AMECO Sport

AMECO Sport Ameco Sport Provides Real-time Sport updates.

መነሻቸውን ያልረሱት ኮከቦችባሕር ዳር: ጥር 5/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ሳዲዮ ማኔ ለሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን በክለብ ደረጃ ደግሞ ለሳዑዲው አልናስር ይጫወታል።ከአልናስር በፊት በባየር ሙኒክ እና...
13/01/2025

መነሻቸውን ያልረሱት ኮከቦች

ባሕር ዳር: ጥር 5/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ሳዲዮ ማኔ ለሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን በክለብ ደረጃ ደግሞ ለሳዑዲው አልናስር ይጫወታል።

ከአልናስር በፊት በባየር ሙኒክ እና በሊቨርፑል ተጫውቷል። በተለይ በሊቨርፑል የነበረው ብቃት ለክለቡ ውጤታማነት ከሚጠቀሱ ተጫዋቾች አንዱ አድርጎታል።

ማኔ ከተጫዋችነቱ ባለፈም በበጎ ተግባራቱ የሚቀናበት ነው። በተወለደበት አካባቢ ማኅበረሰብም ዘንድ "በጎ አሳቢ" የሚል ቅጽል ስም ተሰጥቶታል።

የ32 ዓመቱ ማኔ 17 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዩሮ በዓመት ይከፈለዋል። እንደ አውሮፖውያኑ ዘመን በ2021 ማኔ ሴኔጋል ውስጥ ማኅበረሰቡን ለመጥቀም በማሰብ የሕዝብ ሆስፒታል ለመገንባት ወሰነ። ውሳኔውንም በተግባር ለማስፈጸም 500 ሺህ ዩሮ ለገሰ።

ማኔ ይህን የወሰነው የአባቱን ሞት ተከትሎ እንደኾነ ነው የሚነገረው።

ማኔ አባቱ በሕክምና እጦት መሞታቸውን ሲያስተውል ይህ ችግር በሌሎችም እንዳይደገም በማሰብ ተግባሩን ለመፈጸም ተነሳ፤ አደርገውም።

ሳዲዮ ማኔ ዓለምን መለወጥ ይቻላል የሚል እሳቤ ያለው የኳሱ ዓለም ሰው ሲኾን ይህን ለመከወን ከእያንዳንዱ ግለሰብ ውሳኔ እና የተግባር ሰውነት እንደሚነሳ ነው የሚናገረው።

የተግባር ሰው እንደኾነ የሚነገርለት ማኔ አዲስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ጨምሮ በትውልድ መንደሩ ባምባሊ ውስጥ ሌሎች ሥራዎችንም መሥራት እንደቻለ ነው የሕይወት ታሪኩ የሚያስረዳው።

ማኔ የኮሮና ወረርሽኝ በተቀሰቀሰበት ወቅትም በሽታውን ለመከላከል ለሀገሩ እስከ 40 ሺህ ፓውንድ ለሴኔጋል መንግሥት መስጠቱም ይነገርለታል።

በአፍሪካ ውስጥ ለወጣቶች ተጨማሪ የሥራ ዕድል በመፍጠር አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ መሠራት እንዳለበት ከሚያምኑ እና ከሚደግፉ ሰዎች መካከልም ማኔ የፊት መሥመሩን ይይዛል።

ሌላው ዓለምን መቀየር እንደሚቻል በማሰብ እየተንቀሳቀሰ ያለው የኮትዲቯር የቁርጥ ቀን ልጅ ዲዴ ድሮግባ ነው።

ድሮግባ በኳሱ ዓለም ከሀገሩ አልፎ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ለቼልሲ በመጫወት አፍሪካን ያኮራ አሁን ላይ ራሱን ከኳሱ ያገለለ ሰው ነው።

