02/01/2023
ለነባሩ ጭልጋ ወረዳ አስተዳደር ም/ቤት
በወረዳዉ ማለትም በ16 ቀበሌ በሶስት ጤና ጣቢያ የማህበረሰቡን ሁለተናዊ የጤና ሁኔታ ለማሻሻል አልሞ መስራት ይኖርበታል። ከ3 ጤና ጣቢያዎች 2ቱ በደጋማዉ እና ወይናደጋዉ አካባቢ እንዲሁም 1 ቆላማዉ ቀጠና ይገኛል ።
በጤና ኤክስቴሽን የእናቶችን ፣የህፃናትን ጤና ለማስተካከል መስራት ሲገባዉ ፖለቲካዊ ሽርሙጥና በሆነ መንገድ ተጠምዶ ይገኛል።
ለአብነትም በአደዛ ጤና ጣቢያ ያለዉ የመሰረተ ልማት ግንባታ መጓተት ፣ ስርአት የለሽ የጤና ጣቢያ ሃላፊ እና ሙያተኛ ፣ 2 ካርቶን ኦሚፕራዞል መድሃኒት ማህበረሰቡ ሳይጠቀምበት ኤክስ አደርጎ የተገኘበት ተቋም እንዲሁም Under five የሚሰጠዉን የኩፍኝ(measle) ክትባት above 7 ለሆኑ ህፃናት ላዛ ትምህርት ቤት ላይ ተገኝቶ ክትባት የሰጠ ተቋም እና ሃላፊ ያለበት ጤና ነዉ ። ክትባቱን የሰጠዉ ሙያተኛም አሁን የጤና ጣቢያ ሃላፊ ሁን ተብሎ ተሸልሟል።
ይህ ብቻ አይደለም የዚህ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ነዉር ጫንድባ ጤና ጣቢያን ባዶ ያደረገ ልጅ መጥቶ በምክትልነት እንዲመራዉ ይሁንታ ሰጥቶታል። በዚህም የ 350 ሽ ብር በላይ የጤና መድን ኪሳራ ወረዳዉን አከናንቦታል ።
ማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን ማህበረሰቡ በየጊዜዉ የሚያወጣዉን የህክምና ወጭ በአመት አንዴ በመክፈል ራሱን ከወጭ የሚከላከልበት ስርአት ነዉ። በመሆኑም በዚህ ስርአት የሚታቀፍ ማንኛዉም ሰዉ አምኖበት ጠቀሜታዉን አዉቆ በራሱ ፈቃድ በጤና መድን (health insurance ) ይታቀፋል በእየ አመቱም ክፍያ ይከፍላል። ሁኖም ይህ ደካማ እና ልፍስፍስ ሃላፊዎች ያሉት ተቋም የዉባ ወረርሽኝን ለመከላከል የክልሉ ጤና ቢሮዉ ከለጋሽ አካላት ባገኘዉ ገንዘብ ያሰራጨዉን የዉባ መከላከያ አጎበር ለማህበረሰቡ Timely ከማድረስ ይልቅ የጤና መድን ካልከፈላቹህ አይሰጣቹህም የሚል ህግ የሚያወጣ ደካማ ስብስብ ነዉ።
ጤና መድን መግባት መብት እንጂ ግዴታ አይደለም ማነሽ ሲስተር ለምለም ። ይልቅ በሹፌር እና your former boss በነበረ አሁን ሙያተኛሽ በሆነዉ ሰዉ ሃሳብ እየተመራሽ ሙያተኛን ከማቧደን ፣ስራን ከማበላሸት ከቻልሽ ተቋሙን ምሪዉ ካልቻልሽ ልቀቂ ሃላስ!
የተከበሩ አቶ ዘለቀ እንቢ አለ ፣ወይዘሮ ካሳየ ስመኝ እና ፓርቲያቹህ ይህን ደካማ የአመራር ስምሪት ፣ሙያተኛን የሚያሸማቅ፣ ሌባን የሚያበረታታ ስብስብ ሃይማትሉት ከሆነ በእጃችን ያሉትን ከጫንድባ ጤና ጣቢያ ፣እስከ ዳንጉራ ብሉም በሸድ እስካለዉ አደዛ ጤና ጣቢያ ሙሉ የመድሃኒት፣ የጀኔሬተር፣ የፕላፕሌት እንዲሁም ሌሎች ዝርፊያዎች ለዞን ጤና መምሪያ የምናደርስ መሆኑን እንገልጣለን!
Change is Natural