አልጀዚራ All jezira

  • Home
  • አልጀዚራ All jezira

አልጀዚራ All jezira አለማቀፋዊ እና የተመረጡ ሀገራዊ መረጃዎች ይቀርቡበታል።

ጃፓን ከቱርክ ከባባድ የጦር መሳሪያዎችን ልትገዛ መከላከያ ሚኒስትሯን ወደ ቱርክ ልካለች።  ➯➯➯➯➯አልጀዚራ የጃፓኑ መከላከያ ሚኒስትር ጄን ናካታኒ ቱርክ ናቸው።ጃፓን የመከላከያ ሀይሏን ለማ...
19/08/2025

ጃፓን ከቱርክ ከባባድ የጦር መሳሪያዎችን ልትገዛ መከላከያ ሚኒስትሯን ወደ ቱርክ ልካለች።

➯➯➯➯➯አልጀዚራ

የጃፓኑ መከላከያ ሚኒስትር ጄን ናካታኒ ቱርክ ናቸው።
ጃፓን የመከላከያ ሀይሏን ለማዘመንና ለማጠናከር የቱርክ ጦር ቴክኖሎጂዎች ላይ አይኗን ጥላለች።
በተለይም በዩክሬይን ጦርነት የሩሲያን ጦር ግስጋሴ በመግታት በኩል አስገራሚ ስራን የሰሩት የቱርክ ድሮኖች የጃፓን ተቀዳሚ ምርጫዎች ሆነዋል።

ጃፓን የሩሲያንና የቻይናን ወታደራዊ ግስጋሴ ለመግታትና ዳር ድንበሯን በሚገባ ለመጠበቅ ነው ከቱርክ ጋር በትብብር ለመስራት ወስና መከላከያ ሚኒስትሯን የላከቺው። ናካታኒ ከቱርኩ አቻቼው ያሳር ጉለር ጋር በመሆን የጋራ ጥምረት በሚፈጥሩበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።
ጃፓን ከድሮኖች በተጨማሪ የጦር መርከቦችንና ሌሎች ወታደራዊ ቴክኖሎጂዎችን ከቱርክ ለማስገባት ጠይቃለች።
በአለማችን ላይ በቴክኖሎጂ ከተራቀቁ ሀገር ከቀዳሚዎቹ የሆነቺው ጃፓን በጦር ሜዳ ተፈትነው ያለፉትን የቱርክን ጦር መሳሪያዎች ለመግዛት መወሰኗ የቱርክን የጦር ቴክኖሎጂ ልህቀት ማረጋገጫ ነው።
ቱርክ በድሮን ቴክኖሎጂ ከአለም ቀዳሚ ስትሆን አዳድስ የጦር መሳሪያ ግኝቶችን ወደ ጦሯ በመጨመር እያጠናከረች ትገኛለች።

ከጃፓን በተጨማሪ ኢንዶኔዥያ ፣ ማሌዥያ ፤ ባንግላዴሽ ፣ ዩክሬን ፣ ፖላንድ ፣ ስፔይን ፣ ክሮሺያ ፣ ፓኪስታን ፣ ኢጣሊያ የመሳሰሉ ትላልቅ ሀገራት የቱርክ ጦር መሳሪያዎችን በከፍተኛ ደረጃ እየገዙ ይገኛሉ። ይህም የቱርክን የጦር ኢንዱስትሪ በከፍተኛ ደረጃ እያሳደገው ይገኛል።