ዲዴ ድሮግባ ዓለምን ለመቀየር ከሰፈር መነሳት እንደሚያስፈልግ በማመን እየሠራ ያለ ድንቅ የኳሱ ዓለም ሰው ነው።

ዲዴ ለሕዝብ በማሰብ የተለያዩ የሚያነሳሱ አነቃቂ ሥራዎችን በመሥራትም ይታወቃል።

የ46 ዓመቱ ድሮግባ እ.ኤ.አ. በ 2005 በወቅቱ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ለነበረችው ሀገሩ ኮትዲቮር ሰላምን የሚያበረታታ ንግግር በማቅረብ ችግሩ በንግግር እንዲፈታ የራሱን ሚና ተጫውቷል።

የልጆች የመማር መብት የሚያበረታታ ዲዴር ድሮግባ ፋውንዴሽንን በመመሥረት አካባቢውን ለመቀየር የበኩሉን እየተወጣም ይገኛል።

ፋውንዴሽኑ በኮቴዲቯር ወላጆቻቸውን ላጡ እና አቅመ ደካሞች ሕጻናት የትምህርት ቁሳቁሶችን እንዲያገኙ ማድረግ የቻለም ነው።

እ.ኤ.አ. በ 2018 ድሮግባ እና ሌሎች የእግር ኳስ ተጫዋቾች ከፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተገናኝተው 15 ሚሊዮን ዩሮ በመሰረተ ልማት፣ በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና በአፍሪካ የንግድ ጅምር ዕርዳታ ላይ ኢንቨስት ለማድረግ የሠራው ሥራ ድሮግባን የተግባር ሰው ያስባለው ክስተትም ኾኗል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ማንቸስተር ዩናይትድ አሸነፈ።ባሕር ዳር፡ ጥር 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሦስተኛ ዙር የኤፍ ኤ ካፕ  ጨዋታ አርሰናል ማንቸስተር ዩናይትድን ጋብዞ ጨዋታቸውን አድርገዋል።በጨዋታውም በሙሉ ሰ...
12/01/2025

ማንቸስተር ዩናይትድ አሸነፈ።

ባሕር ዳር፡ ጥር 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሦስተኛ ዙር የኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታ አርሰናል ማንቸስተር ዩናይትድን ጋብዞ ጨዋታቸውን አድርገዋል።

በጨዋታውም በሙሉ ሰዓት ጨዋታ እና በተጨማሪ ሰዓት አንድ አቻ ተለያይተዋል።

አሸናፊውን ለመለየትም ወደ መለያ መለያ ምት አምርተዋል። ማንቸስተር ዩናይትድ 5ለ3 በኾነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

12/01/2025

ስፖርት ዜና፡- ጥር 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ)

በዓለም አደባባይ ሀገር ያስጠሩ ብዙ ስፖርተኞች መነሻቸው ፖሊስ ነው።አዲስ አበባ: ጥር 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 116ኛውን ብሔራዊ የፖሊስ ቀን ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ...
12/01/2025

በዓለም አደባባይ ሀገር ያስጠሩ ብዙ ስፖርተኞች መነሻቸው ፖሊስ ነው።

አዲስ አበባ: ጥር 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 116ኛውን ብሔራዊ የፖሊስ ቀን ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሚገኙ የሥራ ክፍሎች መካከል ሲካሄድ የቆየው ስፖርታዊ ውድድር ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቷል።

ከታኅሣሥ 22/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ በቆየው ስፖርታዊ ውድድር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ፣ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ፣ የአሥተዳዳር እና ልማት ጠቅላይ መምሪያ፣ የኮሚሽነር ጀነራል ተጠሪ የሥራ ክፍሎች እና የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርሲቲ ተሳታፊዎች ነበሩ።

ተወዳዳሪዎች በአትሌቲክስ፣ መረብ ኳስ፣ ገመድ ጉተታ እና በወንዶች እግር ኳስ ውድድራቸውን አድርገዋል። በዚህም ውድድር 640 የስፖርት ልዑካን ተሳታፊ መኾናቸውም ተገልጿል።

