13/12/2024
ክፍል 2: ለጌታ እራሳችንን መስጠት፦
ራሳችንን ለጌታ መስጠት
💎አንድ ሰው የጌታን ፍቅር ሲነካ፣ መሰጠት በቅጽበት ይከተላል። መሰጠት በጌታ ፍቅር ላይ የተመሰረተ ነው። ግን ደግሞ በጌታ መብት ላይም የተመሰረተ ነው። በ1ኛ ቆሮንቶስ 6፡19-20 የተገለጠው እውነት ይህ ነው፦ “በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም”።
💎ጌታችን ስለ እኛ የራሱን ሕይወት ሰጥቷል፤ እኛን መልሶ ሊገዛን ቤዛ ሆኖልናል። በጌታ የተገዛን ነን። ጌታ ስለ ዋጀን በፈቃዳችን ለእርሱ የራሳችንን ነፃነት እናጣለን:: ከእንግዲህ የራሳችን አይደለንም፤ የጌታ ነን። ስለዚህ የራሳችን ስላልሆንን በሥጋችን እግዚአብሔርን እናከብራለን፤ በዋጋ ተገዝተናል። ጌታ በመስቀል ላይ ያፈሰሰው ደም የከፈለው ዋጋ ነው። ስለዚህ፣ የጌታን መብት በተመለከተ፣ የጌታ ነን። በጌታ የተገዛን መሆናችን ግልጽ ሊሆንል ይገባል። በከፍተኛ ዋጋ ተገዝተናል። በብርና በወርቅ ሳይሆን በገዛ ደሙ ገዝቶናል። እዚህ ጋር የጌታን ፍቅር ደግሞም መብቱን እናያለን።
💎ጌታን የምናገለግለው ስለወደደን ነው፣ የምንከተለውም በእኛ ላይ መብት ስላለው ነው። በቤዛነት የተረጋገጠው መብት ራሳችንን ለጌታ እንድንሰጥ ግድ ይለናል። የመሰጠት መሰረት የእርሱ መብት እናም ፍቅሩ ነው። ህጋዊ መብት ነው፣ ከሁሉም የሰው ልጅ ስሜታዊ ፍቅርም በላይ ነው። እራሳችንን ለጌታ የምንሰጥባቸው እነዚህ ሁለት ምክንያቶች ናቸው።
💎አንድ ሰው በጌታ ፍቅር ከተያዘ እና መብቱን ከተገነዘበ በኋላ ሊወስድ የሚገባው ተጨማሪ እርምጃ አለ። ይህ እርምጃ ወደ አዲስ ስፍራ ያመጣዋል። በጌታ ፍቅር እና በመግዛቱ ላይ በመመስረት ራሳችንን ከሌሎች ነገሮች እንለያለን። ከአሁን በኋላ፣ ለጌታ እና ለጌታ እንኖራለን። ይህ መሰጠት ነው።
በወሰኑ አማረ
Join us:- https://t.me/bernabas298page
ዘመናችሁ ይባረክ