Benishangul Gumuz Media

Benishangul Gumuz Media Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Benishangul Gumuz Media, Media/News Company, assosa, Asosa.

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚዲያ የክልሉን ህዝብና መንግስት የመረጃ ፍላጎት በጋዜጠኝነት መርህ ላይ የተመሰረቱ አስተማሪ፣አዝናኝ፣ አሳዋቂ ዜናዎች፣ ፕሮግራሞች እንዲሁም ዶክመንተሪዎች ሰርቶ በማቅረብ በኤሌክትሮኒከስ ሚዲያ እና በማህበራዊ ሚዲያ የአየር ሰዓት ሽፋን ለማዋል የተቋቋመ ድርጅት ነዉ።

ብልፅግና ፓርቲ በሁለተኛው መደበኛ ጉባኤው ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ወክለው የተመረጡ የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት 1ኛ. አቶ አሻድሊ ሀሰን2ኛ. አቶ ጌታሁን አብዲሳ3ኛ. አቶ ኢስ...
02/02/2025

ብልፅግና ፓርቲ በሁለተኛው መደበኛ ጉባኤው ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ወክለው የተመረጡ የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት

1ኛ. አቶ አሻድሊ ሀሰን
2ኛ. አቶ ጌታሁን አብዲሳ
3ኛ. አቶ ኢስሃቅ አብዱልቃድር አብዱልቃድር
4ኛ. ወ/ሮ አስካል አልቦሮ
5ኛ. አቶ ባበክር ኻሊፋ
6ኛ. ወ/ሮ አለምነሽ ይባስ
7ኛ. ወ/ሪት ምስኪያ አብደላ
8ኛ. ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ
9ኛ. ወ/ሮ ቡዜና አልከድር

ሆነው ተመርጠዋል።

የተጣለብን አመኔታ እና ኃላፊነት በአዲስ ቁርጠኝነት ለሥራ እንድንነሳሳ የሚያበረታታን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ...
02/02/2025

የተጣለብን አመኔታ እና ኃላፊነት በአዲስ ቁርጠኝነት ለሥራ እንድንነሳሳ የሚያበረታታን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የብልፅግና ፓርቲን ምርጫ አካሂደናል ብለዋል።

ይኽም ወደ ዲጂታል ሽግግር የምናደርገው የሀገራዊ ጉዞ አካል ነው ሲሉም ነው የገለጹት።

በምርጫው ውጤት በእኔና በምክትል ፕሬዝዳንቶች የተጣለብን አመኔታ እና ኃላፊነት በአዲስ ቁርጠኝነት ለሥራ እንድንነሳሳ የሚያበረታታን ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።

የመንጌ ቤላሻንጉል እግርኳስ ክለብ ለሁለተኛ ዙር ሊግ አንድ ጨዋታ ስኬታማነት የሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ ባለሃብቶች እና ደጋፊዎች በተገኙበት የሲምፖዚየም መርሃግብር እየተካሄደ ይገኛል።በመርሃ...
02/02/2025

የመንጌ ቤላሻንጉል እግርኳስ ክለብ ለሁለተኛ ዙር ሊግ አንድ ጨዋታ ስኬታማነት የሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ ባለሃብቶች እና ደጋፊዎች በተገኙበት የሲምፖዚየም መርሃግብር እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሃ ግብሩ ለድምፃዊ ዳውድ ሃሚድ የምስጋናና ዕውቅና ፕሮግራም ይካሄዳል።

በዕለቱም በተለያዩ ክለቦች መካከል የእግርኳስ ጨዋታ እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

በተካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም እስከአሁን ድረስ 20 ሚሊየን 86 ሺህ ብር ለክለቡ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ተገብቷል።

በፕሮግራሙ ላይ የአሶሳ ዞን ምክትል አስተዳሪ የተለያዩ ወረዳዎች አመራሮች፣ የክለቡ ደጋፊዎች እና ባለሃብቶች ተገኝተዋል።

በንጋቱ አድሱ

ሰበር ዜናጠ/ሚ  ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚደንት ሆነው ተመረጡ።ሦስተኛ ቀኑን የያዘው የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) እጅግ ከፍተኛ በሆነ...
02/02/2025