የኢትየጵያ ፌደራል ፖሊስ የሰዉ ሀብት ሥራ አመራር ዋና መምሪያ ኀላፊ ረዳት ኮሚሽነር ደርቤ ጋቢሳ ውድድሩ ዓላማውን አሳክቶ በከፍተኛ ፉክክር መጠናቀቁን ተናግረዋል። በዓለም አቀፍ ውድድሮች ሀገርን መወከል የሚችሉ ስፖርተኞችን ማግኘት እንደሚቻል ያመላከተ ውድድር ነውም ብለዋል ረዳት ኮሚሽነሩ።

ኢትዮጵያን በዓለም አደባባይ ያስጠሩ ታላላቅ ስፖርተኞች መነሻቸው ከፖሊስ መኾኑን የተናገሩት የባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ መክዩ መሐመድ ይህን አጠናክሮ ማስቀጠል አስፈላጊ መኾኑን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የውስጥ የሥራ ክፍሎች መካካል የተካሄደው ስፖርታዊ ውድድርም ስፖርቱ ላይ የሚፈጥረው አጠቃላይ መነቃቃት ከፍተኛ እንደኾነም ገልጸዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

የፋሲል ከነማን ለማጠናከር ያለመ የሩጫ ውድድር ተካሄደ።ጎንደር: ጥር 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብን የማጠናከር አላማ ያለው የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በጎንደር...
12/01/2025

የፋሲል ከነማን ለማጠናከር ያለመ የሩጫ ውድድር ተካሄደ።

ጎንደር: ጥር 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብን የማጠናከር አላማ ያለው የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በጎንደር ከተማ ተካሂዷል።

የበርካታ ደጋፊዎች ባለቤቱ ፋሲል ከነማ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እየተሳተፈ ይገኛል። ፋሲል ከነማ በገቢ ራሱን ለማጠናከር ከሚያካሂዳቸው ተግባራት አንዱ የሩጫ ውድድር ነው።

5 ኪሎ ሜትር በሚሸፍነው የጎዳና ላይ ውድድር መነሻውን ኮሌጅ ማዞርያ በማድረግ መዳረሻውን ደግሞ መስቀል አደባባይ በማድረግ ነው የተካሄደው።

በውድድሩ የተካፈሉ የስፖርት ክለቡ ደጋፊዎችም በውድድሩ በመሳተፋቸው ደስታን እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል። ከዚህም ባለፈ ክለባቸውን ለመደገፍ በየዓመቱ በውድድሩ እየተሳተፉ መኾኑን ተናግረዋል።

እንደዚህ አይነት ውድድሮች መደረጋቸው በጥምቀት ለምትደምቀው ጎንደር ከተማ ሌላኛው ውበት መኾኑን እና የስፖርት ውድድሩ ወንድማማችነትን የሚያጠናክር ነው ብለዋል።

የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ የደጋፊ ማኅበር ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ብርሃኑ እንደዚህ አይነት ውድድሮች የስፖርት ቤተሰቡን በማሰባሰብ ለአንድ ዓላማ እንዲቆም ያደርጋሉ ብለዋል።

ከውድድሩ የሚገኘውም ገቢ የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብን ለማጠናከር እንደሚረዳ ተገልጿል። ከዚያም ባለፈ የስፖርት ክለቡን ደጋፊዎች በአንድ የሚያሰባስብ ነው ብለዋል።

የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድሩን ያዘጋጀው የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ የደጋፊ ማኅበር በዚህ ውድድር እስከ 10 ሚሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አልሞ እንደተሠራ ገልጿል።

12 ሺህ የመሮጫ ማሊያዎች መሸጣቸውም ተጠቅሷል። ለውድድሩ አሸናፊዎች የምሥክር ወረቀት እና እንደየደረጃቸው የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ውድድሩ ለስድስተኛ ጊዜ ነው የተካሄደው።

