Zuma

Zuma Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Zuma, News & Media Website, .

23/09/2022
17/09/2022

በአማራ ክልል በቅርቡ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች የተላለፈ አስቸኳይ መልዕክት፡፡

የ2014/2015 ዓ.ም በአማራ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በክልሉ ባሉ ዩኒቨርስቲዎች ፈተናው እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወሳል፡፡

በመሆኑም ተፈታኝ ተማሪዎች ቀድመው ሊዘጋጁባቸው የሚገቡ ዋና ዋና ነጥቦች እንደሚከተለው ይቀርባሉ፡፡

1. ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ማዕከልም ይሁን በመፈተኛ ክፍል አድሚሽን ካርድ ይዞ መገኘት ግዴታ በመሆኑ አድሚሽን ካርድ ፎርም ከሞሉበት ትምህርት ቤት እና ወረዳ በአካል በመገኘት እስከ መስከረም 10/2015 ዓ.ም እንዲረከቡ፡፡

2. በአድሚሽን ካርዱ ላይ የስም፣ የስትሪም እና የጾታ ወዘተ..ስህተት ካለ በአስቸኳይ ለትምህርት ቤቱ እና ለወረዳው ሪፖርት እንድታደርጉ በጥብቅ እያሳሰብን ይህንን የማያደርጉ ተማሪዎች ካሉ ፈተና ለመውሰድ እንደሚቸገሩ፤

3. ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጡ የትምህርት ቤት ወይም የኗሪነት መታወቂያ ይዞ መገኘት የሚገባ መሆኑ፤

4. ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ጊዜ እርሳስ፣ ላጲስና የእርሳስ መቅረጫ ይዘው መገኘት ያለባቸው መሆኑ ከዚህ ዉጭ ሌሎች ቁሳቁሶችን በዩኒቨርሲቲ ግቢ እና በመፈተኛ ክፍል መያዝ የተከለከለ መሆኑ፤

5. ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች ትምህርት ቤቱ፣ ወረዳው እና ዞኑ በሚያዘጋጀው የጉዞ ፕሮግራም መሰረት ወደ መፈተኛ ዩኒቨርሲቲ የሚጓዙ መሆኑን በመረዳት ዝግጅት ማድረግ ያለባቸው መሆኑን፤

6. ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ተመደበበት ዩኒቨርሲቲ ሲሄድ አንሶላ፣ ብርድልብስና የትራስ ልብስ ይዞ የመምጣት ይኖርባቸዋል፡፡

ይህን መረጃ ሸር በማድረግ ለተማሪዎችና ተማሪ ወላጆች እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት እንዲደርስ ትብብራችሁን እንድታደርጉ በተፈታኝ ተማሪዎች ስም ቢሮው ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

የመረጃው ምንጭ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ነው

🚩ሲሚንቶ ከፋብሪካ የሚወጣበት አዲሱ የዋጋ ተመን፦👇◼ ደርባ ሲሚንቶ 590᎐59፣ ◼ ዳንጎቴ ሲሚንቶ 549.49፣ ◼ ኢትዮ ሲሚንቶ 595.66፣ ◼ ሙገር ሲሚንቶ 643.95፣ ◼ ሐበሻ ሲሚንቶ ...
14/09/2022

🚩ሲሚንቶ ከፋብሪካ የሚወጣበት አዲሱ የዋጋ ተመን፦👇

◼ ደርባ ሲሚንቶ 590᎐59፣
◼ ዳንጎቴ ሲሚንቶ 549.49፣
◼ ኢትዮ ሲሚንቶ 595.66፣
◼ ሙገር ሲሚንቶ 643.95፣
◼ ሐበሻ ሲሚንቶ 683.44፣
◼ ናሽናል ሲሚንቶ 561.39፣
◼ ካፒታል ሲሚንቶ 633.38፣
◼ ኩዩ ሲሚንቶ 628.10፣
◼ ኢስት ሲሚንቶ 595.66፣
◼ ፒዮኒር ሲሚንቶ 510᎐04 ብር እንዲሸጡ ተወስኗል።