ሰበር ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚደንት ሆነው ተመረጡ።

ሦስተኛ ቀኑን የያዘው የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) እጅግ ከፍተኛ በሆነ ድምጽ መርጧቸዋል።

ተመራጩ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በጉባኤተኛው ፊት ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።

በተያያዘ ዜና ጉባኤው አቶ ተመስገን ጥሩነህን እና አቶ አደም ፋራህን የፓርቲው ምክትል ፕሬዚደንቶች አድርጎ እጅግ ከፍተኛ በሆነ ድምጽ መርጧል።

ሁለቱ ምክትል ፕሬዚደንቶች በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በጉባኤተኛው ፊት ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።

02/02/2025

Amharic News 25-05-2017 E.C

ወጣቱን በተለያዩ የስራ ዘርፎች አደራጅቶ ወደ ስራ በማስገባት ከአካባቢው የተፈጥሮ ሀብት ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ በካማሽ ዞን የዛይ ወረዳ የሀገር ሽማግሌዎች ተናገሩ። በአካባቢው ያለው ሰላ...
01/02/2025

ወጣቱን በተለያዩ የስራ ዘርፎች አደራጅቶ ወደ ስራ በማስገባት ከአካባቢው የተፈጥሮ ሀብት ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ በካማሽ ዞን የዛይ ወረዳ የሀገር ሽማግሌዎች ተናገሩ። በአካባቢው ያለው ሰላም እንዲጸናም ከመንግስት ጋር ተቀናጅተው እየሰሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚድያ አስተያየታቸውን የሰጡ የዛይ ወረዳ የሀገር ሽማግሌዎች እንዳሉት ባለፉት ዓመታት በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግር ወረዳው መጠነ ሰፊ ቀውስ አስተናግዷል።

በችግሩም ክቡር የሆነው የሰው ህይወት ከማለፉም ባሻገር ህብረተሰቡ ለዘመናት ያፈራው ሀብት ንብረት መውደሙንም ነው የሀገር ሽማግሌዎቹ ያስታወሱት።

ሆኖም አሁን ላይ በተከፈለው መስዋዕትነት ዛይና አካባቢው በአስተማማኝ ሰላም ላይ ይገኛሉ ሲሉ የገለጹት የሀገር ሽማግሌዎቹ የተገኘውን ሰላም ማጽናት ደግሞ የሁሉም ዜጋ ሀላፊነት መሆኑን ተናግረዋል።

አሁን ላይ የግለሰብ ጸብ ቢከሰት እንኳን ውሎ ሳያድር በሀገር ሽማግሌዎች ይፈታል ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ ይህን መልካም ጅምር ባህል ለማድረግ እንደሚሰሩም አስረድተዋል።

ወጣቱን በተለያዩ የስራ ዘርፎች አደራጅቶ ወደ ስራ በማስገባት የአካባቢውን የተፈጥሮ ሀብት በአግባቡ እንዲጠቀሙ ማስቻል ደግሞ ከመንግስት የሚጠበቅ ወሳኝ ጉዳይ ነው ብለዋል።

አሁን ላይም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በፍቅር የሚኖሩባት የዛይ ወረዳ ባገኘችው ሰላም ወደ ቀደመ ልማቷ እየተመለሰች ትገኛለች ሲሉም አስተያየታቸው ሰጥተዋል።

የዛይ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አማኑ ደሬሳ በበኩላቸው ዛይና አካባቢው በአስተማማኝ ሰላም ላይ በመገኘቱ የተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ወደ ቀያቸው ተመልሰው በልማት ስራዎች ላይ ተሰማርተዋል ብለዋል።

በቀጣይም ወጣቱን በወርቅ ማህበራትና በተለያዩ የስራ ዘርፎች በማስማራት የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ይሰራል ብለዋል።

በስንታየሁ አድማስ

በሚቀጥሉት ወራት ለኢትዮጵያ ህዝብ ብስራት እናበስራለን፦ የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የብልፅግና ፓርቲ በሚቀጥሉት ወራት ለኢትዮጵያ ህዝብ ብስራት እንደሚያበስር የፓርቲ...
01/02/2025