19/08/2025

ያለሁበት ታክሲ ሰዎችን እየጫነ እየሱስ ጌታ ነው የሚል ድምጽ በሞንታርቦ ከውጭ በኩል ይሰማል።

በዚህ መሀል አንድ ነጠላ አጣፍቶ የለበሰ ኦርቶዶክስ ''ይሄ ጨፋሪ እየሱስን ሲጠራ አያፍርም አስመሳይ ሁላ'' በማለት ተናገረ።አጠገቡ የነበረች አንዲት ፕሮቴስታንትም ሀገር የጋራ ነው ሀይማኖት የግል ነው እያለች ለሱ መልስ ሰጠች።በዚህ ሁኔታ ሰውየው ወደ እርሷ ዞረና ሀውርያቶች መንገድ ላይ ስበኩ ብለዋል? አላት እሷም መልስ ሰጠቺው ከዛም የሰውየው ተራ ደርሶ ምላሽ ሲሰጣት አሁን አንቺ ጥርስሺን አብለጭልጨሽ (ብሬስ አድርጋለች) ወንጌልን ልትሰብኪ ነው? እየሱስ ጥርሳቹሁን አብለጭልጩ ብሏል አላት?
እሷም እና ነጠላ ልበሱልኝ ብሏል አለቺው! ከዛ አንድ ሁለት ሲመላለሱ ቆይተው ነጠላ የለበሰው ያልሆነ ንግግር ሲናገራት እሷም ተረጋጋ እያለች ሰውየውን ለማረጋጋት ስትሞክር 'ኦርቶዶክስ' ተዋህዶ ስላረከኝ አመሰግናለሁ ጌታየ ኢትዮጵያ የቆመቺው በተዋህዶ ነው''እያለ ጮኸ (በጩኸት የሚቀየር እምነት ያለ መስሎት ይሆን አላውቅም)

ከዚህ ቃለ ምልልስ የተረዳሁት ቁምነገር ምንድን ነው?1ኛ የልጅቱን ስነምግባር
ሰውየው ያን ያክል እየጮኸባት እንኳን የነበራት ቀና ምላሽ በብዙ ጴንጤዎች የምናስተውለው ድርጊት ነው።
2ኛ በጩኸት እና በተረት የሚቀየር እምነት እንደሌለ ነው ሰውየው ኢትዮጵያ የቆመቺው በተዋህዶ ነው ገለመሌ ሲል ራሱን ከማስገመት ውጪ ኢትዮጵያ በብዙ ብሄር ብሄረሰቦች እና ሀይማኖቶች እንደቆመች አለማወቁና አስተሳሰቡ 16ኛው ክ/ዘመን ላይ የቀረ የቀነጨረ አስተሳሰብ ነው።

ስለዚህ እኛ እንደሙስሊም ከዚህ የምንረዳው ትልቁ ቁምነገር በስነምግባርህ ዳዕዋ ማድረግ በጣም ትልቅ ጥበብ መሆኑን ነው።
ምክንያቱም ሰው የምትሰብከው ሺ ቃላት ስለደረደርክ ሳይሆን ትንሽየ መልካም ስነምግባር ካሳየኸው ነው።

አሁን እንደ ሙስሊም ያለንበትን የስነምግባር ዝቅጠት ሁላችንም ራሳችንን መመርመር ይገባናል። አብዛኛው ወጣት እኔን ጨምሮ በዲናዊ በአካዳሚካሊም በስነምግባርም የወረድንበት ዘመን ላይ ደርሰናል። ቢያንስ ከ3ቱ አንዱን ያሟላን ስንቶቻችን ነን። so ምን ለማለት ነው እስልምና የተስፋፋው ነጮች እንደሚሉት በሰይፍ ሳይሆን በመልካም ስነምግባር ነው።እዚሁ ሀገራችን ላይ እንኳን ኢስላም በቀላሉ ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ የተስፋፋው አያቶቻችን በነበራቸው የመልካም ስብዕናና መልካም ስነምግባር ነው።

ስለዚህ ሁላችንም ራሳችንን እንጠይቅ እስልምና በእኛ በኩል መጥፎ ስም እየተሰጠው ነው? ወይስ በመልካም? እራሳችንን እንጠይቅ!!!