በተጨማሪም በከተማ አስተዳደሮች እና ክልሎች ይሁንታ ካገኙ አካላት ውጪ ሲሚንቶ ይዞ የሚገኝና በተለያዩ ቦታዎች የሚደረጉ ህገወጥ ግብይቶች ላይ ተቋሙ ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል።

በቸርነትህ አመታትን ታቀዳጃለህመልካም አዲስ አመት  #2015🇪🇹
10/09/2022

በቸርነትህ አመታትን ታቀዳጃለህ
መልካም አዲስ አመት

#2015🇪🇹

መልካም አዲስ አመት🇪🇹❤
10/09/2022

መልካም አዲስ አመት🇪🇹❤

መልካም አዲስ አመት
10/09/2022

መልካም አዲስ አመት

10/09/2022
ይሄ ነገር ወዴት ነው😳🙄
03/09/2022

ይሄ ነገር ወዴት ነው😳🙄

የተወለድንበት ወር ስለኛ ምን ይላል? የእርሶን ወር ይመልከቱና ምስክርነቶን ይስጡን #ጥርበጥር ወር የተወለዱ ሰዎች መንፈሰ ጠንካራ፣ የማይበገርአመለካከት ያላቸው እና ሰዎችእንዲህ አድርጉ ብለ...
03/09/2022

የተወለድንበት ወር ስለኛ ምን ይላል? የእርሶን ወር ይመልከቱና ምስክርነቶን ይስጡን

#ጥር
በጥር ወር የተወለዱ ሰዎች መንፈሰ ጠንካራ፣ የማይበገር
አመለካከት ያላቸው እና ሰዎች
እንዲህ አድርጉ ብለው እንዲመክሯቸው የማይፈልጉ
ናቸው።
በዚህ ወር የተወለዱ ሰዎች ጎበዝ ነገር ግን ሌሎችን
የማይሰሙ አለቃ ይወጣቸዋልም
ተብሏል። እነዚህ ሰዎች በተፈጥሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የማስተማር ብቃት ያላቸው ሲሆን፥ ጠንካራ የስራ ስነ ምግባርን የተላበሱ ናቸው። የመሰላቸውን ለመናገር ወደኋላ የማይሉ መሆናቸውም
ነው የሚነገረው።

#የካቲት
የልደት በአላቸውን በየካቲት ወር የሚያከብሩ ሰዎች
ደግሞ በውይይት የሚያምኑ፣
አመለካከቱ የወረደ ነው ብለው ከሚገምቱት ሰው ጋር
ደግሞ መነጋገር የማይሹ ናቸው
ተብሏል። የፈጣሪ አዕምሮ ባለቤቶች፣ በአዳዲስ እና ልዩ የስራ ዘርፎች መሰማራት ጉብኝት የሚያዘወትሩ፣ ታማኝ እና ሀቀኛ መሆናቸውም ይነገራል።

#መጋቢት
በመጋቢት ወር የተወለዱ ሰዎች አዲስ ሀሳብ ለማፍለቅ
የተፈጠሩ፣ አይን አፋር እና
ጭምት እንደሆኑ ነው መረጃው የሚያመለክተው።
የኪነ ጥበብ ስራዎች ራሳቸውን ለመግለጽ
የሚጠቀሙባቸው ሲሆን፥ ለመመሰጥ ጸጥታን
እንደሚመርጡም ይነገራል።
እነዚህ ሰዎች ለሰዎች ሩህሩህ፣ ቅን እና መልካም አሳቢ
ቢሆኑም የራሳቸውን ሚስጢር
እና ግላዊ ነገር ለመደበቅ የሚሞክሩም ናቸው።
በራሳቸው አለም የሚኖሩ፣ ሰላማዊ አውድ የሚፈልጉ እና
ብዙ ጊዜ ጫጫታ እና ጭንቅንቅ በሚበዛበት ስፍራ የማይገኙ ናቸውም ተብሏል።