በሚቀጥሉት ወራት ለኢትዮጵያ ህዝብ ብስራት እናበስራለን፦ የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የብልፅግና ፓርቲ በሚቀጥሉት ወራት ለኢትዮጵያ ህዝብ ብስራት እንደሚያበስር የፓርቲው ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

“ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተጓዝነው የብልፅግና ጉዞ ምዕራፍ አንድ ከጥልቅ እንቅልፍ፣ ከብዙ ዕዳ መንቃት የጀመርንበት የመነሳት ዘመን ነበር” ብለዋል በብልፅግና ፓርቲ 2ኛ ጉባኤ የመክፈቻ ንግግራቸው።

በዚህ ምዕራፍ የታሰረ ይፈታ፣ የተሰደደ ይመለስ፣ ያኮረፈ ይታረቅ፣ ከመከላከያም ሆነ ከዩኒቨርሲቲ የተባረረ ይመለስ፣ በእምነት ተቋማት የተከፋፈለ ይደመር፣ አቧራ ይራገፍ፤ ፀጋ ይገለጥ በሚል በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል።

ኢትዮጵያ ያለፈችበትን የመነሳት ዘመን አንድ አውሮፕላን መብረር ሲጀምር ተሳፋሪዎቹ ከሚሰማቸው ስሜት ጋር ያመሳሰሉት የፓርቲው ፕሬዚዳንት፤ አውሮፕላኑ የበረራ መስመሩን ከያዘ በኋላ ግን ተሳፋሪዎች ያለምንም መረበሽ መጓዝ ይችላሉ ነው ያሉት።

ብልፅግና ፓርቲ አሁን ምዕራፍ አንድ፣ የመነሳት ዘመንን አጠናቆ የቁልቁለትና የጎንዮሽ ጉዞ የሚያበቃበትን ምዕራፍ ሁለት፣ የማንሰራራት ዘመንን በይፋ የጀመረበት ወቅት መሆኑንም አስታውቀዋል።

እንደ ሀገር ስንዴ በብዛት በማምረት የሀገር ውስጥ ፍጆታን ለማሟላት ብቻ ሳይሆን ለውጭ ገበያ ለመላክ የተቀመጠውን ግብ ማሳካት መቻሉን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ መጪዎቹ ወራት የሕዳሴ ግድብ ግንባታን ጨምሮ ሌሎች ፕሮጀክቶችን አጠናቀን ሪቫን የምንቆርጥበትና አሻራ የምናስቀምጥበት ወቅት ይሆናል ብለዋል።
ሀገሪቱ የጀመረችውን የስኬት ጉዞ ለማስቆም ከውጭም ከውስጥም፣ ከግራም ከቀኝም ጥረት ቢደረግም፤ ፕሮጀክቶቻችንን ተግተን ጨርሰን በሚቀጥሉት ወራት ለኢትዮጵያ ህዝብ የምናበስር ይሆናል ብለዋል።

በአዲስ አበባ አድዋ ድል መታሳቢያ የስብሰባ አዳራሽ እየተካሄደ ያለው የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ዛሬ በሁለተኛ ቀን ውሎው በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ እየተወያየ እንደሚገኝ ኢቢሲ ዘግቧል።

ጥራቱን የጠበቀ ወቅታዊ መረጃዎች ለአድማጭ ለተመልካች ተደራሽ ለማድረግ አበክሮ እየሰራ እንደሚገኝ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚዲያ አስታወቀ ፡፡ ሚዲያው ዓላማውን ከዳር ለማድረስም ለክልል እና ለዞን...
01/02/2025

ጥራቱን የጠበቀ ወቅታዊ መረጃዎች ለአድማጭ ለተመልካች ተደራሽ ለማድረግ አበክሮ እየሰራ እንደሚገኝ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚዲያ አስታወቀ ፡፡

ሚዲያው ዓላማውን ከዳር ለማድረስም ለክልል እና ለዞን ካሜራ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

በስልጠናው መድረኩ ላይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚዲያ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ መለሰ ሰንበታ ሚዲያው በምስልና በድምፅ ጥራት ያለው መረጃ ለአድማጭ ለተመልካቾች ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ነው ብለዋል፡፤

ለስራው ስኬትም በዘርፉ ተዋናይ የሆኑ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን እንዲሁም የካሜራ ባለሙያዎች እውቀትና ክህሎት ለማሳደግ ስልጠና መስጠት መጀመሩንም ምክትል ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል፡፡

