አልተማሩም ነበር፡፡ የቤተክህነቱን ትምህርት አልገፉበትም፡፡ በልጅነታቸው በአድዋ ጦርነት ዘምተው ነበር። ራሽያ ሂደው መድፍ አተኳኮስ ተምረው ነበር፡፡ የግብርናም እውቀት ነበራቸው፡፡ የአቮካዶ ተክል በሀገራችን እንዲለመድ ያደረጉ ናቸው፡፡ ብስልና ሐሳባቸውን በመግለጽ ቀጥተኛ የሚባሉ ሰው ነበሩ፡፡ የልጅ ኢያሱ አማካሪ ነበሩ። የመጀመሪያውን የተጻፈ ሕገ መንግሥት ያረቀቁ ነበሩ። የሕይወት ታሪክ መጽሐፋቸውን አንብቡት ታሪካቸው ብዙ ነው። ቤተክርስቲያን በመሄድ ታቦት ያነግሡ ነበር፡፡ ግን “በዓላት የሥራ ባሕልን ያዳክማል” የሚል አመለካከት ነበራቸው፡፡

2.)አቤ ጉበኛ (1925 -1972 ዓ.ም.) “መሬት የማን ነው?” በሚል ጽሑፉ ላይ አስረድቷል፡፡

-አቤ ደራሲ ነው፡፡ ከፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት በላይ የቤተክህነት ትምህርት ተምሯል፡፡ ቅኔ አዋቂ ነበር፡፡ በተለይ “አንድ ለእናቱ” በተሰኘ ረጅም ታሪካዊ ልብ ወለድ ድርሰቱ ይታወቃል፡፡ ግን ቤተክርስቲያንን በተንሻፈፈ መልኩ ከሚመለከቱ ደራሲያን መካከል አንዱ ነበር፡፡ አቤ ጉበኛ ምን ይላል “በቤተክርስቲያን ….ብዙ ከንቱ ልማድ በሀገራችን ተንሠራፍቶ ይገኛል። ቤተክርስቲያን … የበዓላትን ብዛት ባስቸኳይ ቀንሳ ለመላው ተከታዮቿ ማወጅ አለባት፡፡” (መሬት የማን ነው?፣ገጽ 27፣ 1967 ዓ.ም)

-ለማንኛውም ስለ በዓላት የተሳሳተ አመለካከትና ጥያቄ ሲቀርብ የነበረው በሌላ ሃይማኖት ውስጥ ከነበሩት ብቻ አልነበረም ለማለት ነው፡፡ ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት እና አቤ ጉበኛ በአግባቡ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የበዓላት ጉዳይን በአግባቡ ባያጠኑትም ግን ሐሳባቸውን በጽሑፍ መግለጽ ችለዋል፡፡ የሐሳባቸው መነሻ ምንድን ነበር? አላውቅም። በእነዚህ ሰዎች ሐሳብ ምን ይላሉ?

-ለማንኛውም የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ስለ በዓላት ያላትን አቋምና የሥራ ባህል አስተሳሰብ ለመረዳት በጥናት ላይ ተመሥርቶ የጻፈውን ቢያንስ የመ/ር ብርሃኑ አድማስ “በዓላት ምን? ለምን? እንዴት?” የተሰኘ መጽሐፍ ብናነብ መልካም ነው፡፡

‹‹ሸሙኔ›› የቋንቋና ወግ ጨዋታበዋለልኝ አየለ◌ ◌ ◌የመጽሐፉ ስም፡- ሸሙኔደራሲ፡- መስፍን ወንድወሰንየህትመት ዘመን፡- 2016 ዓ.ምየገጽ ብዛት፡- 217የመሸጫ ዋጋ፡- 496 ብርመጀመሪያ ...
14/01/2025

‹‹ሸሙኔ›› የቋንቋና ወግ ጨዋታ
በዋለልኝ አየለ
◌ ◌ ◌
የመጽሐፉ ስም፡- ሸሙኔ
ደራሲ፡- መስፍን ወንድወሰን
የህትመት ዘመን፡- 2016 ዓ.ም
የገጽ ብዛት፡- 217
የመሸጫ ዋጋ፡- 496 ብር

መጀመሪያ መጽሐፉ በማህበራዊ ገጾች ላይ በአንዳንድ ሰዎች ሲዘዋወር ተመለከትኩ። መጽሐፍ
ፌስቡክ ላይ ማስተዋወቅ የተለመደ ስለሆነ ብዙም ትኩረት አልሰጠሁትም ነበር። እየቆየ ሲሄድ ግን ተደጋገመብኝ። ሰዎች የራሳቸውን አተያይ ጽፈው አየሁ። አብዛኞቹ ቋንቋው ላይ አተኩረዋል። በኋላ ግን የማህበረሰብ ቱባ ቋንቋና ወግ እንደምወድ የሚያውቅ አንድ ጓደኛዬ ይህን መጽሐፍ ማንብ አለብህ አለኝ። አነበብኩት።

ብዙዎች መጽሐፉን ሳላስቀምጥ ነው የጨረስኩት፣ በአንድ ቀን ነው የጨረስኩት፣ በአንድ ምሽት ነው የጨረስኩት… እያሉ ገልጸውታል። እኔ ግን በተቃራኒው ነው የሆነብኝ። ያቺ 215 ገጽ መጽሐፍ ሙሉ ቅዳሜና እሁድ፣ እንዲሁም አንድ ምሽት ወስዳብኛለች። እያነበብኩ ሳለ በአንዲት ዓረፍተ ነገር ወይም አንቀጽ ወደ ሀገር ቤት እሄዳለሁ። ሌባ ጣቴን ያለሁበት ገጽ መሃል ላይ አድርጌ መጽሐፉን አጥፌ በቁዘማ ሄጃለሁ። አንድ ዓረፍተ ነገር ባነበብኩ ቁጥር በአካባቢያዬ የማስታውሰው አንድ ሰውዬ ይመጣል። የረሳሁትን አካባቢ ያስታውሰኛል። አንድ ወግ ሌላ እኔ የማውቀው የአካባቢ ወግ ያመጣብኛል።

መጽሐፉን ሳነብ፣ ካነበብኩት ይልቅ የጻፍኩት ሳይበልጥ አይቀርም። እየቆሰቆሰ የሚያስታውሰኝን የስነ ቃል ግጥሞች ጻፍ ጻፍ ይለኛል። መሳጭ ብቻ ሳይሆን ቆስቋሽ መጽሐፍ ነው። የስነ ጽሑፍ ባለሙያ ስላልሆንኩ ከስነ ጽሑፋዊ ቅርጽና ዘውግ አንፃር ምንም ማለት አልችልም። አንድ ነገር ግን ያጓጓኛል። የስነ ጽሑፍ ባለሙያዎች በዚህ መጽሐፍ ላይ ሒስ ሰርተውበት ማየት! ‹‹ምን
ይሉ ይሆን?›› እላለሁ። ምክንያቱም በየመድረኩ ሲናገሩ እንደሰማኋቸው፣ በመጽሔት ሲከራከሩ እንዳነበብኩት፤ ኪነ ጥበብ ተፈጥሯዊ ስሜትን በነፃነት መግለጽን ይጠይቃል። ስነ ጽሑፍ ያዩትን፣ የሰሙትን እና በውስጥ የተፈጠረን ስሜት መግለጽ ነው። እዚህ ላይ እንግዲህ ‹‹ስታንዳርዳይዜሽን›› እና ‹‹ፖፕላራይዜሽን›› የሚሉት አላቸው። ‹‹ስታንዳርዳይዜሽን›› ማለት አንባቢን ታሳቢ አድርጎ መጻፍ ማለት ነው። የጽሑፉን መልዕክት ታሳቢ በማድረግ ለሆነ ዓላማ የሚጻፍ ማለት ነው። በአጭሩ ለማስተማር ማለት ነው። ይህ ብዙ ጊዜ ለጋዜጣና መጽሔት ሲሆን በዚህ አይነት መንገድ የሚጻፉ መጻሕፍትም አሉ።