12/08/2025

የፍልስጤም ተዋጊዎች 51 የሚጠጉ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን አወደሙ።

12/08/2025

ኢራን የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢኒያሚን ኔታንያሁና የመከላከያ ሚኒስቴሩን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናትን ልት*ገል መሆኑን አስታወቀች።
➯አልጀዚራ

ኢራን የሟች ባለስልጣናትን ምስል ይፋ አድርጋለች። ኮሜንት ላይ በሚገኘው ሊንክ ሙሉ መረጃውን ይከታተሉ።

04/08/2025

ሐማስ የፍልስጤም ሉዓላዊ መንግሥት ኢየሩሳሌምን ዋና ከተማው አድርጎ እስካልተመሰረተ ድረስ ትጥቅ ለመፍታት እንደማይስማማ በድጋሚ አረጋገጠ።

ሐማስ ይህንን ያለው በጋዛ የተኩስ አቁም ድርድር ወቅት እስራኤል ካቀረበቻቸው ቁልፍ ጥያቄዎች መካከል አንዱ ለሆነው በሰጠው ምላሽ ነው።

➯አልጀዚራ

ቱርክ ከአሜሪካ የሚበልጥ ምድር ሰርጓጅ Bunker buster ቦምብ ባለቤት ሆነች።  ➯➯➯➯➯አል ጀዚራ ከ 12 አመታት ጥናት በሗላ ቱርክ በዛሬው እለት እጅግ አውዳሚ የሆነውን በንከር በስተ...
31/07/2025

ቱርክ ከአሜሪካ የሚበልጥ ምድር ሰርጓጅ Bunker buster ቦምብ ባለቤት ሆነች።

➯➯➯➯➯አል ጀዚራ

ከ 12 አመታት ጥናት በሗላ ቱርክ በዛሬው እለት እጅግ አውዳሚ የሆነውን በንከር በስተር ቦምቧን ይፋ አድርጋለች።
ቦምቡ አሜሪካ ኢራን ላይ ከተጠቀመቺው GBU-57 ቦምብ በላይ በ 30 ሜትር በልጦ ወደመሬት በመስረግ ከመሬት ውስጥ ያሉ ኢላማዎችን ያወድማል።
NEB-2 Ghost የተሰኘው ይህ የቱርክ ሰርጓጅ ቦምብ ወደ መሬት በኮንክሪት እና በምሽግ የተሰሩ ኢላማዎቿን ጥሶ 90 ሜትር በመጥለቅ የታቀደለትን ኢላማ ያወድማል። ኮንክሪቶችን ሰባብሮ የማለፍ አቅሙም ከአሜሪካው አቻው በ ሶስት እጥፍ የሚልቅ መሆኑን አናዶሉ ዘግቧል።
ይህም የቱርክን መሬት ሰርጓጅ ቦምብ በዘርፉ እጅግ ምርጡ ቦምብ ያደርገዋል። የአሜሪካው በንከር በስተር ቦምብ ወደመሬት የሚጠልቀው 60 ሜትር በመሆኑ ከ 90 ሜትር ጥልቀት በታች የተገነባውን የኢራንን ኑክሌየር ማውደም እንዳቃተው ይታወቃል። ይሁን እንጅ የቱርኩ አዲሱ በንከር ያንን መፈፀም የሚችል ብቃትን የተጎናጸፈ ሆኖ ተሰርቷል።

ቦምቡ በቱርክ አየር ሀይል ዛሬ ደሴት ላይ የተሞከረ ሲሆን የደሴቷን አለቶች ሰባብሮ 90 ሜትር ከጠለቀ በሗላ በ 160 ሜትር ዙሪያ ያለን ቦታ በማውደም ደሴቷን ያቀፈውን ውቅያኖስ አናግቶታል። ይህም ለቱርክ ትልቅ እመርታ ሆኖ ተመዝግቧል።
ቦምቡ 970 ኪሎግራም የሚመዝን ሲሆን በክብደት ከአሜሪ አቻው ሲያንስ በፍንዳታ አቅሙ ግን ከዚያም ይልቃል ተብሏል።
ቱርክ በትላንትናው እለት ጋዛፕ የተሰኘውን በታሪኳ አውዳሚውን ቦምብ መታጠቋ ይታወቃል
በዚህም ቱርክ ጥድፊያ ላይ መሆኗ ተነግሯል።