በተለይ የካሜራ ባለሙያዎች የሚወስዷቸው ምስሎችና ድምጾች ለአድማጭ ተመልካች ህብረተሰብ ተገቢ መልዕክትና መረጃ ተደራሽ ለማድረግ ለሙያቸው ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚገባም አቶ መለስ ገልጸዋል።

የሚድያ ስራ የቅንጅት ስራን የሚጠይቅ መሆኑንም በመገንዘብም ባለሙያዎቹ የተግባር ስልጠናውን በአግባቡ በመካታተል አቅማቸውን እንዲያሳድጉም አሳስበዋል።

በስልጠናውም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚዲያ ፣የክልል፣ የዞን የከሜራ ባለሙያዎች አየተሰተፉ ነው ።

በቲጃኒ አደም

ሁለተኛ ቀኑን የያዘው የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በምስል፦
01/02/2025

ሁለተኛ ቀኑን የያዘው የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በምስል፦

01/02/2025

Borni k'ana(Seza.....!!!)

01/02/2025

Borni K'ana (Fiin Gowo Aza........!!!)

01/02/2025

Shinasha News 24 05 2017

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ በአሶሳ ከተማ እየተሰራ ያለውን የአስፓልት መንገድ እና የኮሪደር ልማት ሥራ ተዟዙሮ ተመልክቷል።የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ...
01/02/2025

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ በአሶሳ ከተማ እየተሰራ ያለውን የአስፓልት መንገድ እና የኮሪደር ልማት ሥራ ተዟዙሮ ተመልክቷል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ በአሶሳ ከተማ እየተሰራ ያለውን የአስፓልት መንገድና የኮሪደር ልማት ሥራ በሁሉም አቅጣጫ ተዟዙሮ ተመልክቷል።

የአሶሳ ከተማ የአስፓልት መንገድ እና የኮሪደር ልማት ሥራ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት፣ በርብርብና በፍጥነት እየተሰራ መገኘቱን በመመልከታቸው መደሰታቸውን የገለፁት የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ የተከበሩ አቶ መለሰ ኩዊ ይህም ሥራ በተያዘው ግለት ቶሎ ተጠናቆ አልግሎት ላይ እንዲውል መክረዋል።

የክልሉ ነዋሪ፣ የአሶሳ ከተማ ማህበረሰብና ባለሀብት የዚህ ልማት ሥራ የራሱ መሆኑን በመገንዘብ በጉልበቱ፣ በሀሳብና በገንዘቡ መንግስትን ሊያግዘውና ሊደግፈው እንደሚገባ ክቡር አፈ ጉባኤው አቶ መለሰ ኩዊ አሳስበዋል።

ይህ የልማት ሥራ እየተሰራ ባለው ሁኔታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ቶሎ እንደሚጠናቀቅ ቋሚ ኮሚቴው መገምገሙን የገለፁት ክቡር አፈጉባኤው ሥራውን ከግብ ለማድረስም የተጀመረው የገቢ ማሰባሰብ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እናዳለበት አሳስበዋል።

የክልሉ ምክርቤት የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ አላየ ስለሺ በበኩላቸው ሥራው በተያዘው መንገድ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተከፋፍሎ እየተሰራ መሆኑ ጥሩና የሚበረታታ መሆኑን በመጥቀስ የስፓልቱም ሆነ የኮሪደር ሥራው ሲጀመር የከተማው ነዋሪ ያለ ይዞታው አጥር እንዳያጥርና ግንባታዎችን እንዳይገነባ በመሃንዲሶች ክትትል በማድረግ መከልከል ነበረበት ብለዋል።