‹‹ፖፕላራይዜሽን›› ማለት ግን በቀጥታ የተፈጠረውን ስሜት መጻፍ ማለት ነው። ያዩትንና
የሰሙትን መጻፍ ማለት ነው። ዋና ዓላማው ስሜትን መግለጽ ነው። ስነ ጽሑፍ በዚህኛው መንገድ ሲጻፍ ነው ጥሩ ተብሎ ይታመናል፤ ወዲህ ደግሞ ማህበረሰብን ማስተማር አለበት የሚል ክርክር አለ። ሰፊ ማብራሪያውን ለስነ ጽሑፍ ባለሙያዎች እንተወውና ሸሙኔ መጽሐፍን እንመልከት።

የመጽሐፉ መቼት አማራ ሳይንት ውስጥ ነው። በይዘት በኩል፤ ዋና ገጸ ባህሪው አዝማሪ ሲሆን
ከቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት እስከ ኢህአዴግ ድረስ ያሉትን ዘመናት ይመላለስባቸዋል። በተለይም በ1977 ዓ.ም የተከሰተውን ረሃብ የሚገልጽበት መንገድ ያስለቅሳል። ወዲህ ደግሞ ወግና ጨዋታው እንደገና ያስቃል። እያሳቀ እያስለቀሰ ያልኖርንበትን ዘመን ጭምር ያሳየናል። በስነ ጽሑፍ ደረጃ ደግሞ በቋንቋ ይጫወታል።

የስነ ጽሑፍ ውበቱ ቋንቋ ነው ይላሉ ባለቤቶቹ። ቋንቋ ሲባል ታዲያ አንድ ወጥ የሆነ የጋራ አገላለጽ አይደለም፤ የየራሱ ቀለም ያለው የፀሐፊዎች አገላለጽ ማለት ነው። እዚህ ላይ ደራሲው አንድ ልዩ ነገር አሳይቶናል። ብዙዎቻችን ኖርንበት፣ አደግንበት፣ ስንናገራቸው የነበርናቸውን ቃላት ረስተናቸዋል። የምናነባቸው መጻሕፍት፣ ጋዜጦችና መጽሔቶች፣ የምንከታተላቸው መድረኮችና መገናኛ ብዙኃን፣ አዋዋላችንና በዙሪያችን ‹‹ሸሙኔ›› የቋንቋና ወግ ጨዋታ ባሉ ሰዎች ተፅዕኖ ሌላ የቋንቋ ባህል አዳብረናል። ደራሲው በዚህ ሁሉ የትምህርትና የሥራ ሂደት ውስጥ ሲያልፍ (የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መምህር እንደነበር ሰምቻለሁ) ያንን ቱባ ባህልና ቋንቋ አልዘነጋውም። ሰው እንዴት በዚያ ልክ በጥንቃቄ ራሳቸው የተናገሩት እስከሚመስል ድረስ በገጠር ሰዎች ዘዬ ይጽፋል? ወይስ ራሱም ሲናገር በእነዚያ ቃላት ይሆን? (ሲናገር ስላልሰማሁት)፤ ወይስ በቦታው ላይ በቆየባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ የሚናገሩትን እየቀረጸ ነበር? ግራ ቢገባኝ ምናልባት ድምጻቸውን እያዳመጠ ይሆን የጻፈው? የሚል ስሜት ፈጥሮብኛል።

እኔ እልም ያለ ገጠር ውስጥ ነው ያደግኩት። ምንም እንኳን ዘዬ ከአካባቢ አካባቢ የሚለያይ ቢሆንም መጽሐፉ እኔ ባደኩበት አካባቢ የሚነገሩ ብዙ ዘዬዎች አሉበት። ዳሩ ግን እነዚያን ቃላት ከመርሳቴ የተነሳ ሰምቼው የማላውቀው ቃል እየመሰለኝ ‹‹ምን ማለት ይሆን?›› እያልኩ በጽሑፉ ዓውድ ለመረዳት እታገላለሁ። ደግነቱ ጭራሹንም የማላውቃቸውን ቃላት ሳይቀር በዓውዱ መረዳት በጣም ቀላል ነው። እንደ መዝገበ ቃላትም ጭምር ያገለግላል ማለት ነው። መስማት ብቻ ሳይሆን ስናገራቸው የነበሩትን ቃላት ግን እኔ ረስቻቸዋለሁ። በኋላ ትዝ ሲለኝ ለካ ያ ቃል እኔ በጽሑፍ ቋንቋ ተላምጄው እንጂ የሚታወቅ ነበር። እንዲህ እያደረገ በቋንቋ ይጫወታል፤ ያጫውታል።

መጽሐፉ የማህበረሰብ ጥናት (ሶሾሎጂ) ለሚያጠኑ ሰዎች ብዙ ነገር ይነግራል። በነገራችን ላይ የማህበረሰብን ምንነት ለማወቅ ቃለ መጠይቅ ከማድረግ ወይም መጠይቅ ሰጥቶ ከማስሞላት ይልቅ እንደ ሸሙኔ አይነት መጽሐፍ ማንበብ ይበልጣል። ቃለ መጠይቅ በምናደርግበት ጊዜ የሚነግሩን በዚያ ቅጽበት የሚኖራቸውን ስሜት ነው። በሌላ በኩል ውስጣቸው ነፃ አይሆንም። የሆነን ነገር ታሳቢ አድርገው የሚፈሩት ነገር ይኖራል፤ የሆነ ነገር ያሳጣናል ወይም ያስገኝልናል ከሚል የውስጥ ትግል ጋር ነው የሚናገሩት። ምን ብናገር ይፈለጋል? ጠያቂው ምን ፈልጎ ይሆን? ምን ለማድረግ ይሆን? የሚል ነገር በውስጣቸው ይመሳሰላል። ስለዚህ በነፃ ልቦና አናገኛቸውም። ስነ ቃል እና ሌሎች ወጎቻቸው ግን ሰው አዝዟቸው ሳይሆን የውስጥ ስሜት አዝዟቸው፣ ነፍሳቸው የሚመራቸውን የሚናገሩት ነው። ስለዚህ ትክክለኛ የማህበረሰብ ምንነት የሚገኘው ከእንዲህ አይነት ቱባ ባህልና ወግ ነው።

