25/12/2024
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ በ4 አጀንዳዎች ላይ በመምከር የውሳኔ አስተያየቱን ሰጥቷል
የከተማዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መኩሪያ ማርሻዬ በመሩትና የካቢኔ አባላቱ በተወያዩበት በዚህ መድረክ የሰባቱ የጨፌ አካባቢ የNDP ጉዳዮችን በመመልከት የውሳኔ ሀሳብ ሰጥቷል።
በተመሳሳይም የካቢኔ አባላቱ በውይይቱ የሂጠታ ፋራ አካባቢ የውሀ ፕሮጄክትን አስመልክቶ በስፍራው የተነሺዎችን የካሳ ክፍያ እና የምትክ ቦታ ዝግጅት ላይ ውይይት አድርጓል።
በተያያዘም ለ20 ጊዜ እንደ ሀዋሳ ከተማ የወጣውን የሊዝ የመሬት ጨረታ ውጤት ውሳኔን በመመልከት አስተያየቱን ሰጥቷል ዛሬ የተሰበሰበው ካቢኔ ።
በአራተኛ አጀንዳውም የበጀት ድጋፍ የሚፈልጉ የአስተዳደሩ ሴክተር መስሪያ ቤቶችን ዕቅድ በመመልከት ነው ውሳኔውን ያደረገው።