ማህበረሰቡ በከተማ ፕላን መመራት አለበት እንጂ ፕላኑ በሰው መመራት የለበትም ያሉት ክቡር ቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ አላየ ስለሺ አሁንም ከማህበረሰቡ ጋር ውዝግብ ውስጥ ከመግባት ግንዛቤዎችን በመፍጠር ማህበረሰቡ በተቀመጠው የመንገድ ስፋት መሠረት ገባ ብሎ ግንባታዎችን ሊገነባ እንደሚገባና የሀብት ብክነት እንዲቀንስ መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኢንጂነር በፊቱ ጎሹ እንደገለፁት ከዚህ በፊት የከተማ ዲዛይን ተቀርፆ ከመውጣት በስተቀር በተግባር መሬት አውርዶ ከመሥራት ክፍተቶች እንደነበሩ በማውሳት አሁን ግን ከተሞችን ውብ፣ ምቹና ፅዱ ለማድረግ መንግስት በያዘው ዕቅድ መሰረት የአሶሳ ከተማ 19 ኪ.ሜ መንገድ የአስፓልትና የኮሪደር ልማት ሥራ ተጀምሮ በፍጥነት እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።

የከተማው የመንገድ እስፓልትና የኮሪደር ልማት ሥራው በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ባለቤትና በክልሉ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ አስተባባሪነት እየተሰራ እንደሚገኝና ሥራውም ለአራት ኮንትራክተሮች ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ያብራሩት ምክትል ኃላፊው ክረምት ሳይገባ ለማናነቀቅ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

በክልሉ ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ የኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክቴር እና የአሶሳ ከተማ ኮሪደር ልማት ሥራ ሳይት አሰተባባሪ አቶ ደረጀ አርገታ እንደገለፁት የኮሪደር ልማት ሥራው በሁለት ሎት ከኤርፖርት እስከ ኖክ እና ከአዲሱ እስፓልት እስከ ብሉ ስታር ጫፍ 2.5 ኪ.ሜ በቀኝና ግራ በአጠቃላይ የ5 ኪሎ ሜትር መንድ በ10 ሜትር እና 2 ሜ ዩትሊቲ መንገድ ስፋት አጠቃላይ 12 ሜትር ስፋት እየተሰራ እንደሚነኝ አብራርተዋል።

የኮሪደር ልማቱ ፣ የእግረኛና የሳይክል መስመር እንዲሁም ማየት ለተሳናቸው ሰዎች ጭምር ታሳቢ ተደርጎ እየተሰራ እንሚመኝኘና በመንገዶቹም የመዝናኛ በታዎች፣ ኪችኖች፣ ማረፊያዎችና ለመኪና ፓርኪንጎች አገልግሎት እንዲሰጥ ታሳቢ ተደርጎ እንደሚሰራ አቶ ደረጃ አርገታ አክለው ገልፀዋል።

የመንገድ ዳር ሳር ነጠፋና ከጀርባ ዛፎች ተከላ እንደሚደረግ የገለፁት አቶ ደረጀ አርገታ አንዳንድ የመንገድ ውበት ሥራ ለባለሃብቶች፣ ለድርጅቶችና ተቋማት እንደተሰጠ መግለጻቸውን የክልሉ ምክር ቤት መረጃ ያመለክታል።

01/02/2025

Gumuz News 24 05 2017

Namizhiga Warada gaasiya ala Isportiya etakamaasiwa kada kꞌo-eba kowoma,ka babaçama komitee maatꞌocogwa aŋa etabikogash ...
31/01/2025

Namizhiga Warada gaasiya ala Isportiya etakamaasiwa kada kꞌo-eba kowoma,ka babaçama komitee maatꞌocogwa aŋa etabikogash ebadaga,katꞌisa etamazeeça daaŋgaŋa ala Warada aŋ,ka etabitꞌogatsa kamaceesa nndowa Wo Mootile Imiiye kada komiteeya aŋa batꞌogaan maaŋgishats ŋgisha tso.

Komiteeya aŋkwa kada Isportiya kadabooge na kꞌo-eba nakowoma bigatꞌoga mataaꞌela ka kodoŋwa kaaŋ ka aŋ toso.Kakowomaça ebiçaga maaŋatsakꞌo ŋgisha kada maatꞌocagwa Isportiya kowoma kamaam,maatꞌocogoma kaatsa mawaasan,mataaꞌatsa magaalakꞌowatsama kowoma bakalaga baŋgishagatsa.

Madada maakoshamakwa etabiyotaga namayizhil maatꞌocogwa madadama kowoma, kamaatꞌoꞌushan maatꞌocogwama kagashalama,kaats makadꞌakꞌoma,kakowokwa maçaga labaala kamaduwaan madadama kagashalama zanzeen,ka etabitꞌogatsa ka etamazhigakꞌo Warada aŋ Wo Mootile Imiiye bagasaandagakꞌunza.