ሸሙኔ የሚነግረን ይህን የማህበረሰብ ፍልስፍና እና ወግና ልማድ ነው። ድንገት ስቅስቅ ብዬ አለቅሳለሁ። የማለቅሰው በገጸ ባህሪው በተገለጸው ታሪክ ውስጥ በአካባቢያችን ወይም በቤተሰብ የማውቀው እውነተኛ ታሪክ ስላለ ነው። ለምሳሌ፤ ምኸኛት (የአዝማሪው ሚስት) ከሞተች በኋላ ልጆቿ ልብሷን እያወጡ ያሸቱታል። በአካባቢያችን እናት ወይም አባት እህት ወይም ወንድም፣ ልጅ ወይም ሌላ የቅርብ ቤተሰብ ሲሞት ልብስ ይዞ ማልቀስ የተለመደ ነው። ለሚመለከቱ ሰዎች በጣም የሚረብሸው ግን ሟች ከሞተ ከብዙ ጊዜ በኋላ ልብሱን እያወጡ ማሽተት ነው። ይህ የማውቀው ልማድ ስለሆነ እንዲህ አይነት ልማዶችን እየጠቀሰና እያስታወሰ ያስለቅሰኛል።

በገጠር ውስጥ ያለው ማህበረሰብ ፍልስፍና አልተነገረለትም። የኪነ ጥበብ፣ የሳይንስ፣ የእምነት፣ የፍልስፍና ምንጩ ከዚያ ሆኖ፣ ዳሩ ግን አልተነገረለትም። ዘመናዊ በሚባለው ተውጧል። ፍልስፍናቸው ግን ጥልቅ ነው። እንዲያውም መጽሐፉ አንዳንድ ጊዜ ከስነ ጽሑፍ ይልቅ ሪፖርት ይሆንብኛል። እዚህ ላይ ግን አንድ ነገር ታሳቢ ይደረግ። የጋዜጠኝነት ሙያ በባህሪው ከቋንቋ ውበት ይልቅ ገለጻ (ይዘት) ላይ ስለሚያተኩር የዚያ ተፅዕኖ ስለሚኖርብኝ ይሆናል። የገጠር ሰዎች በጣም ሲበዛ አማኝ ናቸው አይደል? ይህንን ማንም ያውቃል። የሚገርመው ግን በፈጣሪ ላይ ሳይቀር ያምጻሉ፤ ፈጣሪን ይቆጣሉ። በነፃነት ይፈላሰፋሉ። ሸሙኔ ይህን ሁሉ ነው የሚነግረን።

ለምሳሌ፤ በመጽሐፉ ገጽ 14 ላይ የሚከተለውን እናገኛለን።
‹‹እግዜርን አኩርፈህ ነበር የሚባለው እውነት ነው?››
‹‹እንዴታ!››
‹‹ከቶ ምን ቢያደርግህ ከኸለቀህ ተጣላህ?››
‹‹የኸለቀ አካላቴን በሞላ በእሳት ጎረብ ቢመታኝ››
‹‹አዲያ አሁን ጠብ ነህ እርቅ?››
‹‹እርቅ። ተርቅም ሽርክ!››
………… እያለ ይቀጥላል።

የገጠር ሰዎች ወግና ጨዋታ ሲያደምቁ በፈጣሪ ላይ ሳይቀር በመቀለድ ነው። ለምሳሌ፤ በክረምት ዝናብ ሳይዘንብ ዋል እደር ካለ ‹‹አንተዬ ይሄ እግዜሃር ክረምት መሆኑን ረሳው እንዴ?›› ብሎ ይጠይቃል አንዱ ገበሬ። ‹‹ምን አንተ ዴሞ እንዴት አይረሳው! አረጄ እኮ!›› እያለ ይመልሳል ሌላኛው። በዚህ ልክ ቀለል ብሏቸው መቃለዳቸው ያስፈራኝ ነበር።
ሸሙኔ መጽሐፍ እንዲህ የረሳናቸውን ወጎች ያስታውሳል። የማህበረሰብን ቱባ ምንነት ይነግረናል። መጽሐፉ ምናልባት ለከተማ አደግ ሰዎች ግን የሚያስቸግር ይመስለኛል። ቀደም ሲል እንዳልኩት የቃላቱን ትርጉም ለማወቅ ዓውዱ ስለሚነግረን አያስቸግርም። አንዳንድ ቦታ ግን ሙሉ ዓረፍተ ነገሩ አዲስ ሊሆንባቸው ይችላል ብዬ የምፈራው አለ። በእርግጥ የስነ ጽሑፍ ውበቱም ይሄው ነው። የሆነ ነገር ፍለጋ አዕምሮን ማሰራት። ሸሙኔ የንግግር ቃላትን ስለሚጠቀም አንዳንድ ሰዎች ያስቸግራቸው ይሆን? እያልኩ እፈራለሁ።
ወይም ደግሞ ‹‹ይሄን ካላወቁት ቀረባቸው!›› እያልኩ እቆጫለሁ። እኔ ሳነበው ዜማውን ጭምር እያስታወስኩ ነው። በዚያ ቃል የተናገረ የሆነ የአካባቢያችን ሰውዬ ይመጣብኛል። ዓረፍተ ነገሩን የማነበው በዚያ ሰውዬ ዜማ ነው።

ለምሳሌ፤ አንድ ቦታ ላይ ‹‹ከዚያ ምን ትመጣለች? እብድ። ›› የሚል አገላለጽ አግኝቼ ‹‹በዚህ እኔ በማውቀው ዜማ ያነቡት ይሆን?›› ብዬ አስቤያለሁ። ዜማ እኮ አይደለም! ምን ልበለው? ብቻ የሆነ የራሱ ቃና ያለው አነጋገር አለ። መልሱን የሚመልሰው ራሱ ጠያቂው ነው። እንዲህ አይነት ወጎችን አምቆ የያዘ ነው።

በከተማ ቦታ ቀልድ አዋቂ ሰው ካለ መተዳደሪያው ነው። ነገር አዋቂ፣ መልስ የሚዋጣላቸው ሰዎች፣ አገላለጻቸው አስቂኝ የሆነ… ሰዎች ብርቅ ስለሚሆኑ ነው መሰለኝ ይደነቅላቸዋል። በሀገር መሪ ደረጃ ሳይቀር (ለምሳሌ አቶ መለስ ዜናዊ) የሚናገሩት መልስ አስቂኝ ስለሚሆን በማህበራዊ ገጾች ለቀልድ ተብሎ ይዘዋወራል። ገጠር ውስጥ ግን ብዙ እንዲህ አይነት ሰዎች አሉ። ወግና ጨዋታ ወዲህ ደግሞ አሽሙር ይችሉበታል። በነገር ወጋ ያደርጋሉ። ሸሙኔ የእነዚህን ሰዎች አሽሙር ሁሉ ሳይቀር ነው የነገረን። ለምሳሌ፤ ስብሰባ ውስጥ ካድሬው በድምጽ ማጉያ (ማይክራፎን) ሲናገር አንዷ ተሰብሳቢ ከጎኗ ላሉ ሰዎች ‹‹አፉ አንሶን ደግሞ ድምጽ ማጉያ ጨመረበት!›› ትላለች። ይህን አሽሙር የተናገረችው ምናልባትም የካድሬው ድምጽ ከሌሎች የበለጠ ትልቅ ሆኖ ሳይሆን፤ ንግግሩ ውሸት እና አሰልቺ ስለሚሆን እንደ ጩኸት ስለሚያዩት ነው። መስማት ስለማይፈልጉ ነው። እንዲህ አይነት አሽሙረኞችም ናቸው። ስብሰባ ላይ ማጨብጨብ የተለመደ ነው። የሸሙኔ ወገኞች ግን ይህ አዲስ ሆኖባቸዋል። እነርሱ ጭብጨባን የሚያውቁት ለዘፈን ወይም ለመዝሙር ነው። ለዚህም ነው ‹‹አጨብጭቡ›› ሲባሉ ‹‹እኛ ያለዘፈን ጭብጨባን የምናውቀው ለእርግማን ነው›› ያሉት። ስብሰባ እርግማን ነው እያሉ ይሆን? የሸሙኔ ሰዎች አሽሙረኛ ስለሆኑ ማን ያውቃል!