ዘጋቢ:- ዳንኤል ወርቄ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

አርሰናል እና ማንቸስተር ዩናይትድ ዛሬ ይፋለማሉ።ባሕር ዳር፡ ጥር 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሦስተኛ ዙር የኤፍ ኤ ካፕ የዋንጫ ጨዋታ አርሰናል ማንቸስተር ዩናይትድን ይጋብዛል።አርሰናሎች ...
12/01/2025

አርሰናል እና ማንቸስተር ዩናይትድ ዛሬ ይፋለማሉ።

ባሕር ዳር፡ ጥር 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሦስተኛ ዙር የኤፍ ኤ ካፕ የዋንጫ ጨዋታ አርሰናል ማንቸስተር ዩናይትድን ይጋብዛል።

አርሰናሎች በቅርብ ጊዜ ባደረጓቸው ጨዋታዎች ከማሸነፍ ሥነ ልቦናቸው እየተንሸራተቱ ይገኛሉ። ቡድኑ በቅርቡ ከአደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች አንዱን አቻ ሲለያይ ሌላኛውን ደግሞ ተሸንፏል። ይህም የቡድኑ የሥነ ልቦና ኹኔታ ጥሩ እንዳልኾነ ማሳያ ነው።

በተመሳሳይ በማንቸስተር ዩናይትድም በኩል ከነበረበት የተሸናፊነት ስሜት እያገገመ ያለ ቢመስልም ቡድኑ አሁንም ወደ ቀድሞው ብቃቱ አለመመለሱን ካደረጋቸው ጨዋታዎች እና ከውጤቱ ለመገንዘብ ይቻላል።

ዩናይትድ ባለፉት ጊዜያት በተከታታይ አራት ጨዋታዎች ከተሸነፈ በኋላ ያደረገው አንድ ጨዋታ ላይ አቻ መውጣቱ ቡድኑ በመጠኑም ከገባበት አጣብቂኝ ለመውጣት ጥረት እያደረገ ለመኾኑ ማሳያ ነው።

በተለይም ቡድኑ በወቅታዊ አቋሙ ጥሩ ከሚባለው ከሊቨርፑል ጋር ባደረገው ጨዋታ አቻ መለያየቱ ተስፋ እንዳለው ያሳያል። ቡድኑ ከታላላቅ ክለቦች ጋር ጨዋታ እንደማይከብደውም ያሳያል።

ይህም ሂደት ዛሬ ሁለቱ ቡድኖች 12፡ 00 ሰዓት ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ እንዲኾን አድርጎታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

የሱፐር ካፕ ፍጻሜ ይጠበቃል።የዘንድሮው የስፔን ሱፐር ካፕ ፍጻሜ በሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎና መካከል ዛሬ ይካሄዳል። ጨዋታው በሳኡዲ አረቢያ የሚከናወን ይኾናል።በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ሪያል ማ...
12/01/2025

የሱፐር ካፕ ፍጻሜ ይጠበቃል።

የዘንድሮው የስፔን ሱፐር ካፕ ፍጻሜ በሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎና መካከል ዛሬ ይካሄዳል። ጨዋታው በሳኡዲ አረቢያ የሚከናወን ይኾናል።

በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ማዮርካን፣ ባርሴሎና ደግሞ አትሌቲኮ ቢልባኦን አሸንፈው ነው ለፍጻሜ የደረሱት።

ሁለቱ ክለቦች ዘንድሮ በላሊጋው ተገናኝተው ነበር። ባርሴሎና 4 ለ 0 ማሸነፉም ይታወሳል።

ባርሴሎና የስፔን ሱፐር ካፕን 14 ጊዜ በማሸነፍ ቀዳሚው ክለብ ነው። ሪያል ማድሪድ ደግሞ 13 ጊዜ በመድረኩ ከፍ ብሏል።

ሁለቱ ባላንጣዎች ዛሬ ዋንጫውን ለማንሳት የሚያደርጉት ተጋድሎም በዚህ ዋንጫ ያለን የታሪክ የበላይነት የማስቀጠል እና ታሪክን መጋራት የሚል ተጨማሪ ምክኒያት አለው።