Ambaanima bildꞌabaga na Mizhiga Warada Mangist Kominikeeshiniya tso.

"ብልፅግና አልቆ መገንባትን አስቀድሞ የሚያስብ ፓርቲ ነው"- የብልጽግና ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)   ብልፅግና ፓርቲ ሊያፈርስ የሚፈልገውን ብቻ ማፍረስ ሳይሆን አል...
31/01/2025

"ብልፅግና አልቆ መገንባትን አስቀድሞ የሚያስብ ፓርቲ ነው"- የብልጽግና ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ብልፅግና ፓርቲ ሊያፈርስ የሚፈልገውን ብቻ ማፍረስ ሳይሆን አልቆ መገንባትንም አስቀድሞ የሚያስብ ፓርቲ ነው ሲሉ የብልጽግና ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛው ጠቅላላ ጉባኤ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት "ከቃል እስከ ባህል" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ይገኛል።

የፓርቲው ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ብልፅግና ሊያፈርስ የሚፈልገው በርካታ ኋላቀር አሰራሮች እና ልምምዶች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳሉ ቢያውቅም አልቆ መገንባትን አስቀድሞ የሚያስብ ፓርቲ ነው ብለዋል፡፡

ለዚህም ነው "ፒያሳን ማፍረስ ሳይሆን አልቆ መገንባት የብልፅግና መለያው የሆነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ የፓርቲ ፖለቲካ ታሪክ 60 ዓመታትን ያልተሻገረ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በእነዚህ ዓመታት የነበረን የፓርቲ ፖለቲካ ልምምድ የምንፈልገውን ለውጥ ማመላከት ላይ ውስንነት የነበረበት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

"ኢትዮጵያ ውስጥ የፓርቲ ፖለቲካ ስንጀመር ብልፅግናን እስከፈጠርንበት ድረስ ያሉ ድካሞች ውድቀቶች ልንሻገራቸው ያልቻልናቸው አንድ ፓርቲ ለውጥ ፈጣሪ ብቻ ሳይሆን ለውጥ መሪ መሆኑን አለመገንዘባችን ነው" ብለዋል፡፡

ለውጥ መፍጠር ብቻውን ለውጥ ለመመራት የሚያስችል ብቃት እስካልፈጠረ ድረስ የተሟላ የፓርቲ ህልውና አይኖረውም ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ለውጥ መፍጠር ማለት ስላለው ችግር ድካም ውድቀት አብዝቶ መናገር ሳይሆን መፍትሄም ማፍለቅ ይጠይቃል ነው ያሉት፡፡

"ኢትዮጵያ ውስጥ ላለፉት ሃምሳ እና ስልሳ አመታት የነበረን የፓርቲ ፖለቲካ ልምምድ የምንጠላውን አብዝተን መውቀስ፤ ልናፈርስ ልንንድ የፈለግነውን በብዙ ማስረጃ መክሰስ እንጂ ልንገነባ የምናስበውን ልናመጣ የምንመኘውን ለውጥ ማመላከት ላይ ውስንነት ነበረብን" ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ጉባኤው ትናንትን፣ ዛሬን እና ነገን የሚያስተሳስሩ አቅጣጫዎች የሚቀመጥበት ነው - አቶ አደም ፋራህየብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛው መደበኛ ጉባኤ ትናንትን፣ ዛሬን እና ነገን የሚያስተሳስሩ አቅጣጫዎ...
31/01/2025

ጉባኤው ትናንትን፣ ዛሬን እና ነገን የሚያስተሳስሩ አቅጣጫዎች የሚቀመጥበት ነው - አቶ አደም ፋራህ

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛው መደበኛ ጉባኤ ትናንትን፣ ዛሬን እና ነገን የሚያስተሳስሩ አቅጣጫዎች የሚቀመጥበት መሆኑን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሀላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ገለጹ።

ብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን "ከቃል እስከ ባህል" በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ የአድዋ ድል መታሰቢያ ማካሄድ ጀምሯል፡፡