ሸሙኔ ታሪክም ነው። የቋንቋ ታሪክ። ዘመን የየራሱ ባህሪ አለው። የየራሱ ቀለም አለው። ይህን ግን በጽሑፍ ውስጥ አናገኘውም። ምክንያቱም በብዛት የሚጻፈው የተማረ የሚባለው የህብረተሰብ ክፍል በሚኖርበት ከተማ ውስጥ ያለው ሁነት ነው። በዚህም ምክንያት አንዳንድ ገላጭ ቃላት ባክነው ቀርተዋል። ‹‹ቀንኛ›› የሚለውን ቃል ሸሙኔ ውስጥ ሳገኘው፤ ‹‹ይሄ ነገር ግን ለምን በሀገር አቀፉ አማርኛ ውስጥ አልታወቀም?›› አልኩ። ቀንኛ ማለት ቀን የሚበላ (ምሳ) ማለት ነው። በእኛ አካባቢ ቁርስ የሚባል ቃል አይታወቅም። ቁርስን ተክቶ የሚያገለግለው ቃል ምሳ ነው። በአጭሩ፤ በጠዋት የሚበላው ምሳ፣ ቀን የሚበላው ቀንኛ የሚባል ሲሆን ማታ የሚበላው ግን በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚታወቅበት ስም እራት ይባላል። ቀንኛን እንዳይታወቅ እና አካባቢያዊ ዘዬ ብቻ ሆኖ እንዲቀር ያደረገው የተጻፈላቸውና የተነገረላቸው ሌሎች ስለሆኑ ነው። ቋንቋ ደግሞ ማህበረሰባዊ ስምምነት ስለሆነ በብዛት በሚነገረው ነው። ሸሙኔ ግን በራሳቸው በገጸ ባህሪያቱ አካባቢያዊ ቃላት ስለሚነግረን የቋንቋ ጥናት ታሪክም ይሆናል።

አንድ ግራ የገባኝ አገላለጽ ግን አለ። የአክብሮት ስም (አንቱታ) ሲጠቀም ‹‹እርሳቸው›› መሆን የሚገባውን ‹‹እርስዎ›› በሚል ይገልጸዋል። ለምሳሌ፤ ‹‹ገበያ የዋሉም አይመስሉ አያ ጉልላት›› አልኩዎ እንደደረስኩብዎ (ገጽ 112)። ›› ይላል። ከዓውዱ መረዳት እንደሚቻለው ለማለት የተፈለገው ‹‹አልኳቸው እንደደረስኩባቸው›› ነው። ‹‹አልኩዎ፣ እንደደረስኩብዎ›› ሲል ለራሱ ለባለቤቱ የሚናገር ይመስላል። እየነገረን ያለው ግን ለእኛ ለተደራሲያን ነው። ትረካው በአንደኛ መደብ ስለሆነና ራሱ ሸሙኔ ስለሚተርከው የሸሙኔ ዘዬ ይሆን? ምናልባት በዚያ አካባቢ ያሉ ሰዎች የአክብሮት ስም የሚጠቀሙት በዚሁ አገላለጽ ሆኖ ይሆን? እንዲያ ሊሆን ይችላል ብዬ አሰብኩ።

ምንም እንኳን በዓውድ መረዳት ቢቻልም ለአንዳንድ ቃላት ግን የግርጌ ማስታወሻ ቢኖራቸው ጥሩ ነበር። ለስነ ጽሑፋዊ ውበት ጥሩ ላይሆን ይችላል። ስነ ጽሑፍ ማብራሪያና ገለጻ ሲበዛበት ጥሩ አይደለም ይባላል፤ ዳሩ ግን አንዳንድ ነገሮችን ግልጽ ለማድረግ በቅንፍ ውስጥ ይጠቀማል። ስለዚህ የመፍቻ ቃላት ቢኖሩ ጥሩ ነበር። መጽሐፉ ከስነ ጽሑፍነት ባሻገር የባህልና የቋንቋ ጥናት ጽሐፉ ከስነ ጽሑፍነት ባሻገር የባህልና የቋንቋ ጥናት የሚያደርጉ ሰዎች ሊያነቡት የሚገባ ነውና አንብቡት!
◌ ◌ ◌
(ኀሙስ ነሐሴ 09፣ 2016 ዓ.ም. ከወጣው አዲስ ዘመን ጋዜጣ የተወሰደ)

መጽሐፈ ቀለሚንጦስዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore    አድራሻችን👇🇪🇹 ባሕር ዳር ቀበሌ 04  ➠ ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል +251918004191   +2...
13/01/2025

መጽሐፈ ቀለሚንጦስ
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
አድራሻችን👇
🇪🇹 ባሕር ዳር ቀበሌ 04
➠ ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል
+251918004191 +251902093535
Contact -
https://t.me/yoftahiebooks

የኢትዮጵያ ድንበሮች ታሪክ  ✔ የሕጋዊ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ዝክረ-ነገር ➾ ከ ፲፰፻፷ ዓ.ም እስካሁን ፲፱፻፷፬ (1868 - 1972)      ✅    በአክሊሉ ታደሰ በጅጋዮፍታሔ መጻሕፍት መ...
11/01/2025

የኢትዮጵያ ድንበሮች ታሪክ
✔ የሕጋዊ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ዝክረ-ነገር

➾ ከ ፲፰፻፷ ዓ.ም እስካሁን ፲፱፻፷፬ (1868 - 1972)
✅ በአክሊሉ ታደሰ በጅጋ
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
አድራሻችን👇
🇪🇹 ባሕር ዳር ቀበሌ 04
➠ ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል
+251918004191 +251902093535
Contact -
https://t.me/yoftahiebooks

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሰን!!              ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore    አድራሻችን👇🇪🇹 ባሕር ዳር ቀበሌ...
11/01/2025

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሰን!!


ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
አድራሻችን👇
🇪🇹 ባሕር ዳር ቀበሌ 04
➠ ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል
+251918004191 +251902093535
Contact -
https://t.me/yoftahiebooks

የማይሰበረው ኤርሚያስ አመልጋ   በአንተነህ ግዛው የተጻፈ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሰን!!              ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yofta...
11/01/2025

የማይሰበረው ኤርሚያስ አመልጋ
በአንተነህ ግዛው የተጻፈ
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሰን!!