ጨዋታው ምሽት አራት ሰዓት ይጀምራል።

ፋሲል ከነማ ከሀድያ ሆሳዕና ጋር አቻ ተለያየ።ቀን ዘጠኝ ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም  በተደረገው ጨዋታ ሀድያ ሆሳዕና በ35ኛው ደቂቃ ብሩክ በየነ ባስቆጠራት ግ...
11/01/2025

ፋሲል ከነማ ከሀድያ ሆሳዕና ጋር አቻ ተለያየ።

ቀን ዘጠኝ ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሀድያ ሆሳዕና በ35ኛው ደቂቃ ብሩክ በየነ ባስቆጠራት ግብ መሪ መኾን ችለዋል።

በጨዋታው ሁለተኛ አጋማሽ ሀድያ ሆሳዕናዎች ውጤታቸውን አስጠብቀው ለመውጣት ተጫውተዋል።

ፋሲሎች አቻ የሚኾኑበትን ግብ ለማግኘት ተጭነው ተጫውተዋል።

80ኛው ደቂቃ ላይም ማርቲን ኪዛ ግብ አስቆጥሮ ጨዋታው አንድ አቻ ተጠናቋል።

ምሽት 12 ሰዓት ደግሞ ወላይታ ድቻ ከኢትዮጵያ መድን ይጫወታሉ።

የዋልያዎቹ የመሐል ሜዳ ተሰላፊ ጋቶች ፓኖም የኢራቅን ቡድን ተቀላቀለ። ባሕር ዳር: ጥር 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የዋልያዎቹ የመሐል ሜዳ ተሰላፊ ጋቶች ፓኖም የኢራቁን የእግር ኳስ ቡድን ...
11/01/2025

የዋልያዎቹ የመሐል ሜዳ ተሰላፊ ጋቶች ፓኖም የኢራቅን ቡድን ተቀላቀለ።

ባሕር ዳር: ጥር 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የዋልያዎቹ የመሐል ሜዳ ተሰላፊ ጋቶች ፓኖም የኢራቁን የእግር ኳስ ቡድን ኒውሮዝ ስፖርት ክለብ መቀላቀሉን ክለቡን ጠቅሶ ኢራቂ ስታርስ በድረ ገጹ አስነብቧል።

ጋቶች ፓኖም የአንድ ዓመት የኮንትራት ውል መፈረሙም ታውቋል።

ጋቶች ፓኖም በኢራቅ ቆይታው ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከፍተኛ ግብ አግቢ በመኾን ካጠናቀቁት ኦኪኪ ኦፎላቢ እና እስማኤል ኦሮ አጎሮ ጋር በሊጉ የሚጫወት ይኾናል።

በኢራቅ ሊግ 20 ቡድኖች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ጋቶች ፓኖም የፈረመበት የኒውሮዝ ስፖርት ቡድን ደግሞ በሊጉ 17ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ፋሲል ከነማ ከሀድያ ሆሳዕና ይጫዎታሉ። ባሕር ዳር: ጥር 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሜዳ በሚደረገው የ13ኛው ሳምንት መርሐ ግብር ሀድያ ሆሳዕናን ከ...
11/01/2025

ፋሲል ከነማ ከሀድያ ሆሳዕና ይጫዎታሉ።

ባሕር ዳር: ጥር 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሜዳ በሚደረገው የ13ኛው ሳምንት መርሐ ግብር ሀድያ ሆሳዕናን ከፋሲል ከነማ ያገናኛል። ጨዋታውም ጠንካራ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።

ሀድያ ሆሳዕና በስድስት ተከታታይ ጨዋታዎች ባለመሸነፍ በሁሉም መመዘኛ ጥሩ አቋም ላይ ይገኛል። ቡድኑ በአምስት ጨዋታዎች ደግሞ መረቡን አላስደፈረም።