#ሚያዚያ
ትዕዛዝን በአግባቡ የማይቀበሉ፣ ነገሮችን በራሳቸው
መንገድ የሚመለከቱ እና ሌሎችንም
በዚሁ አስተሳሰባቸው ወደራሳቸው ለማምጣት የሚጥሩ ፤
በሚያዚያ ወር ይህቺን አለም
የተቀላቀሉ ሰዎች መገለጫ ነው ይላል የናቹራል ሂሊንግ
ሜጋዚን ድረ ገፅ ዘገባ።
በአቅራቢያቸው ከሚገኝ ማንኛውም አካል ትኩረት እና
ፍቅር ይሻሉ፤ በጀብዱ የተሞላ
ህይዎት ይፈልጋሉ፤ አንዳንድ ጊዜም ጠንከር ባለ
ንግግራቸው ይታወቃሉ።
በህዝብ ፊት የሚያደርጉት ነገር ግድ የማይሰጣቸውና
ቢጸጸቱ እንኳን ከድርጊታቸው በኋላ
መሆኑም ይነገራል።

#ግንቦት
ለሁኔታዎች የሚቀያየሩ (የገበታ ውሃ)፣ የዛሬ እና ነገ
ፍላጎታቸው የተለያየ፣ ብቸኝነት
የሚከብዳቸው እና ጠንካራ የማህበራዊ ህይወት ያላቸው
ናቸው። በዚህ ወር የተወለዱ ሰዎች ስሜታቸውን በደንብ
የመግለጽ ብቃት ያላቸው ሲሆን፥ በተለያዩ የእድሜ ክልል ከሚገኙ ሰዎች ጋርም ማውራት ይወዳሉ።
በቀላሉ ለድብርት የሚጋለጡ በመሆኑም የተለያዩ
የመዝናኛ አማራጮችን ይመለከታሉ ተብሏል።

#ሰኔ
በሰኔ ወር ከምቹው የእናታቸው ማህጸን ወደዚህች አለም
የተቀላቀሉት ደግሞ ሰዎች
የሚወዱት አይን አፋርነት እና ጭምትነትን የተላበሱ ናቸው
ይላል ዘገባው። በቀላሉ ስሜታቸው የሚቀያየር እና ለሌሎች ሰዎች ደህንነት አብዝተው የሚጨነቁ መሆናቸውንም መረጃው ያመለክታል። አርቆ የመመልከት እና ሀሳባቸውን ወደ እውን የመቀየር ልዩ ችሎታ እንዳላቸውም ይነገራል።

#ሀምሌ
በሀምሌ ወር የተወለዱ ሰዎች በሰኔ ከተወለዱት ጋር
ተመሳሳይ ባህሪ እንዳላቸው ነው
የሚነገረው።
ይሁን እንጂ ወሬ የሚያበዙ፣ ከላይ ከላይ በራስ
መተማመን ያላቸው እና ለጋስ መስለው
ለመታየት የሚሞክሩ ነገር ግን በውስጣቸው ተንኮል እና
ሚስጢር የሚይዙ፤ ህመማቸውን
ለሌሎች ሰዎች ከመናገር የሚታቀቡ ናቸው።
በመዝናኛ ስፍራ የማይጠፉ፣ በሀይል የተሞሉ እና ጨዋታ
አዋቂዎች በመሆናቸውም
ሰዎች በአቅራቢያቸው አይጠፉም።

#በነሃሴ ወር የተወለዱ ሰዎችም፦
- ጥልቅ ሀሳብ እና ትንተና በሚፈልጉ ስራዎች ስኬታማ
ናቸው።
- ህይወት በደረጃ እና በምክንያት የምትራመድ ነች ብለው
ያስባሉ።

ነፍስ ይማር አይባል~ ነፍስን ያላወቁ ሁለት ፍሬ አበባ ~ተቀጥፈው ደረቁያፅናችሁ አይባል ~መፅናናት ይከብዳልእንዲህ አይነት ሀዘን ~በምን ቃል ይበርዳል።በአስቸኳይ አስተማሪ የሆነ ቅጣት ይፈረ...
02/09/2022

ነፍስ ይማር አይባል~ ነፍስን ያላወቁ
ሁለት ፍሬ አበባ ~ተቀጥፈው ደረቁ
ያፅናችሁ አይባል ~መፅናናት ይከብዳል
እንዲህ አይነት ሀዘን ~በምን ቃል ይበርዳል።