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
አድራሻችን👇
🇪🇹 ባሕር ዳር ቀበሌ 04
➠ ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል
+251918004191 +251902093535
Contact -
https://t.me/yoftahiebooks

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሰን!!መልካም በዓል              ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore    አድራሻችን👇🇪🇹 ባሕ...
07/01/2025

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሰን!!
መልካም በዓል

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
አድራሻችን👇
🇪🇹 ባሕር ዳር ቀበሌ 04
➠ ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል
+251918004191 +251902093535
Contact -
https://t.me/yoftahiebooks

ቡልቻ ደመቅሳ ሰንበቶ፡ ነፍስ ይማር   | ክቡር አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ዛሬ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ታሪካቸውንም እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን ለሀገር የሰሩ ሰዎችን ...
06/01/2025

ቡልቻ ደመቅሳ ሰንበቶ፡ ነፍስ ይማር

| ክቡር አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ዛሬ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ታሪካቸውንም እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡

ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን ለሀገር የሰሩ ሰዎችን ግለ-ታሪክ በዚህ ድረ-ገጽ ላይ እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ እነዚህ ግለ-ታሪካቸውን የምንጽፍላቸው ሰዎች ኢትዮጵያን ጠንክረው ያገለገሉ ሲሆኑ ለብዙዎችም አርአያ የሆኑ ናቸው፡፡ ከእነዚህ አንዱ ደግሞ ክቡር አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ናቸው፡፡

እኒህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ በምጣኔ ሀብት ባለሙያነታቸው ከንጉሱ ዘመን ጀምሮ ያገለገሉ ታላቅ ሰው ናቸው፡፡ ስለ አቶ ቡልቻ በእንግሊዝኛ ቋንቋ አንድ የግለ-ታሪክ መጽሀፍ ታትሞ ለንባብ የበቃ ሲሆን በበርካታ መገናኛ ብዙሀንም አበርክቷቸው በጉልህ ተጽፏል፡፡ የዚህ ግለ-ታሪክ አሰናጅ ዮአኪን ዳንኤል የአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ቤተሰብን፤ የቅርብ ሰዎችን በማነጋገር ይህን ግለ-ታሪካቸውን እንድታነቡ ጋብዛለች፡፡

ትውልድ እና እድገታቸው

በምእራብ ወለጋ ዞን በቦጂ ብርመጂ ወረዳ በ ጊንቢ ዞን ከ አባታቸው አቶ ደመቅሳ ሰንበቶ እና ከእናታቸው ነሲሴ ሰርዳ በ1923 ዓ.ም ተወለዱ፡፡
አቶ ቡሌቻ ደመቅሳ የቤተሰቡ 4ኛ ልጅ እና ብቸኛ ወንድ ልጅ ናቸው፡፡ ክቡር አቶ ቡልቻ አባታቸውን በልጅነት በሞት ቢያጡም አጎታቸው ጎቡ ሰንበቶ እንደ አባት ሆነው የወንድማቸውን አደራ ተቀብለው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ አቅማቸው የፈቀደውን ሁሉ አድርገውላቸዋል ፡፡

የትምህርት ህይወታቸው
የመጀመርያ ደረጃ ትምህርታቸውን በጊንቢ አድቬንቲስት እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በኩየራ አድቬንቲስት ተምረዋል፡፡ በወቅቱ ምንም እንኳን ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ትምህርታቸውን ቢያጠናቅቁም ከመንግስት ትምህርት ቤት ተከታትለው ካጠናቀቁ ተማሪዎች ውጭ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመግባት እድል አይገኝም ነበር፡፡

ክቡር አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ግን የቀድሞ የዩንቨርሲቲ አስተዳዳሪዎችን ዶክሜንታቸውን በማሳየት እና በማናገር ተቀባይነትን አግኝተው ወደ አራት ኪሎ ዩንቨርሲቲ በመግባት የመጀመርያ ዲግሪያቸውን በመከታተል በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ከፍተኛ ውጤት በማምጣትም ተመርቀዋል፡፡
ዩንቨርስቲው ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ለተመረቁ 10 ተማሪዎች መካከል አንዱ በመሆን ወደ አሜሪካ በመሄድ በ ሲራኪዩዝ ዩንቨርሲቲ ውስጥ ተመድበው ትምህርታቸውን ተከታትለው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ትዳር እና ህይወት

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከቀድሞ ባለቤታቸው ገና የ 18 አመት ወጣት እያሉ ነበር ከ ትዳር አጋራቸውን አዲስ አበባ ውስጥ የነርሲንግ ተማሪ የሆነችውን መንበረ ዱጉማ ጋር የተጋቡት፡፡ አቶ ቡልቻ እና መንበረ በ 26 አመታቸው የ አምስት ልጆች ወላጆች ነበሩ ፡፡ ከሁለተኛ ባለቤታቸው ከሆነችው ወ/ሮ ሄለን ገ/እግዚያብሄር ጋር ለስራ ምክንያት ወደ ግብጽ ሀገር በሚመላለሱበት ወቅት ነበር የተገናኙት ፡፡ አቶ ቡልቻ እና ወ/ሮ ሄለን አብረው በቆዩበት 50 የትዳር ዓመት አንድ ልጅን በመውለድ በአጠቃላይ የስድስት ልጆች አባት እንዲሁም አስራ አንድ የልጅ ልጅ አያት ሆነዋል፡፡

የስራ ዘመን ታሪክ
ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ በመምህርነት ሀገራቸውን አገልግለዋል፡፡ በገንዘብ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ውስጥ በበጀት ዳሬክተር እንዲሁም ምክትል የገንዘብ ሚኒስተር በመሆን አገልግለዋል፡፡ በወቅቱም በ ዳግማዊ ቀዳማዊ ንጉሰ ነገስት ሀይለስላሴ እጅግ የሚወደዱ እና ቅቡልነት ያላቸው ሰው ናቸው፡፡ የደርግ መንግስት ስልጣን ላይ ሊወጣ አከባቢ የፋይናንስ ሚንስቴር መስሪያ ቤቱን ለቀው ወደ ሀገረ አሜሪካ ሄደው ነበር ፡፡ ደርግ የስልጣን መንበሩን እንደ ተቆጣጠረ ወደ 60 የሚጠጉ ባለስልጣናትን እና ሙሁራንን ሲገድል የሳቸው ባልደረቦችን በማጣታቸው በእጅጉን ያዝናሉ፡፡ በዩኤን ዲፒ እንዲሁም በአለም ባንክ 20 አፍሪካ ሀገራትን ወክለው ሰርተዋል፡፡

የምጣኔ ሀብት አበርክቶ

ከደርግ ውድቀት በኋላ ወደ ሀገራቸው ከ17 አመት የውጭ ሀገር ቆይታ በኋላ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ቀጥለዋል፡፡
ክቡር አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከምጣኔ ሀብት አበርክቷቸው አዋሽ ባንክ እንዲቋቋም እና እውን ያለበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ የባንኩ መስራችና ፕሬዚዳንት በመሆን ረዘም ላለ ጊዜ ካለ ክፍያ ሰርተዋል፡፡ በተጨማሪም የባንኩ ቦርድ አባል በመሆን አገልግለዋል፡፡ የራሳቸውን አስተዋጽኦ
የፖለቲካ ታሪክ
በሀገራችን ዲሞክራሲ እንዲስፋፋ በፖለቲካው ዓለም ተሰማርተው የራሳቸውን አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ እንዲሁም የኦሮሞ ኮንግረስ ፓርቲ ውስጥ በመሳተፍ እና ምርጫ በመወዳደር አሸንፈው ፓርላማ በመግባት የወቅቱ ጠቅላይ ሚንስተር የነበሩትን አቶ መለስ ዜናዊን በመተቸት ና ሀሳባቸውን በነጻነት በመሰንዘር ይታወሳሉ፡፡