በጉባኤው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሀላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ብልጽግና ፓርቲ ሚዛናዊነትንና አስተሳሳሪ ትርክቶችን መሠረት በማድረግ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የነበሩትን ተቃርኖዎች የሚያስታርቅ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ይህን በሙሉ ቁመና ተፈጻሚ ለማድረግም ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ያለ ልዩነት በማቀፍ እውነተኛና ህብረ ብሔራዊ ፓርቲ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ብልጽግና የሁሉንም ኢትዮጵያውያን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት በፍትሃዊነትና በዘላቂነት ለማረጋገጥም የዲሞክራሲ ባህልን ማጎልበትና የወንድማማችነትና የእህትማማችነት እሴትን ማዳበር ወሳኝ መሆኑን በማመን ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ፓርቲው ቃልን በተግባር ማረጋገጥን መሰረት በማድረግም የገጠሙትን ተግዳሮቶች ህዝብን በማሳተፍ በብቃት መሻገር መቻሉንም አብራርተዋል፡፡

ብልጽግና ፈተናን ወደ ዕድል በመቀየር ለዛሬና ለመጪው ትውልድ ዘላቂ ጥቅምና መብት ጥብቅና በመቆም በህልም ጉልበት ለእመርታዊ ዕድገት በመትጋት ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

በሁለተኛ መደበኛ ጉባኤው በመጀመሪያው ጉባኤ ለህዝብ ቃል የተገቡ ጉዳዮች የሚፈተሹበት፣ በህዝብ እርካታ በመመዘን፣ የአመራርና አባላት ሁኔታን በጥልቀት እንደሚገመግምም ጠቁመዋል፡፡

ትናንትና፣ ዛሬንና ነገን የሚያስተሳስሩ አቅጣጫዎች የሚቀመጡበት ጉባኤ መሆኑንም ተናግረዋል።

ብልጽግና ፓርቲ ከጉባኤ እስከ ጉባኤ ለህዝቡ ቃል በገባው መሰረት በስንዴ ምርት ራስን ከመቻል ባሻገር ኤክስፖርት ማድረግ መቻሉንም ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርም ስኬታማ ስራዎች የተከናወኑበት፣ ምርትና ምርታማነት በከፍተኛ ሁኔታ ያደገበት እንዲሁም የህዳሴ ግድብን የመገባደድ ደረጃ ላይ የደረሰበት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ደረጃቸውን የጠበቁ የቱሪስት መዳረሻዎች የተገነቡበት እንዲሁም በዲጂታል ዘርፍ ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለህዝብ መስጠት የተቻለበት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በአጠቃላይ ከጉባኤ እስከ ጉባኤ ስኬታማ እና ዘመን ተሻጋሪ ስራዎች መከናወናቸውን አቶ አደም መግለጻቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ብልፅግና በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የነበሩ ተቃርኖዎችን የሚያስታርቅ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል፦ አደም ፋራህብልፅግና በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የነበሩ ተቃርኖዎችን የሚያስታርቅ አዲስ ምዕራፍ መክፈ...
31/01/2025

ብልፅግና በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የነበሩ ተቃርኖዎችን የሚያስታርቅ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል፦ አደም ፋራህ

ብልፅግና በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የነበሩ ተቃርኖዎችን የሚያስታርቅ አዲስ ምዕራፍ መክፈቱን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ተናግረዋል፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንቱ ብልፅግና ሚዛናዊነትን፣ አስተሳሳሪ ትርክትን እንዲሁም ሁለንተናዊ ብልፅግናን መሰረት አድርጎ የተቋቋመ ፓርቲ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ብልፅግና እውን ለማድረግም ፤ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ያለ ልዩነት በማቀፍ እየሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡

እውነተኛ የኅብረ ብሔራዊ ፓርቲ ሥርዓትን በመተግበርም የዜጎችን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት በፍትሃዊነት እና በዘላቂነት ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

ሁለተኛው የብልፅግና ፓርቲ ጉባዔ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ከተለያዩ ሀገራት የመጡ እህት ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት እየተካሄደ መሆኑን ኢቢሲ ዘግቧል።

Address

Assosa
Asosa
251

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Benishangul Gumuz Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Benishangul Gumuz Media:

Videos

Share