በዛሬው ጨዋታ ፋሲልን ካሸነፈ ነጥቡን 25 በማድረስ የሊጉ መሪ መቻልን በአንድ ነጥብ በልጦ የሊጉ መሪነትን ይጨብጣል።

በሀድያ ሆሳዕና በኩል እዮብ ዓለማየሁ፣ ዳግም ንጉሴ፣ በረከት ወንድሙ እና መለሰ ሚሻሞ በጉዳት ምክንያት አይሰለፉም።

የሀድያ ሆሳዕና ተጋጣሚ ፋሲል ከነማ የመከላከል አደረጃጀቱ ብርቱ በመኾኑ ለሀድያ ሆሳዕና ፈተና ይኾንበታል ተብሎ ይጠበቃል።

አጼዎቹ በፊናቸው ከጨዋታ ጨዋታ ከፍተኛ የደረጃ መሻሻል እያሳዩ ይገኛሉ። ላለፉት ሦስት ተከታታይ ጨዋታዎችም መረባቸውን አላስደፈሩም።

የኾነው ኾኖ በዛሬው ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች ለማሸነፍ ወደ ሜዳ ስለሚገቡ ጨዋታውን ተጠባቂ ያደርገዋል።

በፋሲል ከነማ በኩል ዮናታን ፍስሐ፣ ኪሩቤል ዳኜ እና በረከት ግዛው በጉዳት ምክንያት ከጨዋታው ውጭ መኾናቸው ታውቋል።

ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ ቀደም ለስምንት ጊዜያት ተገናኝተዋል። ፋሲል ከነማ 4 ጊዜያት ሀዲያ ሆሳዕና አንድ ጊዜ አሸንፈዋል። በሦስት ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።

ምሽት 12:00 ሰዓት ደግሞ ወላይታ ድቻ ከኢትዮጵያ መድን ይጫወታሉ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ስፖርት ዜና፡- ጥር 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ)
10/01/2025

ስፖርት ዜና፡- ጥር 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ)

ስፖርት ዜና፡- ጥር 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ)

አማድ ዲያሎ በማንቸስተር ዩናይትድ ውሉን አራዘመ።ባሕር ዳር: ጥር 1/2017 ዓ.ም (አሚኮ) አማድ ክለቡ ማንቸስተር ዩናይትድ አስቸጋሪ የውድድር ጊዜ እያሳለፈ ቢኾን በግሉ ጥሩ ጊዜን እያሳለ...
09/01/2025

አማድ ዲያሎ በማንቸስተር ዩናይትድ ውሉን አራዘመ።

ባሕር ዳር: ጥር 1/2017 ዓ.ም (አሚኮ) አማድ ክለቡ ማንቸስተር ዩናይትድ አስቸጋሪ የውድድር ጊዜ እያሳለፈ ቢኾን በግሉ ጥሩ ጊዜን እያሳለፈ ይገኛል። በ27 ጨዋታዎች ስድስት ግቦችን አስቆጥሯል።

የተጫዋቹ ውል በውድድር ዓመቱ ይጠናቀቅ ነበር። አሁን የፈረመው ውል ግን ኮትዲቯራዊን ለቀጣይ አምስት ዓመታት በኦልድ ትራፎርድ ያቆየዋል።

ክለቡ ከተቀናቃኞቹ ማንቸስተር ሲቲ እና ሊቨርፑል ጋር በነበረው ጨዋታም ግብ ማስቆጠሩ በክለቡ ደጋፊዎች ዘንድ በአጭር ጊዜ እንዲወደድም አድርጎታል።

አማድ ከጣሊያኑ አታላንታ ከአራት ዓመት በፊት ነበር ዩናይትድ የተቀላቀለው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ኤቨርተን አሠልጣኙን አሰናበተ።ባሕር ዳር: ጥር 1/2017 ዓ.ም (አሚኮ)የእንግሊዙ ክለብ ኤቨርተን አሠልጣኝ ሲንዲያችን አሰናብቷል። በየዓመቱ ወረደ ሲባል እንደምን የሚተርፈው የመርሲሳይዱ ክ...
09/01/2025