ሀገርን መውደድ ፣ ማንነትን ማክበር ፡ ሀቀኝነት ሰው ወዳድነት፡ ሩህሩህነት የእርሳቸው መገለጫ ጭምር ነው፡፡

የቅርብ ሰዎች አስተያየት
ወ/ሮ ሄለን ገ/እግዚአብሄር
ባለቤት
እኔ ግብጽ ሀገር ሆኜ ኢትዮጵያን ኤምባሲ ውስጥ እሰራ ነበር፡፡እርሱ ደግሞ ካይሮ ለኮንፈረንስ ከመጡ ልኡኳን መካከል አንዱ ነበር፡፡ ከእህትሽ መልእክት መጥቶልሻል ከኢትዮጵያ አለኝ፡፡ በወቅቱ በጣም ደስ አለኝ፡፡ ምክንያቱም አለም አቀፍ የስልክ ልውውጥ ስላልነበረ እጅግ በጣም ደስ አለኝ፡፡ የመጣልኝ መልእክት ለመቀበል ቸኮልኩኝ፡፡ እሱ ከስብሰባ እንደጨረሱ ‹‹…ቡና እንጠጣ›› አለኝ፡፡ እሺ ብዬ ቡና እየጠጣን ‹‹…ስለ አንቺ ብዙ የሰማሁት ጥሩ ነገር አለ›› አለኝ›› ፡፡ ቀጥሎ ስለ እራሴ ልንገርሽ አለኝ እኔ ደግሞ በልቤ እዩ ሁሉ ምንያስፈልጋል እያልኩ አዳመጥኩት ፡፡ ስለ ራሱ ከነገረኝ በኋላ መልእክት አልመጣልሽም አለኝ ትውውቃችንን እንዲህ ጀምረን አብረን በብዙ ውጣውረድ ውስጥ አልፈን 50 የትዳር አመታትን አብረን ኖረናል፡፡ የፓርላማ አባል ሆኖ ላመነበት ሀሳብ ሲሟገት ነበር፡፡ እኔም እንደ ባለቤት በምችለው ሁሉ ከአጠገቡ ሳልለይ እረዳው ነበር፡፡
ሰው በመርዳት ያምናል ፡፡ የተቸገረ ሰው ካለ አቅሙ የፈቀደውን ሁሉ ያደርጋል፡፡

ልጅ
ብስራት ቡልቻ

አባቴ እራሱንም ለመደገፍም ይሁን ቤተሰብን ለመደገፍ እያስተማረ መማር ነበረበት፡፡ እንግሊዘኛ ቋንቋ ቶሎ ስለለመደ ከሚሲዬኖች ጋር በማስተርጎም ስራ እየሰራ ትንሽ ደሞዝ እያገኘ እራሱን እየደገፈ ያስተምርም ነበር፡፡አባቴ ሀቅ የሚናገር ቅጥፈትን የሚቃወም እውነት ተናጋሪ ነው፡፡
አባቴ ውጭ ሀገር ሆኖ የረር ተራራን ማየት ሁሌም ይናፍቀው ነበር፡፡

አቶ ለይኩን ብርሃኑ
የቀድሞ የብሄራዊ ባንክ ገዥ እና የአዋሽ ባንክ ፕሬዚዳንት የነበሩ
በአካባቢያችን እንደ አርአያ ከሚታዩና እና ከተማሩ ሰዎች መካከል አቶ ይልማ ዴሬሳ እና አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ናቸው፡፡ እኛ ልጅ ሆነን እነርሱን እንደ አርአያ እያየን ነው ያደግነው፡፡ ታንዛኒያ ሀገር ለአንድ ስብሰባ ሄጄ ስብሰባችንን እንደ ጨረስን ቡና እየጠጣን አንድ ኢትዮጵያዊ እኮ አለ አለን፡፡ አዎ ብዙ ኢትዮጵያዊያን እኮ እዚህ ሊኖሩ ይችላሉ አልኩት፡፡ ቀበል አለኝ እና አቶ ቡልቻ ደመቅሳ የሚባል ሰው ታውቃለህ አለኝ ፡፡ በመገረም እርሳቸውን ከልጅነት ጀምሮ በዝና ነው የማውቀው አልኩት፡፡ ለመጀመርያ ጊዜ አቶ ቡልቻን በአካል ያወኩት ያኔ ነው፡፡ ያኔ የጀመረው ግንኙነታችን እስካሁን ድረስ የተለያዩ ስራዎችን አብረን በመስራት በተጨማሪም ቤተሰብ ሆነን ቀጥለናል፡፡ ያገራችን ኢኮኖሚ

እንዲያድግ የራሱን

አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡ በተለይ በግሉ ዘርፍ ባንኮች ብዙም ባልነበሩበት ወቅት እርሳቸው ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን አዋሽ ባንክ እንዲከፈት እና እንዲስፋፋ የራሱን አስተዋፆ አበርክቷል፡፡

ሶፍያ ይልማ
ቤተሰብ
በወቅቱ አባቴ የገንዘብ ሚኒስቴርን ዘመናዊ እንዲሆን የተማሩ ሰዎችን ከያሉበት እያሰባሰበ ነበር ፡፡ ከነዚህ ሰዎች መካከል አቶ ቡልቻ ደመቅሳ አንዱ ነበር ፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር ዘመናዊ እንዲሆን መስሪያ ቤቱን ባገለገሉበት ወቅት የራሳቸውን አስተዋጽኦ አሳርፈዋል፡፡
ወ/ሮ እሌኒ ከበደ
የቀድሞ ፀሃፊ
አቶ ቡልቻ እና እኔ ትውውቃችን ገንዘብ ሚኒስቴር ውስጥ ፀሃፊ በነበርኩበት ወቅት ነበር፡፡ ያኔ እንደ እርሳቸው እንደ አለቃም እንደ ቤተሰብም ሆነን አብረን ሰርተን ነበር፡፡ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በወቅቱ በነበሩት ንጉስ እጅግ ተቀባይነት ያላቸው እና ገንዘብ ካለ አግባብ እንዲወጣ የማይፈቅዱ ስራቸውን በአግባቡ የሚሰሩ እና ሰው አክባሪ ሰው ናቸው፡፡ የዛን ጊዜ የጀመርነው ቤተሰባዊነት እስከ አሁን ድረስ አብረን ዘልቀናል፡፡ ጥሩ ቤተሰቦቼ ናቸው፤ በሰርግም በለቅሶም ቢሆን ከነ ሙሉ ቤተሰባቸው እንጠያየቃለን፡፡
ሉሲ ገ/እግዚሃቤር
ቤተሰብ
ጋሼ ሀገሩን የሚወድ ሰው አክባሪ ባህሉን የመጣበትን ማህበረሰብ የሚያከብር እና የሚያስከብር ሀሳብ ያለው ሰው ነው፡፡ እኔም ልጅ እያለው ትምህርታችን ላይ እንድንበረታ ጠንክረን እንድናጠና የራሱን አስተዋፆ አበርክቷል፡፡ እኔም አውን አስተማሪ ነኝ፡፡ እሱ አንብቡ አጥኑ ስለሚል ያኔ የጀመርኩት ጥናት አስተማሪነትን እንድወደው እና እንድሰራበት የጋሼ አስተዋፆ ቀላል አይደለም፡፡