➯አልጀዚራ

"ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር የእስራኤል እና የፍልስጤም ሀገርነት ጉዳይ መፍትሔ ማበጀት አለብን" ሲሉ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ተናገሩ  ➯➯➯➯➯➯አል ጀዚራ ተመድ የሁለት ሀገርነት መፍትሔ ጉዳይ ላ...
31/07/2025

"ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር የእስራኤል እና የፍልስጤም ሀገርነት ጉዳይ መፍትሔ ማበጀት አለብን" ሲሉ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ተናገሩ

➯➯➯➯➯➯አል ጀዚራ

ተመድ የሁለት ሀገርነት መፍትሔ ጉዳይ ላይ ለመወያየት አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደ።

ድርጅቱ የእስራኤልና ፍልስጤምን ውጥረት በዘላቂነት ለመፍታት ያግዛል ባለው የሁለት ሀገርነት መፍትሔ (two state solution) የሁለቱንም ሀገራት ህዝቦች በሉዓላዊ ሀገር የሚኖሩ ሰላማዊ ዜጎች ያደርጋቸዋል ብሏል።

የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ "ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር የሁለት ሀገርነት መፍትሔን እውን ማድረግ አለብን" ሲሉ ተናግረዋል።

እስራኤልና አሜሪካ፣ እስራኤልና ፍልስጤም ራሳቸውን የቻሉ ሉዓላዊ ሀገራት እንዲሆኑ በሚመክረው ስብሰባ ላይ አልተገኙም ተብሏል።

ስብሰባው የተጠራው በፈረንሳይ እና ሳውዲ አረቢያ አማካኝነት የተጠራ እንደሆነ ተገልጿል።

➯አልጀዚራ

ከኢትዮጵያ ወደ ጋዛ የሄዱ የምግብ ፓኬጆች ለተጎጂዎች መከፋፈላቸው ተገለፀ።  ➯➯➯➯➯አል ጀዚራ በአንድ ግለሰብ አማካኝነት ከኢትዮጵያውያን የተሰበሰቡ የምግብ ፓኬጆችን ያከተተና ግምታቸው ከ2...
30/07/2025

ከኢትዮጵያ ወደ ጋዛ የሄዱ የምግብ ፓኬጆች ለተጎጂዎች መከፋፈላቸው ተገለፀ።

➯➯➯➯➯አል ጀዚራ

በአንድ ግለሰብ አማካኝነት ከኢትዮጵያውያን የተሰበሰቡ የምግብ ፓኬጆችን ያከተተና ግምታቸው ከ200ሺ የኢትዮጵያ ብር በላይ የሚሆን የምግብ እርዳታ ወደ ጋዛ መላኩ ተገልጿል።

ደቡብ አፍሪካ ከሚገኘው gift of givers ከተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ይህንን እርዳታ ለዜጎች መድረሱን የሚያሳይ በተንቀሳቃሽ ምስል የተደገፈ መረጃ ተጋርቷል።

ነገርግን አንዳንድ ግለሰቦች እርዳታ የተሰጣቸው ሶርያውያን እንጂ ጋዛውያን አይደሉም ያሉ ሲሆን ወደ ጋዛ ምንም አይነት የእርዳታ መኪና መግባት በማይቻልበት ሁኔታ ግለሰቦች እንዴት እርዳታ ይዘው ሊገቡ ይችላሉ የሚል ጥያቄ እያነሱ ይገኛሉ።

በጋዛ ከሰሞኑ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድምጽ እና ጫና የተለያዩ የእርዳታ መኪኖች ገቡ ቢባልም እስከ አሁን የተረጋገጠ መረጃ አልተገኘም።

➯አልጀዚራ

የየመን ጦር ሃይሎች ይፋዊ መግለጫ ሰጡ  ➯➯➯➯➯አልጀዚራ  🛑 ደረጃ 4 ተጀመረ - በእስራኤል ላይ አጠቃላይ የባህር ኃይል እገዳ! ሁሉን ቻይ በሆነው አላህ ላይ ሙሉ በሙሉ በመደገፍ የየመን ...
29/07/2025

የየመን ጦር ሃይሎች ይፋዊ መግለጫ ሰጡ

➯➯➯➯➯አልጀዚራ

🛑 ደረጃ 4 ተጀመረ - በእስራኤል ላይ አጠቃላይ የባህር ኃይል እገዳ!