በአስቸኳይ አስተማሪ የሆነ ቅጣት ይፈረድልን
የኛም እህቶች ናቸው።🙏😭😭

 #ሠበር*ማሳሰቢያ የህወሓት ዲጂታል ሰራዊት አባላት የትግል ስልታቸውን መቀየራቸውን አስተውሉ! እንደዚህ ቀደሙ የህወሓት ፀር ከሆነው የህብረተሰብ ክፍል ጋር በመቃረን የሚደረገውን የማህበራዊ ...
02/09/2022

#ሠበር
*ማሳሰቢያ

የህወሓት ዲጂታል ሰራዊት አባላት የትግል ስልታቸውን መቀየራቸውን አስተውሉ! እንደዚህ ቀደሙ የህወሓት ፀር ከሆነው የህብረተሰብ ክፍል ጋር በመቃረን የሚደረገውን የማህበራዊ ሚዲያ ላይ የትግል ስልትን በመቀየር በአዲስ ስልት ሲንቀሳቀሱ እያስተዋልን ነው።

ይኸውም ራሳቸውን በሐሰተኛ ማንነት በመደበቅ የፕሮፋይል ምሥላቸውንም እንደቀድሞ “ትግራይ-ጄኖሳይድ” ዓይነት መፈክሮችን የሚያስተጋቡ ምሥሎችን ከመጠቀም ይልቅ በኢትዮጵያ ባንዲራና አብዛኛው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ በሚያከብራቸው ጀግኖች ምስል በመሸፈን እንዲሁም በሀሳብ ደረጃ የህወሓትን ፍልሰፍናዎች እንደድሮው በቀጥታ ከማስተጋባት ይልቅ በተዘዋዋሪ የህወሓትን አይዲዮሎጂ የሚያግዙ መረጃዎችን በማሰራጨት፣ ህወሓትን ትክክለኛ ለማስመሠል የሚረዱ ጥርጣሬዎችን በመፍጠር፣ በጠያቂ መልክ ሲንቀሳቀሱ እየታዘብን ነው።

ስለሆነም መላው ሀገር-ወዳድ ኢትዮጵያዊ የጉዳዩን አደገኛ አካሄድ ተረድቶ መፍትሔ ሊያበጅለት ይገባል። በተለይ ብዙ ተከታይ ያላችሁ የማህበረሰብ አንቂዎች አብዛኞቹ የዲጂታል ሰራዊቱ እንቅስቃሴዎች ኢላማቸውን ያነጣጠሩት በእናንተ ዙሪያ መሆናቸውን ተገንዝባችሁ ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥታችሁ የጥንቃቄ እርምጃ እንድትወስዱ ለማሳሰብ እወዳለሁ።

 #በዋግኽምራ ግምባር ‼ዛሬ በዚዝ ግምባር በተደረገው ጦርነት መከላከያ ሰራዊት የጁንታውን ኃይል በመደምሰስ ጁንታው ይጠቀምበት የነበረውን ዋሻ ሲፈተሽ የተገኘ ነው።ለተረጂ ህዝብ የተላከ የእር...
01/09/2022

#በዋግኽምራ ግምባር ‼
ዛሬ በዚዝ ግምባር በተደረገው ጦርነት መከላከያ ሰራዊት የጁንታውን ኃይል በመደምሰስ ጁንታው ይጠቀምበት የነበረውን ዋሻ ሲፈተሽ የተገኘ ነው።

ለተረጂ ህዝብ የተላከ የእርዳታ ምግብ ለጦርነት እየተጠቀመው መሆኑን ግልፅ ማሳያ...