ኤቨርተን አሠልጣኙን አሰናበተ።

ባሕር ዳር: ጥር 1/2017 ዓ.ም (አሚኮ)
የእንግሊዙ ክለብ ኤቨርተን አሠልጣኝ ሲንዲያችን አሰናብቷል።

በየዓመቱ ወረደ ሲባል እንደምን የሚተርፈው የመርሲሳይዱ ክለብ በኤፍኤካፕ ከፒተርፕራህ ጋር ለመጫወት ሰዓታት ሲቀሩት አሠልጣኙን ማሰናበቱ እያነጋገረ ነው።

ክለቡ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በ19 ጨዋታ 17 ነጥብ በመያዝ 16ኛ ደረጃን ይዞ ይገኛል። ኤቨርተን አሠልጣኙ የተባረሩት በድንገተኛ ምክኒያት ነው ማለቱን ቢቢሲ በስፖርት ገጹ አስነብቧል።

ክለቡ ምሽት 4:45 የሚደረገውን የኤፍኤካፕ ጨዋታ የክለቡ የከ18 ዓመት በታች አሠልጣኝ ሌይተን ቤንስ እና የክለቡ አምበል ሽምስ ኮልማን እንዲመሩት ክለቡ ወስኗል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ስፖርት ዜና፡- ጥር 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ)
09/01/2025

ስፖርት ዜና፡- ጥር 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ)

ስፖርት ዜና፡- ጥር 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ)

ዌስትሃም ግርሃም ፖተርን አሠልጣኝ አደረገ።የእንግሊዙ ዌስትሃም ስፔናዊ ጁሊያን ሊፕቴጌን አሰናብቶ ፖተርን ቀጥሯል። ዌስትሃም በስፔናዊ አሠልጣኝ ውጤታማ መኾን አልቻለም። ይህን ተከትሎ ሊፕቴጌ...
09/01/2025

ዌስትሃም ግርሃም ፖተርን አሠልጣኝ አደረገ።

የእንግሊዙ ዌስትሃም ስፔናዊ ጁሊያን ሊፕቴጌን አሰናብቶ ፖተርን ቀጥሯል። ዌስትሃም በስፔናዊ አሠልጣኝ ውጤታማ መኾን አልቻለም። ይህን ተከትሎ ሊፕቴጌን ማሰናበቱ ይታወሳል።

በእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ ከ20 ጨዋታ 23 ነጥብ በመሰብሰብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ግራሃም ፖተር በዌስትሃም ለሁለት ዓመት ተኩል ለመቆየት ነው የፈረሙት። ግራሃም ፖተር በቼልሲ እና በብራይተን በማሰልጠን አሳልፈዋል።

ባሕር ዳር ከተማ ተጋጣሚውን በማሸነፍ የሊጉ መሪ ኾነ፡፡ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የ13ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ታኅሣሥ 30/2017 ዓ.ም ሲቀጥል ባሕር...
08/01/2025

ባሕር ዳር ከተማ ተጋጣሚውን በማሸነፍ የሊጉ መሪ ኾነ፡፡

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የ13ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ታኅሣሥ 30/2017 ዓ.ም ሲቀጥል ባሕር ዳር ከተማን ከሀዋሳ ከተማ ያገናኘው ጨዋታ በባሕር ዳር ከተማ አሸናፊነት ተጠናቅቋል፡፡

በጨዋታውም 80ኛው ደቂቃ ጄሮም ፊሊፕ ባስቆጠራት ጎል ነው ማሸነፍ የቻለው። ውጤቱን ተከትሎም ባሕር ዳር ከተማ የሊጉ መሪ ኾኗል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ስፖርት ዜና፡- ታኅሳስ 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ)
08/01/2025

ስፖርት ዜና፡- ታኅሳስ 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ)

ስፖርት ዜና፡- ታኅሳስ 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ)

Address

Bahirdar
Bahir Dar
6000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AMECO Sport posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to AMECO Sport:

Share