ሁሉን ቻይ በሆነው አላህ ላይ ሙሉ በሙሉ በመደገፍ የየመን ጦር ሃይሎች ወታደራዊ ዘመቻቸውን አዲስ እና የተጠናከረ ምዕራፍ በይፋ አውጀዋል - 4ኛውን የባህር ኃይል በጽዮናዊ ጠላት ላይ ተግባራዊ ማድረግ።

📢 ይህ ምን ማለት ነው፡-

ከእስራኤል ወደቦች ጋር የተገናኘ ማንኛውም መርከብ - የኩባንያውን፣ ባንዲራ ያድርግም አያድርግም በቀጠናዉ - ዋነኛ ኢላማ ይሆናል።

ዜግነቱ ምንም ይሁን ምን. ባለመርከቡ ከእስራኤል ጋር የሚሰራ ከሆነ፣ እንደሚመታ ይወቅ ።

ይህ ለሁሉም ዓለም አቀፍ የመርከብ ኩባንያዎች ግልጽ ማስጠንቀቂያ ነው።
❗ ሁሉንም ከእስራኤል ወደቦች ጋር ያለውን ግንኙነት አሁን ያቋርጡ… ወይም ውጤቱን ይጋፈጡ።

💥 ሚሳኤሎቻችን እና ሰው አልባ አውሮፕላኖቻችን በደረሱበት ቦታ - ከቀይ ባህር እስከ ሩቅ - አድኖ ይመታል።

➯አልጀዚራ

አልሸባብ ከሞቃዲሾ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያለችን ከተማ ዳግም መያዙን ገለፀ። ➯➯➯➯➯አልጀዚራ አልሸባብ ባለፉት ቀናት ከሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለችው ሳቢ...
27/07/2025

አልሸባብ ከሞቃዲሾ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያለችን ከተማ ዳግም መያዙን ገለፀ።

➯➯➯➯➯አልጀዚራ

አልሸባብ ባለፉት ቀናት ከሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለችው ሳቢድ ከተማ ከባድ ውጊያ ማድረጉን ገልፆ በኡጋንዳ እና ሶማሊያ ጦር ላይ ከፍተኛ ጥቃት ሰንዝሮ ከተማዋን ዳግም መቆጣጠሩን ገልጿል።

በተጨማሪ አልሸባብ በከተማዋ ያለን የሶማሊያ ጦር እና የኡጋንዳ ሰላም አስከባሪ ጦር ማዘዣዎችን እንደዚሁም መኪኖችን እና መሳሪያዎችን መያዙን ገልጿል።

የሳቢድ ከተማን ከወር በፊት የሶማሊያና የኡጋንዳ ጦር ከአልሸባብ ነፃ አውጥተውት የነበረ ሲሆን ከተማዋ በአልሸባብ እጅ ዳግም በመወደቋ ላይ የሶማሊያ ጦርም ሆኑ የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ያሉት ነገር የለም።

አልሸባብ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ኃይሉን እያጠናከረ በርካታ ከተሞችን መያዝ ሲጀምር በሶማሊያ ያለው የህብረቱ ተልዕኮ ከበጀት ድጋፍ ጋር በተገናኘ የሚፈልገውን ያህል እየተንቀሳቀሰ እንዳልሆነ ተነግሯል።

➯አል ጀዚራ

Address


Telephone

+251918398494

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አልጀዚራ All jezira posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share