የኢትዮጵያ ወታደር የቆሰለውን ባልደረባውን በጀርባው ተሸክሞ በ1935 ዓ.ም
31/08/2022

የኢትዮጵያ ወታደር የቆሰለውን ባልደረባውን በጀርባው ተሸክሞ በ1935 ዓ.ም

31/08/2022

የቻይና ወታደሮች ሩሲያ ገቡ

ነሐሴ 25/2014 (ዋልታ) የቻይና ጦር በሩሲያ ግዛት ውስጥ በሚካሄደው ወታደራዊ ልምምድ ላይ ለመሳተፍ ሞስኮ መድረሱ ተነግሯል።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በለቀቀው የቪዲዮ ምስል ላይ የቻይና ጦር ለግዙፉ ወታደራዊ ልምምድ ዝግጅት ሩሲያ መድረሱ ታይቷል።

ቮስቶክ 2022 የሚል መጠሪያ የተሰጠው ወታደራዊ ልምምድ ለ7 ቀናት በሩቅ ምስራቅ ሩሲያ እና በጃፓን ባሕር ላይ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በዚህ ወታደራዊ ልምምድ ላይ አዘጋጇ ሩሲያን ጨምሮ ቻይና፣ ቤላሩስ፣ ታጃኪስታን፣ ህንድ፣ ሞንጎሊያ እና ሌሎችን ሀገራት ይሳተፋሉ ተብሏል።

ከሀገራቱ የተውጣጡ 50 ሺሕ ወታደሮች በልምምዱ ላይ የሚሳተፉ ሲሆን ከ5 ሺሕ በላይ የተለያዩ አይነት የጦር መሳሪያዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ መባሉን አል ዐይን ዘግቧል፡፡

ከጦር መሳሪያዎቹ መካከልም 140 የጦር አውሮፕላኖች እና 60 የጦር መርከቦች እንደሚገኙበትም የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር መግለጫ አመላክቷል

AddisWalta - AW
አዲስ ዋልታ
Walta Media and Communication Corporate

ስለ ኢትዮጵያ የማታውቀው ታሪክ ኢትዮጵያውያን የጠላት ወታደሮችን ለመያዝ አንበሶችን በማሰልጠን ከአቦሸማኔ፣ ንቦች ጋር ጎን ለጎን በመታገል በቅኝ ግዛት ውስጥ የተካሄዱ ጦርነቶችን ሁሉ በማሸነ...
31/08/2022

ስለ ኢትዮጵያ የማታውቀው ታሪክ ኢትዮጵያውያን የጠላት ወታደሮችን ለመያዝ አንበሶችን በማሰልጠን ከአቦሸማኔ፣ ንቦች ጋር ጎን ለጎን በመታገል በቅኝ ግዛት ውስጥ የተካሄዱ ጦርነቶችን ሁሉ በማሸነፍ በአለም ላይ በቅኝ ያልተገዛች ብቸኛ ሀገር እንድትሆን አስችሏቸዋል። በአድዋ ጦርነት ሾተል በተባለው የሰይፍ ጦርነት የተካኑ ኢትዮጵያውያን ወራሪ የጣሊያን ወታደሮችን ከእጅ ለእጅ ጦርነት አወደሙ። የአድዋ ጦርነት የመጀመርያው ኢታሎ-ኢትዮጵያ ጦርነት ከፍተኛ ጦርነት ነበር። እሑድ መጋቢት 1 ቀን 1896 ዓ.ም የአድዋ ከተማ አካባቢ የኢትዮጵያ ጦር የጣሊያን ወራሪ ጦር ድል አደረገ። ወሳኙ ድል የኢጣሊያ መንግሥት የቅኝ ግዛት ግዛቷን በአፍሪካ ቀንድ ለማስፋፋት የጀመረችውን ዘመቻ አከሸፈው። ኢትዮጵያውያን ጣሊያኖችን ለሁለት ሳምንታት ከበው በእቴጌ ጣይቱ ምክር የምሽጉን ውሃ ቆርጠዋል። የጣሊያን አዛዥ መሳሪያቸውን ይዘው እንዲወጡ ከተፈቀደላቸው እጃቸውን ለመስጠት ተስማሙ። ምኒልክም ከሰፈራቸው መውጣት እንደሚችሉ ተስማሙ። #ሾፍ አፍሪካ #ኢትዮጵያ #አፍሪካ #ቅኝ ግዛት #ባህል

ታካሚ ከ3001 ዓ.ዓ. ጀምሮ የዓለምን ታሪክ ስንመለከት፣ ዛሬ እንደ ሳሃራ ምድር የምናውቀው ሰፊው አረንጓዴ ሳቫና ከደረቀበት ጊዜ አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ... ጨዋታው የሚካሄድበትን ጊዜ ይ...
31/08/2022