ኢ/ር ተረፈ ራስ ወርቅ
ጓደኛ
አቶ ቡልቻ ክርክር የሚወድ ያለውን ሀሳብ በስርኣት የሚያስረዳ ሰው ነው፡፡የገዳ ስርኣትን እንድማር እና እናዳውቅ ለመጀመርያ ጊዜ ያስተማረኝ አቶ ቡልቻ ነበር፡፡
ኢ/ር እሸቱ አበበ
ጓደኛ
አቶ ቡልቻ ወለጋ ጊንቢ ተወልዶ ይደግ እንጂ የወለጋ ልጅ ብቻ አይደለም የመላው ኢትዮጵያዊ ልጅ ነው፡፡ሁሌ ሳስበው ኢትዮጵያ በሚለው ሀሳብ ነው ፡፡ ሁሉን ነገር ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያን የሚል ሀሳብ ነው ያለው፡፡

አቶ ሙላቱ ገመቹ
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ ም/ሰብሳቢ
የኦሮሞ ፓርቲዎች ባልተስፋፉበት ወቅት አቶ ቡልቻ ፓርቲ አቋቁመው ለኦሮሞ ህዝብ ድምፅ ለመሆን ጥረዋል ፡፡ ፓርላማ ውስጥም በመግባት ሃሳባቸውን በነጻነት ሲናገሩ ልክ ያልሆነን ሀሳብ ሲተቹ ነው የማውቃቸው፡፡ አቶ ቡልቻ እስከአሁን ድረስ አቅማቸው የፈቀደውን ሁሉ ፓርቲያችንን እየደገፉ እና እየረዱ ይገኛሉ፡፡ እኔ ሰው ወዳድና እውነት ተናጋሪ ከምላቸው ሰዎች መካካል አንዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ናቸው፡፡ የአዋሽ ባንክ ሲቋቋም እርሳቸው ካለ ክፍያ ረዘም ላለ ጊዜ በነጻ በማገልገል ባንኩ አሁን ያለበትን አቋም እንዲይዝ የራሳቸውን አበርክቶ አበርክተዋል፡፡ ይህ ከፖለቲካው ባሻግር ለሀገራችን ምጣኔ ሀብት የራሳቸውን አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በምጣኔ ሃብት ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ስጦታ ተበረክቶላቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አክሲዮን ማህበር በጋራ ባዘጋጁት ሥነ ስርዓት ላይ ለአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ለገጣፎ በሚገኘው በመኖሪያ ቤታቸው ተገኝተው ስጦታ አበርክተውላቸዋል፡፡

ለ91 ዓመቱ አዛውንት ስጦታው የተበረከተላቸው ለሀገራቸው በምጣኔ ሃብት ዘርፍ ላበረከቱላት የረዥም ዘመን አገልግሎት ነው፡፡ ሰኔ 25 2014 ነበር እውቅና ያገኙት፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቅርስነት የሚያዝ የልዩ ታሪካዊ ሁነቶች ማስታወሻ የወርቅ ሳንቲም በመሸለም የወርቅ ካባም አልብሷቸዋል፡፡

አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ደግሞ የምስጋና የምስክር ወረቀት እና የወርቅ ሜዳሊያ አበርክቶላቸዋል፡፡

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ፣ የአዋሽ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ፀሐይ ሽፈራው ፣ የአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ባለቤት ወይዘሮ ሔለን ገብረእግዚአብሔርና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ጊምቢ በሚገኘው ደጃዝማች ገብረእግዚአብሄር ተማሪ ቤት የተከታተሉ ሲሆን የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በሻሸመኔ የሚሽን ተማሪ ቤት ተከታትለዋል፡፡ አቶ ቡልቻ ከአሜሪካን ሀገር በ1953 የማስተርስ ዲግሪያቸውን በኢኮኖሚክስ ካገኙ በኋላ በገንዘብ ሚኒስቴር ረዳት ሚኒስትር በመሆን አቅምና እውቃታቸውን ከሀገራቸው አውለዋል፡፡ በ1955 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ፋክሊቲን በመቀላቀልም በ1959 በዲግሪ ለመመረቅ ችለዋል፡፡ ክቡር አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከህግ ትምህርት ቤት ሲመረቁ በጊዜው የታተመውን ሚዛንና ሰይፍ የተሰኘውን የተማሪዎች የምረቃ መጽሄት እንዳየነው ከሆነ ከአቶ ቡልቻ ጋር እንደ አቶ አበበ ወርቄ ፤ ክቡር አቶ አበራ ጀንበሬ እና በደርግ ዘመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ብርሀኑ ባይህ የመሳሰሉ ሰዎች አብረዋቸው የተማሩ ነበሩ፡፡

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ኢትዮጵያን ወክለው በዓለም ባንክ ውስጥ የቦርድ አባል ሆነውም ሰርተዋል፡፡
ከጌጡ ተመስገን ገጽ የተወሰደ
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore ነፍስ ይማር

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore    አድራሻችን👇🇪🇹 ባሕር ዳር ቀበሌ 04  ➠ ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል +251918004191   +251902093535...
05/01/2025

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
አድራሻችን👇
🇪🇹 ባሕር ዳር ቀበሌ 04
➠ ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል
+251918004191 +251902093535
Contact -
https://t.me/yoftahiebooks

ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው   ኢትዮጵያ ውሰጥ ለሚገኙ የነቀርሳ(ካንሰር) (cancer) ህሙማንን ለማሳከም የሚውል ነው።                   ልብ አልባው ዶክተር               ...
05/01/2025

ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ኢትዮጵያ ውሰጥ ለሚገኙ የነቀርሳ(ካንሰር) (cancer) ህሙማንን ለማሳከም የሚውል ነው።

ልብ አልባው ዶክተር
ከአስቴር አበበ
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
አድራሻችን👇
🇪🇹 ባሕር ዳር ቀበሌ 04
➠ ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል
+251918004191 +251902093535
Contact -
https://t.me/yoftahiebooks

አገር -በቀል(በእውቀቱ ስዩም)ከአራት ቀናት በፊት የመሬት መንቀጥቀጥ አገሬን ሲጎበኛት እኔ  ወደ አዲስ አበባ  ለመመለስ ሻንጣየን እየሸካከፍኩ ነበር፤ ድንገት የጨሰ  የቢዘነስ  ሀሳብ ብልጭ...
05/01/2025

አገር -በቀል
(በእውቀቱ ስዩም)

ከአራት ቀናት በፊት የመሬት መንቀጥቀጥ አገሬን ሲጎበኛት እኔ ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ ሻንጣየን እየሸካከፍኩ ነበር፤ ድንገት የጨሰ የቢዘነስ ሀሳብ ብልጭ አለልኝ - የድንኩዋን ሪልስቴት መገንባት!

