18/06/2024
የጋሞ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ የተለያዩ የፈጠራ ስራዎችን ለእይታና ለውድድር አቀረበ።
የጋሞ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት ቦዳ ከወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደር መዋቅር ጋር በመሆን የተካሔደው ኤግዚቢሺን በቴክኖሎጂና ኢንፎርሜሽን የተሻለ ትውልድ ለመፍጠር የሚኖረው ጠቀሜታ የጎላ ነው ብለዋል።
በዚህም በቴክኖሎጂ የሚባክነውን የሰው ሐይል ተክቶ ለመስራት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የተናገሩት ሀላፊዋ ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ ያገኙትን ዕውቀት በተግባር ስደገፍ የጎላ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል።
ወ/ሮ ሰላማዊት ዘመናዊ የሆኑ ቴክኖሎጅዎችን መመሪመር፣መቅዳትና ማላመድ የሚያስችሉ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስራዎችን እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀው በ10 ዓመት ዕቅድ ችግር ፈቺ የልማትና የለውጥ ዘመን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል።
የጋሞ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ሰብስቤ ቡናቤ ሁሉም መዋቅር ICT የበለፀገ እንዲሆን በሰው ሀይልና በበጀት የመደገፍ ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
በፈጣራ ሥራ ማሳያ አውደ ርዕይ ከተለያዩ መዋቅሮች የተጋበዙ የፈጠራ ባለቤቶች ተሣታፊ ሆነዋል።
ዘጋቢ ማስረሻ ዘውዴ