ታካሚ ከ3001 ዓ.ዓ. ጀምሮ የዓለምን ታሪክ ስንመለከት፣ ዛሬ እንደ ሳሃራ ምድር የምናውቀው ሰፊው አረንጓዴ ሳቫና ከደረቀበት ጊዜ አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ... ጨዋታው የሚካሄድበትን ጊዜ ይጠቁማል። አዳኙን የማሳደድ እድል" ታሪክ እንደሚያሳየው እነዚህ ክበቦች, በታሪክ ውስጥ, እራሳቸውን ደጋግመው ደጋግመው ነበር. አፍሪካውያን አውሮፓ በሌለበት ዘመን... ግሪክ፣ ሮም ወይም አሜሪካ በሌሉበት ጊዜ፣ ዓለምን ለሺህ ዓመታት ሲገዙ ቆይተው ነበር። በበረዶ የታሸጉ መሬቶች ነበሩ ነገር ግን እንደ ማጅርስ፣ ፒክትስ፣ አልማይን፣ ቪሲጎት፣ ጎጥስ፣ ቫራንግያውያን፣ አስትሮጎቶች፣ ሳክሶኖች፣ ኦስካኖች እና ኡምብራውያን ወዘተ የመሳሰሉ አረመኔያዊ የጎሳ ቡድኖች አልነበሩም። ነገር ግን እነዚህ የጎሳ ቡድኖች ከ12ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት ‹በረዶ ፓኮች› ውስጥ ወጥተዋል...‹‹ብዙውን ዘመናዊ ዘመን በተለይም ከ15ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ይገዙ ነበር። አፍሪካ አሁን ከአፍሪካ ውጪ ባሉ ኃያላን እየተመራች ነው። (አፍሪካ አለምን ስትገዛ)። -የአፍሪካ መጽሔት ታሪክ፣ ቅጽ 4፣ 2022 እንግሊዝኛ/ፈረንሳይኛ/ሃውሳ/ቲቪ/ስዋሂሊ/ስፓኒሽ/Xhosa/Twi/...

❌🚫 Of course, priests, youths, children, women, men are all enemies! The children that the TPLF is ending look like thes...
28/08/2022

❌🚫
Of course, priests, youths, children, women, men are all enemies! The children that the TPLF is ending look like these! After a few moments of jealousy, we can see in which front these children died, as the images of Zobel's front are still there!

የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ!አሸባሪው ሕወሐት በአንድ በኩል የተለመደውን የሰው ኃይል ማዕበልን በመጠቀም የቆቦ ከተማ ከውጭ በብዙ አቅጣጫ እያጠቃ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ በከተማ ውስጥ ሠርጎ ገቦች...
27/08/2022

የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ!

አሸባሪው ሕወሐት በአንድ በኩል የተለመደውን የሰው ኃይል ማዕበልን በመጠቀም የቆቦ ከተማ ከውጭ በብዙ አቅጣጫ እያጠቃ ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ በከተማ ውስጥ ሠርጎ ገቦችን በማሥረግ የሕዝቡን ደኅንነት አደጋ ውስጥ በሚያስገባ መልኩ የከተማ ውስጥ ውጊያ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ እየፈጠረ ይገኛል።

የሕዝብን ከፍተኛ ፍጅት ለማስወገድ ሲባል የመከላከያ ኃይል የቆቦ ከተማን በመልቀቅ እና ወደ ኋላ መጥቶ ለመከላከል የሚስችለውን ወታደራዊ ይዞታዎችን ለመያዝ ተገዷል።

አሸባሪው ኃይል የትግራይን ወጣት እየማገደ በሕዝብ ማዕበል ማጥቃቱን ካላቆመ መከላከያ ሕጋዊ ፣ ሞራላዊና ታሪካዊ ግዴታውን ለመወጣት የሚገደድ ይኾናል።

ነሐሴ 21 ቀን 2014 ዓም
አዲስ አበባ

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

Address


Telephone

+251963804862

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zuma posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share