የምድር መፈራገጥ በዚህ ከቀጠለ አዲሳባና ተጎራባች ከተሞች ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች ባለ ትልልቅ ፎቅ ህንጻዎች ላይ የመኖር ፍላጎታቸው ይቀንሳል፤ ሟርቴን አፌ ላይ እንደ ሰም ያቅልጠው እንጂ፥ በዚህ አያያዝ ፥ፎቆች መኖርያ መሆናቸው ቀርቶ መቀበርያ እንዳይሆኑ ያሰጋል፤ ስለዚህ ሰዎች፥ ቢደረመስ እንኳን ለክፉ በማይሰጥ የገለባ ጎጆ ውስጥ፥አለዝያም በድንኳን ውስጥ መኖርን መምረጣቸው አይቀርም፤

አባታችን አብርሀም ኣያሌ አመታት በድንኳን የኖረ ልዝብም ሆነ የከረረ ድሀ ስለነበረ አይደለም፤ በዘመኑ ኢለን መስክን የሚቦንስ ቱጃር ነበር፤ አብርሽ በዳስ ውስጥ የተጠለለው፥ ትልልቅ ህንጻ የመገንባት ጥበብ ስላልተገለጠለት አልነበረም፤ ለባቤል የተገለጠ ጥበብ ለአብርሀም እንዴት ይጋረድበታል? አብርሀም በድንኩዋን የኖረው ከምድሪቱ ባህርይ ስለገባው ነው፤

"አብርሀም ሪል ስቴት" የተባለ የድንኳን ሪልስቴት እገነባለሁ፤ ሕዝቤ ከከዋክብት ርቆ፥ ወደ ምድር ቀርቦ የሰላም እንቅልፍ ይተኛል! አለቀ!

ከጥቂት ቀናት በሁዋላ የእንቅጥቅጡ ጉልበት እየጨመረ ሄደ፤ የቢዝነስ ሀሳቤን ትቼ በሕይወት ስለመቆየት ማሰብ ጀመርኩ፤

ትናንት ከበየነ ጋር ዲሲ ውስጥ እየተራመድን ስጋቴን አዋየሁት፤

“ ወደ አገሬ ለመመለስ ዘጠኝ ቀን ቀርቶኛል ፤ መሬት እያሸበሸበች እንዳትቀበለኝ እፈራለሁ “

“ነገሩ እስኪለይለት እዚህ ለምን ትንሽ አትቆይም፤ ትኬቱን ለወር አራዝመው” አለኝ፤

“ ይሻላል?” አልሁት ፥በምክሩ ውስጥ ውስጡን እየተደሰትኩ፤

“አስብበት “

እያሰብኩበት ብዙ አልተራመድኩም፤ ከጫማየ ስር ያለው የበረዶ ጥፍጥፍ ሲያዳልጠኝ ትዝ ይለኛል፤ የሆኑ ሰዎች ባቅራቢየው ካለ ፎቅ የወረወሩኝ እንጂ አዳልጦኝ የወደቅሁ አልመሰለኝም፤ አየር ላይ ትንሽ ውየ መሬት ላይ ሳርፍ ባካባቢው የቆመው፥ የማርቲን ሉተር ሀውልት ተነቃነቀ፤

በየነ እንደ ቆሰለ አርበኛ አፋፍሶ ካነሳኝ በሁዋላ፥

“ተረፍክ?”

“መንጋጋየ ከመነቃነቁ በስተቀር ደህና ነኝ”

“ ከዚህ እድሜህ በሁዋላ መንጋጋ ምን ይሰራልሀል? እንዲህ አይነት አደጋ ገጥሟቸው በሕይወት የሚኖሩ ብዙ ሰዎች አይገኙም"

“ጎን አጥንቴ ላይ የስብራት ስሜት አለኝ” አልኩት እያቃሰትኩ፤

“ነጮች ሆስፒታል ብወስድህ፥ ሀኪሞች እግረመንገዳቸውን ሌላ በሽታ ሊያገኙብህ ይችላሉ፤ የማውቀው የቡርኪናፋሶ ወጌሻ አለ፤ እዚያ ልውሰድህ”

ወደ መኪናው አቅጣጫ እንደ ጀብ እያነከስኩ ትንሽ እንደተራመድሁ እንደገና ተንሸራተትሁ፤ በየነ እንደ በረኛ ቀለበኝና እንዲህ አለ፤

“ግዴለህም ወደ አገርህ በጊዜ ግባ! መሞትህ ካልቀረ አገር በቀል -ሞት ይሻልሀል”

 ይህ " ሳብራ " የተሰኘው መጽሐፍ የኢትዮጵያ ተራራዎችና ገደሎች ብዙ ረቂቅ መንፈሳዊ ክዋኔዎች የሚፈጸምባቸው ምሥጢር ጓዳዎች መኾናቸውን የሚያሳይ መጽሐፍ ነው። " ሳብራ "ን ማንበብ ስጀምር...
03/01/2025


ይህ " ሳብራ " የተሰኘው መጽሐፍ የኢትዮጵያ ተራራዎችና ገደሎች ብዙ ረቂቅ መንፈሳዊ ክዋኔዎች የሚፈጸምባቸው ምሥጢር ጓዳዎች መኾናቸውን የሚያሳይ መጽሐፍ ነው። " ሳብራ "ን ማንበብ ስጀምር የሰሜን ተራራዎችን በሕሊና አብሮ ሲያዞረኝ ከቆየ በኋላ ወደ ነበርኩበት የተመስኩት መጽሐፉ ሲያልቅ ነው። ከዚህም ጋር የምዕራባውያን ሰዎች አማካሪዎች እየመሰሉ በልዩ ልዩ ዘዴ ወደ ኢትዮጵያውያን ባለሥልጣናት በመጠጋት በኢትዮጵያ ሊቃውንትና ጥበብ ላይ ሲፈጽሟቸው የኖሩትን ተንኮሎችና ጥፋቶችንም ያሳያል። በአጠቃላይ ''ሳብራ'' ጥሩ የጎብኝዎች መሪ ሊኾን የሚችል ብዙ ቁም ነገሮችን የሚያስጨብጥ መጽሐፍ ነው።
ሳብራ
በጌታቸው ተስፋው ዋለ(ዲያቆን)

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
አድራሻችን👇
🇪🇹 ባሕር ዳር ቀበሌ 04
➠ ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል
+251918004191 +251902093535
Contact -
https://t.me/yoftahiebooks

በየካቲት ጣጣችን ክትት     በምሕረት አቤሴሎምዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore    አድራሻችን👇🇪🇹 ባሕር ዳር ቀበሌ 04  ➠ ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል...
02/01/2025

በየካቲት ጣጣችን ክትት
በምሕረት አቤሴሎም
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
አድራሻችን👇
🇪🇹 ባሕር ዳር ቀበሌ 04
➠ ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል
+251918004191 +251902093535
Contact -
https://t.me/yoftahiebooks

Address

St. Giorgis Road
Bahir Dar
6000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore:

Videos

Share